Monday, October 2, 2017

ከባህርዳር ዩኒቨርሲቲ ፖሊ ቴክኒክ ካምፓስ ተማሪዎች ያለ አግባብ እየተባረሩ መሆኑ ታወቀ (የአርበኞች ግንቦት 7 ድምፅ ሬዲዮ)


የባህር ዳር ዩንቨርስቲ ፖሊ ቶክኒክ ካምፓስ የአራተኛ አመት የኢንጅነሪንግ ተማሪዎች መብታቸውን በመጠየቃቸው ምክንያት 1500 ከዩኒቨርሲቲው ግቢ እንዲባረሩ ተደርጓል፡፡ ተማሪዎችም ያለአግባብ አንወጣም በማለታቸው ምክንያት በፌደራል ፖሊሶች እየተዋከቡ ይገኛሉ፡፡ አብዛኞቹ ተማሪዎች ከሌላ ክፍለሃገር የመጡ በመሆናቸው ምክንያት በእጃቸውም ምንም ገንዘብ የሌላቸው በመሆኑ ወደ ቤተ ክርስቲያን እና መስጊድ ለመጠጋት ቢሄዱም የወያኔ ቅጥረኛ ወታደሮች እየተከታተሉ ክልከላ እያደረጉባቸው ይገኛሉ፡፡ተማሪዎች ማደሪያ ስለሌላቸው በአካባቢው ወደ ሚገኘው ጊዮርጊስ ቤተክርስትያን ለማደርና እቃቸውን ለማስቀመጥ ወደ ቤተክርስቲያኑ ሲደርሱ የወያኔ ልዩ ሀይል ወታደር ከቦ ጠበቃቸው እናም ክልከላ በመፈፀም ከቤተክርስቲያኑ አካባቢ እንዲርቁ በማስገደድ ላይ ናቸው፡፡ በዚህ ግራ የተጋቡት ተማሪዎቹ ጉዟቸውን ወደ ሌላ ቤተክርስቲያን አድርገዋል ስለሆነም የባህርዳር ህዝብ እዲያስጠጋቸውና እዲደርስላቸው በመማፀን ላይ ይገኛሉ፡፡
Mon 02 Oct 2017Image may contain: 1 person, standing and outdoor

No comments:

Post a Comment