ህወሓት ለ27 ዓመታት የገዛው በአሻጥር ነው።
ከቁጥር ከሚያታክቱ የህወሓት አሻጥሮች በቅድሚያ አዕምሮዬ ውስጥ የሚመጣው በረሀ በነበረት ጊዜ ከላይ ስንዴ በተን በተን የተደረገባቸው በአሸዋ የተሞሉ ከረጢቶችን ለየዋህ ለጋሾች የሸጠበት አጋጣሚ ነው። ይህ አዕምሮዬ ውስጥ ይቀረጽ እንጂ ከዚያ በኋላ ከፈፀማቸው አሻጥሮች አንፃር ሲታይ ይኸኛው የዕቃ ዕቃ ጨዋታ ነው።
የመንግሥት መዋቅር ከተቆጣጠረ በኋላ ህወሓት አሻጭረኛነቱ ባሰበት። ቁጥር ማምታት፤ ሕዝብን ከሕዝብ በተጠና መንገድ ማጋጨት፤ የአንድ እምነት ተከታዮችን ከሌሎች ጋር ማጣላት፤ ድርጅቶችን ውስጣቸው ሰርጎ በመግባት ማበጣበጥ፤ ሕዝብን በሽብር ጥቃት ገድሎ በሌሎች ማሳበብ .... ወዘተ ... ወዘተ
ህወሓት በአሻጥር ተወልዶ፤ በአሻጥር አድጎ ፤ በአሻጥር ጎልብቶ፤ በአሻጥር እያረጀ ነው።
ዛሬ፣ አሁን እነዚህን ዓረፍተ ነገሮች በምተይብባቸው ደቂቃዎች፣ የጌታቸው አሰፋ እና ገብሬ ዲላ የአሻጥር ኤክስፐርቶች ብርቱ ሥራ ላይ ናቸው።
በዚህ ወቅት የምመክረው አንድ ነገር ነው። ለህወሓት አሻጥሮች መንገድ አንስጥ። ሲያጣሉን ከተጣላንላቸው አሻጥሩ ግቡን መታ ማለት ነው። ስሜቶቻችንን ተቆጣጥረን ዓይኖቻችንን በግባችን ሳንነቅል መንገዳችን ከቀጠልን አሻጥሩን አከሸፍን።
የህወሓትን አሻጥሮች ማክሸፍ የሚቻለው በመካከላችን መተማመንን ስንገነባ ነው። የጋራ ጠላት መኖር መተማመንን ይፈጥል። ህወሓት የኢትዮጵዊያን ሁሉ የጋራ ጠላት ነው። ይህን አምነን ከተቀበልን የህወሓት አሻጥሮች ውጤት አይኖራቸውም።
ኢትዮጵያ ለዘላለም ትኑር!
ድል ለኢትዮጵያ ሕዝብ !!!
No comments:
Post a Comment