Wednesday, December 6, 2017

የአግ7 አርበኞች ለአጋዚ ወታደር አገልግሎት ሊውል በነበረ ነዳጅ ላይ ጥቃት ፈፀሙ

ህወሓት በጎን ለይምሰል ሱዳን ወረረችን እያለ በጓሮ በር እየተሞዳመደ ከሕዝብ ደብቆ ሊያስገባው የነበር ሸቀጥም በአርበኞች ወድማል ፡፡ የአግ7 አርበኞች እጅግ ጥበብ በተሞላበት ኦፕሪሽን ዛሬ ህዳር 26 2010 ዓ/ም ንጋት 10:40 ላይ በሰሜን ጎንደር ጭልጋ ወረዳ ነጋዴ ባህር አካባቤ በህወሓት አጋዚ ታጅቦ ከሱዳን ካርቱም በመነሳት ወደ ኢትዮጲያ በመግባት ለአጋዚ ልዬ ኮማንዶ መቀሳቀሻ ሊሆን የነበረን በበርካታ ተሽከርካሪዎች የተጫነን ነዳጅ እና ሊላ ሸቀጦች ሙሉ በሙሉ አርበኞች አውድመውታል፡፡ በአሁኑ ሳዓት ሕዝብን ለማምታታት እና እየተደረገ ያለውን የነፃነት ትግል አቅጣጫ ለማስቀየስ በህወሓት አቀነባባሪነት የሱዳን ወታደሮችን ወደ ኢትዮጲያ በማስገባት ግዛታችንን በማስያዝ የተወረርኩኝ ፕሮፕጋንዳ እየነዛ ባለበት ወቅት ጨለማን ተገን በማድረግ ከሱዳን ነዳጅ እና የተለያዩ ሸቀጦችን ከህዘብ በመደበቅ እያስገባ ይገኛል ፡፡ በመሆኑም ይህ ዘረኛ ስርዓት በአሁኑ ጊዜ ንፁሀን ዜጎችን በጠራራ ፀሀይ በአልሞ ተካሹ ቅልብ ኃይል በሆነው በአጋዚ ክፍለ ጦር እየጨፈጨፈ ይገኛል ለዚህ ገዳይ ኃይል ህወሓት የሚፈልገውን ሁሉ በማቅረብ የሚታወቅ ሲሆን ፡ ከሚቀርብለት ትልቅ ነገር አንድ እና ዋናው ዘመናዊ ተሽከርካሪዎች እና ነዳጅ ነው ፡ ይህን የተረዱ አርበኞች ከአሁን ቀደምም ከካርቱም ተነስቶ ጭልጋን በማለፍ ጎንደር ሊገባ የነበረን ነዳጅ የጫነ ተሽከርካሪ ማውደማቸው ይታወሳል ፡፡ ዛሬም እጅግ አስደናቂ በሆነ ተጋድሎ በድጋሚ ታላቅ ስራ ሰርተዋል ፡፡ በአካባቢው ከፍተኛ ውጥረት ነግሳል ፡ አርበኞችም በሰላም ወደ ቦታቸው ተመልሰዋል ፡፡ 
ያለውን ሁኔታ እየተከታተልን እንገልፃለን ፡፡ 
ድል ለሕዝብ !!! 
የአግ7 የሰሜን ኢትዮጵያ ዕዝ ፡፡No automatic alt text available.

No comments:

Post a Comment