Friday, December 15, 2017

የአውሮፓ ፓርላማ በጠራውና ኢትዮጵያን በተመለከተው አስቸኳይ ስብሰባ ላይ የኢትዮጵያ ሀገራዊ ንቅናቄ የሽግግር ሰነድ ማቅረቡ ተገለጸ። (ኢሳት ዲሲ–ታህሳስ 6/2010)

የሽግግር ሰነዱ አሁን በስልጣን ላይ ያለው የህወሃት አገዛዝ ከወደቀ በኋላ በኢትዮጵያ የሚደረገውን የሽግግር ስርዓት የሚያሳይ መሆኑ ተመልክቷል። በስብሰባው ላይ የተገኙት የኢትዮጵያ ሀገራዊ ንቅናቄ ከፍተኛ አመራሮች ለኢሳት እንደገለጹት የአውሮፓ ፓርላማ የኢትዮጵያ ቀውስ አሳሳቢ መሆኑን በመረዳት ከዚህ ቀደም ይከተለው የነበረውን አካሄድ በመተው የለውጥ ሃይሎች የመፍትሄ ሀሳብ እንዲያቀርቡ ጠይቋል። Image may contain: 3 people, people sitting and indoorየአውሮፓ ፓርላማ በኢትዮጵያ ጉዳይ ላይ የምክክር መድረክ ሲያዘጋጅ የዛሬው የመጀመሪያው አይደለም። በኢትዮጵያ የፖለቲካ ትኩሳት በተፈጠረ ቁጥር በተለይም ከተቃዋሚ ሃይሎች ጋር ስብሰባ መቀመጥ የተለመደ ነበር። የዛሬው በአውሮፓ ፓርላማ የተዘጋጀው ስብሰባ ግን የተለየ ነው ይላሉ የኢትዮጵያ ሀገራዊ ንቅናቄ አመራሮች። ከዚህ ቀደም የቀውሱ ፈጣሪ የሆነውን የህወሀት አገዛዝ በስልጣን ላይ እንዲቆይ የሚፈልጉት የምዕራብ መንግስታት መፍትሄውንም ከዚያው ከስርዓቱ የሚጠበቅ እንዲሆን ሲያደርጉ ቆይተዋል። አሁን ኢትዮጵያ የደረሰችበት የቀውስ ደረጃ የበፊቱን አካሄዳቸውን እንዲቀይሩ እንዳደረጋቸው በስብሰባው ላይ የተጋበዙት አካላት ለኢሳት ገልጸዋል። የኢትዮጵያ ሀገራዊ ንቅናቄ የስራ አስፈጻሚ ኮሚቴ ሰብሳቢ ዶክተር ዲማ ነገዎ እንደሚሉት የአውሮፓ ፓርላማ የኢትዮጵያ ቀውስ ያሳሰባቸው በመሆኑ ቀውሱን ለመፍታት የቀድሞውን አካሄድ ለመተው መፈለጋቸውን ፍንጭ ያሳዩበት ስብሰባ ነው የዛሬው። ዶክተር ዲማ ኢትዮጵያ ውስጥ እየተከሰተ ያለው ቀውስ ለናንተም ይተርፋልና አስቡበት የሚል ግልጽ መልዕክት ዛሬ ለአውሮፓዎቹ እንዲደርሳቸው አድርገናል ሲሉ ገልጸዋል። ኢትዮጵያ አሁን የምትገኝበት አሳሳቢ ቀውስ በስልጣን ላይ ባለው የህወሃት አገዛዝ መፍትሄ የሚገኝ እንዳልሆነ የተረዳው የአውሮፓ ፓርላማ ስርዓቱን ለመለወጥ የሚታገሉ ሃይሎችን በመጋበዝ ስለወደፊቷ ኢትዮጵያ በተነጋገረበት በዛሬው መድረክ የተገኙት የኢትዮጵያ ሀገራዊ ንቅናቄ ተባባሪ ሊቀመንበር እንዲሁም የአርበኞች ግንቦት ሰባት ንቅናቄ ሊቀመንበር ፕሮፌሰር ብርሃኑ ነጋ የአውሮፓ ፓርላማ በሁለት ምክንያቶች የዛሬው ስብሰባ እንደጠሩት ገልጸዋል። አንደኛው የኢትዮጵያ ህዝብ በጋራ ትግል እያደረገ መሆኑን፣ የስርዓት ለውጥ ከመጣም ለኢትዮጵያ አደገኛ እንደማይሆን ለመፈተሽ ሲሆን ሁለተኛው በተቃዋሚዎች በኩል ከስርዓት ለውጥ በኋላ ያላቸውን ዝግጅት ለማወቅ የተዘጋጀ ስብሰባ መሆኑን ፕ/ር ብርሃኑ ጠቅሰው በአውሮፓ ፓርላማ በተጠየቅነው መሰረት የሽግግር ሰነድ አቅርበናል ብለዋል። በስብሰባው ላይ የአውሮፓ ፓርላማም ሆነ ሌሎች የምዕራቡ መንግስታት ቢፈልጉም ባይፈልጉም የኢትዮጵያ ህዝብ የጀመረው ትግል ወደኋላ የማይቀለበስ መሆኑን በግልጽ እንዲያውቁት መደረጉን የኢትዮጵያ ሀገራዊ ንቅናቄ አመራሮች ገልጸዋል። የአውሮፓ ፓርላማም እስከዛሬ በነበረው መንገድ መቀጠል ቀውሱን የሚያባብስ መሆኑን በመረዳት ከሌሎች አካላት ጋር እንደሚመካከርበት መግለጹን ለማወቅ ተችሏል። በስበሳባው ላይ የተካፈሉት የአውሮፓ ፓርላማ አባል ማዳም አና ጎሜዝ የአውሮፓ ህብረት በውጭ የሚገኙና ለፍትህና ነጻነት የሚሰሩ ሚዲያዎችን በገንዘብ ማገዝ ይኖርበታል ማለታቸው ተጠቅሷል። በስብሰባው ላይ ከተለያዩ የኢትዮጵያ የተቃዋሚ ሃይሎች የተወከሉ እንዲሁም በሰብዓዊ መብት ላይ ከሚንቀሳቀሱ የኢትዮጵያ ድርጅቶች የተጋበዙ ተወያዮች ተገኝተውበታል።

4 comments:

  1. የአማራ ህዝብ የሌለበት፣ ያልተወከለበት፣ ሀሳቡን ፍላጎቱን ያልገለፀበት የሽግግር መንግስት ዳግም በኢትዮጵያ ይቋቋም ዘንድ አንፈቅድም! "ሀገራዊ ንቅናቄ" በሚል ስም የአማራ ወኪል ፍለጋ ስትዳክሩ ቤታችን እግር ጥሏችሁ ሰነዳችሁንም ሆነ አላማችሁን አይተን ተረድተናል። ከአላማና ግባችሁ ውስጥ አንዱም የአማራን ህዝብ ጥያቄ እንደማይመልስ ተረድተን በራችንን ዘግተናል። በራችንን ብቻ ዘግተን ግን አንቀርም ከሌሎች በአማራነት ብቻ ከተደራጁ ድርጅቶች ጋር በመሆን ለአማራ ህዝብ መግቢያ መጠለያ የሚሆን አማራዊ ቤት እንቀልሳለን!!! ይህ ትውልድ በ1984 ከነበረው ትውልድ እጅግ እንደሚለይ እንድትገነዘቡት እፈልጋለሁ፣ መብቱን ጠይቆ ማግኘት ባይችል ወይም በማናለብኝነት መብታችን ቢነፈግ የእኛ የሆነን ሁሉ በሀይል ማስጠበቅ እንዳለብን እናምናለን አምነንም እናስፈፅማለን!
    [አብሳሌም ፍቅሩ]

    ReplyDelete
  2. No Amhara represented at this fake meeting. No difference from TPLF anti-Amhara

    ReplyDelete
  3. የዐማራን ሕዝብ ከሆነ ለመሸጋገሪያነት ካልሆነ በማግለል ሂደት ላይ መሰረት ባደረገ ፣ ወቅታዊ የዐማራውን የህልውና የማንነት ጥያቄዎች ያልመለሰ፣ በአጠቃላይም ለዐማራ ሕዝብ ጥላቻና ንቀት ባላቸው ኃይሎች የሸፍጥ ጉዞ የተደገሰ የሰላምና የሽግግር ስራዓት በኢትዮጵያ ይመጣል ብሎ ማሰብ ከቅዠት ያለፈ አይሆንም። የዐማራ ሕዝብ በስመ ኢትዮጵያ ተታሎ ለባርነት ራሱን አሳልፎ አይሰጥም፣ እንዳውም የጀመረውን የዐማራ የህልውናና የማነነት ትግል በማጠናከር የአካባቢውን ጂዖ ፖለቲካዊ ዑደት ይለውጣል።
    ድል ለዐማራ ሕዝብ
    ፈለገአስራት

    ReplyDelete
  4. we Amhara people doesn't recognize this kind of bullshit,Ginbot zero I call in my expression Ginbot negative trying to draft this with out Amhara peoples/ethnic representation. we are aware this phenomena this so called mentioned political party is trying to still the Amhara Resistance freedom fight going on in Ethiopia for his own Agenda by ignoring the fact on ground due to this we strongly advice the European meditator to think on this issue.we don't want any suppressing rule to take over again and make our people in bondage. Victory to our Amhara people there after Ethiopia based on political principle not the other way round.

    ReplyDelete