Sunday, June 7, 2015

ኢሳት

ከአገር የተሰደዱት ጋዜጠኞች ሳይሆኑ አሸባሪዎች ናቸዉ ተባሉ።
ኢሳት ዜና (ግንቦት 27 2007)
ባለፈው አመት የኢትዮጵያ መንግስት የፈጸመባቸዉን ወከባ በመሸሽ ከሃገር የተሰደዱ ጋዜጠኞችን እዉነተኛ ጋዜጠኞች አይደሉም ሲሉ በቅርቡ በኬንያ የኢትዮጵያ አምባሳደር ሆነዉ የተሾሙት ልዑክ ገለጡ።
በወቅታዊ የኬንያና የኢትዮጵያ ጉዳዮች ዙሪያ ዘ ስታንዳርድ (The Standard) ከተሰኘ ጋዜጣ ጋር ቃለ-ምልልስ ያደረጉት አምባሳደር ዲና ሙፍቲ፥ በኬንያ በስደት ላይ የሚገኙትን ጋዜጠኞች የእዉነት ጋዜጠኞች አይደሉም ሲሉ ገልጸዋቸዋል።
የፍትህ ሚኒስትር አምስት መጽሄቶችንና ጋዜጦችን ከህትመት ውጭ በማድረግ ጋዜጠኞቹ ህዝብን ለአመጽ የሚያነሳሱ ጽሁፎችን አሰራጭተዋል ሲል በሌሉበት ክስ መስርቶ ይገኛል።
CPJን ጨምሮ የተለያዩ አለም አቀፍ የጋዜጠኞች መብት ተቆርቋሪ ድርጅቶች በጋዜጠኞች ላይ የተወሰደዉን እርምጃ በማዉገዝ መግለጫ ማውጣታቸው ይታወሳል።
የሽብርተኛ ወንጀል ህጉ ተግባራዊ መደረግ ከጀመረ ከአራት አመት ወዲህ ቁጥሩ ከፍተኛ የሆነ የተቃዋሚ ፓርቲ አመራሮችና ጋዜጠኞች እንዲሁም ሌሎች ሰዎች ለእስር መዳረጋቸዉን የተለያዩ አካላት ይገልጻሉ።

No comments:

Post a Comment