Sunday, October 8, 2017

የአባዱላ ነገር (D'r Tadesse Biru Kersmo)


የአቶ አባዱላ ገመዳ የሥራ መልቀቂያ ማቅረብ ፓለቲካዊ እንድምታ ከነገ ጀምሮ የሚታይ ነገር ይሆናል። የህወሓት ሰዎች ከሚከተሉት አንዱን ይመርጣሉ ብዬ አስባለሁ።
ሀ) ምንም እንዳልተፈጠረ ማስመሰል።
ቀድሞውኑ ጥያቄው አልቀረበም ይባል ይሆናል። ጥያቄው መቅረቡ ማስተባበል ካስቸገረ ደግሞ በጤና እክል ምክንያት የተጠየቀ መሆኑ፤ በዚህም ምክንያት የአባዱላ ማመልከቻ ተራ ነገር አድርገው ሊያቀርቡት ይሞክሩ ይሆናል። ከቅርብ ጊዜ ወዲህ የህወሓት ሰዎች ከነባራዊ እውነታ እየራቁ በቅዥት ዓለም የሚንሳፈፉ ሰዎች ሆነዋል። ስለሆነም ይህ ቢሆንስ (scenario) የማይመስል የሚባል አይደለም።
ለ) ማተራመስ።
ህወሓቶች አምርረው ሹም ሽሮችን በማከታተል ሁሉንም (የእውነቱን ብቻ ሳይሆን የይስሙላ ስልጣኖችንም) ጠቅልሎ ወደመያዝ ሊያመሩ ይችላሉ። የስልጣን ሽግግጉ ትግራይም ውስጥ ሊኖር ይችላል። ይህ ተግባራዊ ከሆነ ህወሓት ብአዴንና ኦህዴን አፍርሶ እንደገና ሊፈጥራቸው ይሞክራል፤ የሚሳካለት ግን አይመስለኝም።
ምንም ይሁን ምን የአባዱላ ገመዳ ውሳኔ የአቶ ለማ መገርሳን ክንድ አጠንክሯል። የኦህዴድ መሪዎች ህወሓት የማይወደውን ውሳኔ መወሰን የሚደፍሩ መሆናቸውን አስመስክሯል። አባዱላ ገፍቶ፣ ደፍሮ ከወጣ ብቻውን አይሆንም። ከነገ ጀምሮ የሚኖሩ የሸንጎ ስብሰባዎች የኦህዴድ ሰዎች በንቃት የሚሳተፉበት ይሆናሉ። ብአዴንም በዚህ መበረታታቱ አይቀርም። ደኢህዴንም ከእንቅፉ ለመንቃት መገላበጡ አይቀርም።
ህወሓት “ኢህአዴግ” የተባለውን ቀፎ ምን እንደሚያደርገው አይታወቅም። በአሁኑ ሰዓት የህወሓት የቅርብ ወዳጆች ሶህዴፓ፣ ሀብሊ፣ አብዴፓ፣ ቤጉሕዴፓና ጋብዴፓ እንጂ ኦህዴድ፣ ብአዴንና ደኢህዴን አይደሉም። የኢትዮጵያ ፓለቲካ የምትከታተሉ ሰዎች እነዚህን ድርጅቶች እወቋቸው - ሶህዴፓ፣ ሀብሊ፣ አብዴፓ፣ ቤጉሕዴፓና ጋብዴፓ። ህወሓት እነዚህን ድርጅቶች አቅፎ ኢትዮጵያን ለመግዛት ያልም ይሆናል።Image may contain: 1 person

No comments:

Post a Comment