Wednesday, December 20, 2017

የዶክተር ደብረጺዮን ገመና ሲፈተሽ •••••••••••••••••••••••••••••••• በትግራይ ክልል ኮሙዩኒኬሽን ቢሮ ኃላፊ ይፋ ወጣ የተባለውና በፌስቡክ ላይ የተሰራጨው የዶክተር ደብረጺዮን ገብረሚካኤል ኢንተርኔት አጠቃቀም ታሪክ ብዙ ገመና አጋልጧል:: የወሲብ ፊልም እንደሚመለከቱ እና በየተጓዙበት ውጭ ሀገራት ሴተኛ አዳሪዎችን እንደሚያሳድዱ ከ200 በላይ አባሪ ማስረጃ ፎቶዎች የያዘው መረጃ ይዘረዝራል:: መረጃው መውጣቱ በራሱ በህወሓት ውስጥ የስልጣን ሽኩቻ እንደነበረ ማረጋገጫም ሆኗል። በእነ አባይ ወልዱ እና ደብረጺዮን ካድሬዎች መካከል የቃላት መጠዛጠዝ እንደነበር ማህበራዊ ሚዲያን ለሚከታተል ግልጽ ነው:: የቢሮው ኃላፊ ገብረሚካኤል መለስ በደብረጺዮን ካድሬዎች ቡድን ከፍተኛ የውግዘት ዘመቻ ሲካሄድባቸው ማየትና ከዚያ በኋላ የተለጠፉት መረጃዎች መነሳታቸው እንዲሁም "በኔ ስም ሌላ ፌስቡክ ተከፍቶ ነው" በሚል እንዲያስትባብሉ መደረጉ ይብለጥ መረጃው ትክክል መሆኑን አረጋግጧል። ገጹ የሰውዬው ካልሆነ ስለምን እሳቸው ላይ መዝመት አስፈለገ? በእርግጥ መረጃው እንዴት ተዓማኒ ይሆናል? በኦሬገን ዩኒቨርስቲ በሚዲያ ላይ የድክትሬት ጥናቱን የሚያደርገው እንዳልካቸው ኃይለሚካኤል ተጨማሪ ማረጋገጫ አለኝ ይላል:: ዝግጅቱን ያደምጡ ዘንድ ጋብዘናል::

No comments:

Post a Comment