Thursday, December 21, 2017

ይድረስ ለደኢህዴን አባላት (ዶ/ር ታደሰ ብሩ)

የደቡብ ኢትዮጵያ ህዝቦች ዴሞክራሲያዊ ንቅናቄ (ደኢህዴን) አባላት የሆናችሁ እና ማገናዘቢያ ልቦና ያላችሁ ወገኖች!በሕወታችሁ ውስጥ ትልቁን ውሳኔ መስጠት ያለባችሁ ወቅት ላይ ናቸው። እንደ እውነቱ ከሆነ በራሳችሁ ስንፍና ምክንያት ተረጋግታችሁ ለማሰብ እንኳን በቂ ጊዜ እንዳይኖራችሁ አድርጋችኋል። ከሚከተሉት አማራጮች አንዱን መርጣችሁ ተግባራዊ ካላደረጋችሁ እየመጣ ያለው ማእበል ጠራርጎ ይወስዳችኋል፤ ቀሪ እድሜ ካላችሁ የፀፀትና የእፍረት ይሆንባችኋል፤ የታሪክ ጥላሸት ትቀባላችሁ።Resultado de imagen de ዶ/ር ታደሰ ብሩ
ወገኖቼ ከፊታችሁ የተደቀኑት ሁለት ምርጫዎች የሚከተሉት ናቸው። (1) የህወሓት አገልጋይነታችውን አጽንታችሁ ራሳችሁን ቤተሰቦቻችሁንና አገራችን ኢትዮጵያን መግደል መቀጠል፤ ወይም (2) እንደ ኦህዴድና ብአዴን ጓዶቻችሁ ለራሳችሁ ክብር በመስጠት የህወሓትን አምባገንነት በመገዳደር ሕዝባዊ ትግሉን ማገዝ።
የመጀመሪያው መምረጥ ማለት ለራሳችሁና ለቤተሰቦቻችሁ ባርነትን ለአገራችን ውድቀትና ውርደት መምረጥ ማለት ነው። ይህንን አማራጭ የሚያስመርጧችሁ በውስጣች ያለው አድርባይነት፣ ስግግብነት፣ አልጠግብ ባይነት፥ ፍርሃት፣ አቅመቢስነትና ጨለምተኝነት መሆናቸው ልብ በሉ። የህወሓት ምርጥ አገልጋይ ለመሆን የምታደርጉት መርመጥመጥ ለጊዜው “የሚያኖር” ቢመስላችሁም እጅግ ... እጅግ ... እጅግ ... እጅግ... እጅግ ... እጅግ ከፍተኛ ዋጋ እንደሚያስከፍላችሁ እወቁ። የማይቀረው ማዕበል ሲመጣ ከህሊና ፀፀት በተጨማሪ ብዙ ዋጋ እንደሚያስከፍላችሁ ካሁኑ እወቁት።
ሁለተኛው አማራጭ ከህሊናችሁ ጋር ታርቃችሁ የምትኖሩበት፤ እስካሁን የበደላችሁትን ሕዝብ የምትክሱበት አማራጭ ነው። ይህን አማራጭ ለመምረጥ የሚያስፈልጓችሁ ልበሙሉነት፣ ተስፋ እና በሕዝብ ኃይል መተማመን ነው። ይህ አማራጭ ለጊዜው አስቸጋሪ ይመስል ይሆናል ስትጀምሩት ግን በሩቅ ስታስቡት እንደሚያስፈራው እንዳልሆነ ትገነዘባላችሁ።
ደኢህዴን ራሱ ወጥነት የሌለው ድሪቶ ድርጅት እንደሆነ እገነዘባለሁ። ይህንን እኔ ብቻ ሳልሆን ብዙ ኢትዮጵያዊያን የሚያውቁት ሀቅ ነው። እንዲህ ዓይነቱን ድሪቶ መተርተር ደግሞ ቀላል ነው።
በመጀመሪያ ደኢህዴን ራሱ በፈጠረው ፈለግ (ስንጥቅ) በትኑት። የሲዳማ ካድሬዎች የሲዳማ አንጃን ፍጥሩ። የወላይታ፣ የሀድያ፣ የጉራጌ፣ የጋሞ፣ የከፍቾ፣ የስልጢ ... ወዘተ የየራሳችሁን አንጃ በመፍጠር ደኢህዴንን አዳክሙት፤ ግደሉት። ከዚያ በኢትዮጵያዊነት ተሰባሰቡ። በዘር መደራጀት በሀገር ላይ የሚያመጣውን አደጋ ተገንዝባችኋል ብዬ ተስፋ አደርጋለሁ።
ፍጠኑ ጊዜ የላችሁም።

No comments:

Post a Comment