Sunday, October 1, 2017

እንኳን ለእሬቻ በአል አደረሳችሁ (አርበኞች ግንቦት7)

September 29, 2017
የእሬቻ በአል ብዙ ብዙ ቁስሎችን ጥሎብን አልፏል፡፡ ብዙ ወንድሞቻችንን እህቶቻችንን እናት አባቶቻንንና ህፃናት ልጆችን በአገዛዙ የጭካኔ አገዳደል አጥተናል፡፡ ገንዘብ ከመለመንና  ህይወትን ከቁሳዊ ትርፉ በቀር የሰው ልጅ በራሱ ሃብት መሆኑ ያልገባው ቢገባውም ለማሽመድመድ የሚሞክረው አገዛዙ ባለፈው አመት የእሬቻ በአል አከባበር ላይ  ብዙዎችን ለሞትና ለአካል ጉዳት በሺዎች የሚቆጠሩትን ደግሞ ለእስርና ለስደት ዳርጓል፡፡ የሚገርመው ያንን ሁሉ ሃዘን ሰቆቃና እንግልት ማለፋችን ሳያንስ ዛሬ ደግሞ ያኔ ጉዳት ለደረሰባቸው ዜጎች በድንገት የሞቱ የሚል ሃውልት በመገንባት ዛሬም ቀልዱን ቀጥሏል ፡፡ በእራሱ በአገዛዙ ወታደሮች የጥይት አረር እንደወጡ ሳይመለሱ የቀሩ ሮጠው እንኳን ያልጠገቡ ለጋ ህፃናት በድንገት የሞቱ ተብሎ ተፅፎ ሲቀለድባቸው ማየትን የመሰለ ከባድ ህመም የለም፡፡
በመሰረቱ ይህ ሃውልት ከጅምሩስ ለምን ተሰራ? ምንን ለማሳየትስ ተፈልጎ ነው? ሃውልቱ የተሰራው ብለን ስናስብ አሁን የሚከበረው የእሬቻ በአል ላይ ህዝቡ አገዛዙ በፈፀመው ግፍ ተፀፅቷል ብሎ እንዲያምን መሆኑ ግልፅ ነው ፡፡ ይህን ሃሳቡን ያወቀበት ህዝቡ ደግሞ ከዚህ ሃውልት ላይ በድንገት የሞቱ የምትለዋን ማጭበርበሪያ ጭንብልህን አውልቃት ብለው ስለሞገቱት ሳይወድ በግዱ ሊፍቃት ችሏል፡፡
ሌላው ደግሞ ለህዝብ የሚቆረቆርና እንደ መንፈሳዊ አባት ሆኖ ህዝብ ሲያጠፋም አጠፋህ መንግስትም ሲበድል በደልክ የሚል አባት አጥተን በእየ እስር ቤቱ እየዞሩ በውሸት መስክሩ ልማቱን አታደናቅፉ የሚሉ አድር ባይ  አባቶች በሞሉባት ሃገር ላይ እንደ ኦሮሚያ አባገዳዎች  ለሃገሩና ለህዝቡ የሚቆረቆር አባት ማግኘታችን ኢትዮጲያዬ እውነትም ተስፋ አለሽ እንድንል ያደርገናል ፡፡ እንግዲህ እሁድ በሚከበረው የእሬቻ በአል ላይ የኦሮሚያ ቄሮዎችና አባገዳዎች በአሉን ለማክበር እንዲህ መሆን አለበት ያሉትን በመግለጫም ጭምር አስቀምጠዋል፡፡ ይኸውም በእሬቻ በአል ላይ ማንም የዚህ አምባገነን ስርአት ሹም የሆነ ሰው ሁሉ በአሉ ላይ ተገኝቶ ምንም የሚያደርገው ንግግር እንዳይኖር ፣ የልማት ማስታወቂያ እንዳይነገር ፣ ዜጎች በሚራቡባት ብዙዎች በሚታሰሩባት በሚገደሉባትና በሚሰደዱባት ሃገር ውስጥ እየኖርን ልማቱ ምጥቀቱ የሚል ውዥንብር አንፈልግም ! ስለዚህ ማንም የአገዛዙ አካል ወይም ወኪል በአላችን ላይ ንግግር ማድረግ አይችልም ሲሉ በግልፅ አስቀምጠዋል፡፡እንዲሁም ቄሮዎቹ የማንም ድርጅት ይሁን ክልል ባንዲራ አይውለበለብም የሚል አቋምም ወስደዋል፡፡ ይህ ደግሞ ለሁሉም ኢትዮጲያዊ ትልቅ ድል ነው፡፡
አገዛዙ 50 የሚሆኑ ሰዎች በድንገት ሞቱ ቢልም እኛ የምናውቀውና ከጉያችን የተለዩን ከ500 በላይ የሚሆ
ኑ ነገ ለሃገር ብዙ የሚጠቅሙ ወጣቶችን አጥተናል፡፡ ነገር ግን በዚህ አዝነን ልባችን ደምቶም እንኳን ቢሆን የተሰዉትን ጓዶቻችንን አላማ የተሰዉለትን ራዕይ እኛ ማሳካት የምንችለው ጠንክረን መታገል ስንችል ነው፡፡ ዛሬ አጠገባችን ባለመኖራቸው ብናዝንም እነሱን የቀጠፋቸውን ስርዓት ለማስደሰት ልቅሶ አንቀመጥም! ከከተማው ጀምረን በዓሉ እስከሚከበርበት ቦታ ድረስ እየጨፈርን ሄደን ስለተሰዉ ጓዶቻችን ድምፃችንን ከፍ አድርገን እንናገራለን! በአጭር ያስቀራቸውንም ስርዓት እስከመጨረሻው እንቃወማለን፡፡ አካላቸው አብሮን ባይሆንም አደራቸውን ተሸክመናልና አናፈገፍግም! የሚሉና በርካታ ሃሳቦችን አዝለው ማየታችን እጅግ ያኮራናል፡፡
እኛም በዚህ አጋጣሚ ማለትና ማስተላፍ የምንፈልገው ነገር ቢኖር በመጀመሪያ አገዛዙ አሁን ያሰራውን ሃውልት በሁለት መልኩ እንድትረዱት እንፈልጋለን
  1. በእሬቻ በአል ላይ በተሰዉት ዜጎች አዝኛለሁ ለማለት ነው፡፡ አስቡት እንግዲህ ጅራፍ እራሱ ገርፎ እራሱ ይጮሃል እንደሚባለው ወያኔም እራሱ ጨፍጭፎ እራሱ ሃውልት ያሰራና አዝኛለሁ ብሎ ያፌዛል፡፡ የጉድ ሃገር!
  2. ዘንድሮ በሚከበረው የእሬቻ በዓል ላይ አገዛዙ የሚደርስበትን ተቃውሞ ለመከላከል አስቦ የገነባው ሃውልት እንደሚሆን እርግጠኞች ነን፡፡ ምክንያቱም አቅዶ አስታጥቆ ባሰማራው የአጋዚ ሰራዊት አስገድሎ አስጨፍጭፎ ሲያበቃ “አዝኛለሁ በድንገት ነው” ቢልም ይህ ፍፁም ውሸትና አይን ያወጣ ክህደት ነው፡፡ ይህን ከወዲሁ ተረድተንና አስበን የተሰዉት ጓዶቻችንን አላማ ከግብ ለማድረስ ይህን አፋኝ ስርዓት አቅም ማሳጣትና ማስወገድ አለብን እንላለን፡፡

lammilee keenya waggaa darbe ayyaana irreechaa irratti lubbuun isaanii darbeef waaqayyoo lubbuu isaanii kan jannataa nuuf haagochu.

ባለፈው አመት በእሬቻ በዓል ላይ ህይወታቸውን ላጡት ወገኖቻን ፈጣሪ ነፍሳቸውን በገነት ያኑርልን
ሰላም

No comments:

Post a Comment