ውስጥ የመድረክና የሰማያዊ ፓርቲን መርጠን እያለን ድምፃችን በኢህአዴግ ተሰርቋል በማለት አራት ሺህ የሚገመት ነዋሪ ህዝብ የተቃውሞ ሰላማዊ ሰልፍ ማካሄዱን ተገለፀ፣የጎንደር ከተማ ህዝብ እኛ ለውጥ ፈላጊዎች ስለሆን ሊያስተዳድሩን ይችላሉ ብለን የመረጥናቸው የመድረክና የሰማያዊ ድርጅት ተወካዮች እያሉ የኢህአዴግ ስርዓት ገዢ መንግስት ግን ስልጣኑን በመጠቀም የህዝቡን ድምፅ ሰርቆና አጭበርብሮ ተቃዋሚዎችን አሸነፍኩ ብሎ የተናገረውን አንቀበለውም በማለት። ከ 4 ሺህ በላይ የከተማዋ ነዋሪ የተሳተፈበት ሰላማዊ ሰልፍ ግንቦት 25/2007 ዓ/ም ማካሄዱን የደረሰን መረጃ አመለከተ፣
ተቃውሞው ኢህአዴግ በጎንደር ከተማ 83% ድምፅ አግኝቻለሁ ብሎ የለጠፈውን ፅሁፍ ተከትሎ የተካሄደ መሆኑና ሰልፈኞቹ ያሰሙት ከነበረው መፈክርም “እኛ ለተቃዋሚዎች እንጂ ኢህአዴግን አልመረጥንም፤ የህዝቡን ድምፅ የሰረቁ የገዢው መንግስት ካድሬዎች መጠየቅ አለባቸው” የሚሉና ሌሎችም ሲሆኑ በተለያዩ የአገራችን አካባቢዎችም ድምፃችን ተነጥቀናል በማለት ብሶቱን እያሰማ ያለው ህዝብ ሰሚ ጀሮ ማጣቱን ባለፈው የዜና እወጃችን በተደጋጋሚ መግለፃችን ይታወቃል፣
No comments:
Post a Comment