Sunday, October 1, 2017

በዛሬው የኢሬቻ በዓል የተሳተፉ ወጣቶች በከፍተኛ ድምጽ የተቃውሞ መፈክሮች ሲያሰሙ ነበር። DW (Amharic)

ከመፈክሮቻቸው ውስጥ "ዶ/ር መረራ፣ በቀለ ገርባ ይፈቱ" ፣ "ኦሮሞዎችን መግደል ይቁም" የሚሉ ይገኙበታል። በበዓሉ ከተደመጡ መፈክሮች መካከል "ጭቆና በቃን፣ ለኦሮሞዎች ከሶማሌ ክልል መፈናቀል ምክንያት የሆኑ ለፍርድ ይቅረቡ፣ ነፃነት ለኦሮሚያ" የሚሉ ነበሩበት። የበዓሉ ታዳሚ ወጣቶች ተቃውሟቸውን በመፈክር እና በዘፈን ከማሰማታቸው ባሻገር ባለፈው ዓመት ህይወታቸውን ያጡ ዜጎችን ለማስታወስ ተንበርክከው፣ እጃቸውን በ"X" ምልክት በማጣመር ሀዘናቸውን ገልጸዋል። በስፍራው የነበሩ የኦሮሚያ ክልል ፖሊሶች ተቃውሞውን በዝምታ አልፈውታል። ጸጥታ ለማስጠበቅ ከተሰማሩ ወጣቶች ጋር በመሆንም ሁኔታውን ለማረጋጋት እና በዓሉ በሰላም እንዲጠናቀቅ በድምጽ ማጉያ መልዕክት ሲያስተላልፉ ታይተዋል። (ፎቶ- ከተስፋለም ወልደየስ ማኅደር)Image may contain: one or more people, crowd, sky and outdoor

No comments:

Post a Comment