የህብር ሬዲዮ ሐምሌ 12 ቀን 2007 ፕሮግራም
<...የዶ/ር ብርሃኑ ኤርትራ መግባት አርበኞች ግንቦት ሰባት ጦርነት ከጀመረበት በላይ በለውጥ ደጋፊው ሐይል ትልቅ መነቃቃትና ድጋፍ የፈጠረ ነው። በስርዓቱ ደጋፊዎችና በሌሎች ደግሞ ተቃውሞ ሲስተናገድበት ተስተውሏል...እርምጃው የኢትዮጵያን ቀጣይ ፖለቲካ አመላካች ነው። በሃምሳዎቹ ዕድሜ የሚገኙትና በቅርቡ ሙሉ ፕሮፌሰርነት ማዕረግ ያገኙት ዶ/ር ብርሃኑ የሳቸው ወደ በረሃ መግባት በሰራዊቱ፣በራሱ በገዢው ፓርቲም ውስጥም ትልቅ ልዩነት መፍጠሩ አይቀርም።ይልቅ ማሰብ የሚያስፈልገው ለውጡን ተከትሎ ሊመጣ የሚችለውን...>
ጋዜጠኛ ሲሳይ አጌና ለህብር ሬዲዮ የዶ/ር ብርሃኑ ነጋ በረሃ መውረድ በትግሉ ላይ የሚያመጣውን ለውጥ በተመለከተ ተጠይቆ ከሰጠን ሰፋ ያለ ማብራሪያ የተወሰደ(ሙሉውን ያዳምጡት)
<...ጥሬ ስጋ መብላትን ያመጣው አባቶቻችን ጣላትን ሲዋጉ እሳት አንድደው በመመገብ በቀላሉ ጠላት ያሉበትን እአወቀ ጥቃት ሲሰነዝር ለመሸሽ ...> የጥሬ ስጋ አመጋገብ ባህላችን እና ኣለም አቀፍ የዘገባ ትኩረት ማግኘቱ( ልዩ ጥንቅር)
<...ከዩኒቨርስቲው ውስጥ ያባረሩኝ ያው ፖለቲካ ነው ለስሙ የጡረታ ዕድሜ ደርሷል ይላሉ እኔን በሀይለስላሴ ጊዜ ያስተማሩኝ ህንዶች ሳይቀሩ በአዲስ አበባ ዩኒቨርስቲ እአስተማሩ ነው...ፕ/ት ኦባማ ከመጡ አይቀር መድረክ ለማነጋገር ያንድ ወገን የገዢውን ፓርቲ ብቻ ሰምተው እንዳይሄዱ እድል እንዲሰጠን ጠይቀናል።የኦባማ መጥቶ መሄድ ግን...>
ዶ/ር መረራ ጉዲና ከአዲስ አበባ ዩኒቨርስቲ ስለተባረሩበት ውሳኔ፣በአገር ቤት ስላለው የተቃውሞ ፖለቲካና የኦባማን ጉዞ አስመልክቶ ከሰጡን ቃለ መጠይቅ የተወሰደ(ሙሉውን ያዳምጡት)
ሌሎችም
ዜናዎቻችን
* የዶ/ር ብርሃኑ ነጋ ኤርትራ ትግሉን በአካል ለመቀላቀል መሔድ በማህበራዊ ሚዲያው ሰፊ መነቃቃትን ፈጠረ
– የአገዛዙ ደጋፊዎች ድንጋጤ ተስተውሏል
* አንድ ወታደር ሶስት ኮሌኔሎችን ገድሎ በርካቶችን ካቆሰለ በኋላ ራሱን ማጥፋቱ ተገለፀ
* በአዲስ አበባ ከተማ ውስጥ በሁለት መኪናዎች ውስጥ የተደበቁ የጦር መሳሪያዎች በቁጥጥር ስር ዋሉ
_ አሽከረካሪዎቹ እየታደኑ ናቸው ተብሏል
* አቶ አንዳርጋቸው ፅጌ ለምስክርነት ፍ/ቤት እንዲቀርቡ የሰጠው ውሳኔ ተግባራዊነት አጠራጣሪ ሆኗል
* መድረክ ፕሬዝዳንት ኦባማ በኢትዮጵያ ቆይታቸው ወቅት እንዲያነጋግሩት ጥያቄ ማቅረቡን ዶ/ር መረራ ጉዲና ገለፁ
– የአሜሪካ ኤምባሲ ባለስልጣናት በጉዳዩ ላይ ለመወያየት ቀጠሮ ይዘዋል
* ሁበር በካሊፎርኒያ የ7.3 ሚሊዮን ዶላር ቅጣትና በአንድ ወር ውስጥ አገልግሎቱን እንዲያቋርጥ ዳኛ ውሳኔ ሰጠ
– ውሳኔውን በመቃወም ኩባንያው ይግባኝ የማለት እቅድ እንዳለው ገለፀ
* የካናዳ መንግስት በኢዮጵያ ውስጥ የታሰረ ዘጋዋን ባለመወሰዷ ከፈተኛ ትችት ገጠማት
* ኬንያ ኢትዮጵያዊያን መኮነኖችንን ማሰሯን እና ለኪሳራ እንደዳረጓት ባለሰላጣናቱዋ ገለጹ
* የእስራኤል መንግስት ኢትዮጵያዊው አባ ወራን ከቤተሰቦቻቸው ነጥሎ ለያባርራቸው ወሰነ
* አምባሳደር ግርማ ብሩ መገንጠልን ከሚቃወሙ ወገኖች የከረረ ጥያቄ ገጠማቸው
– “እረ ሰለኮንደሚኒየም ከማወራት በፊት ኣንድ አድረጉን ፣አትገነጣጥሉን” አንድ ተቃዋሚ ለአቶ ግርማ ያቀረቡት ምክር
* አትሌት ገንዘቤ ዲባባ ለ23 አመታት ያልተደፈረ የአለም ክብረወስንን ሰበረች
– የታላቅ እህቷን ረኮርድም ለመሰበር ቋምጣለች
ሌሎችም ዜናዎች አሉ
- See more at: http://www.zehabesha.com/amharic/archives/45206#sthash.9LlmD2iD.dpuf
No comments:
Post a Comment