Monday, July 13, 2015

በአሜሪካን ሀገር ሎሳንጀለስ ከተማ በአርበኞች ግንቦት 7 ህዝባዊ ስብሰባ ላይ ለትግሉ ማጠናከሪያ ከ37 ሺ ዶላር በላይ መዋጮ ተሰበሰበ

July 12, 2015
ምንጭ – አባይ ሚድያ
LA Patriotic Ginbot 7 fundraising campaign

በሎሳንጀለስ ከተማ የአርበኞች ግንቦት 7 ህዝባዊ ስብሰባ በተሳካ መልኩ መጠናቀቁን ከስፍራው የደረሰን ሪፖርት ያመላክታል።
ቅዳሜ ጁላይ 11, 2015 በተደረገው ህዝባዊ ስብሰባ የድርጅቱ አመራር አቶ ኤፍሬም ማዴቦ በአካል እና እንዲሁም ከለንደን አቶ ብዙነህ ጽጌ በስካይፒ በተገኙበት ታላቅና ባይነቱ ልዩ ና የደመቀ ዝግጅት በማድረግ በሎሳንጀለስ የሚገኙ ኢትዮጵያውያን ወያኔን ለመጣል ለሚደረገው ትግል ህዝባዊ ሃይሉ ህይወቱን እየሰጠ እኛ በገንዘብ የማንረዳበት ምንም ምክንያት በሚል ሀገራዊ ስሜት ንቁ ተሳትፎ በማድረግ ከ37ሺ በላይ የአሜሪካን ዶላር ለአርበኞች ግንቦት 7 አበርክተዋል።
አቶ ኤፍሬም ለተሰብሳቢው ሲገልጹ አርበኞች ግንቦት 7 ታሪካዊ እና ኢትዮጵያ ውስጥ ለሚፈጠረው ዲሞክራሲያዊ እና ፍትሃዊ ስርአት አርበኞቹ ስለኢትዮጵያ እየተጋደሉ ነው ትግል መራራ ነው። ይህን ወደን ሳይሆን ተገደን እንድንገባ የተደረግንበት የነጻነት የህልውና ትግል ነው። ብለዋል
አቶ ብዙነህ በበኩላቸው ታሪካዊው ጉዞ ተጀመረ እንጂ አልተጨረሰም። የእናንተ ደጀንነት ለኢትዮጵያ ጅግኖች ብርታት ነው። ወቅቱ በወሬ የምንወጠርበት ሰይሆን በስራ እና በተግባር የምንፈተንበት ሰአት ላይ ነን። ትግሉ የአርበኞች ግንቦት 7 እለታዊ ስራ ነው። ኢትዮጵያ ከህወሃት መንጋጋ እስክትላቀቅ ድረስ ስራችን ላይ በማተኮር ተባብረን ወደ ነጻነት የምናደርገው ጉዞ ይቀጥላል። ሲሉ ተናግረዋል።
ሎሳንጀለስ በርካታ ሀገር ወዳድ ኢትዮጵያውያን የሚገኙባት ከተመማ ስትሆን ይህ ስብሰባ በአይነቱ ልዩ በርካታ ህዝብ የተገኙበት እንደነበር አዘጋጆቹ ገልጻዋል። ለአካባቢው ህዝብም ምስጋናቸውን አቅርበዋል። ይህ የምናደርገው ስራ ከብዙው ጥቂቱ ነው ሲሉ የቻፕተሩ ተወካይ ተናግረዋል።
ምንጭ – አባይ ሚድያ

No comments:

Post a Comment