Saturday, June 6, 2015

የወያኔ ምርጫ በብረት ማሸነፍ ከሆነ እኛም ብረት ይዘን እንመጣለን!!!!! ከ- መርጋ ደጀኔ (ኖርዌይ)

ADescription: C:\Users\New\Desktop\10847915_412860505548694_8664987974965671025_n.jpg

የወያኔ ምርጫ በብረት ማሸነፍ ከሆነ እኛም ብረት ይዘን እንመጣለን!!!!!
ከ- መርጋ ደጀኔ (ኖርዌይ)
2007 የኢትዮጵያ ምርጫ 1997 ምርጫ በሃላ 2002 ላይ ቀዝቃዛ የነበረ ቢሆንም አሁን እንደ ገና ህዝቡ በግልፅ ወያኔን በቃኝ ብሎ አልፈልግህም ያለበት ወቅት  ነው ።ወያኔ  በመላው ኢትዮጵያ ቢሸነፍም በአፈሙዝ በማስገደድ ፤በማፈን ፤ብሎም በመግደል የዘንድሮን ምርጫ በወያኔ ካድሬዎች  ኮሮጆዎችን ቀድመው የንብ ምልክት ያለው የምርጫ ወረቀት ሞልቶ በመገኘት የሌላ የተቃዋሚ ፓርቲ ተመራጮች  እና ታዛቢዎችን በማዋከብ ፤በማባረር ፤በማስገደድ በመላው ኢትዮጵያ ኢሀአዲግ እንዳሸነፈ ተደርጎ እውነት በማይነገርበት ሚዲያው በአይጋ ፎረምና በኢ.ቢስ መቶ በመቶ እንዳሸነፈ ነግሮናል።  የህዝብን ድምጽ  አፍነው መዝለቅ  እንዴት እንደሚችሉት አይገባኝም  ግን ባሰማራቸው ታጣቂዎች የኢትዮጵያዊያኑ ድምፅ  በጠራራ ጸሐይ ዘርፈዋል። ..
የወያኔ ምርጫ በያዘው መሳሪያ ተማምኖ ህዝቡን ማፈንና ምንም አያመጡም እኔ ብቻ ነኝ በሃይልና በጉልበት የምገዛው ከሆነ ምርጫህን ወደነዋል እንግዲያውስ ጠብቀን ፦እኛም የምርጫ ወረቀት ሳይሆን ፤አንተ ድምፅን ያፈንክበትን  መሳሪያ ፤ባዶ እጃችንን ሳይሆን ፤አንተ ህዝብን የምትገልበትን ብረት አንስተን እንመጣለን። የወያኔ ምርጫ ይሄ  ብቻ ስለሆነ  የኛም ምርጫ ይሄ ነው።
የኢትዮጵያ ህዝብ ሆይ ሰሜን ፤ደቡብ ፤ሳትል ምስራቅ ፤መዕራብ ሳትል ዘር ፤ቋንቋ ፤ሃይማኖት፤ ሳይለይህ እናት አባታችንን የገደለ ፤ወንድም እህቶቻችንን የገደለ ፤የኢትዮጵያን ህዝብ ያሰረና ያሰቃየ ፤ብሎም አገርን እየገደለ ያለውን ወያኔን መለያየት ሳይኖር  ልናጠፋውና  በኢትዮጵያ ምድር ስቃይ እንዳይኖር ማድረግ የሁላችንም ኢትዮጵያዊ ግዴታ ነው።.
ወያኔ 24 ዓመት ሙሉ አየነው አፉና  ልቡ የተለያየ ነው ።ወረቀት ላይ የሰፈረው ህግና በስራ ላይ የምናየው አይገናኝም ።የትኛውም  ህግ ለወያኔወች አይሰራም  ህግ የሚባል ነገር አይገዛቸውም በየጊዜው ለነሱ የሚመች ከሆነ  አዳዲስ ህግ እያወጡ ህዝባችን ቀና ብሎ እንዳይሄድና በአገሩ በነጻነት እንዳይንቀሳቀስ  እስረኛ  አድርጎ እና ተሸማቃቂ ሆኖ  እንዲኖር  እያስገደዱት ነው
የኢትዮጵያ ሕዝብ ሆይ ግን እስከመቼ ? ጀግንነቱ ፤ወኔው ብልሃቱ ፤ድፍረቱ ፤ቆራጥነቱ፤ አብሮ ስንወለድ የተሰጠን የፈጣሪ ጸጋ  እያለን ይህንን እንዳናደርግ ምን አይነት አዚም ነው የተጣናወተን በቃ ከእንግዲህ በሃላ የተኛውም ይንቃ ነገ እንዲህ ሊሆን ይችላል የሚል ተስፋ ያለው ተስፋው ተማጦ ማለቁን ይወቅ ሃገሬን በታላቅ በደልና  ለቅሶ  መከፋት እና ሃዘን ላይ ናት። ይህ ሁሉ በደል የደረሰው  በአንድ ጥቂት ጉሩፖች የኢትዮጵያን ሕዝብ ሃብት እና ንብረት  ለብቻቸው ተቆጣጥረውት በሞኖፕል በመያዝ  እና የሕዝብን መብት እረግጠው መኖር የሚፈልጉ ወያኔ  የተባሉ  ጥቁር እባቦችን ማስወገድ አለብን
ከእባብ  ደግሞ እንቁላል መጠበቅ ሞኝነት ነው ከእባብ የሚጠበቀው ያው መረዝ ነው   ከወያኔ  የምንጠብቀው ለኢትዮጵያ ሕዝብ የሚጠቅም ምንም የለም ።ስለዚህ  በአንድነት ከዳር እስከዳር  ተነስተን ተመለሶ እንዳያንሰራራ ላንዴና ለመጨረሻ ወደ ከርሰ መቃብሩ የምናስገባበት ጊዜ ነው
ጥቂት ወያኔወች እራሳቸውን አንደላቀው ለመኖር ለምን የኢትዮጵያ ሕዝብ ይሰደዳል ፤ጥቂት ወያኔወችን ለመሾም ለምን የኢትዮጵያ ሕዝብ ይታሰራል ፤ጥቂት ወያኔወችን ለማኖር የኢትዮጵያ ሕዝብ ለምን ይገደላል ፤ይህ ነገር በቃ ሊባል  ይገባል። ወያኔ በካርድ በኢትዮጵያ ሕዝብ  መቶ በመቶ እንደተሸነፈ አውቃል። አሸናፊ ነኝ ብሎ  የተናገረው  በያዘው መሳርያ አስገድዶ  እና  አፍኖ  ነው ወያኔ  በመሳርያ የሚያምን ከሆነ  እኛም መሳርያ ይዘን እንመጣለን። ኢትዮጵያን ሊያጠፋ እና ሊገላት የመጣውን ሽፍታ ለማጥፋት ሳንለያይ እንነሳ። የመከራው ቀንበርን አሸክመህው  ስቃይ  ያበዛህበት  ቀንበሩን ሰብሮ መከራውን ወደ ወያኔ አዙሮ  በስፈረው መስፈርይ ተስፍሮለት ለኢትዮጵያ ሕዝብ ያሰብከውን መከራ  አንተው ትጋተዋለህ  ትቀበለዋለህ  

ድል ለኢትዮጵያ ሕዝብ!!!!
-መርጋ ደጀኔ

01.06.2015

No comments:

Post a Comment