Thursday, December 7, 2017

የህወሃት ብሄራዊ መረጃ ስለላ ሶፍት ዌር ተሰናከል Cyber bit crashed


የህወሃት ብሐራዊ መረጃ በአገር ውስጥም ሆነ በውጭ አገር የሚኖሩ ሰላማዊ ዜጎችን ለመሰለል ከእስራኤል ኩባንያ የተገኘ ማላዋሪ ( Malware ) የተሰኘ የስለላ ዘዴ ቢጠቀምም የስለላላ መረቡ ኢላማ በተደረጉ ተሰላዬች ቁጥጥር ስር ወድቋል.. ፒ.ኤስ.ኤስ.(PSS) ፒሲ ሰርቪሊያንስ ሲስተም ( PC Surveillance System ) ተብሎ የሚጠራ የዊንዶ ፕሮግራም የተጠቀመዉ የህወሃት ብሄራዊ መረጃ ያሳበዉን ሳያሳካ አለማቀፋዊ ስህተት ዉስጥ እራሱን ከቷል።
( Cyber bit, an Israel-based cyber-security company ) ሳይበርቢት ከተባለ የእስራኤል የደህንነት ድርጅት የተገዛዉ ይህ አደገኛ የጠለፋ መሳሪያ በሐገር ዉስጥ እና በዉጭ ሐገር የሚኖሩ ኢትዮጵያዊያንን ለመሰለል በከፍተኛ ሁኔታ ጥቅም ላይ ሊዉል የታሰበ ነበር።
አንድ ሲትዝን ላብ ( Citizen Lab researchers promptly notified )የተባለ አጥኚ ቡድን እንዳተተዉ የኢትዮጵያ መንግስት በገዛ ህዝቦቹ ላይ ስለላ ሲያካሄድ ይህ የመጀመሪያዉ አለመሆኑን ገልጾ በቀጣይ ለኢትዮጵያ መንግስት አደጋ የሆኑ የስለላ ሚስጥሮች መዉጣትና በሀገር ዉስጥ በሚኖሩ የመንግስት ሰራተኞች ወይም ምሁራን ላይ የተደረገዉ የስለላ ደባ ስርአቱን ወደ ማይታመንበትና ወደ አዘቅት እንደሚከተዉ ፍንጭ ሰጥቷል 
በተለይም ከዚህ ቀደም የኢትዮጵያ መንግስት ያገለላቸዉ እነ ሃኪንግ ቲም እና ጋማ ቡድን ( HackingTeam and Gamma Group ) የተባሉ ሁለት ሶፍት ዌር ካምፓኒዎች ከእስራኤሉ ሳይበር ቢት ጋር በጋራ ለመስራት መስማማታቸዉ ለስጋቱ መበራከት አንዱና ዋናዉ ሲሆን በስለላ ስራዉ ላይ የተሰማሩ ግለሰቦች ኮማንድ ኮንትሮል መቆጣጠሪያ ሲዋቅሩ በመሰናከላቸዉ ( command and control (C&C) server ) የስለላ ተቋሙ ሚስጥሮችና መረጃዎች መዝረክረካቸዉንም ፍንጮች አክለዉ አስቀምጠዋል። 
ይህ ምሥጢራዊ የስለላ ስራ ባለፈው ዓመት 2016 የተጀመረ ሲሆን የተለያዩ ድረ ገጾችን የፌስ ቡክ የዉስጥ መስመሮችን ኢሜሎችን እና የተለያዩ የመገናኛ አዉታሮችን ለመስበር ድህረ ጣቢያዎች ላይ የቪዲዮ ወይም ፒዲኤፍ ፋይሎችን ለማየት አዶቤ ፍላሽ ማጫወቻ ዝማኔ ወይም (Adobe PdfWriter ) የተባለ መተግበሪያ ሶፍት ዌሮችን ለማውረድ፣ የአይፒ አድራሻዎች ምዝግቦችን እና የመሳሰሉትን ለማረጋገጥ ታስቦ የነበረ ሲሆን የህወሃት የስለላ ቡድን አባላቶች የሐገር ዉስጥ እና ከሐገር ዉጭ በሚኖሩ ዜጎቻቸዉ ላይ ስለላ ለማካሄድ ሲሞክሩ እጅ ከፍንጅ ተይዘዋል።
Ethiopian operatives make crucial mistake 
ድል ለኢትዮጵያ ህዝብ

No comments:

Post a Comment