Monday, June 8, 2015

የኢትዮጵያ አየር ኃይል ምስጢሮች ክፍል ሁለት


የኢትዮጵያ አየር ኃይል ምስጢሮች
ክፍል ሁለት
===============================የኢትዮጵያ አየር ኃይል ምስጢሮች
ክፍል ሁለት
ህዝባዊ ወያኔ ሓርነት ትግራይ ረጅም አመታትን በፈጀ ድካምና ልፋት የተገነባውን የኢትዮጵያ አየር ኃይል በአንድ ጀምበር ከመሰረቱ ሲንደው የቴክኒካዊና አካዳሚያዊ ዕውቀቶች በአዝጋሚ የጉዞ ሂደትና መወራረሶች የሚመጡ መሆናቸውን መቶ በመቶ ዘንግቶታል፡፡ ወይንም ጭራሹኑ አያውቀውም ነበር ማለት ነው፡፡
በመሆኑም ህዝባዊ ወያኔ ሓርነት ትግራይ አየር ኃይሉን አፈራርሶት ከዜሮ በመጀመር የመገንባት ሙከራ ሂደቱን የጊዜ ዑደቱን እንዳይጠብቅ አስገድዶታል፡፡ ክፍተቱን ለመሙላት ሲባል ከበረሃ የመጡ ታጋዮችን ወደ ውጭ ልኮ ከ3-9 ወራት ብቻ የፈጀ ስልጠና ወስደው እንዲመለሱ አድርጓል፡፡
ከህወሓት በፊት በነበሩት መንግስታት የስልጣን ዘመናት ግን ወደ ውጭ አገር የሚላኩ ሰልጣኖች ከ2-3 ዓመታት ትምህርት ላይ ቆይተው ይመለሱ ነበር፡፡ በመሆኑም ምንም እንኳን የችግሩ ገፈት ቀማሽና ዋናው ተጎጅ አገሪቱ ብትሆንም ራሱ ህወሓት ብዙ ዋጋ ከፍሎበታል፡፡
ህዝባዊ ወያኔ ሓርነት ትግራይ አየር ኃይሉን አፈራርሶ እንደገና ለመስራት በሞከረበት ወቅት ሞያተኞችን ለማሰልጠን ምልመላ ሲያደርግ በእጣት ከሚቆጠሩት እጅግ በጣም ጥቂት የብአዴን፣ የኦህዴድና ደህዴን አባላት በስተቀር በራሱ ታጋዮች ብቻ ሞልቶታል፡፡ ምልመላው በአብዛኛው አካላዊ ብቃታቸውና አእምሯዊ ሁኔታቸው ጥያቄ ውስጥ የገባ ታጋዮች የተካተቱበት ነበር፡፡ ጆሯቸው በከፊል የማይሰማ፣ የቀለም ዓይነ ስውርነት ያለባቸው፣ በአጭርና ረጅም እይታ ችግሮች የተጠቁ፣ እግሮቻቸው አጭርና ረጅም የሆኑ በርካቶች ነበሩ፡፡ ከእነዚህ ታጋዮች ሰለሞን ገ/ስላሴ አንዱ ነው፡፡ባጠቃላይ ምልመላውን በተመለከተ ዋነኛው መስፈረት አካላዊና ስነ-ልቦናዊ ጤንነትን እንዲሁም በተጨማሪ አካዳሚያዊ ብቃትን ያካተተ ሳይሆን ዋነኛው መመዘኛ ፖለቲካዊ ታማኝነት ነበር፡፡ በመሆኑም መጨረሻው አላማረም፡፡ አብዛኞቹ ከፍተኛ ወጭ ተደርጎ ከሰለጠኑ በኋላ የተማሩትን ሞያ ጨርሶ ተግባራዊ ማድረግ ባለመቻላቸው ወድቀዋል፡፡
በ1988 ዓ.ም በሞጆ ሰማይ ላይ ይበር የነበረ አውሮፕላን በድንገት ከገበያ ላይ ወድቆ ብዙ የሰው ህይወት አጥፍቷል፤ በርካታ የአገር ሀብት አውድሟል፡፡
በቅርቡ ደግሞ በሐምሌ ወር 2005 ዓ.ም እጅግ በጣም በውድ ዋጋ የተገዛውን ኤል 100 የመጓጓዣ አውሮፕላን ከሶማሊያ ወደ ኢትዮጵያ እንዲያበር የተመደበው ሰለሞን ገ/ስላሴ አውሮፕላኑ ገና መሬት ሳይለቅ በማኮብኮብ ላይ እያለ ከሜዳ አውጥቶ በርካታ ንብረት እንደጫነ አጋይቶታል፡፡
እነዚህ ታማኝነትን መሰረት አድርገው ለአብራሪነት የተመለመሉ የህወሓት ታጋዮች በረራ በሚማሩበት ወቅት እርስበርስ እየተጋጩ እና አውሮፕላኑን ከሰማይ ወደ ምድር በማውረድ እየከሰከሱ አጥፍቶ ጠፊ በመሆን ከጎናቸው ተቀምጠው በነበሩ አስተማሪዎቻቸው ላይ ጭርም አደጋ በማድረስ ምርጥ ምርጥ የቀድሞ አየር ኃይል አብራሪዎችን ህይወት ቅርጥፍ አድርገው በልተዋል፡፡ በእርግጥ በብቃት ማነስ ብቻ ሳይሆን ጌታቸው ህወሓትም የቀድሞ አየር ኃይል አብራሪዎችን ለማጥፋት የሸረበው ስውር ሴራ እንደነበር ጭምርም ይጠረጠራል፡፡
የአየር ኃይሉ ትምህርትና ስልጠና በየጊዜው ስለሚከለስና ስለሚቀየር ምንም አይነት የዕውቀት መወራረስ ባለመኖሩ ምክንያት ክፍተቱ እየሰፋና ችግሩ በእጅጉ እየከፋ መጥቷል፡፡ በቅርቡ በ2004 ዓ.ም የሚግ 23 አብራሪ የነበረው ሻምበል ማዕረገ ህይወት ገዛኸኝ የሚያበረው አውሮፕላን ከቆመበት በሌላ ከሰማይ በመጣ አውሮፕላን ተገጭቶ ህይወቱ አልፏል፡፡ ሻምበል ማዕረገ ህይወት ገዛኸኝ ለበረራ ኤስ.ኤፍ 260 አውሮፕላን ውስጥ ተቀምጦ ለመነሳት በማኮብኮቢያ ሜዳው ላይ ሆኖ ዝግጅት እያደረገ ባለበት ሁኔታ ሻለቃ ወልዱ ኬዳ የተባለ አብራሪ የሚያበረውን አውሮፕላን ለማሳረፍ አስቦ ከላይ እያምዘገዘገ በማምጣት ገጭቶ ገድሎታል፡፡ ሻለቃ ወልዱ ኬዳ ያበረው የነበረውን አውሮፕላን ለማሳረፍ ገና በማንዣበብ ላይ እያለ የአየር ትራፊክ ተቆጣጣሪዎች የሻምበል ማዕረገ ህይወት አውሮፕላን አኮብኩቦ ከሜዳው እስኪነሳ መጠባበቅ እንዳለበት እያስጠነቀቁት ነው ባልተጠበቅ ሁኔታ በችሎታ ማነስ ምክንያት አውሮፕላኑን ላዩ ላይ የጣለበት፡፡
ሻምበል ማዕረገ ህይወት ገዛኸኝ በቴክኒካዊና አካዳሚያዊ ዕውቀቱ የላቀና በ1999 ዓ.ም ሶማሊያ ውስጥ በተደረገው ጦርነት የተሰጠውን ግዳጅ የተወጣና አብራሪ አጥቶ እስካሁንም ድረስ አየር ኃይል ጠቅላይ ሰፈር ግቢ ውስጥ ቆሞ ሳር የበቀለበትን ሱ 25 አውሮፕላን ለማብረር የሚያስችል አቅም ያለው ብቁ ሞያተኛ ነበር፡፡ ነገር ግን የሞያ ብቃት ማነስና የስነ-ምግባር ችግር የሚታይበት ሻለቃ ወልዱ ኬዳ ሙሉ በሙሉ አጥፊ ሆኖ እያለ አደጋው የደረሰው ሟች በፈፀመው ስህተት ምክንያት ነው ተብሎ በሀሰት ምስክር ወንጀሉ በጦር ፍርድ ቤት ችሎት ተድበስብሶ አልፏል፡፡
አየር ኃይል አብራሪዎቹ ብቻ ሳይሆኑ አውሮፕላኖቹም ከፍተኛ የሆነ ቴክኒካዊ ችግር አለባቸው፡፡ ለአገልግሎት የሚውሉት የበረራ ቁሳቁሶች ጊዜ ያለፈባቸውና ብልሽት ፈፅሞ የማይጠፋባቸው ናቸው፡፡
መቶ አለቃ ሙሉጌታ ጋሻው የተባለ የሻምበል ማዕረገ ህይወት ገዛኸኝ የአጎት ልጅና አብሮ አደግ ያበረው የነበረው ኤል 39 አውሮፕላን በአየር ላይ እንዳለ የሞተሩ ጉልበት ዜሮ ሆኖበት /አይድል ገብቶ አልወጣም ብሎት/ በጃንጥላ ለመውረድ ሲሞክር ጃንጥላውም አልዘረጋ ብሎት በብርሃን ፍጥነት ወደታች በመምዘግዘግ እንደ እንቁላል መሬት ላይ ተፈጥፍጦ ህይወቱ አልፋለች፡፡ የህወሓት አየር ኃይል ችግሮች እንዲህ እጥፍ ድርብና ውጤታቸው እጅግ በጣም ዘግናኝ ነው፡፡
በአየር ኃይሉ ውስጥ የህወሓት ሰዎች በፈጠሩት ችግር ምክንያት በተከሰተው እጥፍ ድርብ አደጋ ህይወቱን የከፈለው መቶ አለቃ ሙሉጌታ ጋሻው አለ የሚባል ብቸኛው የሱ 27 አውሮፕላን አብራሪ ነበር፡፡
ምንም እንኳን ህዝባዊ ወያኔ ሓርነት ትግራይ አየር ኃይሉን የራሱን ታጋዮች ብቻ ሰግስጎ በመሙላት በቁጥጥሩ ስር የማድረግ ዕቅድ ቢኖረውም በቴክኒካዊ፣ አካዳሚያዊ፣ ወታደራዊ አስተዳደር ስጋና ደም አዋቅሮ ነብስ የመዝራት አቅም ግን ጨርሶ የለውም፡፡ በመሆኑም በኢትዮ-ኤርትራ ጦርነት ጊዜ አገሪቱን እንደተቆጣጠረ ጠራርጎ አስወጥቷቸው በዓለም ዙሪያ ተበታትነው ለሚገኙት 200 የጦር አውሮፕላን አብራሪዎች የተማፅኖ ጥሪውን አቅርቦላቸዋል፡፡
ህወሓት አገሪቱን ከተቆጣጠረበት ጊዜ 1983 ዓ.ም ወዲህ በአየር ኃይሉ ውስጥ የዕውቀት መወራረስ ባለመኖሩ ከጊዜ ወደ ጊዜ እድገቱ እያሽቆለቆለ መጥቶ ዘሬ አለ የለም ከሚባበት ደረጃ ላይ ደርሶ ይገኛል፡፡ ህወሓት የፈጠራቸው አብዛኞቹ የአየር ኃይል አብራሪዎች የሚታወቁት በብልፅግናቸው እንጂ በሞያቸው ባለመሆኑ በተተኪዎቻቸው ዘንድ በአርአያነት ሊጠቀሱ በሚችሉበት ደረጃ ላይ አይገኙም፡፡ ሜጀር ጀነራል አምሃ ደስታ፤ ሜጀር ጀነራል ፋንታ በላይ፣ ብርጋዴር ጀነራል ሶሎሞን በጋሻውና ብርጋዴር ጀነራል ለገሰ ተፈራ የመሳሰሉ ዕውቅና ምርጥ ምርጥ አብራሪዎችን፣ አስተማሪዎችንና መሪዎችን የፈጠረው የኢትዮጵያ አየር ኃይል ማህፀን ዛሬ ጨርሶ መክኖ አንድ እንኳን ስሙ በመልካም ሊጠራ የሚችል ሰው አላፈራም፡፡ የቆዩ ነባር እሴቶቹም ተንደው ታሪክ አልባ ብቻ ሳይሆን ጥርስ የሌለው አንበሳም ጭምር ሆኖ ይገኛል፡፡
ህወሓቶች የሩሲያ ዜግነት ያላቸው ቅጥረኛ አብራሮዎችን ያውም ደግሞ እዚህ ግባ የማይባል የጦር ሜዳ ድል የራሳቸው ታጋዮች ታሪክ ሲያደርጉት በግልፅ እየታዩ ነው፡፡
የህወሓት አብራሪዎች የስርቆት፣ ተራ የማጭበርበርና ስውር ሴራ የመዶለት እንጂ ራሳቸው የፈፀሙት ለትውልድ ሊተላለፍ የሚችል ቅንጣት ያክል እንኳን ታሪክ የላቸውም፡፡ በፀረ-ህዝብነት የቆመውን ህወሓት የስልጣን ፍላጎት ከሟሟላት በዘለለ ለኢትዮጵያ ያበረከቱት በጉልህ ሊጠቀስ የሚችል አዎንታዊ አስተዋፅኦ አላበረከቱም፡፡ ሰለሞን ገብረ ስላሴን የመሳሰሉ ሀብት የማካበት ስርቆት ስራ ላይ ተጠምደው በረዳት አብራሪነት ብቻ ለ14 ዓመታት በማሳለፍ በሞያቸው ባለመትጋት የሚታወቁ የህወሓት ሰዎች እልፍ አዕላፍ ናቸው፡፡
በህወሓት ስር በሚገኘው አየር ኃይል ውስጥ "ቅልብ አብራሪዎች" እየተባሉ የሚጠሩ አባላት ይበዛሉ፡፡ እነዚህ በአየር ኃይሉ ጠ/መምሪያ ውስጥ በብዛት እንደሚገኙ በግልፅ የሚታወቁት "ቅልብ አብራሪዎች" የመጓጓዣ አውሮፕላን ኃላፊ ሆነው አውሮፕላን ማብረር የማይችሉ፣ ኢንስትራክተር ፓይለት ሆነው በተግባር ሲመዘኑ ዜሮ የሆኑ፣ የውጊያ ሄሊኮፕተር ስኳድሮን አዛዥ ሆነው ሄሊኮፕተር ላይ መሳፈር አንጂ ሄሊኮፕተር ለውጊያ ማንቀሳቀስ የማይችሉ፣ የበረራ ትምህርት ቤት ኃላፊ ሆነው ማስተማር የተሳናቸው ናቸው፡፡ ነገር ግን በሌሎች አብራሪዎች ደምና ላብ ነግሰው እየኖሩ ነው፡፡
ከዋና ዋና ቅልብ አብራሪዎች መካከል የቀድሞውን የአየር ሃይል አዣዥ ሜጀር ጀነራል ሞላ ኃይለ ማርያምን ጨምሮ የሰሜን አየር ምድብ አዛዥ ኮሎኔል ለምለም ኃይሌ፣ የምስራቅ አየር ምድብ አዛዥ ኮሎኔል አበበ ተካየ፣ ትራንስፖርት ኃላፊ የሆነው ኮሎኔል ታደለና ኮሎኔል ንጉሴ መስፍን ይገኙበታል፡፡
የምስራቅ አየር ምድብ አዛዥ ኮሎኔል አበበ ተካ በ1999 ዓ.ም ሶማሊያ ውስጥ በተደረገው ጦርነት ውስጥ ተዋጊ ሄሊኮፕተር ለማብረር ሞክሮ መተኮስ ያለበትን ሮኬት እንዳለ ወደ ምድር ወርውሮ ብቻ ነብሴን አውጭኝ ሸምጥጦ በአየር ምድቡ አባላት ዘንድ የአንድ ሰሞን መሳቂያና መሳለቂያ ሆኖ ከርሞ ነበር፡፡ በዶላር መሸቀጥና በኮንትሮ ባንድ ንግድ ስራ ተጠምዶ ሞያውን ለማሻሻል ፋታ ያላገኘው ኮሎኔል አበበ ተካ የፈፀመው ድርጊት ክላሽንኮቭን ከመተኮስ ይልቅ እንዳለ ከነጥይቱ ወደ ጠላት አምዘግዝጎ እንደመወርወር ይቆጠራል፡፡
የአየር ኃይሉን የአሰለጣጠን ሂደት በተመለከተ ለስልጠና ተመልምለው የሚገቡ የህወሓት ታጋዮች እስተማሪወቻቸው የሆኑትን የቀድሞ ሠራዊት አባላት ስለሚንቁ የመማር ማስተማር ሂደቱ ከመሰረቱ ጤናማ አይደለም፡፡ እነዚህ ከመሬት ተነስተው የቀድሞ አየር ኃይል አባላት ስለነበሩ ብቻ አስተማሪዎቻቸውን የሚንቁ የህወሓት ታጋዮች ሁሉም ማለት በሚቻል ሁኔታ የሚሠጣቸውን ትምህርት በቀላሉ የመረዳት ችሎታ የሚጎድላቸውና በፈተና ደጋግሞ የመውደቅ አባዜ የተጠናወታቸው ናቸው፡፡ በፈተና ሲወድቁም "የአመለካከት ልዩነት ችግሮች እንጂ እኛ በዕውቀት ከእናንተ አናንስም" በማለት እነዚያኑ መከረኛ አስተማሪዎቻቸውን ያሸማቅቃሉ፡፡ አመራሮችም ጣልቃ እየገቡ የቀድሞው አየር ኃይል አባላት የነበሩ አስተማሪዎችን በማስፈራራትና በማንገራገር የወደቁትን ታጋዮች ደጋግመው እንዲፈትኗቸው ቀጭን ትዕዛዥ እየሰጡ ጫና በማሳደር ስቃያቸውን ያበዙታል፡፡
ኩረጃ በአየር ኃይል ውጥ እንደ ባህል እየተቆጠረ መጥቷል፡፡ ሰልጣኝ የህወሓት ታጋዮች ስለ አውሮፕላኑ ሞተርና የአካል ክፍል ሳይማሩ ዘለው በአብራሪነት ስራ ላይ የሚሰማሩበት ዕድል ሰፊ ነው፡፡ እንደምንም ተመርቀው አብራሪ ሲሆኑ ደግሞ በችሎታ ከረዳት አብራሪያቸው እጅግ በጣም ያነሱ ሲሆኑ በተደጋጋሚ ታይተዋል፡፡
በአየር ኃይሉ ውስጥ ከዝቅተኛ እስከ ከፍተኛ የኃላፊነት ቦታ የስልጣን ወንበር ይዘው የሚገኙት የህወሓት ሰዎች ብቻ መሆናቸው አገር ያወቀው ፀሐይ የሞቀው ጉዳይ ነው፡፡ የአሳ ግማቱ ከአናቱ እንዲሉ የህወሓት ታጋይ የሆኑ የአየር ኃይሉ አባላት የሞያ ስነ-ምግባር ጉድለት፣ ዕውቀት አጠርነትና ሞራለቢስነት የአመራሮቹ ውድቀት ነፀብራቅ ነው፡፡ በአመራር ደረጃ የሚገኙ የህወሓት መኮንኖች አየር ኃይሉን የወንጀል ቋት አድርገውት ይገኛሉ፡፡ በኢትዮጵያ ምድር ላይ ሚያደርጓት እያዳንዷ እርምጃቸው የግፍ ዱካ ብቻ ትታ የምታልፍ ናት፡፡
ምንም እንኳን የህወሓታዊነት ምንጩ ድንቁርና እና ባዶነት መሆኑ ለማንም የተሰወረ ባይሆንም የመኮንኖቹ ለቦታው በሚመጥን ዕውቀት ላይ የተመሰረተ አመራር አለመኖር የፈጠረው ችግር ተዘርዝሮ የሚያልቅ አይደለም፡፡
ሜጀር ጀነራል አበበ ተክለ ኃይማኖት /ጀቤ/ የአየር ኃይሉ አዛዥ በነበረበት ዘመን በአሉዌት ሄሊኮፕተር ወደ ጋምቤላ ሲጓዝ ከአብራሪው ጎን ተቀምጦ ሄሊኮፕተሯን ለማብረር እንደሚፈልግ ይጠይቀዋል፡፡ አብራሪው ጀነራሉን በመፍራት በዚህ ላይ ደግሞ ከፍተኛ አለቃው ነው ያለምንም ማንገራገር ቦታውን ለቀቀለት፡፡ ከዚያም ጀነራሉ ከአብራሪው የወሰዳትን አሉዌት ሄሊኮፕተር ወዲያውኑ አውርዶ ምድር ላይ እንደ እምቧይ አፈረጣት፡፡ አበበ ተ/ኃይማኖት የአየር ኃይል ተሿሚ እንጂ ሞያተኛ አልነበረም፡፡ የህወሓት ጀነራሎች ቅሌትና የስነ-ምግባር ጉድለት እንደዚህ ጥጉን ያለፈ ነው፡፡
በአየር ኃይል የሚያማምሩ ቢሮዎች ውስጥ ከመጎለትና የዘነጡ የቆዳ ወንበሮችን ከማሞቅ የዘለለ ሚና የሌላቸው የህወሓት መኮንኖች በስርቆት፣ አድሏዊ አሰራሮችና ሴራ በመጎንጎን የተካኑ ናቸው፡፡ የአገዛዙ መገለጫ የሆነው ጎሰኝነት በእነሱ ዘንድ ወደ መንደር ቡድንተኝነት ሸለቆ መቀመቅ የወረደ ነው፡፡
የአሜሪካ መንግስት ለአየር ኃይሉ አባላት በጠቅላላ ስልጠና ሊሰጥ ስምምነት ላይ ተደርሶ ለበረራ ስልጠናው የሚያስፈልገውን ነዳጅ አየር ኃይሉ በራሱ ገንዘብ ወጭ አድርጎ እንዲገዛና በኋላ ላይ በደረሰኝ እንደሚያወራርዱላቸው ነገሯቸው፡፡ ይህን ያሉት የአሜሪካ መንግስት ሰዎች ናቸው፡፡ ከዚያም የአየር ኃይሉ አመራሮች ገንዘቡ በጥሬው ካልተሰጣቸው በስተቀር የተባለውን ነዳጅ በሚያስፈልገው መጠን ሊገዙ የሚችሉበት ቆይቶ የሚወራረድ ሂሳብ የሚሆን ወጭ የገንዘብ ካዝናቸው ውስጥ እንደሌላቸው ቅሬታ አቀረቡ፡፡ በመጨረሻ ከብዙ ውጣ ውረድ በኋላ የአሜሪካ መንግስት ሰዎች ዶላሩን እንዳለ አሸከሟቸው፡፡ ዋና አዛዥ የነበረው ሜጀር ጀነራል ሞላ ኃይለ ማርያም፣ ኮሎኔል ሙሉጌታ ወልደ ሩፋኤል እና ኮሎኔል ደሳለኝ አበበ ተመሳጥረው ነዳጁን ከዚያው ከአየር ኃይሉ ዴፖ በመሙላት ዶላሩን በመከፋፈል ወደ ግል ኪሳቸው አስገብተውታል፡፡ አየር ኃይሉ ከምድር ኃይሉ ጋር ወደ ሶማሊያ በዘመተ ቁጥር ከተባበሩት መንግስታትም ሆነ ከሌሎች ሀብታም አገራት በቀጥታ ለሰራዊቱ የሚከፈለውን ገንዘብ በምስራቅ አየር ምድብ አዛዥ ኮሎሎኔል አበበ ተካ አማካኝነት ተረክበው ኤታማጆር ሹሙን ጀነራ ሳሞራ የኑስን ጨምሮ ሌሎችም የመከላከያ ከፍተኛ ኃላፊዎች ይከፋፈሉታል፡፡ ከዚያም ለዘመቻው የሚያስፈልገውን ወጭ ከመከላከያ ፋይናንስ በማውጣት ይሸፍኑታል፡፡ የግንባታ ቁሳቁሶችን ከአየር ኃይል ግቢ በድብቅ በማስወጣት የግላቸውን ቪላ የገነቡትን ቤት ይቁጠራቸው፡፡
ከቻርተር በረራዎች /ከኪራይ/ የሚገኘውን ወፈር ያለ ገቢ ወደየ ግል የባንክ ሂሳባቸው በቀጥታ ይጨምሩታል፡፡ ለምሳሌ ባንድ ወቅት "የናሽናል ጂኦግራፊ" አዘጋጆች ወደ ኢትዮጵያ መጥተው ሄሊኮፕተር በመከራየት ወደ ኤርታሌ አምርተው ነበር፡፡ ታድያ የህዝብ ንብረት ከሆነው ሄሊኮፕተር ኪራይ የተገኘውን ገቢ የአየር ኃይሉ ቁንጮ የሆኑት ህወሓቶች በመዝረፍ ጮማ ቆርጠውበታል ዊስኪ ተራጭተውበታል፡፡
ነገር ግን አየር ኃይሉ የበረራ ትጥቆችን እንኳን የሟሟላት አቅም የለውም ተብሎ በየአውደ ውጊያውና በበረራ ልምምድ ላይ በየጊዜው ከሚሞቱ አብራሪዎች በድን ላይ ጃኬቶች ሳይቀሩ ተወስደው በአልኮል እየተወለወሉ አገልግሎት ላይ እንዲውሉ ይደረጋል፡፡ ለሰላም ማስከበር ተልዕኮ ወደ ዳርፉር የሄዱት አባላት በላብ ያደፉና በእርጅና ምክንያት የተበጣጠሱ የበረራ ትጥቆችን ይዘው ነበር፡፡ አንድ አንሶላ ለሁለት ቀደው እንዲካፈሉ ተሰጥቷቸዋል፡፡ የታደላቸው አልጋና ፍራሽም ቢሆን ለህፃን ልጅ መኝታ የሚሆን ነበር፡፡
የበረራ ትጥቆች በእርዳታም ሆነ በግዥ ከውጭ በመጡ ጊዜ በአመራር ደረጃ ያሉና የህወሓት ሰዎች ብቻ የሚከፋፈሉት ሲሆን በተለይም ጃኬትና መነፅሩን ለሌሎች በቋንቋ ልዩነታቸው ብቻ ባዕድ ሆነው የተለዩ ባይተዋር አባላት በውድ ዋጋ ይሸጡላቸዋል፡፡ በመሆኑም በበረራ ትጥቅ አለመሟላት ብቻ ቁጥር ስፍር የሌላቸው አደጋዎች ደርሰዋል.

No comments:

Post a Comment