Saturday, October 7, 2017

ሰበር ዜና

የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት አፈ ጉባዔ አባዱላ ገመዳ ሥልጣናቸውን በፈቃዳቸው ለመልቀቅ ደብዳቤ ማስገባታቸውን አዲስ ስታንዳርድ ዘገበ።
ለአባዱላ ሥልጣን መልቀቅ ዋነኛው ምክንያት ከ150 ሺህ በላይ የኦሮሞ ተወላጆች የተፈናቀሉበት በምስራቅ ኢትዮጵያ የተከሰተው የሰሞኑ ግጭት መፍትሄ ሊያገኝ አለመቻሉ ነው ተብሏል።
በዚህ ምክንያት ባለፉት ሳምንታት አፈ ጉባዔው ከሌሎች ከፍተኛ የመንግስት ሹመኞች ጋር ከፍ ያለ መካረር ውስጥ ገብተው መሰንበታቸውብም ጋዜጣው አስነብቧል።
በተያዘው ሳምንት የጠቅላይ ሚኒስትሩ ፕሮቶኮል ሹምና አንድ ብርጋዲየር ጀነራል ስርአቱን መክዳታቸው ይታወቃል።
Sat 07 Oct 2017
Image may contain: one or more people

No comments:

Post a Comment