በኦሮሚያ ኤሊባቦር ዞን የሚደረገውን ተቃውሞ ተከትሎ በተቀሰቀሰ ግጭት የበርካታ ሰዎች ህይወት መጥፋቱ ይታወቃል። ከብሄራዊ መረጃና ደህንነት አገልግሎት የተገኘው መረጃ እንደሚያሳየው የደህንነት ተቋሙ በተለያዩ ቦታዎች የሚደረጉ ተቃውሞዎችን ወደ ብሄር ግጭት እንዲያመሩ የሚያስችል ስራዎችን እያከናወኑ መሆኑን ነው። በዚህ መሰረት በኤሊባር የተፈጠረው የአማራ ማህብረሰብን ኢላማ ያደረገ ጥቃት በደህንነቱ የተከናወነ እንደሆነ ለማወቅ ተችሏል። በሃገር ውስጥ ደህንነት ዋና መምሪያ ውስጥ ከፍተኛ ስልጣን ያላቸው የኦህዴድ አባላት የሆኑ አቶ አዲሱ በዳዳ እና አቶ ተስፋዬ ኡርጌ የተባሉ የኦሮሚያን ክልል የደህንነት ጉዳዮች በበላይነት የሚከታተሉ ግለሰቦች አማካኝነት ነው በአማራውና በኦሮሚያ ክልል ተወላጆች መካከል የብሄር ግጭት እንዲነሳ ለማድረግ የሚጥሩት። እንደ አንድ ኦፕሬሽን ተይዞ እየተሰራበት ባለ በዚህ ጉዳይላይ የኦሮሚያ ክልል የአስተዳደርና ጸጥታ ቢሮ ሃላፊ የሆነው ረዳት ኮሚሽነር ደመላሽ ገ/መስቀል በዋና ተሳታፊነት እንደሚገኝ ታውቋል። ይህን ኦፕሬሽን የደህንነቱ ቁንጮ ከሆነው አቶ ጌታቸው አሰፋ ትእዛዝ እየተቀበለ በበላይነት እየመራ የሚገኘው የህወሃት አባል የሆነው የሃገር ውስጥ ደህንነት ዋና መምሪያ ሃላፊ አቶ አማኑኤል ኪሮስ የተባለ ግለሰብ ነው። እንዲሁም አቶ ደርበው ደመላሽ የተባሉ በደህንነቱ ውስጥ በከፍተኛ ሃላፊነት የሚገኙ ግለሰብ በረዳትነት ብሄሮችን ከብሄር የማጋጨት ኦፕሬሽኖችን ከአቶ አማኑኤል ኪሮስ ጋር በመሆን ያከናውናሉ። የደህንነቱ መስሪያቤት በአቶ አዲሱ በዳዳ እና በአቶ ተስፋዬ ኡርጌ አማካኝነት አሁን ያለውን የኦሮሚያ ክልል ሃላፊዎችን ይቃወማሉ የሚባሉ ሰዎችን እየመለመሉና እያደራጁ እንደሆነ ከደህንነት መስሪያ ቤት የተገኘው መረጃ ያመለክታል። የኦህዴድ አባል የሆኑት በኦሮሚያ ገጠር መንገድ በሃላፊነት እየሰሩ ያሉት አቶ ጀማል አባሶ የዚህ በደህንነቱ ለሚደረገው ኦፕሬሽን በዋና ተሳታፊነት እያገለገሉ ይገኛሉ። በአቶ ለማ መገርሳና በዶ/ር አቢይ አህመድ የሚመራው የኦሮሚያ ክልላዊ መንግስት በደህንነቱ መስሪያ ቤት ከፍተኛ አሻጥር እየተሰራበት እንደሆነና እነዚህ የኦህዴድ መሪዎች በሌላ መካከለኛ ላይ ባሉ የኦህዴድ አመራሮች ለመተካት የሚያስችሉ ዝግጅቶች እየተደረጉ እንደሆነ ለማወቅ ተችሏል።
No comments:
Post a Comment