Sunday, June 14, 2015

ኢሳት ዜና


በደቡብ አፍሪካ ከተቃዋሚዎች ሊደርስበት ይችላል ከተባለዉ ከፍተኛ ተቃዉሞ በመሸሸግ ከፍተኛ የሆነ ክፍያን ወጪ በማድረግ የሐገርና የወገንን ሐብትና ጉልበት እያባከነ የሚግኘዉ የወያኔ ብድን ለቴድሮስ አድሐኖም ሲባል ብቻ በዉድነቱ የማይቀመሰውን ሆሊዳይ ኢን ሆቴል ተኮናትሮታል ከወያኔዉ ኢንባሲ የወጣዉ መረጃ እንደሚያመለክተዉ 123 (rivonia road sandton holiday inn hotel ) የተደበቀዉ ቴድሮስ አድሐኖም የወያኔ ደግፊዎችን በ15/2015 የፊታችን ሰኞ ከአፍሪካ ህብረቱ ማብቂያ ስብሰባ በኃላ ማምሻዉን ከ12 ሰአት አንስቶ ለመሰብሰብ ያቀደ ቢሆንም የወያኔ ደጋፊዎች በየግላቸዉ በፍራቻ ላይ እንደሚገኙ እየገለፁ ይገኛሉ።። ይህ በእንዲህ እንዳለ በተለይም በጆሐንስበርግ የሚገኙ ተቃዋሚዎችን ለመከፋፈልና ብይግል ለመወጠር ሲባል ብቻ የወያኔ መረጃ ሰራተኞች ባቀዱት እቅድ መሰረት በወያኔ ኢንባሲ አማካኝነት አማራዉን ህብረተሰብ ብቻ ለይቶ በነገዉ እለት 14/2015 ከምሽቱ 12።00 ሰአት ግራንድ ኮርት ( grand court )በተባለ የመሰብሰቢያ ስፍራ የጠራ ሲሆን በምላሹ አማራዉ ህብረተሰብ ተለይቶ መጠራቱን ዉድቅ ማድረጉን ከስፍራዉ የደረሰን መረጃ ያመለክታል።።
በደቡብ የአፍሪካ ህብረቱን ስብሰባ ለመካፈል ከተቀላቀሉት የአህጉሪቱ ባለስልጣናት መካከል የናይጀሪያዋ ባለስልጣል በዘራፊዎች መደፈሯ የሚታወስ ሲሆን ወያኔዎቹ ከዚህና ከተቃዋሚዎቻቸዉ ቁጣ የተነሳ ጭንቀት ዉስጥ ገብተዋል።። 
ጉድሽ ወያኔ

No comments:

Post a Comment