Wednesday, May 23, 2018
Monday, May 21, 2018
Friday, May 11, 2018
አቶ አባይ ጸሃዬን ጨምሮ አራት ከፍተኛ የመንግስት ባለስልጣናት ተባረሩ (ኢሳት ዲሲ–ግንቦት 3/2010)አቶ አባይ ጸሃዬን ጨምሮ አራት ከፍተኛ የመንግስት ባለስልጣናት ተባረሩ። ለኢሳት በደረሰው የስንብት ደብዳቤ ላይ እንደተመለከተው አቶ አባይ ጸሀይን ጨምሮ አራቱ ባለስልጣናት ከስልጣናቸው የተነሱት ሚያዚያ 11 እና 12/ 2010 ጠቅላይ ሚኒስትር አብይ አህመድ በጻፉት ደብዳቤ ነው። በሁለት ተከታታይ ቀናት የስንበት ደብዳቤ የደረሳቸው ባለስልጣናት ከአቶ አባይ ጸሐዬ በተጨማሪ ጠቅላይ ዐቃቢ ህጉ አቶ ጌታቸው አምባዬ፣ የመለስ አካዳሚ ፕሬዝዳንት አቶ ቴድሮስ ሐጎስ፣ እንዲሁም የኢንሳ ምክትል ዳይሬክተር ኮሎኔል ታዜር ገብረ እግዚአብሔር ናቸው። ለአቶ አባይ ጸሐዬ ሚያዚያ 12/ 2010 ከጠቅላይ ሚኒስትር አብይ አሕመድ የተጻፈው ድብዳቤ ከመጋቢት 09/2006 ጀምሮ በሚኒስትር ማዕረግ የፖሊሲ ጥናትና ምርምር ማዕከል ዋና ዳይሬክተር ሆነው በማግልግል ላይ መሆናቸውን ያስታውሳል። ላበረከቱትም አስተዋጽኦ ምስጋና በማስቀደም ከሚያዚያ 12/2010 ጀምሮ ከሃላፊነት የተነሱ መሆናቸውን ይገልጻል። ለሌላው የሕወሃት አመራር ለአቶ ቴድሮስ ሃጎስ በተመሳሳይ ቀን የተጻፈው የስንብት ደብዳቤ አቶ ቴድሮስ ሃጎስ ከህዳር 15/2008 ጀምሮ የመለስ ዜናዎ ስራ አመራር አካዳሚ ፕሬዝዳንት ሆነው በማገልገል ላይ መሆናቸውን ይገልጻል። ከምስጋና ጋርም ከሚያዚያ 12/2010 ጀምሮ ከሃላፊነት የተነሱ መሆናቸውን ደብዳቤው ያመለክታል። የሃገሪቱ የሳይበር የስለላ ተቋም ማለትም ኢንሳ ምክትል ዳይሬክተር ለሆኑት ለኮለኔል ታዜር ገብረእግዚአብሔር በርሔ የተጻፈውም የስንብት ደብዳቤ ከየካቲት 14/2006 ጀምሮ በዚሁ ሃላፊነት ላይ እንደነበሩ በመዘርዘር ከሚያዚያ 12/2010 ጀምሮ ከሃለፊነታቸው መነሳታቸውን ከምስጋና ጋር ይገልጻል። ከሶስቱ የህወሃት ሰዎች በተጨማሪ አንድ ቀን ቀደም ብሎ ለብአዴኑ አቶ ጌታቸው አምባዬ የተጻፈው የስንብት ደብዳቤም ከመስከረም 25/2010 ጀምሮ በጠቅላይ አቃቤ ሕግነት ሲያገለግሉ መቆየታቸውን በማስታወስ ከሚያዚያ 11/2010 ጀምሮ ከምስጋና ጋር ከሃላፊነት መነሳታቸውን ያመለክታል። እነዚህ ከሃላፊነት ተነሱ ከተባሉት ግለሰቦች ሶስቱ ዛሬ የትና በምን ሃላፊነት ላይ እንዳሉ የሚታወቅ ነገር የለም። የስንብት ደብዳቤ የደረሳቸውና የኢንሳ ምክትል ዳይሬክተር የነበሩት ኮለኔል ታዜር ገብረእግዚአብሔር ግን ትላንት በተሰጠው ሹመት የከተማ ልማትና ቤቶች ሚኒስትር ዴኤታ ሆነው መሾማቸው ተሰምቷል። ሆኖም ከስኳር ፕሮጀክት ጋር በተያያዘ በቢሊየን ብር ስርቆት ጉዳይ የሚነሱት አቶ አባይ ጸሃዬ እንዴት በሕግ አይጠየቁም የሚሉ ድምጾች በመሰማት ላይ ናቸው። የኢንሳ ዋና ዳይሬክተር ሜጀር ጄነራል ተክለብርሃን ወልደ አረጋይ እና የሜቴክ ዋና ዳይሬክተር ሜጀር ክንፈ ዳኘው በሌሎች ሰዎች መተካታቸው ይታወሳል። ሁለቱም የህወሃት ታጋዮች ናቸው።
Tuesday, May 1, 2018
Thursday, April 26, 2018
ሰበር_ዜና ዘመቻ_ነበሮ" ዘመቻ ገዛኸኝ ነብሮ " በሚል ስም በተሰየመ ዘመቻ የአግ7 አርበኞች የህወሓት ወታደራዊ ካምፕ ላይ ጥቃት ፈፀሙ!
ሚያዚያ 17 ቀን 2010 ዓም ከምሽቱ 4:25 ሲሆን የአግ7 አርበኞች በጎንደር ከተማ አዘዞ የሚገኘውን የህወሓት ወታደራዊ ካምፕ ላይ ጥቃት የፈፀሙ ሲሆን በዚህ ጥቃት በርካታ የህወሓት ወታደሮች ጉዳት ደርሶባቸዋል፡፡
የተኩስ ልውውጡ ከምሽቱ 4:20 እስከ ለሊት 7:40 ማለትም ለ 3:20 ያክል የቆየ ሲሆን በካምፑ የሚገኙ 3 በሮች ማለትም ወደ ጎንደር አዘዞ ድልድይ ወደ ጭልጋ አዲሱ አውቶብስ ማረፊያ እና ከላይ ወደ ሎዛ ማሪያም በኩል ባሉ 3 የጥበቃ ክፍሎች ላይ ጉዳት ደርሷል፡፡ በዚህ ካምፕ የህወሓት የምዕራብ ዕዝ 42ኛ ክፍለጦር መገኛ ሲሆን የአዛዡ ጄኔራል ሲሳይ ጥበቃ ክፍልም ጉዳት ደርሶበታል፡፡ ይህ "ዘመቻ ነብሮ" ታቅዶበትና ልዩ ዝግጅት ተደርጎበት በተለይም "የአርበኛን ደም አርበኛ ነው የሚመልሰው" በማለት አርበኛ ገዛኽኝ ገብረመስቀል (ነብሮ) ከተሰዋበት ቀን ጀምሮ በሰሜን ጎንደር ቀጠና የሚንቀሳቀሱ የአግ7 አርበኞች በዚህ ጀግና ስም አንድ የተመረጠ ዘመቻ ለማካሔድ በመነጋገር የተሰራ አኩሪ ስራ ነው፡፡ አሁን እየደረሰን ባለው መረጃ የተኩስ ልውውጡ በምሽት በመሆኑ የደረሰው ጉዳት ከፍተኛ ሊሆን እንደሚችል ቢገመትም በወቅቱ 2 አንቡላንሶች የሞቱ እና የቆሰሉ ወታደሮቹን እያነሱ እንደነበር የአይን እማኞች አረጋግጠዋል በነበረው ውጊያ በአይን የታዩ የሞቱ የህወሓት ወታደሮች 13 ሲሆኑ ቆስለው ጎንደር ሆስፒታል የገቡ ደግሞ 9 ናቸው፡፡ በዚህ የተኩስ ልውውጥ የፍንዳታ እና ከፍተኛ ድምፅ ይሰማ እንደነበር እንዲሁም ከካምፑ ውስጥ አንድ ክፍል በፍንዳታው እንደፈረሰ የአይን እማኞች ገልፀዋል፡፡ ይህን ዘመቻ የተሳተፉ የቁርጥ ቀን ጀግኖች በሰላም ወደ ቀጠናቸው ተመልሰዋል፡፡ "አርበኛ ቢሰዋም እሱ የተሰዋለትን ዓላማ ከግብ የማድረሱ ትግል ይቀጥላል" በሚል መርህ ተከታታይ ድሎች ይኖራሉ፡፡ በአካባቢው ያለውን ዝርዝር ሁኔታ እየተከታተልን እናሳውቃለን፡፡ ድል ለሕዝብ !! የአግ7 ዘመቻ ነፃ ትውልድ፡፡
Tuesday, April 24, 2018
በደል ይረሳል ወይስ ይለመዳል! (የአርበኞች ግንቦት 7 ድምፅ ሬዲዮ)
የዕለተ ማክሰኞ ሚያዚያ 16 ቀን 2010ዓ.ም. ፕሮግራሞቻችንየዕለቱ አርዕስተ ዜና
* የጀግናው የገዛኧኝ ገብረ መስቀል (ነብሮ) መሰዋት የነጻነት ጉዞአችንን ይበልጥ እንዲጠናከር ተጨማሪ አደራ ጥሎብን አልፏል ሲሉ በደቡብ አፍሪካ የሚገኙ ኢትዮጵያዊያ ተናገሩ።
* ህወሓት የሚዘውረው ኢህአዴግ የፖለቲካ እስረኞችን እፈታለሁ ቢልም እስከ አሁን በተለያዩ እስር ቤቶች በርካታ ታሳሪዎች ያለፍርድ ታስረው ይገኛሉ ተባለ።
* ኮማንድ ፖስቱ ለጠቅላይ ሚኒስተሩና ለፖለቲካው አመራር ሪፖርት አላቀርብም ማለቱ ተሰማ።
፠በደል ይረሳል ወይስ ይለመዳል – አርበኛ ታጋይ ሜሮን አለማየሁ
የተሰኘው መሰናዷችን ትከታተሉት ዘንድ ግብዣችን ነው
ኢትዮጵያ ለዘላለም በክብር ትኑር !!!
አንድነት ሃይል ነው!
Monday, April 23, 2018
Sunday, April 22, 2018
Saturday, April 21, 2018
ኮማንድ ፖስቱ ለጠቅላይ ሚኒስተሩና ለፖለቲካው አመራር ሪፖርት አላቀርብም ማለቱ ተሰማ (የጸጥታ ኃይሎች ዜና (ሚያዚያ 13, 2010 ዓ.ም)
በፓርላማ ውድቅ የተደረገው ነገር ግን ህወሃት በጉልበት ያጸደቀው የአስቸኳ ጊዜ አዋጅ ከተደነገገበት የካቲት 9/2010 ዓ.ም ጀምሮ አገራችን ሙሉ በሙሉ በወታደራዊ አገዛዝ ስር ወድቃ እየማቀቀች እንደሚገኝ ይታወቃል። በመሆኑም ይህን የአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ በበላይነት የሚያስፈጽሙትና የሚቆጣጠሩት ጠቅላይ ሚኒስተሩ፣የመረጃና ደህንነት መስሪያ ቤቱ፣ የመከላከያ ሚኒስተሩ፣ የመከላከያ ኢታማዦር ሹም እንዲሁም የፌድራል ፖሊስ ኮሚሽነር ናቸው።
በዚህም መሰረት በአስቸኳይ ጊዜ አዋጁ የተገኙ ውጤቶች፣ የጠፉ ጥፋቶች፣በአጠቃላይ የአስቸኳይ ጊዜ አዋጁን አፈጻጸም እንዲገመገሙ በየቀጠናው የተሰበሰቡ መረጃዎች ተጠቃለው ለጠቅላይ ሚኒስተሩ ዝርዝር ሪፖርት እንዲደረግ ያዛል።
ይሁን እንጂ ኮማንድ ፖስቱን በበላይነት የሚቆጣጠሩት የመከላከያ ሰራዊቱ አዛዦች የሆኑት የህወሃት ወታደራዊ አዛዦች ስለ አስቸኳይ ጊዜ አዋጁ ዝርዝር መረጃ እንዲሁም በአስቸኳይ ጊዜ አዋጁ ምክንያት በመላ አገሪቱ ስለታሰሩት ዜጎች ለአዲሱ ጠቅላይ ሚኒስተር ለዶ/ር አቢይ አህመድ እንዲሁም ለፖለቲካው አመራር ሪፖርት አናደርግም ማለታቸውን የመረጃ ምንጮቻችን ጠቁመዋል።
የመረጃ ምንጮቻችን አክለው የህወሃት ሰዎች ለዶክተር አቢይ ሪፖርት ብናቀርብ ነገሮችን ያበላሽብናል ብለው መስጋታቸውን አብራርተዋል። በተለይ ጄነራል ሳሞራ የኑስ <<ትላንት ለእኔ በተጠንቀቅ ሰላምታ ይሰጠኝ ለነበረ ለአንድ ተራ ወታደር ዛሬ ገና ለገና ጠቅላይ ሚኒስትር ሆነ ብየ ሪፖርት አላቀርብም >> ሲል መናገሩ ተከትሎ ሁኔታው ዶ/ር አቢይ አህመድ የአስቸኳይ ጊዜ አዋጁን አፈጻጸም ያበላሽብናል ከሚል የመነጨ ብቻ ሳይሆን ከነሳሞራ አንሸነፍም ባይነት እንዲሁም የመታብይና የበታችነት ስሜት የተቀዳ መሆኑን መረጃዎች አመላክተዋል። በዚህም ምክንያት በእነሳሞራ በአጠቃላይ በህወሃት ሰዎች ጥርስ ውስጥ የገቡት አዲሱ ጠቅላይ ሚኒስተር የሃገሪቱ ጠቅላይ ሚኒስተር ሆነው ከተሰየሙ ከመጋቢት 24 ጀምሮ ስለ አስቸኳይ ጊዜ አዋጁ አፈጻጸም ዝርዝር ሪፖርት ለጠቅላይ ሚኒስተሩ አልቀረበም ተብሏል።
በህገመንግስቱ መሰረት አንቀጽ 74 ንዑስ አንቀጽ አንድ ላይ ጠቅላይ ሚኒስተሩ የጦር ሃሎች ጠቅላይ አዛዥ ናቸው ይላል። ስለሆነም የመከላከያ ሰራዊቱ ኤታ ማዦር ሹም ዝርዝር ሪፖርት ለጠቅላይ ሚኒስተሩ የማቅረብ ግዴታ እንዳለበት ያስገድዳል። ነገር ግን ህወሃት ህግ የሚያወጣው እራሱ እንዲገዛበት ሳይሆን ሰዎችን እያስፈራራ ሰጥ ለጥ አድርጎ ለመግዛት እንዲያመቸው መሆኑ ግልጽ ነው። ለዚህም ነው ለጠቅላይ ሚኒስተሩ ስለአስቸኳይ ጊዜ አዋጁ ዝርዝር አፈጻጸምና ስለታሰሩ ሰዎች ሪፖርት አላቀርብም ያለው ሲሉ ሁኔታውን በቅርበት የሚከታተሉ አካላት እየገለጹ የሚገኙት።
በተጨማሪም ዶክተር አቢይ በበአለ-ሲመታቸው እለት <<በተለያየ ጊዜ መስዋእትነት ለከፈሉ የመብት ተከራካሪዎች፣ ፖለቲከኞች፣ በቅጡ ሳይቦርቁ ህይወታቸውን ለተቀጠፉ ለውጥ ፈላጊዎች፣ ለስነልቦናና ለአካል ቀውስ ለተዳረጉ ቤተሰቦች ከልብ የመነጨ ይቅርታ እጠይቃለሁ>> በማለታቸው የመከላከያ ያሉ የህወሃት የጦር አዛዦችን በጣም ማስቆጣቱን ከመከላከያ የደረሰን መረጃ አመልክቷል።
በዚህም ምክንያት እነሳሞራ የኑስ እንዲህ አይነት አቋም ላለውና እኛን ሆንብሎ በህዝብ ለማስጠላት ለቆመ ጠቅላይ ሚኒስተር የአስቸኳይ ጊዜ አዋጁን የተመለከተ አፈጻጸምም ሆነ፣ ስለታሰሩ ሰዎች እንዲሁም እርምጃ ስለተወሰደባቸው አካላት ምንም አይነት ሪፖርት ላለመስጠት እያንገራገሩ እንደሚገኙ ታውቋል። ከዚሁ ጋር ተያይዞ በመከላከያ ውስጥ ጄነራል ሳሞራ ከስልጣኑ ይነሳል በማለት በሰፊው እየተወራ እንደሆነ ምንጮቻችን አክለው ገልጸዋል።
Wednesday, April 18, 2018
አሁን ባለው የፌደራሊዝም ስርዓት አንድ ጠንካራ ኢትዮጵያን መገንባት አይቻል ( ጋዜጠኛ ፋሲል የኔዓለም)
ላለፉት 26 ዓመታት ክልል ከአገር በላይ ሆኖ እንዲታይ ከፍተኛ ቅስቀሳ ሲካሄድ በመቆየቱ፣ ቀላል የማይባል የአዲሱ ትውልድ አባላትና “ከራሴ በፊት ለኢትዮጵያ እናቴ” ሲሉ የነበሩ ከእኔ በፊት የነበሩና የእኔ ትውልድ ሰዎች ሳይቀሩ “ከአገሬ በፊት ክልሌ” እያሉ ሲዘምሩ እየሰማን ነው። ከወያኔ በፊት የነበሩ ትውልዶች “ክልሌን ላስቀድም ወይስ አገሬን?” በሚል ምርጫ ከራሳቸው ጋር ውዝግብ ውስጥ የገቡበት ሁኔታ አልነበረም፤ እያንዳንዱ ዜጋ ታማኝነቱ ሁሉ፣ አንድና አንድ፣ ለአገሩ ነበር። በጊዜው የነበረው በክፍለሃገር ደረጃ የተዋቀረው አስተዳደር የተለያዩ ብሄረሰቦችን አቅፎ የያዘ በመሆኑ፣ በአንድ ክፍለሃገር ስር ይኖር የነበረ የአንድ ብሄረሰብ ተወላጅ “ከአገሬ ክፍለሃገሬ” የሚልበት ሁኔታ አልነበረም። ዛሬ ክልል የሚባለው አጥር ከብሄር ማንነት ጋር በእጅጉ ተቆራኝቷል። “ክልል ይፍረስ” ብትል “ብሄርህ ይጥፋ” እንዳልክ ተቆጥሮ ጦር ይሰበቅብሃል። ክልልን የብሄር ማንነት መገለጫ አድርገህ ደግሞ “አድልዎ”ን ልታጠፋ አትችልም፤ "አድልዎን አጠፋሁ" ብትል እንኳን ከትችት አታመልጥም። ህዝብ ከክልሉ በፊት አገሩን እንዲያስቀድም ከፈለክ አሁን ያለውን ብሄር ተኮር ፌደራሊዝም መቀየር አለብህ፤ ይህን ሳትቀይር ጠንካራ አገር እገነባለሁ ብለህ የምታልም ከሆነ ህልምህ ህልም ሆኖ ይቀራል… አማራ እና አሮሞው፣ አማራና ሶማሊው፣ አማራና ትግሬው፣ አማራ እና ጋምቤላው ወዘተ በኢትዮጵያ ምድር እንደፈለገ ተንቀሳቅሶ ሰርቶ፣ ተዝናንቶ እንዲኖር የሚከልለው አጥር ሊኖር አይገባም። የውጭ አገር ድንበር አንሶን በአገራችን የድንበር አጥር እንዲኖር መፍቀድ ማለት በነጻነት ተንቀሳቅሰን የመኖር መብታችንን አሳልፈን ሰጠን ማለት ነው። አንበሳን እንደልቡ ከሚፈነጭበት ጫካ አውጥተህ በጉሮኖ ( zoo) ውስጥ ስላኖርከው መብቱን አከበርክለት ማለት አይደለም፤ ለአንበሳው የሚሻለው አዲሱ የክልል አጥር ሳይሆን መላ ጫካው የራሱ እንደሆነ ተስምቶት እንዲፈነጭበት ስትፈቅድለት ነው...
በዜጎች ላይ የሚደርስ እልቂትና መፈናቀል ይቁም፤ ለዘላቂ መፍትሄ እንታገል!!! (አርበኞች ግንቦት 7 )
ሚያዝያ 9 ቀን 2010 ዓም በቦረና ዞን ሞያሌ ከተማ ውስጥ በሰላማዊ ሰዎች ላይ በተወረወረ ቦንብ እና በጭፍን በተተኮሱ ጥይቶች ሳቢያ የዜጎች ሕይወት ጠፍቷል፤ ወደ 70 በሚጠጉ ዜጎች ላይ ደግሞ ከባድ የአካል ጉዳቶች ደርሰዋል። የከተማዋና አካባቢ ነዋሪዎች በሆኑ የቦረናና የገሪ ብሄረሰብ ተወላጆች መካከል የተከሰተ ግጭትን መነሻ በማድረግ ይህንን ኢሰብዓዊ ድርጊት የፈፀሙት የኢትዮጵያ ሶማሌ ክልል ያስታጠቃቸው ወታደሮች መሆናቸው የከተማው መስተዳደር የሥራ ኃላፊ መግለፃቸው ሁኔታውን የበለጠ አሳሳቢ ያደርገዋል።
ሁለት ወራት እንኳን ባልሞላው ጊዜ ውስጥ በዚሁ ከተማ የኮማንድ ፓስት አባላት ነን የሚሉ የአገዛዙ ወታደሮች በዜጎች ላይ ተመሳሳይ ጥቃት ፈጽመው በርካቶች ሕይወታቸው ሲያልፍ በአስር ሺዎች የሚቆጠሩ ኢትዮጵያዊያን ወደ ጎረቤት አገር ኬኒያ መሰደዳቸው ይታወቃል። ወደ ጎረቤት አገር የተሰደዱ ወገኖቻችን ወደ ቀያቸው አልተመለሱም። ያ ቁስል ሳይሽር ይኸኛው መደገሙ ሁኔታውን እጅግ አሳዛኝ ያደርገዋል።
የኢትዮጵያ ሶማሊ እና የኦሮሚያ ክልላዊ መንግሥታት በምስራቅና በደቡብ የአገራችን ክፍሎች ለሚፈጠሩ ማኅበራዊ ግጭቶች መፍትሄ በመስጠት ፋንታ የችግሩ አካል እየሆኑ መታየታቸው የዜጎች ሰላም እና የሀገር አንድነት አደጋ ላይ መውደቃቸው አመላካች ነው። በእነዚህ ተከታታይ ግጭቶች ሳቢያ ኢትዮጵያዊያን በከፍተኛ ቁጥር ለሞት፣ ለአካልና ስነልቦና ጉዳቶች እና ለጅምላ መፈናቀል እየዳረጉ በመሆናቸው ችግሩ አፋጣኝ መፍትሄ የሚሻ ነው።
ይህ የማያባራ የኢትዮጵያዊያን ሰቆቃ የህወሓት/ኢህአዴግ አገዛዝ ውጤት እንደሆነ ንቅናቄዓችን ይገነዘባል።
በሌላ በኩል ደግሞ በጉጂ ዞን በጉጂ እና በጌዲዮ ተወላጆች መካከል የተቀሰቀሰ ግጭት ለበርካታ ዜጎች ህልፈት፤ በአስር ሺዎች ለሚቆጠሩ ዜጎች መፈናቀልና ለበርካታ መንደሮች በእሳት መጋየት ምክንያት ሆኗል። ግጭቱ ከዕለት ዕለት አድማሱን እያሰፋ መሆኑ አርበኞች ግንቦት 7ን ያሳስበዋል። እዚህም የኦሮሚያ እና የደቡብ ኢትዮጵያ ክልላዊ መንግሥቶች ግጭቶችን ማብረድ አልተቻላቸውም። እዚህም የኮማንድ ፓስት አባላት ግጭቱን ሲያባብሱ እንጂ ሲያረግቡ አልታዩም።
ተመሳሳይ ችግሮች በአማራና በትግራይ እና በትግራይና በአፋር ክልላዊ መንግሥቶች መካከልም ይታያል። የአስቸኳይ ጊዜ አዋጁ የፈጠረው የመታፈን ስሜት ግጭቶችን እያሰፋ መሆኑ ዘወትር የሚስተዋል ክስተት እየሆነ ነው። ማኅበራዊ ግጭቶች በተለመደው ባህላዊ መንገድ ብቻ መፈታት የማይችሉ፤ መዋቅራዊ መፍትሄ የሚሹ ሀገራዊ አጀንዳዎች ሆነዋል።
አርበኞች ግንቦት 7 የዜጎች ደህንነት በማናቸውም ጉዳዮች ቅድሚያ የሚሰጠው እንደሆነ ያምናል። የመንግሥትን ሥልጣን የያዘው አካልም ከዚህ የሚያስቀድመው ጉዳይ ሊኖር አይገባም ብሎ ያምናል።
ህወሓት/ኢህአዴግ በህገወጥ መንገድ ለሁለተኛ ግዜ በአገራችን ላይ ያወጀው የአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ ፀጥታን በማስፈን ፈንታ የሕዝብን ሰላም እያደፈረሰ መሆኑ አርበኞች ግንቦት 7 ይገነዘባል፤ የኮማንድ ፓስት አባላት በተለያዩ ስፍራዎች ሕዝብን ከሕዝብ በማጋጨት የአገዛዙ እድሜ ለማራዘም የሚያደርጉትን ጥረት አጥብቆ ያወግዛል፤ አዲሱ ጠቅላይ ሚኒስትር ለዚህ መሠረታዊ ችግር ስር ነቀል መዋቅራዊ መላ እንዲሹለትም ይመክራል።
አርበኞች ግንቦት 7 በተለያዩ የአገራችን ክፍሎች በተቀሰቀሱ ግጭቶች ሳቢያ ሕይወታቸው ላጡ ቤተሰቦች መጽናናትን ይመኛል፤ በእነዚህ ግጭቶች ምክንያት ለአካልና ስነልቦናዊ ቀውስ ለተዳረጉ እና ከቀያቸው ለተፈናቀሉ ወገኖቻችን አጋርነቱን ይገልፃል። በዚህ ወንጀል እጃቸው ያለበት ሁሉ በህግ ፊት እንዲቀርቡና እስከዛሬ በወገኖቻችን ላይ እየተፈጸመ ላለው ሰቆቃ ዘላቂ መፍትሄ ለማምጣት የሚያደርገውን ትግል አጠናክሮ እንደሚቀጥልም ያስታውቃል።
በአገራችን ለሚከሰቱ ማኅበራዊ ግጭቶች ዘላቂ መፍትሄ ማግኘት የሚቻለው ስር ነቀል የፓለቲካ ሥርዓት ለውጥ ሲደረግ ብቻ እንደሆነ አርበኞች ግንቦት 7 ያምናል። በዚህም ምክንያት፤ የኢትዮጵያ ሕዝብ ሙሉ ትኩረቱን የፓለቲካ ሥርዓቱን ለመለወጥ በሚያስችለው ትግል ላይ እንዲያደርግ አርበኞች ግንቦት 7 ጥሪውን ያቀርባል።
ድል ለኢትዮጵያ ሕዝብ !!!
Tuesday, April 17, 2018
(የአርበኞች ግንቦት 7 ድምፅ ሬዲዮ)
በደል ይረሳል ወይስ ይለመዳል!
(ሚያዚያ 09 ቀን 2010)
የግንቦት ሰባት መስራች አባልና የንቅናቄው ዋና ጸሀፊ በሆነው ታጋይ አንዳርጋቸው ጽጌ ላይ የሚያጠነጥን አጠር ያለ ዝግጅት.... ትከታተሉት ዘንድ ግብዣችን ነው።
www.patriotg7.org ላይ መከታተል የምትችሉ መሆኑን እንገልፃለን፡
ድል ለኢትዮጵያ ህዝብ!
አገራችን በልጆቿ ነጻ ትወጣለች!
( የአርበኞች ግንቦት 7 ድምፅ ሬዲዮ)
የዕለተ ማክሰኞ ሚያዚያ 09 ቀን 2010ዓ.ም. ፕሮግራሞቻችን
************************
የዕለቱ አርዕስተ ዜና
* የአርበኞች ግንቦት 7 አባላት የህወሓት ታጣቂ ሰራዊት ላይ ከባድ እርምጃ መውሰዳቸውን ዘመቻ ነጻ ትውልድ ዘገበ።
* የህወሓት የዘር ፖለቲካ ቀውስ አሁንም በድጋሚ በጉጅና በጌዲዮ ብሄሮች መካከል መቀስቀሱ ታወቀ።
ቀጣዩ
በደል ይረሳል ወይስ ይለመዳል!
የተሰኘው መሰናዷችን ትከታተሉት ዘንድ ግብዣችን ነው
www.patriotg7.org ላይ መከታተል የምትችሉ መሆኑን እንገልፃለን፡
አንድነት ሃይል ነው!
ኢትዮጵያ በክብር ለዘላለም ትኑር!!!
Monday, April 16, 2018
”ቢቢሲ ሃርድ ቶክ” ቆይታ ህወሓት እና “የብሄራዊ ጥቅም” ( አቶ ነዓምን ዘለቀ )
በቅድሚያ ምስጋና፦
ባለፈው ሳምንት በአለም አቀፍ ደረጃ ታዋቂ ከሆነው የቢቢሲ ሃርድ ቶክ/BBC Hardtalk ጋር ቆይታ ማድረጌ ይታወቃል። የፕሮግራሙ ይዘት ጠንከር ያሉ ሙግቶችን ተሞርኩዞ ምላሽ የሚሰጥበት በመሆኑ በብዙዎች ዘንድ የሚደፈር አለመሆኑም ይተወቃል። ወደ ኋላ ሔዶ ለማስታወስ ያህል የፕሮግራሙ አዘጋጆች ከወያኔ ቁንጮ ከነበረው ሟቹ መለስ ዜናዊና የቅንጅት ሊ/መንበር ከነበሩት ኢንጂነር ሐይሉ ሻወል ጋር እንደዚህ አይነት ፖለቲካዊ ሙግት ያደረገው የዛሬ 12 አመት በምርጫ 97 ማግስት ነበር። ከዛ ወዲህ በአገራችን ኢትዮጵያ የፖለቲካ ጉዳዮች ላይ በሚዲያው ቀርቦ ሙግት የገጠመው ኢትዮጵያዊ አላስታወስም።
ይህን በመመልከት ይመስላል የንቅናቄያችን አመራሮች አባላትና ደጋፊዎች፤ በተለያዩ የፖለቲካ ድርጅቶት ውስጥ ያላችሁ አመራሮችና አባላት፤ የስርአት ለውጥ ፈላጊ ኢትዮጵያውያንና በርካታ ምሁራ ስሜታችሁን ገልጻችሁልኛል። በአካል፣ በስልክ በማህበራዊ ድረ-ገጽና አስተያየቶች ደርሰውኛል። በኢትዮጵያ ጉዳይ ላይ ትኩረት የሚሰጡ ድረ-ገጾች እንዲሁም እንደ ኢሳት ያሉ የኢትዮጵያ ህዝብ አይንና ጆሮ የሆኑ የሚዲያ ተቋማት “የቢቢሲ ሃርድ ቶክ” ፕሮግራሙን ተመስርተው ውይይትም በማድርግ በተለያየ ምልከታዎችን እንዳይ ስላደረጋችሁኝ በድጋሚ ለድረ-ገጾቹም ሆነ ለሚዲያ ተቋማቱ ምስጋናዬ ይድረሳችሁ። ለሰጣችሁኝ አበረታች ግብረ-መልስ ላቅ ያለ ምስጋናዬን ከወዲሁ ማቅረብ እወዳለሁ።
ይህ በእንዲህ እንዳለ አክብሮታችሁን የላካችሁልኝ የንቅናቄያችን አባላትም ሆነ የተቀራችሁ ኢትዮጵያውያን አንድ ነገር አስምሬ ልነግራችሁ የምፈልገው ጉዳይ አለኝ። ኣኔ ብዙሃን ወደማይደፍሩት የቢቢሲ ሞጋች ፕሮግራም ላይ ለመቅረብ ፍቃደኛ የሆንኩት ዋነኛ ምክንያት በመኖሩ ነው። ይኸውም አመራር የሆንኩት አርበኞች ግንቦት ሰባት ነድፎ የሚታገልባቸው የማታገያ ነጥቦች መዳረሻ ግልጽ ስለሆኑ ነው። ለሁሉም ግልጽ ኣንደሆነው ንቅናቄያችን የኢትዮጵያን ሉአላዊነት፣ አንድነት፣ እንዲሁም ብሄራዊ ጥቅም ለድርድር የሚያቀርብ አይደለም።
ኢትዮጵያዊነት ማለት አንዱዓለም ተፈራ (እስከመቼ)
“ኢትዮጵያዊነት ማለት፤ ኢትዮጵያዊያንን መውደድ፣ ኢትዮጵያን ማፍቀር፤ የኢትዮጵያን መንግሥት በተገቢው መንገድ መደገፍና፤ ይህ መንግሥት የተሳሳተ መንገድ ሲይዝ መቃወም ማለት ነው። በሥልጣን ላይ ያለው ክፍል ፀረ-ኢትዮጵያዊያንና ፀረ-ኢትዮጵያ ሲሆን፤ ያንን ክፍል በማንኛውም መንገድ ማስወገድ፤ የያንዳንዱ ኢትዮጵያዊና የያንዳንዷ ኢትዮጵያዊት፤ ኢትዮጵያዊ ግዴታ ነው።”
አብዛኛዎቻችን በየጊዜው የምናነሳው ጉዳይ፤ ሀገራችን ኢትዮጵያ ያለችበትን የፖለቲካ ሀቅና በኢትዮጵያ ሕዝብ ላይ እየደረሰ ያለውን በደል ነው። ኢትዮጵያዊ ነኝ ወይንም አይደለሁም የሚለውን ጥያቄ አይደለም። በየቦታው፣ በተገኘው አጋጣሚ፣ በየዕለቱ በሕዝቡ ላይ የሚደረገውን በደል እናውጠነጥናለን። ኢትዮጵያዊያን ናቸው ወይንም አይደሉም የሚለው ከጥያቄያችን መካከል አይደለም። መቼም አርባ ዓመት ሙሉ፤ በአረመኔው መንግሥቱ ኃይለማርያምና በወገንተኛው የትግሬዎች ነፃ አውጪ ግንባር መንግሥት፤ በኢትዮጵያ ህዝብ ላይ የደረሰውን ግፍና በደል ገና ብዙ ፀሐፊዎች ብዙ ይውሉበታል፣ ሊቃውንት ይቀኙበታል፣ አንጎርጓሪዎች ይደረድሩበታል፣ ሰዓሊዎች ያቀልሙታል፣ ገጣሚዎች ይሰነኙበታል፣ መጽሐፎች ይደረሱበታል። ያ ግን፤ ከኛ ቀጥለው የሚመጡት ኢትዮጵያዊያን፤ ስለኛ ስለቀደምናቸው ኢትዮጵያዊያን ለማወቅ የሚያደርጉት ጥረት ውጤት ነው እንጂ፤ ኢትዮጵያዊ ስለመሆናችን ወይም ኢትዮጵያዊ ስላለመሆናችን አይደለም።
እንግዲህ የአሁኑ ሰዓት ኢትዮጵያዊነት ምንድን ነው? የሚለውን በደንብ መረዳት አለብን። ይኼን ስናደርግ፤ የሀገራችንን የኢትዮጵያን የፖለቲካ ሀቅ በትክክል እንረዳና፤ በኢትዮጵያዊነታችን፤ ምን ማድረግ እንዳለብንና ማን ኢትዮጵያዊነቷን እየተወጣች እንደሆነች እንገነዘባለን። ትናንትም፣ ዛሬም ነገም ኢትዮጵያዊነት ማለት፤ ኢትዮጵያዊያንን መውደድ፣ ሀገርን ኢትዮጵያን ማፍቀር፤ የኢትዮጵያን መንግሥት በተገቢው መንገድ መደገፍና፤ ይህ መንግሥት የተሳሳተ መንገድ ሲይዝ መቃወም ማለት ነው። በሥልጣን ላይ ያለው ክፍል ፀረ-ኢትዮጵያዊያንና ፀረ-ኢትዮጵያ ሲሆን፤ ያንን ክፍል በማንኛውም መንገድ ማስወገድ፤ የያንዳንዱ ኢትዮጵያዊና የያንዳንዷ ኢትዮጵያዊት፤ ኢትዮጵያዊ ግዴታ ነው። ወራሪ ሆኖ ሲገኝ ደግሞ፤ ይህ ግዴታ፤ ወደ መኖር ወይንም አለመኖር የሕይወት ትንቅንቅ ስለሚያመራ፤ አማራጭ የማይሠጥ ጥሪ ይሆናል። ይህ ፖለቲከኛ መሆንን ወይንም አለመሆንን አይጠይቅም። ይህ ታጋይ መሆንን ወይንም አለመሆንን አይጠይቅም። ይህ ሀገራዊ ግዴታን ነው የሚገልጸው። ይህ የኢትዮጵያዊ ሕይወት፣ የትናንት፣ የዛሬና የነገ ሕልውና ጥያቄ ነው። አሁን በሀገራችን በኢትዮጵያ ውስጥ፤ ኢትዮጵያዊ መንግሥት የለም። ሕግና ሥርዓት የሚያከብር ቡድን አይደልም በሥልጣን ላይ ያለው። ራሱ የሚያወጣቸውን ሕጎች የሚያፈርስ፤ ኢትዮጵያዊነትን ለማጥፋት የተነሳ ክፍል ነው በሥልጣን ላይ የተቀመጠው። ኢትዮጵያዊያንን እየከፋፈለ፣ አንድነት እንዳይኖረን የሚጥር መንግሥት በሥልጣን ላይ አለ። የኢትዮጵያ ሕዝብ ደግሞ፤ “ኢትዮጵያዊ ነኝ። አልከፋፈልም። ጠላታችን የትግሬዎች ነፃ አውጪ ግንባር መንግሥት ነው።” እያለ ትግል ይዟል። ስለዚህ፤ የአሁኗ ኢትዮጵያዊትና የአሁኑ ኢትዮጵያዊ፤ ኢትዮጵያዊ ግዴታችን፤ ይኼን ፀረ-ኢትዮጵያዊያን መንግሥት ከታጋዩ ህዝብ ጎን ተሰልፎ ማስወገድ ነው። ሕዝባዊ ንቅናቄ ከፊታችን ተደግኗል። የውዴታ ሳይሆን ግድ ሆኖብን፤ የምርጫ ሳይሆን አማራጭ ሳይኖረን ንቅናቄው አፍጥጦብናል። የዴሞክራሲ ቅንጦት ሳይሆን የሀገር አድን ጥያቄ ቀርቧል።
ባጭሩ ኢትዮጵያዊነት ማለት፤ የኢትዮጵያ ጠላት የሆነውን ወራሪ መንግሥት ማወገድ ነው። ይኼን የኔ ብሎ ያልተነሳ ግለሰብ፤ ኢትዮጵያዊነቱ ምኑ ላይ ነው? በርግጥ ትግሉ ረጅም ነው። ትግሉ የተመሰቃቀለ ነው። በሥልጣን ላይ ተቀምጦ ፀረ-ኢትዮጵያዊነት ፍልስፍናውና መመሪያው የሆነው የትግሬዎች ነፃ አውጪ ግንባር ብቻ ሳይሆን፤ ይኼኑ ፍልስፍናና መመሪያ የራሳቸው ያደረጉ ሌሎች ክፍሎችም የኢትዮጵያዊነት ትግላችን አንድ ክፍል ናቸው። በትግሉ ውስጥ ያለን ኢትዮጵያዊያን በሙሉ ይኼን ሀቅ አጥብቀን መያዝ አለብን። ኢትዮጵያ ለዘመናት መንግሥት ኖሯት ስትተዳደር የነበረች ሀገር ለመሆኗ አጥጋቢ መረጃዎች አሉ። እኒህ መንግሥታት በየተከሰቱበት የታሪክ ወቅት፤ በጎም ሆነ በጎነት የጎደለው ተግባር አከናውነው አልፈዋል። በዚህ ረጅም ታሪካችን፤ የመንግሥታዊ ማዕከላቸውን በሰሜን ወይንም በደቡብ፤ በምሥራቅ ወይንም በምዕራብ እንደታሪካዊ ወቅቱም ተንቀሳቃሽ በማድረግ፣ የተለያዩ የጦር አሠላለፍን በማዘጋጀት፣ ጥንካሬያቸው እንደፈቀደላቸው፤ የሀገሪቱንም ደንበር ሲያሠፉና ስትጠብባቸው ነበር። አንዱ ከሌላው ጎጥ፤ ሃይማኖት ሳያግደው፣ የዘር ሐረግ ሳይከለክለው፣ እንደ ጥንካሬያቸውና የፖለቲካ ግኘታ አመቺነታቸው ሲጋቡና ሲዋለዱ ነበር። በኢትዮጵያዊነት ገዝተዋል። እናም በተለያዩ ጊዜያት፤ በተለያዩ መንግሥታት ዘመን፤ የተለያዩ ህዝባዊ ጥያቄዎች ተነስተዋል። ሕዝባዊ አመፆች ተካሂደዋል። መፈንቅለ መንግሥት ተደርገዋል። በንጉሥ ላይ ንጉሥ ተነስቷል። ንግሥታት ዘውድ ጭነው ገዝተዋል።
Sunday, April 15, 2018
ሀገር ማለት የኔ ልጅ - (በዶ/ር በድሉ ዋቅጅራ)
ሀገር ማለት ልጄ፣ ሀገር ማለት፣
እንዳይመስልሽ የተወለድሽበት ቦታ ፣
የተወለድሽበት አፈር፤
እትብትሽ የተቀበረበት ፣ ቀድመሽ የተነፈሽው
አየር፤
ብቻ እንዳይመስልሽ።
ሀገር ረቂቅ ነው ቃሉ፤
አገር ውስብስብ ነው ውሉ።
ሀገር ማለት ልጄ ፣
ሀገር ማለት ምስል ነው ፣በህሊና የምታኖሪው፤
ከማማ ማህጸን ከወጣሽበት ቀን ጀምሮ ፤
በጠባሽው ጡት፣ ወይም ጡጦ ፣
በዳህሽበት ደጃፍ፣ በወደቅሽበት ፈፋ፤
በተማርሽበት ትምህርት ቤት፣
በተሻገርሽው ዥረት ፤
በተሳልሽበት ታቦት ፣ወይ በተማፀንሽው ከራማ ፤
በእውቀትሽና በህይወትሽ፣
በእውነትሽና በስሜትሽ ፣
የምትቀበይው ምስል ነው ፣ በህሊናሽ
የምታኖሪው፤
ስትወጅ ሰንደቅ ታደርጊው፡፡
ቢያስጠላሽ የማትቀይሪው።
ሀገር ማለት የኔ ልጅ ፣
ሀገር ማለት ቋንቋ ነው በአንደበት አይናገሩት፤
በጆሮ አያዳምጡት፤
አማርኛ ኦሮሞኛ ፣ አፋርኛ ቅማንተኛ፤
ጉራግኛ ወይ ትግርኛ፣ ብለው የማይፈርጁት ።
የኔ ልጅ፣
አማራውና አፋሩ፣ ኦሮሞው ሲዳማው ፣
ጉራጌኛሽን ባይሰማ፤
ያለገባው እንዳይመስልሽ ፣ ሀዘን ደስታሽን
ያልተጋራ።
የየልቦናችንን ሀቅ፣ ፍንትው አድርጎ እያሳየ፤
ህዝቦችን ከሰንደቃቸው፣ አስተሳስሮ ያቆየ፡፡
ሀገር ቋንቋ ነው ልጄ፣ የሁለንተናሽ መስታወት፤
ሲከፋሽ ትሽሽጊበት ፣ ሲደላሽ ትኳኳየዪበት ።
የኔ ልጅ ፣
አያት ቅም አያትሽ ፣ሰላም ሲሆን ከወልቂጤ
አድማስ ማዶ ሸቅጦ፣
ሲያቀና ወረቱን፤
ለእኔና ለአንቺ መኖሪያ፣ ሲያቀና ቀዬና ቤቱን፤
ሀገር ጠላት ሲደፍራትም፣ ጦሩን ሰብቆ እየፎከረ፤
ከኦሮሞው ከትግሬው፣ ከአፋሩ ከወላይታው፣ . . .
ከሁሉም የጦቢያ ልጆች ፣
አጥንቱን እየማገረ፤
ሀገር ይሉት መግባቢያ ፣ሰንደቅ ይሉት መለያ ፣
ሲያቆይልሽ፤
በጉራግኛ ማትገልጭው፣ በጎጥ የማትገድቢው፣
ስንት አለ ታሪክ መሰለሽ!
እና የእኔ ልጅ፣
ለዚህ ነው ሀገር ይሉት ቋንቋ፣ ላንቺ
የሚያስፈልግሽ፤
ከወልቂጤ አድማስ ማዶ፣ ለተሳሰረ ታሪክሽ፤
ከወልቂጤ አድማስ ማዶ ፣ ለተወጠነው
እድገትሽ።
እና ልብ በይ ልጄ ! ሀገር ማለት ቋንቋ ነው፣
ባንደበት አይናገሩት፤
በጆሮ አያዳምጡት።
ከሁሉም በላይ ልጄ ፣
ተፈጥሮ ከቸረው በረከት ፣ የላቡን ፍሬ የሚበላ፤
ሀገር ማለት ወገን ነው፣ የእኔ የምትይው ከለላ።
ትመኪበት ጥሪት፣ ትደምቂበት ብርሃንሽ፤
የሰብዕናሽ ግማሽ ውል ፣ወገን ነው ማሕተምሽ፡፡
ዜጋው ነው ልጄ ሀገርሽ።
መሬትማ የእኔ ልጅ፣
በእምነትሽና እውቀትሽ፣ ከልለሽ ካላበጀሽው፤
ለእድገትሽ ውጥን ካልሆነ ፣ለተስፋሽ
ካልተመገብሽው፤
መሬትማ ባዳ ነው፣ ላለማው የሚለማ፤
ለተስማማው የሚስማማ።
ዥረቱም ግድ የለውም ፣ ቦይ ለማሰለት ይፈሳል
ተራራውም ደንቆሮ ነው ፣ ለቦረቦረው ይበሳል።
መሬቱ አደለም የኔ ልጅ፣ እድርተኛው ነው
ሃገርሽ፤
ስትቸገሪ ታድጎ፣ ስትታመሚ አስታሞ፣ ስትሞቺ
አፈር ሚያለብስሽ።
በእጅሽ ያለ ብሩህ ጽጌ ፣ ሰው ነው ልጄ ሀገርሽ፤
ወገን ነው ልጄ ሀገርሽ።
እና የኔ ልጅ፣
ሀገር ረቂቅ ነው ቃሉ፤
ሀገር ውስብስብ ነው ውሉ።
Saturday, April 14, 2018
የለውጥ እንቅስቃሴን ለማራመድ ለሀገር አቀፍ ሕዝባዊ እምቢኝነት ዝግጁ እንሁን (የአርበኞች ግንቦት 7 ርዕሰ አንቀጽ)
የዶ/ር አብይ አህመድ በጠ/ሚኒስትርነት መሾም በሕዝባዊ ትግሉ ላይ ስለሚኖረው ተጽዕኖ ማብራሪያ እንዲሰጣቸው በርካታ ወገኖች ጥያቄ አቅርበዋል።
በንቅናቄዓችን ሰነዶች ላይ በግልጽ እንደሰፈረው የአርበኞች ግንቦት 7 ራዕይ “እያንዳንዱ ኢትዮጵያዊ ዴሞክራሲያዊና ሰብዓዊ መብቱ የተከበረበት፤ የኢኮኖሚ ብልፅግናና ማኅበራዊ ፍትህ የሚገኝበት፤ የዜጎች ሕይወት፣ ደህንነትና ጥቅም የተከበረበት እና የሕዝቧ አንድነትና ትስስር የጠነከረበት ሃገር ኖሮት ማየት ነው።”
የአርበኞች ግንቦት 7 ተልዕኮ ደግሞ “የመንግሥትና የፖለቲካ ሥልጣን በሰላማዊና ዴሞክራሲያዊ ሂደት የሚያዝበት፤ የሃገሪቱ ዜጎች ምርጫ በተግባር የሚገለፅበት፤ ማኅበራዊና የፖለቲካ ችግሮች በዲሞክራሲያዊ መንገድ የሚፈቱበት እና ዲሞክራሲያዊ ባህል የሚበለፅግበት ብሄራዊ የፖለቲካዊ ሥርዓት እንዲገነባ ማገዝ ነው።”
የአብዛኛው የኢትዮጵያ ሕዝብ ፍላጎት ከንቅናቄዓችን ራዕይና ተልዕኮ የተለየ አይደለም። አብዛኛው የኢትዮጵያ ሕዝብ የሀገሩ ባለቤት መሆን ይፈልጋል፤ መሪዎቹን በነፃነት መምረጥና መሻር እና በአገራችን ማኅበራዊ ፍትህ ሰፍኖ ማየት ይሻል።
ዶ/ር አብይ አህመድ ይህን የሕዝብ ፍላጎት ማሳካት የሚችሉ መሪ ናቸውን?
የዶክተር አቢይ ነጥብ መጣል! (ኤርሚያስ ለገሰ)
#ነጥብ አንድ : " የወርቅ ፍልቃቂ!"
ዶክተር አቢይ በመቀሌ ጉዞውና ከተመረጡ የህውሓት አባላት ጋር ባደረገው ምክክር በርካታ ነጥቦች ጥሏል። አንዳንዶቹ በጣም የሚያስደነግጡ ናቸው። ለምሳሌ የአቶ መለስ ዜናዊን የሙት መንፈስ የወረሰ በሚመስል ሁኔታ " የትግራይ ሕዝብ በእሳት የተፈተነ ወርቅ ነው!" በማለት ሲናገር የተሰብሳቢው ጭብጨባ አስደማሚ ነበር። መቼም ይሄ ከናዚዝም የሚቀዳ አነጋገር አቶ መለስን ምን ያህል ራቁቱን እንዳሳየው ዶክተር አቢይ ያጣው አይመስለኝም።
ዶክተር አቢይ አንድን ብሔረሰብ አግንኖ ለማውጣት ከፍ ከፍ ለማድረግ የሚካሄድ ጥረት ሁሉ ከፍተኛ አደጋ ሊያመጣ እንደሚችል የሚያጣው አይመስለኝም። አንደዚህ አይነት አባባል በሌሎች ላይ ጥላቻ ያሳድራል። የወርቅ ፍልቃቂ የተባለው ጐሳ የገዥነት፣ ከሕግ በላይ የመሆን መንፈስ እንደሚፈጥርበት ሳይታለም የተፈታ ነው። በሂደትም ወደ ነሀስና ብር ብሎም ወደ ጨርቅ የወረደው ሀይል ወደ አመፅ በመሄድ የጥቃት ሰለባ ሊያደርጋቸው ይችላል።
እንደ አንድ ሞጋች ደጋፊው ዶክተር አቢይ ከአቶ መለስ በፍፁም መውረስ የለበትም ብዬ ከምመኘው የመጀመሪያው ነገር " የወርቅ፣ ነሀስ፣ብርና ጨርቅ ብሔር" ጽንሰ አሳብ ነበር። ይሄ ጽንሰ አሳባ አደገኛ ከመሆኑም ባሻገር የንቀት፣ ጥላቻ፣ የብዝበዛና የጭቆናና ኢፍትሐዊነት ይፈጥራል። በዚህ አደገኛ አባባሉ ዶክተር አቢይ ሊያፍር ይገባል። ከእንደዚህ አይነት ከፋፋይና አስቀያሚ ንግግር ራሱን ማቀብ ይኖርበታል። የኢትዬጲያን ሕዝብ በወርቅና ጨርቅ በመከፋፈል ለአንዱ ኩራት ለሌላው ውርደት የፈጠረውን፣ አደህይቶ የገዛውን፣ አገርን ታሪክ አልባ ያደረገውን፣ አሰቃይቶ መግዛት ፓሊሲው ያደረገውን መለስ ዜናዊ በአንደበቱ ማሞካሸት ያሳፍራል። ያሳቅቃል።
#ነጥብ ሁለት: " ማይ መቐለ!"
ዶክተር አቢይ አህመድ በዛሬው የመቀሌ ንግግሩ፣
" የመቀሌን ውሃ በተመለከተ ምንም የማውቀው ነገር የለም። የመቀሌ ውሃ መቼ ተጀመረ፣ የት ደረሰ ሚስጥሩን አላውቀውም። የትግራይ ህዝብ እንዲያውቅ የምፈልገው አንድ ጉዳይ ቢኖር የመቀሌም፣ የአክሱምም፣ በሙሉ በትግራይ ያለ የመጠጥ ውሃ ጉዳይ የፌዴራል መንግስትን አይመለከትም። መቶ ፐርሰንት የክልል ስራ ነው" ነበር ያለው።
ይሄንን የዶክተር አቢይ ምላሽ ስሰማ በጣም ደንግጫለሁ። ዶክተሩ ተረጋግተው መቀመጥ ባለመቻላቸው አጠገባቸው ምን እየተሰራ እንደሆነ ማወቅ አለመቻላቸውን አመላክቶኛል። "በሙሉ በትግራይ ያለ የመጠጥ ውሃ ጉዳይ የፌዴራል መንግስትን አይመለከትም፣ መቶ ፐርሰንት የክልሉ መንግስት ነው" ማለታቸው ከመረጃ እጥረት የመነጨ ወይንስ ሽምጥጥ አድርጐ መካድ ይሆን የሚል ጥያቄ ጭሮብኛል። እንደ ሞጋች ደጋፊነቴ ላምናቸው ስለምፈልግ ዶክተሩ ተረጋግቶ ባለመቀመጥ ምክንያት የመረጃ እጥረት አጋጥሟቸዋል ብዬ ማመን እፈልጋለሁ።
እናም ለዶክተሩ መረጃውን ልሙላላቸው።
#የህውሓት ንብረት የሆነው ሬዲዬ ፋና ከትላንት ወዲያ እንደዘገበው የፌዴራል መንግስቱ የመቀሌን የመጠጥ ውሃ አቅርቦት በሁለት እጥፍ ለማሳደግ 8ቢሊዬን ብር ከቻይና መንግስት ተበድሮ የግድብ ግንባታ ጀምሯል። በዘገባው መሰረት " የሰሜኗ ኮከብ መቐለ!" በየቀኑ የሚያስፈልጋት የውሃ መጠን 50ሺህ ሜትር ኪዩብ ነው። በአሁን ሰአት እየቀረበላት ያለው ደግሞ 25ሺህ ሜትር ኪዩብ ( 50 በመቶ) ያህል ነው።
የትግራይ ክልላዊ መንግስት በራሱ በጀት 18ሺህ ሜትር ኪዩብ የሚያስገኝ ግድብ አጠናቋል። ከላይ ከተጠቀሰው ጋር ስንደምረው " የሰሜኗ ኮከብ!" የቀን አቅርቦቷ 43ሺህ ሜትር ኪዩብ ይሆናል። መሰረታዊ የሂሳብ ስሌቶችን ተጠቅሞ መደመርና መቀነስ ለሰራ ( አባዱላን አይመለከትም) መቐለ የቀን ፍላጐቷን ለማሟላት የሚቀራት 7ሺህ ሜትሪክ ኪዩብ ብቻ ነው።
አሁን ወደ ፌዴራሉ የቻይና ብድር እንመለስ። የፌዴራል መንግስቱ ከቻይና ተበድሮ ( ወለዱ ስንት እንደሆነ አልተገለጠም) ለመቐሌ በሚሰጠው 8ቢሊዬን ብር ተጨማሪ በየቀኑ 147ሺህ ሜትሪክ ኪዩብ ውሃ አቅርቦት ይኖራል። አሁንም መደመርና መቀነስ ሲሰራ በአጠቃላይ በመቀሌ በቀን የሚመነጨው የመጠጥ ውሃ መጠን ከፍላጐቱ በ140ሺህ ኪዩቢክ ሜትር ብልጫ ይኖረዋል።
እንግዲህ ፍርዱን ለዶክተር አቢይና አንባቢያን እተዋለው። ፌዴራል መንግስቱ በመቶ ሚሊዬን የኢትዬጲያ ህዝብ ስም 8 ቢሊዬን ብር ተበድሮ ( ያውም የወለድ መጠኗ እስከ 35% የምታደርሰው ቻይና) ለመቐሌ እየሰጠ እውቀት የለኝም ማለት ምን ማለት ነው? በፓርቲ ሚዲያ ለአለም ህዝብ የተገለጠ መረጃ አለማንበብ ማለት ምን ማለት ነው? ፌዴራል መንግስቱ ያን ያህል ገንዘብ ተበድሮ ሲያበቃ " ክልሉ እንጂ ፌዴራል አያገባውም!" ብሎ መናገር አያሸማቅቅም ወይ? ሐይለማርያም ደሳለኝ ( የቀድሞ ተጠቅላይ በሉኝ ብሏል!) በአንድ ወቅት መረጃዎች አይደርሱኝም ብሎ ከተናገረው በምን ይለያል?
#ተጨማሪ ነጥቦች
የንፁህ መጠጥ ውሃን በተመለከተ የቀረምኳቸውን አንዳንድ መረጃዎች ለዶክተር አቢይ ላካፍለውና የመጀመሪያ ክፍል ፅሁፌን ላጠናቅ። ተጨማሪ መረጃዎች ካሉ እባካችሁ አንባቢያን ጨምሩለት።
#አንደኛ: -የከተሞችን የመጠጥ ውሃ ችግር ለመፍታት ብድር የተገኘው በፈረንጆቹ አቆጣጠር Nov 2011 ከቻይና መንግስት ነው። የብድሩ መጠን 100 ሚሊዬን የአሜሪካን ዶላር ሲሆን የብድሩ ተጠቃሚ አዲስ አበባ ነበረች። ሁለተኛው ብድር የተገኘው May 2012 ከአለም ባንክ ሲሆን የብድሩ መጠን 150 ሚሊዬን የአሜሪካ ዶላር ነው። የብድሩ ተጠቃሚ የሆኑ ከተሞች አዲሳአባ፣ ጐንደር፣ ሐዋሳ፣ መቐሌ፣ ጅማ፣ ድሬደዋ ነበሩ። የከተሞች የህዝብ ብዛት በቅደም ተከተል አዲሳአባ፣ አዳማ፣ ጐንደር፣ መቀሌ፣ ሐዋሳ መሆኑን ማእከላዊ ስታስቲክስ ባለስልጣን ያሳውቃል።
#ሁለተኛ :- በተባበሩት መንግስታት የልማት ፕሮግራም (UNDP) እና በውሃ ጉዳዬች ላይ ጥናት በሚያደርግ water.org ጥናት መሰረት 61 ሚሊዬን የሚጠጋው የኢትዬጲያ ሕዝብ የንጹህ መጠጥ ውሃ አያገኝም።
#የመፍትሔ ሐሳብ
ሞጋች ደጋፊ ስህተቶቹን ብቻ ነቅሶ የሚያወጣ ሳይሆን የመፍትሔ ሃሳቦችንም ይጠቁማል። በዚህ መሰረት ዶክተር አቢይ በተሰጠው ስልጣን ማእቀፍ ውስጥ ሆኖ የሚከተለውን እንዲያደርግ ምክረ ሃሳብ ቀርቧል።
#1: የፌዴራል መንግስት ፕሮጀክት ድልድል በህዝብ ብዛትና በቆዳ ስፋት ከሆነ በኢህአዴግ መቃብር ላይ ይሆናል ያለውን አቶ አባይ ፀሀዬ ከመንግስታዊ ስልጣኑ በአስቸኳይ ማባረር።
#2: የህውሓት ስራ አስፈፃሚና የፋይናንስ እና ኢኮኖሚ ልማት ትብብር ሚኒስትር የሆነውን ዶክተር አብርሃም ተከስተ መጥራት። ለከተሞች ፌዴራል መንግስት ባለፋት 5 አመታት ለመጠጥ ውሃ የተወሰዱ ብድሮችን ለኢትዬጲያ ሕዝብ ይፋ እንዲያደርግ ማድረግ። በፓርላማም ቀርቦ ዝርዝር ማብራሪያ እንዲሰጥ ማድረግ።
…//…
Friday, March 30, 2018
The New EPRDF Chairman Must Respond Positively to the People’s Demand – Press Release March 29, 2018
The Ethiopian People’s Revolutionary Democratic Front (EPRDF) government has finally elected Dr. Abiy Ahmed as its new party Chairman to replace the outgoing Prime Minister Hailemariam Desalegn. While Dr. Abiy’s election answers the question of who will replace Hailemariam, it also raises two other important questions: whether the replacement represents the usual trickery from the TPLF playbook, or is it a genuine effort by reformists within the regime to address the demands of the Ethiopian people? We will soon learn the answers to these questions.
Thursday, March 29, 2018
አዲሱ የኢህአዴግ ሊ/መንበር የኢትዮጵያን ህዝብ ጥያቄ በተግባር መመለስ አለበት! ( የአርበኞች ግንቦት 7 መግለጫ )
March 28, 2018
አዲሱ የኢህአዴግ ሊ/መንበር የኢትዮጵያን ህዝብ ጥያቄ በተግባር መመለስ አለበት!
አቶ ኃ/ማሪያም ደሳለኝ የሥልጣን መልቀቂያ ጥያቄ ካቀረቡ ከአርባ ቀን በኋላ እና በመጀመሪያ የኢህአዴግ ስራ አስፈጻሚ ኮሚቴ ለብዙ ቀናት ቀጥሎም ምክር ቤቱ ከአንድ ሳምንት በላይ የፈጀ ስብሰባ ከተቀመጠ በኋላ ዶ/ር አቢይ አህመድን የግንባሩ ሊ/ቀመንበር አድርጎ መርጧል። የዶ/ር አቢይ የኢህአዴግ ሊ/መንበር ሆኖ መመረጥ የሚቀጥለዉ የኢትዮጵያ ጠ/ሚኒስትር ማን ሊሆን ይችላል በሚል በአትኩሮት ሲጠበቅ ለነበረው ጥያቄ የመጀመሪያ ዙር ምላሽ ሰጥቷል። ለመሆኑ የዶ/ር አብይ መመረጥ የተለመደው የወያኔ የሴራ አካሄድ ውጤት ነዉ? ወይስ ኢህአዴግ የህዝብን እውነተኛ የለውጥ ፍላጎት ሰምቶ መንገዱን ለማስተካከል የወሰደዉ ዕርምጃ ነዉ? የኢህአዴግ ዉሳኔ እነዚህን ጥያቄዎች ያጠቃለለ ጥልቅ ውይይት ተካሂዶበት የተወሰነ መሆኑንና ያለመሆኑን በቅርቡ የምንሰማውና በተግባርም የምናየው ይሆናል።
የዶ/ር አብይ መመረጥ ኢህአዴግ ውስጥ ያሉት እስካሁን የህወሀት ሎሌ ሆነው ሲያገለግሉ የነበሩት ድርጅቶችና በህወሓት ውስጥም ያሉ አንዳንድ ለውጥ ፈላጊዎች በጋራ አሸንፈው ከሆነና እነ ዶ/ር አብይ በተለይ በኦህዴድ ምክር ቤት ስብሰባ መግለጫ ላይ ያወጡትን ለውጥ ፈላጊ አቅጣጫ ተግባራዊ ለማድረግ ወስነው ከሆነ እሰየው ነው። የኢህአዴግ ዉሳኔ በአገራችን በኢትዮጵያ ላይ የተደቀነውን ከፍተኛ አደጋ ለመከላከል፥ ችግሩን በሰላማዊ መንገድ ለመፍታትና ብሎም ወደ እውነተኛ ዴሞክራሲያዊ ስርዓት ለመሸጋገር የሚያስችል እንቅስቃሴ ውስጥ የሚገባ ከሆነ ለውጥ ፈላጊው ህዝብ ሁሉ የሚፈልገው ነውና በአዎንታዊ መልኩ የምንወስደው ነው።
Monday, March 26, 2018
Monday, March 19, 2018
"ያመናልበለው" እኛ ኢትዮጵያውያን በነጻነታችን ቀን በህብር በአንድነት በየ አደባባዩ በፍቅር በጋራ የምንጨፍርበት የጋራ ሀገራዊ ጭፈራ " አያመና በለው ያመና በለው አማራው ሲነካ ያመናል በለው፣ ኦሮሞው ሲነካ ያመና በለው፣ ጉራጌው ሲነካ ያመና በለው፣ አፋሩ ሲነካ ያመናል በለው ፣ ሲዳማው ሲነካ ያመናል በለው፣ ቤንሻንጉል ሲነካ ያመናል በለው፣ ሀድያው ሲነካ ያመና በለው፣ ከምባታው ሲነካ ያመና በለው፣ ኮንሶውም ሲነካ ያመና በለው" አጣጥሙት ወኔ ሰንቁበት ያ መ ና ል በ ለ ው
የትዊተር ዘመቻ አቢ ይለቀቅ! አቢ ይለቀቅ! (አማርኛ ከስር ያንብቡ) Fri Abi! Fri Abi! Fri Abi!
Abi is among distinguished Ethiopian political activists in Norway. He fought the Ethiopian regime both in Ethiopia and in Norway where he sought asylum. He is a member and coordinator of political organizations and media. The Norwegian Utlendingsmyndighetene denied him protection and he is now in trandum ready for expulsion in a country that has declared martial law where Ethiopian regime kills people who protest the regime every day. It's a serious mistake and unacceptable decision that puts abis lives at risk. Therefore Ethiopians in Norway and anyone who fights for human rights must fight to liberate abi and save him from expulsion from Norway. No Norwegian or politician must stand still when a political aktivists life put at risk in democratic countries like Norway. Free Abi! Free Abi! Free Abi!
==============
Free Brother! Free Brother! Free Brother!
Abi is among prominent Ethiopian political activists in Norway. He fought against the Ethiopian regime both in Ethiopia and in Norway where he sought asylum. He is a member and coordinator of political organizations and media. The Norwegian Immigration Authority refused protection and he is now in Trandum ready for expulsion in a country that has declared a state of emergency where the Ethiopian regime kills people protesting the regime every day. It's a serious mistake and unacceptable decision that puts Abi's life at risk. Therefore, Ethiopians in Norway and all who fight for human rights must fight to liberate Abi and save him from expulsion from Norway. No Nordmann or politicians must stand still when a political activist's life is at risk in a democratic country like Norway. Free Abi! Free Abi! Free Abi!
አቢ በኖርዌይ ውስጥ በኢትዮጵያ ፖለቲካ ጉዳይ በንቃት ከሚሳተፉት ኢትዮጵያውያን ውስጥ ነው።አቢ የፖለቲካ ጥገኝነት ከጠየቀባት ኖርዌይ ውስጥ ሆኖ ላለፉት ዓመታት ሁሉ አሁን በኢትዮጵያ ያለውን አገዛዝ ከሚቃወሙት ኢትዮጵያውያን ውስጥ ነው።አቢ ካለፈው ዓርብ ጀምሮ የኖርዌይ ፖሊስ ይዞት በግዳጅ ወደ ኢትዮጵያ ለመመለስ እስካሁን እስር ቤት ይገኛል።ኢትዮጵያውያን አቢ እንዲለቀቅ የሶሻል ሚድያ ዘመቻ ከፍተዋል። ይህንን ለብዙዎች በመላክ ዘመቻውን ይቀላቀሉ።
አቢ በነፃ ይለቀቅ!!
Thursday, March 1, 2018
Tuesday, February 20, 2018
Friday, February 16, 2018
Tuesday, February 13, 2018
Sunday, February 11, 2018
በሀሳብ መንገድ ላይ “ድንቁርና ጨካኝ ነው!!” (ተመስገን)
ሶቅራጥስ በመርዝ ተገድሏል፣ ክርስቶስ ተሰቅሏል፣ ብሩኖ ከእነ ህይወቱ በእሳት ጋይቷል፣ ጋንዲ በጥይት ተደብድቧል፣ ኦሾም ተመርዞ ነው የሞተው ይባላል፡፡ … ኧረ ስንቱ!! … ድንቁርና ጨካኝ ነው!!
ሁሉም ሰላማዊና የፍቅር ሰዎች ነበሩ፡፡ ሁሉም ለሰው ልጆች እኩልነት ቆመዋል፡፡ ሁሉም ዓለማቀፍ ሰብዕና ነበራቸው፡፡ … ለዘር፣ ለቀለም፣ ለሃይማኖት ልዩነት አላጎነበሱም፡፡ … ሁሉም ዕውነትን በማስተማራቸው፣ ዕውነትን በመጋፈጣቸው፣ ጊዜ በሰቀላቸው ጉልበተኞችና ደንቆሮ ወገኖቻቸው መዳፍ ተጨፍልቀዋል፡፡ ደግነቱ እነሱ ቢያልፉም ሃሳቦቻቸውና አስተምህሮቶቻቸው አላለፉም። ሃሳቦቻቸው ምድራችንን የሰው ልጆች ሲዖል ከመሆን ታድገዋታል፡፡
ሶቅራጥስ ለመሞት ሲዘጋጅ፣ የጓደኞቹን ሀዘንና ብስጭት ተመልክቶ፡-
“በድኔ እንጂ ‘ሚቀበረው ሃሳቤ‘ኮ አይደለም … አይዟችሁ!!” … (Be of good cheer, and say that you are burying my body) ነበር ያላቸው። እንዳለውም፤ ድንቁርና ሲሸማቀቅ፣ ጉልበተኛም በጊዜ ሂደት ሲዋረድና ሲንበረከክ እየታየ፣ እዚህ ዘመን ላይ ተደርሷል፡፡
ወዳጄ፡- በሃይልና በጦርነት የተያዘ የመንግስት ሥልጣን፤ በአፋጣኝ ወደ ዴሞክራሲያዊነት ካልተቀየረ መዘዙ ብዙ ነው፡፡ … ሄራክሊተስ እንደፃፈው፤ ጦርነት አንዳንዱን አምላክ፣ አንዳንዱን ሰው፣ አንዳንዱን ባርያ፣ አንዳንዱን ደግሞ ነጻ አድርጎ ስለሚያልፍ፣ ብዙኃኑን ለመከራና ስቃይ ይዳርጋል፡፡
ጉልበት፤ የደንቆሮዎች መመኪያ ነው ይባላል። ጉልበተኞች፤ ጊዜ እስቲከዳቸውና ጥሏቸው እስኪሸሽ ወይም ታላቁ ቮልቴር፤ “ሚስማር በሚስማር ይነቀላል” እንዳለው፤ ሌላ ሚስማር እስኪመታቸው ድረስ የሚመጣውን ለመቀበልና ተተኪውን ለመጋተር ቢያደፍጡም ዞሮ፣ ዞሮ የሚሆን ከመሆን፣ የተፃፈው ከመነበብ አይቀርም። … ራቀም ቀረበ፣ ተወደደም ተጠላ፣ ተፈራም አልተፈራ፣ … ጊዜ ለባለተራው “ሞገስ” ሊሆን፣ እዛ ጋ ቆሞ ያሽሟጥጣል!!
ወዳጄ፡- ጦርነት፣ ጦርነትን እየወለደ፣ አንዱ ጉልበተኛ ሌላውን እየተካ በሄደ ቁጥር ጦሱ ለብዙኃኑ ነው፡፡ ገልባጭ ተገልባጩን መቆንጠጡ ደግሞ መቼም አይቀሬ ነው፡፡ “በሰላም መለያየት” (Happy divorce) ያለው ሲኒማ ውስጥ ወይም ቼዝ ጨዋታ ላይ ነው፡፡ በሰላም መለያየት የሚፈልግ … ነፃ፣ ዴሞክራሲያዊና ሁሉን አቀፋዊ የውይይት መድረክ አዘጋጅቶ የመሰለፍ፣ የመናገርና የመፃፍን ጨምሮ ሌሎች ተፈጥሯዊና ህገ መንግስታዊ መብቶችን አክብሮ፣ የሰለጠነ መንገድን በመከተል፣ ለሰላማዊ ሽግግር (peaceful transition) መሥራትና መታገል ይኖርበታል፡፡ የግልበጣ ነገር ከተነሳ፣ አንድ ወንድሜ በነገረኝ ቀልድ እንዝናና፡-
ሰውየውና ሚስቱ አልፎ፣ አልፎ ይጣላሉ። ይደባደባሉ፡፡ በተጣሉ ቁጥር ሴቲቱ ጉልበት ነበራትና አስተኝታ ትወቅጠዋለች፡፡ አንድ ቀን እንደለመደችው፤ጉብ ብላ ስትጠፈጥፈው፣ አጅሬ እንደ ምንም አቅሙን አሟጦ ገለበጣትና፣ ደህና አድርጎ ያቀምሳት ጀመር፡፡ .. ሴቲቱ ኡኡታዋን አቀለጠችው፡፡ ጎረቤት እየተሯሯጠ መጥቶ ሊገላግል ሲሞክር … ሰውየው፤ “እባካችሁ ተዉኝ! አዲስ ግልብጥ ነኝ፤ ትንሽ ልኮርኩማት” … ሲል ተማጸናቸው፡፡
ወዳጄ፡- ጉልበተኛ ለመልካም ሃሳብህ ያንገላታሃል፣ በገዛ ቤትህ ያስርሃል፣ በገዛ ሀገርህ ስደተኛ ያደርግሃል፡፡ ጉልበተኛ ንብረትህን ይዘርፋል፣ ስራህን ይቀማል፣ ቤተሰብህን ያፈርሳል፡፡ … ጉልበተኛ በዝምታህ ይበሳጫል፣ ስምህን ያጠፋል፣ ሳትነካው፣ ሳትደርስበት ይንኳኳል፡፡ ደንገጡሮቹም እንደዛ ናቸው!! … ጥቅምና ጊዜያዊ ደስታ ያሰክራቸዋል፣ አቅላቸውን የሳቱ አውደልዳዮች ያደርጋቸዋል፡፡ ለእውቀትና ምክንያታዊነት ቦታ የላቸውም፡፡ እያዩ አያዩም፣ እየሰሙ አያዳምጡም። ብዙ መስለው ትንሽ፣ የሚስቁና የሚያሽካኩ ሆነው፣ ነፍሳቸው የምታለቅስባቸው፣ የደላቸውንና የተመቻቸው መስለው፣ የመኖር ጣር ያነቃቸው ናቸው፡፡ ደስታ በገንዘብ የሚሸመት ይመስላቸዋል፡፡
ሾፐን ሃወር፤ “ደስታ የሚገኘው ከሃሳባችን ውስጥ እንጂ ከኪሳችን በሞላነው ገንዘብ አይደለም። (Our happiness depends on what we have on our heads rather than on what we have in pockets) ማለቱ አውደልዳዮቹ ዘንድ አይሰራም። ድንቁርና ጨካኝ ነው!!
“ማሰብ በሌለበት ሁኔታ የሚነግሰው ሁካታና ግርግር ነው፡፡ ብቸኛም ቢሆኑ ራሳቸውን ሆነው የሚኖሩ ሰዎች ይሻላሉ፡፡ አውደልዳዮች፤ ጨካኝና አመፀኞች ብቻ አይደሉም፡፡ በዕውቀት ሳይሆን በምላስ የሚነዱ፣ በቆንጆ ቃላት የሚታለሉ ጅሎች ናቸው፡፡ በመዳብ እንደተሰራ ባዶ ማሰሮ ትንሽ ሲነኩ ያለ ማቋረጥ ይጮሃሉ” የሚለን ፕሌቶ፤ “ሞት ለሶቅራጥስ!” እያሉ ሲጮሁ የነበሩትን አውደልዳዮች በመታዘብ ነው፤ እየደጋገመ፤ “ድንቁርና ጨካኝ ነው” እያለ የሚያስጠነቅቀንም ለዚህ ነው፡፡ እውነት ነው፡፡ ድንቁርና ጨካኝ ነው!!
ወዳጄ፡- ለዕውቀት፣ ለሰላምና ለነፃነት ዕድል መስጠት ያስፈልጋል፡፡ አንድነት የሚፀነሰው እዛ ነው፡፡ የእውነተኛ ልማት መሰረትም እነሱ ናቸው። አውሮፓውያን ለዕውቀት ትልቅ ቦታ አላቸው። አንድ ቀን በንግድና ገበያ ልማት ትስሰር ሳቢያ ወደ አንድነት እንደሚመጡ፣ ፍሬድሪክ ኒች፣ ከመቶ ሰላሳና አርባ ዓመታት በፊት ተንብዮ ነበር፡፡ ትንቢቱም ተፈጽሟል፡፡ የአውሮፓውያኑን አንድነት ሳስታውስ፣ የአህጉራችን ነገር ያሳስበኛል። አፍሪካውያን ምሁራንም፤ የአውሮፓውያኑ ዓይነት ህልም ነበራቸው፡፡ ህልማቸው፣ ምናልባት አንድ ቀን ዕውን ሊሆን ይችላል፡፡ አሁን ባለንበት ሁኔታ ግን እንኳን ለአፍሪካዊ አንድነት ልንቆም፣ “ኢትዮጵያዊ ነኝ” ማለት እንኳ የተረሳ ይመስላል፡፡
“ህዝቦች የሃገራቸውን ስም ጠርተው እንደዚህ ነኝ ማለት፣ እስከ መከልከል በደረሰበት ዘመን፤ አፍሪካዊነት ምን ይበጃል? ጋናዊ ሆኖ፣ “ጋናዊ ነኝ” ካላለ፣ አፍሪካዊነት ቢቀርበት ምን ይጎዳዋል? “ፅድቁ ቀርቶብኝ በቅጡ በኮነነኝ” ይባል የለ? … የገዛ ሀገሩ አፈር እየሸተተው፣ በወንዙ እየተለቃለቀ፣ነገር ግን የማንነቱን መታወቂያ በስውር ተነጥቆ፣ የሃገር ውስጥ ስደተኛ ለሆነ ህዝብ፤ “አፍሪካዊ ነኝ” ማለቱ ይጠቅመው ይሆን?” … ፍርዱን ለአንባቢ ትቼዋለሁ።
* * *
ወዳጄ፡- ለሃሳብም ሆነ ለጉልበት ባርነት ጊዜው አልፏል፡፡ ሀገርም ሀገር፤ ሰውም ሰው የሚሆነው፣ ከሙስና የፀዳ አስተዋይ ህብረተሰብ የሚፈጠረው፣ የሀገር ፍቅርና አንድነት የሚደምቀው፣ ለዕውቀት፣ ለነፃ ሀሳብና ፍልስፍና መስፋፋት ቅድሚያ ሲሰጥ ነው፡፡ በራሱ የሚተማመን ዜጋ የሚበረክተው፣ ችግሮችን በብልሃትና በዘዴ መፍታት የሚቻለው፣ አድልዎ የሌለበት ፍትሃዊ አስተዳደር የሚገነባው፤ በድንቁርና ላይ ሲዘመት ይመስለኛል፡፡ ዕውነት ዕውነት እልሃለሁ፤ ድንቁርና ጨካኝ ነው!!
“ዕውቀት፤ ሙሰኛና ፈሪ ከመሆን ያድናል” (Learning conquers or mitigates the fear of death and adverse fortune) የሚለን ፍራንሲስ ቤከን ነው፡፡ ቤከን፣ ይህንኑ እውነት እንዲያረጋግጥልንም ባለቅኔ ቨርጂልን ምስክርነት አቁሞታል፡፡ ቨርጂልም፡-
“የነገሮችን ምንነት መርምሮ የሚረዳ ሰው … እሱ ደስተኛ ነው፡፡ ፍርሃት፣ ስግብግብነትና አጉል ምኞት አያንበረክኩትም፡፡” (Happy the man who has learned the causes of things, and has put under his feet all fears and inexorable fate, and the noisy strife of the hell of greed) በማለት ቤከንን አስጨብጭቧል፡፡
ወደ መነሻችን ስንመለስ፣ በጉልበትና በተፅዕኖ ሃሳብን ለማፈን መሞከርና አሳቢዎችን ማንገላታት፣ በቆሸሸ መስታወት ውስጥ የራስን ገፅ እንደ መመልከት ይሆናል፡፡ በነገራችን ላይ ወዳጄ፡- ሎዮናርዶ ዳቪንቺ የመጨረሻው እራት “The last supper” የተባለውን ስዕል እንዲሰራ በተጠየቀበት ጊዜ ያለማመንታት ነበር የተቀበለው፡፡ ዳቪንቺ በተወጠረው ሸራ ፊት ለፊት ረዥም ሰዓት ቁጭ ብሎ ያስብ ነበር፡፡ ሚካኤል አንጀሎ፤ “ስዕል በአእምሮ እንጂ በእጅ አይሳልም፡፡” (One paints not with the hands but with the brain) እንዳለው፡፡ … ይሄ ያልገባቸው አለቃ (Abot) በየጊዜው እየመጡ፤ “አሁንም አልጀመርክም?” በማለት ከሃሳቡ እየቀሰቀሱ, ተፅዕኖ ሊያደርጉበት ፈለጉ፡፡ …
ዳቪንቺ ተበሳጨ፡፡ ስራው ተጠናቆ ታላቅ የጥበብ ውጤት መሆኑ በዓለም ጠቢባን ዘንድ ተናኘ፡፡ ቀስ በቀስ ስዕሉ ሲጠና፣ ዳቪንቺ፤ የአስቆሮቱ ይሁዳን የወከለበት ምስል፣ አለቃ (Abot) ራሳቸው ነበሩ፡፡ “Davinch’ used the gentle man as unconsious model for the figure of Judas” … በማለት ቬነዲቶ ክሮቼ ጽፎልናል፡፡
ወዳጄ! እውቀት የሚጫኗትን እንኳ በጥበብ መንገድ ነው፣ክፋታቸውን የምታሳየው፡፡ ድንቁርና ግን ጨካኝ ነው!!
ሠላም!!
Thursday, February 8, 2018
Wednesday, February 7, 2018
Tuesday, February 6, 2018
Monday, February 5, 2018
Sunday, February 4, 2018
Saturday, February 3, 2018
ድምፃዊ ሻምበል በላይነህ ከዋሺንግተን እስከ ኤርትራ በርሃ -SHABEL BELAYNEHE: FROM WASHINGTON ...
ድምፃዊ ሻምበል በላይነህ ከዋሺንግተን እስከ ኤርትራ በርሃ -SHABEL BELAYNEHE: FROM WASHINGTON ...
የአርበኞች ግንቦት 7 ተልዕኮ ራዕይ
የአርበኞች ግንቦት 7 ንቅናቄ፣ እያንዳንዱ ኢትዮጵያዊ ዴሞክራሲያዊና ሰብአዊ መብቱ የተከበረበት፣ የኢኮኖሚ ብልፅግናና ማኅባራዊ ፍትህ የሚያገኙበት፣ የዜጎች ህይወት፣ ደህንነትና ጥቅም የተከበረበት ሃገር እንዲኖረው ማድረግ ነው።
ተልዕኮ
የአርበኞች ግንቦት 7 ንቅናቄ፣ ቀዳሚ ተልዕኮ የመንግስትና የፖለቲካ ስልጣን በሠላማዊና ዴሞክራሲያዊ ሂደት የሚያዝበትንና የሃገሪቱ ዜጎች ምርጫ በተግባር የሚገለፅበትን ብሄራዊ ሥርአት እንዲገነባ ማገዝ ነው።
መሰረታዊ ዕሴቶችና መርሆዎች
የግለሰቦችና የህዝብ መብቶች መከበር የአዲሱ ፖለቶቲካዊ ሥርአት የሚዕዘን ድንጋይ ነው፣
የአዲሱ ፖለቲካዊ ስርአት የጀርባ አጥንት በመሆን የአምባገነን መንግስታትንም ሆነ ፓርቲዎችን፣ እንዲሁም ፖለቲከኞችን መረን ያጣ ሥልጣን ለመቆጣጠር፣ ነፃ መንግስታዊ የሆኑና ያልሆኑ ተቋማት ምሥረታና መጠናከር አስፈላጊነቱን በማመን፣ ነፃ የፖሊስና የመከላከያ
ሃይል፣ ነፃ የምርጫ ቦርድና ነፃ ፕሬስ እንዲመሰረቱና እንዲጠናከሩ መታገል፣
የሃይማኖት፣ የዘውግ፣ የባህልና የመልክአ ምድራዊ አቀማመጥ ልዩነቶች የሚያደምቁን ውበቶቻችን እንጂ፣ የርስ በርስ መጠቃቂያ መሳሪያዎች አለመሆናቸውን በማመን፣ ይህንን ውበት ያላበሱን ልዩነቶቻችንን የሚያከብር በሃገራዊ አርበኛነት ላይ የቆመ ጠንካራ ህብረተሰብ መገንባት፣
ዜጎች ከሚጋሩት ህይወት፣ ህልምና ተስፋ እንዲሁም በታሪክ ካዳበሩት የጋራ ትስስር ይልቅ፣ የዘውግ፣ የሃይማኖትና ባህላዊ ልዩነቶቻቸውን ለአጭር ጊዜ የፖለቲካ ጥቅም የሚቆምሩ ፖለቲካዊና ተውፊታዊ ጎታች ሃይሎችን መታገል፣
ዜጎች በዘውግ ጀርባቸው፣ በሃይማኖታቸው፣ በቋንቋቸው፣ በባህላቸው፣ በእድሜያቸው፣ በጾታቸው ወይም በመልክአ ምድራዊ ልዩነቶቻቸው ወይም በግላዊ አቅመ-ደካማነታቸው የተነሳ አድልኦ የማይፈጸምባቸውና የዜግነት የእኩልነት መብታቸው የሚከበርበት ፖለቲካዊ ሁኔታ ማመቻቸት፣
ሃገሪቱን ለማገልገል የቆረጡ፣ ታታሪ፣ ብሩህ፣ አርቆ አሳቢና ሆደ-ሰፊ፣ ለዜጎች አርአያ የሚሆኑ መሪዋች እንዲፈጠሩ ማገዝ፣
የመልካም አስተዳደር፣ የተጠያቂነትና የግልፅነት መርሆዎች፣ ህዝብን ማዕከል ካደረገ የውሳኔ አሰጣጥ ጋር ተሳስረው በተግባር የሚተረጎሙበትን ሥርአት መመሥረት፣
በጥረት የሚገኝ ውጤት የሚከበርበት፣ ሃገርን ማገልገል ድንቅ የሚባልበት፣ ችሎታና ታታሪነት ብቻ የሽልማት መስፈርቶች የሆኑበት፣ ዜጎች በፖለቲካ ትስስራቸውና በዘውግ ማንነታቸው ሳይሆን በአበርክቶአቸው የድካማቸውን ውጤት የሚያገኙበትና የሚወደሱበት ፖለቲካዊ ሥርአት መመሥረት፣
ከሌሎች የፖለቲካ ፓርቲዎችና ህዝባዊ ግንባሮች ጋር ቅንብርና ትብብር በመፍጠር፣ በመሃላቸው ያለውን ውጥረት ማርገብ፣ ብሎም፣ ሁሉን በአካተተ፣ ሰፊ የፖለቲካዊ ስርአት አማካይነት ብሄራዊ ሰላምና መረጋጋት መፍጠር፣
ማንኛውም የፖለቲካ ፓርቲ፣ የህዝብ ግንባርና እንዲሁም መብትና ጥቅሜ አልተጠበቀም የሚል ቡድን፣ በፖለቲካ ዕምነቱም ሆነ ፕሮግራሙ የተነሳ የማይገለልበትን፣ ሁሉን አቀፍ የፖለቲካ ሥርአት ማቋቋም ነው።
Friday, February 2, 2018
Thursday, February 1, 2018
ከአርበኞች ግንቦት ሰባትና ከትግራይ ህዝብ ዴሞክራሲያዊ ንቅናቄ የተሰጠ የጋራ መግለጫ
February 1, 2018
ከአርበኞች ግንቦት ሰባትና ከትግራይ ህዝብ ዴሞክራሲያዊ ንቅናቄ የተሰጠ የጋራ መግለጫ ( PDF )
በትግራይ ሥም እየማለና እየተገዘተ ለመንግሥት በትረ ሥልጣን የበቃው ህዝባዊ ወያኔ ሃርነት ትግራይ ላለፉት 26 አመታት በአገራችንና በህዝባችን ላይ ያልፈጸመው በደል የለም። ክፉንና ደጉን በመጋራት ለዘመናት ተቻችሎና ተፋቅሮ የኖረውን ህዝብ በቋንቋና በሃይማኖት በመከፋፈል በመካከላቸው የጠላትነት ግንብ ለመገንባት አቅም የፈቀደለትን ሁሉ አድርጎአል። የአገሪቱን የአንድነት ታሪክ ጥላሸት በመቀባትና ህብረተሰባችንን ድርና ማግ ሆኖው ያስተሳሰሩ የጋራ እሴቶችን በማጣጣል አንዱ የሌላው ጠላት ተደርጎ እርስ በርስ እንዳተያይና እንዳይተማመን በርካታ ተግባራትን አከናውኖአል። እራሱ የሚቆጣጠራቸውን የፖለቲካ ድርጅቶች በየክልሉ እያቋቋመና በራሳቸው ጸንተው የማይቆሙ ግለሰቦችን በመሪነት እያስቀመጠ በአገሪቱና በህዝቡ ጥቅሞች ላይ ዘላቂ ጉዳት ያላቸው ወንጀሎችን ፈጽሞአል።
እራሱን ብቸኛ የትግራይ ተወካይ በማድረግ “ህወሃትና የትግራይ ህዝብ አንድ ነው” የሚል ስብከት በህበረተሰቡ ውስጥ በማሰራጨት ለሚሰራቸው ወንጀሎች የትግራይን ህዝብ ምሽግ ለማድረግ ብዙ ጥሮአል። ለረጅም ዘመናት በሁሉም የአገሪቱ ክልሎች ኑሮውን መስርቶ ከአገሩ ህዝብ ጋር በሠላም ይኖር የነበረውን የትግራይ ተወላጅ በማስገደድና በማባበል አባል ካደረገ ቦኋላ በህዝብ ላይ ለሚፈጽማቸው ጥቃቶች መረጃ አቀባይ፤ ጉዳይ አስፈጻሚና ያካባቢው የሥርዓቱ የድጋፍ ኃይል አድርጎ ተጠቅሞበታል። በዚህም የተነሳ ለአመታት ተፋቅሮና ተከባብሮ ከሚኖረው ህዝብ ጋር እንዲጋጭና በጠላትነት እንዲተያይ አድርጎታል።
Wednesday, January 31, 2018
Professor Berhanu Nega (ከታዲሎ ደሴ)
ብዙ የአለም ሀገሮች ታላቅ ደረጃ ያደረሷቸው ፣ አባታችን እያሉ የሚጠሯቸው መሪዎች አሏቸው።ለምሳሌ ደቡብ አፍሪካውያን ከአፓርታይድ አሰቃቂ አገዛዝ ያወጣቸውን ኔልሰን ማንዴላን “ማዲባ” ሲሉ በአባትነት ክብር ይጠሩታል። ህንዳውያን ከእንግሊዝ ቅኝ አገዛዝ ያወጣቸውን ማህተመ ጋንዲን እንዲሁ በፍቅርና በጥበብ ተምሳሌትነት ህያው ያደርጉታል። ማሃተመ ማለት አዋቂ፣ የተከበረ፣ ጥበበኛ፣ ሊቅ፣ መምህር ማለት ነው። ቻይናውያን ማኦ ዜዱንግን የዕውነተኛ ኮሚኒስት አባት ይሏቸዋል ። ይህ የሚያሳየን ሕዝቦች በታሪክ ሂደት ውስጥ የሚገጥሟቸውን ችግሮች የፈቱላቸውንና ዘላቂና አስተማማኝ የሰላምና የዕድገት መሰረትን ጥለው ያለፉ ቀደምቶቻቸውን በጽሁፍ፣ በአፈታሪክ፣ በጨዋታ፣ በተረትና በተለያዩ ኪነ-ጥበባዊ ስራዎቻቸው እንደሚያሞግሷቸው፣ እንደሚዘክሯቸውና ባለውለታነታቸውን እንደሚመሰክሩላቸው ያሳየናል። እነኚህ ግለሰቦች ባጭሩ የህዝብና የሃገር አባት ተብለው ይጠራሉ።
ይህ ዕውነት ደግም በኛዋ ኢትዮጵያና በኢትዮጵያዊያን ዘንድም የሚሰራበት ክስተት ነው። ጥንታዊና ዘመናዊ ኢትዮጵያን በመወጠኑና በመቅረጹ ረገድ ከነችግሮቻቸውም ቢሆን ብዙ የለፉና የታገሉ ባለውለታዎች ነበሩን፣ አሁንም አሉን። አጼ ቴዎድሮስ፣ አጼ ዮሀንስ፣ ራስ ጎበና፣ አጼ ሚኒሊክ በዋናነት የሚጠቀሱ ናቸው።እነሱ የሚችሉትን ሁሉ አድርገው አልፈዋል። ዕውቅና፣ ክብርና ቦታ መስጠቱ የኛ የተከታዮቻቸው ሃላፊነት ይሆናል ማለት ነው።
"እኛ ካልገዛናችሁ እንገነጠላለን" "እኛ ካልገዛናችሁ ሀገር ትፈርሳለች " ------------------------------ የሰው ልጅ በጥይት እንደ ቅጠል እየረገፈ ስለቁሳቁስ እና ንብረት መውደም ሲጨነቁ የከረሙት ህወሓቶች ለ26 ዓመታት ለመከፋፈያና ለማስፈራሪያ ሲጠቀሙበት የነበረውን አንቀጽ 39ን አቧራውን አራግፈው ስለመገንጠል እያቀነቀኑ ነው። ይህ የፕሮፓጋንዳ አካሄድ ከምን የመነጨ ነው? በርግጥ ህወሓት የትግራይ ሕዝብ ውክልና አለውን? በፕሮፓጋንዳ አፈቀላጤዎቹ ማህበራዊ ገጽ ላይ እየሄዱ መልስ መስጠቱና መከራከሩ ለተቃዋሚው ፋይዳ አለው ወይ? የሚዲያ ጥናት ባለሞያው ጋዜጠኛ እንዳልካቸው ኃይልሚካኤል የህወሓት ስልጣንና ጥቅም ከሌለ ኢትዮጲያ ትፍረስ የሚለው አስተሳሰብ በምርጫ 97 ወቅት ከሟቹ ጠቅላይ ሚኒስትር መለስ ዜናዊ ጀምሮ የነበረ እንደሆነ ይገልጻል። ሕዝቡ እንደቀደሞው ሁለተኛ ዜጋ ሆኖ ለህወሓት ተንበርክኮ የሚኖርበት ዘመን አብቅቶ ኢፍትሐዊነትን እየታገለ በመሆኑ በደኸው ላይ ተንደላቀው የሚኖሩ የስርዓቱ ተጠቃሚዎች ደንግጠው በቅዠት እየለፈለፉ ነው። የዛሬው ዛሬ ዝግጅት በዚህ ላይ ያተኩራል።
Tuesday, January 30, 2018
Monday, January 29, 2018
የመርሳ ከተማ አስተዳዳሪ ተገደሉ፤ የወልዲያ ተቃውሞ ዳግም በከፍተኛ ሁኔታ ተቀሰቀሰ
የመርሳ ከተማ አስተዳዳሪ ተገደሉ፤ የወልዲያ ተቃውሞ ዳግም በከፍተኛ ሁኔታ ተቀሰቀሰ
Sunday, January 28, 2018
Friday, January 26, 2018
Thursday, January 25, 2018
ትግሉ ከተጠቂነት ወደ አጥቂነት መሸጋገር አለበት !!
በወልዲያ ፣ ትላንትና ዛሬ ደግሞ በቆቦ የወያኔ ፋሽስቶች በህዝባችን ላይ እያደረጉ ያለው ዘግናኝ ጭፍጨፋ ይህ ወራሪና ቅኝ ገዢ መስል ኣረመኔ የጥቁር ሙሶሊኒዎች አገዛዝ ፈጽሞ የፓሊሲም የባህሪም ለወጥ ማድረግ የማይችል መሆኑን ያረገጋገጠበት ነው።
ከእባብ የእርግብ እንቁላል እንደማይጠበቅ ከወያኔ ስርአት የሚመጣ አንዳችም ለውጥ አይኖርም!
የኢትዮጵያ ሕዝብ የጀመረውን የነጻነት ትግል ማቀጣጠል ጊዜው አሁን ነው! በየአካባቢው ተደራጅቶ በመረጃና በጥናት ወያኔን መምታት አለበት።
ትግሉ ከተጠቂነት ወደ አጥቂነት መሸጋገር አለበት! የወያኔ ፋሽስቶች ወጣት ሴት አዛውንት እየገደሉ የኢትዮጵያ ህዝብ ዘላለም ተጠቂ፣ ተበዳይ፣ ተረጋጭ፣ ተዋራጅ፣ ሆኖ ፈጽሞ መቀጠል የለበትም።
ይህን ጨካኝ አረመኔ ጸረ ህዝብ ወራሪ ቡድን ራሱ የሚደማ፣ የሚሞት፣ ሊወድም የሚችል መሆኑን በተግባር ማሳየት፣ ማረጋገጥም ያስፈልጋል።
በሁሉም የኢትዩጵያ አካባቢዎች ይህን በተግባር መፈጸም በጥቂቶቹ ፋስቶች ጎራ ብርክን የሚያስፈን ነው ብሎም ስርአቱን ገዝግዞ የሚያወድም መሆኑን መጠራጠር የለብንም።
ሁሉንም ቦታ ሊሽፍኑ አይችሉም ሃይላቸው እንዲበታተን በሁሉም አካባቢ ትግሉ መጠመድ፣ ወያኔም መመታት መድማት አለበት!
ሰለዚህ ኢትዮጵያዊ ሁሉ ይደራጅ፣ ይተባበር፣ ይታጠቅ ራስንና ወገኖችን ከወያኔ አረመኔ ነፈሰ ገዳዮች ይከላከል።
ወያኔንና ንብረቶቹን ማወደም ፣ ማዳክም፣ መቦርቦር የስረአቱን ውደቀት የሚያፋጥን የነጻነት ጎህ የሚቀድ ይሆናል!!
እንደራጅ! እናደራጅ! መደራጀት ! ተደራጅቶም ወያኔ በየአካባቢው ማዋከብ፣ መወጠር ወቅቱ አሁን ነው !!ጊዜው አሁን ነው!!
ከተጠቂነት ወደ አጥቂነት መሸጋገሪያው ጊዜ አሁን ነው!!
እያንዳንዱ ይህን መልክት በአገኘው መስመር ለህዝባችን ያስተላልፍ ! ያደራጅ ! አርበኞች ግንቦት 7 በሁሉም አካባቢዎች የህዝቡን ትግል የሚያጠናክሩ አርምጃዎችን ይወስዳል።
ድል ለኢትዮጵያ ህዝብ መሆኑ አይቀሬ ነው!!
ህወሃት ለአገርና ለህዝብ ጥቅም ብሎ መታደስ የሚችል ድርጅት አይደለም። ትግሉ ተጠናክሮ መቀጠል ይኖርበታል (የአርበኞች ግንቦት 7 ርዕስ አንቀጽ)
ህዝባዊ ወያኔ ሃሪነት ትግራይ የመንግሥት በትረ ሥልጣን ከተቆጣጠረበት 1983 ጀምሮ ጠባብ አላማውን ለማሳካት ሲል በርካታ ወንጀሎችንና ክህደቶችን በአገርና በወገን ላይ ሲፈጽም የኖረ ድርጅት ነው። ከነዚህ ወንጀሎች አንዱና ምናልባትም ለረጅም ጊዜ ተንሰራፍቶ ሥልጣን ላይ ለመቆየት ያስቻለው እርስ በራሳችን እንዳንተማመን በመካከላችን የዘራው የጥላቻ ፖለቲካ ነው። በህወሃት የጥላቻ ፖለቲካ መሠረት ኢትዮጵያችን አያት ቅድሜ አያቶቻችን በጋራ በከፈሉት መስዋዕትነት የተመሠረተችና ከተከታታይ የባዕድ ወረራ ነጻነቷን ጠብቃ የኖረች አገር ሳትሆን አንድ ማህበረሰብ ሌለውን ቅኝ በመግዛት የፈጠራት አገር ነች። ይህ ቅኝ ገዥ ሃይል ደግሞ ሥልጣን ላይ የተፈራረቁ መንግሥታት እስከዛሬ አገራችን ውስጥ ላደረሱት የአስተዳደር በደሎች ሁሉ ተጠያቂ ነው። ላለፉት 26 አመታት የመንግሥት ተቋማትና ሚዲያዎች በቅንጅት ሲያስተምሩና ሲቀሰቅሱ የኖሩት እንዲህ አይነት መሠረት የሌለውን መርዘኛና ከፋፋይ ቅስቀሳ ህብረተሰቡ ውስጥ ለማሰረጽ እና በአገራችን ላይ የጋራ ኩራት እንዳይኖረን የማድረግ ደባ ነው። በዚህ አፍራሽ ፕሮፖጋንዳ ምክንያት በኢትዮጵያዊነታቸው እንዲሸማቀቁ ተደርገው ያደጉ ፤ በደረሰባቸው የማንነት ቀውስ አዲስ ማንነት ፍለጋ የህገመንግሥቱን አንቀጽ 39 ተስፋ የሚያደርጉ ዜጎች ቁጥር በቀላሉ የሚገመት አልሆነም። ሌላው ቀርቶ በጥቁር ህዝቦች ሁሉ ዘንድ እንደ ነጻነት አርማ ተደርጎ የሚታየው አረንጓደ ብጫ ቀይ ባንድራችን የኩራታችን ምልክት ሳይሆን የባርነት ምልክት ተደርጎ እንዲታይ ያልተሠራ ሻጥር የለም። ለአንድነታችንና ለሉአላዊነታችን ከፍተኛ ዋጋ የከፈሉ ጀግኖች አባቶቻችን ታሪክ ተንቋሾ እንዲናፍርባቸው ተደርጎአል። በአመታት ጥረት የተገነቡ ብሄራዊ ተቋሞቻችን እንዲፈርሱና አገራቸውን በቅንነት ሲያገለግሉ የነበሩ ብዙ ሺዎች እንዲባረሩ ተፈርዶባቸዋል። ብሄራዊ መከታችን የነበረው የቀድሞ ጦር በፋሽስትነት ተፈርጆ እንዲፈርስና ከአምስት መቶ ሺ በላይ አባላቱ ለልመናና ለጎዳና ተዳዳሪነት እንዲዳረጉ ተደርገዋል። ኢትዮጵያዊ ሪህራሄና ወገንተኝነት በጎደለው ጭካኔ በብዙ መቶ ሺ የሚቆጠሩ ዜጎች ተወልደው ካደጉበት ቄያቸው እንዲፈናቀሉና መሬታቸው ለባዕዳንና ለሥርዓቱ አገልጋዮች እንዲከፋፈል በማድረግ ከፍተኛ ሃብት ተካብቶበታል። ይሉኝታና ሃፍረት በሌለው ጋጥ ወጥነት አብዛኛውን የመንግሥት ሠራተኛና የግል ንግድ ባለቤቶችን ከሥራቸው በማፈናቀል በምትኩ የአንድ ቡድን አባላት በበላይነት የሚቆጣጠሩት የኢኮኖሚና የፖለቲካ ሥልጣን ተፈጥሮአል። ይህንን ግፍና ኢፍትሃዊ አሠራር የተቃወሙትን ዜጎች ሁሉ በገቡበት ገብቶ ለማጥፋት በተወሰደው እርምጃ በጠራራ ጸሃይ በርካታ ዜጎች በየአደባባዩ ተገድለዋል ፤ ታስረዋል ፤ ተገርፈዋል ፤ አገራቸውን ጥለው እንዲሰደዱ ተደርጎዋል። ከግዲያ ተርፈው ዛሬ ድረስ በየ እስር ቤቱ የሚማቅቁና ፤ እዚያ እስር ቤት ውስጥ በተፈጸመባቸው ድብደባ አካል ጉዳተኛ ሆነው የሚሰቃዩ ዜጎች ቁጥር ስፍር የለውም።
Wednesday, January 24, 2018
Sunday, January 21, 2018
ህወሃት ለአገርና ለህዝብ ጥቅም ብሎ መታደስ የሚችል ድርጅት አይደለም። ትግሉ ተጠናክሮ መቀጠል ይኖርበታል!!! {አርበኞች ግንቦት 7 ርእሰ አንቀጽ}
January 20, 2018
ህዝባዊ ወያኔ ሃሪነት ትግራይ የመንግሥት በትረ ሥልጣን ከተቆጣጠረበት 1983 ጀምሮ ጠባብ አላማውን ለማሳካት ሲል በርካታ ወንጀሎችንና ክህደቶችን በአገርና በወገን ላይ ሲፈጽም የኖረ ድርጅት ነው። ከነዚህ ወንጀሎች አንዱና ምናልባትም ለረጅም ጊዜ ተንሰራፍቶ ሥልጣን ላይ ለመቆየት ያስቻለው እርስ በራሳችን እንዳንተማመን በመካከላችን የዘራው የጥላቻ ፖለቲካ ነው። በህወሃት የጥላቻ ፖለቲካ መሠረት ኢትዮጵያችን አያት ቅድሜ አያቶቻችን በጋራ በከፈሉት መስዋዕትነት የተመሠረተችና ከተከታታይ የባዕድ ወረራ ነጻነቷን ጠብቃ የኖረች አገር ሳትሆን አንድ ማህበረሰብ ሌለውን ቅኝ በመግዛት የፈጠራት አገር ነች። ይህ ቅኝ ገዥ ሃይል ደግሞ ሥልጣን ላይ የተፈራረቁ መንግሥታት እስከዛሬ አገራችን ውስጥ ላደረሱት የአስተዳደር በደሎች ሁሉ ተጠያቂ ነው። ላለፉት 26 አመታት የመንግሥት ተቋማትና ሚዲያዎች በቅንጅት ሲያስተምሩና ሲቀሰቅሱ የኖሩት እንዲህ አይነት መሠረት የሌለውን መርዘኛና ከፋፋይ ቅስቀሳ ህብረተሰቡ ውስጥ ለማሰረጽ እና በአገራችን ላይ የጋራ ኩራት እንዳይኖረን የማድረግ ደባ ነው። በዚህ አፍራሽ ፕሮፖጋንዳ ምክንያት በኢትዮጵያዊነታቸው እንዲሸማቀቁ ተደርገው ያደጉ ፤ በደረሰባቸው የማንነት ቀውስ አዲስ ማንነት ፍለጋ የህገመንግሥቱን አንቀጽ 39 ተስፋ የሚያደርጉ ዜጎች ቁጥር በቀላሉ የሚገመት አልሆነም። ሌላው ቀርቶ በጥቁር ህዝቦች ሁሉ ዘንድ እንደ ነጻነት አርማ ተደርጎ የሚታየው አረንጓደ ብጫ ቀይ ባንድራችን የኩራታችን ምልክት ሳይሆን የባርነት ምልክት ተደርጎ እንዲታይ ያልተሠራ ሻጥር የለም። ለአንድነታችንና ለሉአላዊነታችን ከፍተኛ ዋጋ የከፈሉ ጀግኖች አባቶቻችን ታሪክ ተንቋሾ እንዲናፍርባቸው ተደርጎአል። በአመታት ጥረት የተገነቡ ብሄራዊ ተቋሞቻችን እንዲፈርሱና አገራቸውን በቅንነት ሲያገለግሉ የነበሩ ብዙ ሺዎች እንዲባረሩ ተፈርዶባቸዋል። ብሄራዊ መከታችን የነበረው የቀድሞ ጦር በፋሽስትነት ተፈርጆ እንዲፈርስና ከአምስት መቶ ሺ በላይ አባላቱ ለልመናና ለጎዳና ተዳዳሪነት እንዲዳረጉ ተደርገዋል። ኢትዮጵያዊ ሪህራሄና ወገንተኝነት በጎደለው ጭካኔ በብዙ መቶ ሺ የሚቆጠሩ ዜጎች ተወልደው ካደጉበት ቄያቸው እንዲፈናቀሉና መሬታቸው ለባዕዳንና ለሥርዓቱ አገልጋዮች እንዲከፋፈል በማድረግ ከፍተኛ ሃብት ተካብቶበታል። ይሉኝታና ሃፍረት በሌለው ጋጥ ወጥነት አብዛኛውን የመንግሥት ሠራተኛና የግል ንግድ ባለቤቶችን ከሥራቸው በማፈናቀል በምትኩ የአንድ ቡድን አባላት በበላይነት የሚቆጣጠሩት የኢኮኖሚና የፖለቲካ ሥልጣን ተፈጥሮአል። ይህንን ግፍና ኢፍትሃዊ አሠራር የተቃወሙትን ዜጎች ሁሉ በገቡበት ገብቶ ለማጥፋት በተወሰደው እርምጃ በጠራራ ጸሃይ በርካታ ዜጎች በየአደባባዩ ተገድለዋል ፤ ታስረዋል ፤ ተገርፈዋል ፤ አገራቸውን ጥለው እንዲሰደዱ ተደርጎዋል። ከግዲያ ተርፈው ዛሬ ድረስ በየ እስር ቤቱ የሚማቅቁና ፤ እዚያ እስር ቤት ውስጥ በተፈጸመባቸው ድብደባ አካል ጉዳተኛ ሆነው የሚሰቃዩ ዜጎች ቁጥር ስፍር የለውም።
Saturday, January 20, 2018
Friday, January 19, 2018
Subscribe to:
Posts (Atom)