Tuesday, October 31, 2017
በእነ ንግስት ይርጋ የክስ መዝገብ ብይን ለመስጠት በሚል በድጋሜ ቀጠሮ ተሰጥቷል የቃሊቲ ማረሚያ ቤት የፍ/ቤት ትዕዛዝ አላከበረም ተብሏል (Ethiopia Human Rights Project)
#FreeNigist #Ethiopia
በእነ ንግስት ይርጋ የክስ መዝገብ ብይን ለመስጠት በሚል በድጋሜ ቀጠሮ ተሰጥቷል
የቃሊቲ ማረሚያ ቤት የፍ/ቤት ትዕዛዝ አላከበረም ተብሏል
የፌደራሉ ከፍተኛ ፍ/ቤት ልደታ ምድብ 4ኛ ወንጀል ችሎት የሽብር ክስ የቀረበባቸውን የእነ ንግስት ይርጋ የክስ መዝገብ የአቃቤ ህግ ማስረጃን መርምሮ ተከሳሾች የቀረበባቸውን የወንጀል ክስ መከላከል ያስፈልጋቸዋል ወይስ መከላከል ሳያስፈልጋቸው በነጻ ሊሰናበቱ ይገባል የሚለውን ብይን ለማሰማት ለዛሬ ጥቅምት 21/2010 ዓ.ም ቀጠሮ ይዞ የነበር ቢሆንም፣ ዳኞች መዝገቡን መርምሮ ለመስራት ተጨማሪ ጊዜ ያስፈልገናል በሚል በድጋሜ ቀጠሮ ሰጥተዋል፡፡
አክቲቪስት ንግስት ይርጋን ጨምሮ ስድስት ተከሳሾችን የያዘው የእነ ንግስት ይርጋ መዝገብ ነሐሴ 12/2009 ዓ.ም ለብይን በሚል ቀጠሮ ከተያዘ በኋላ ብይኑ አልደረሰም በሚል ለዛሬ ተላልፎ እንደነበር ይታወሳል፡፡ ሆኖም ግን ዛሬም መዝገቡ ተመርምሮ ብይኑ ባለመሰራቱ ለሁለተኛ ጊዜ ለህዳር 01/2010 ዓ.ም ተለዋጭ ቀጠሮ ተሰጥቷል፡፡
በሌላ በኩል ቃሊቲ ማ/ቤት የምትገኘው አክቲቪስት ንግስት ይርጋ በእስር ቤት የጥየቃ ሰዓትና የጠያቂ ገደብ ተጥሎብኛል የሚሉና ሌሎች የሰብዓዊ መብት ጥሰቶች አቤቱታ አቅርባ ይህ እንዲስተካከል ፍ/ቤቱ ለቃሊቲ ማ/ቤት አስተዳደር ትዕዛዝ ሰጥቶ የነበር ቢሆንም ማ/ቤቱ ትዕዛዝን አለማክበሩ ተገልጹዋል፡፡
‹‹ሐምሌ 21/2009 ዓ.ም ፍ/ቤቱ ትዕዛዝ ሰጥቶልኝ ነበር፡፡ ሆኖም ማ/ቤት አስተዳደሩ የፍ/ቤቱን ትዕዛዝ አክብሮ መብቶቼን ባለማክበሩ በድጋሜ ነሃሴ 12/2009 ዓ.ም አቤቱታ አቅርቤ፣ ለዛሬ ማ/ቤት አስተዳደር ለምን ትዕዛዙን እንዳላከበረ መልስ እንዲሰጥ ታዝዞ ነበር፡፡ ይባስ ብሎ በማ/ቤቱ አስተዳደር ቢሮ እየተጠራሁ ‹አንቺ ማን ስለሆንሽ ነው ማ/ቤቱን የምትከሽው፣ አንቺ ከማን ትበልጫለሽ እየተባልሁ ማስጠንቀቂያ እየተሰጠኝ ነው›› በማለት ንግስት ይርጋ ስላለው ሁኔታ አቤቱታ አሰምታለች፡፡
ሌሎችም ተከሳሾች አቤቱታ እንዳላቸው ቢገልጹም ፍ/ቤቱ አቤቱታቸውን በጽሁፍ ካቀረቡ ብቻ እንደሚቀበላቸው በመግለጽ እንዳይይገሩ ከልክሏል፡፡
ፍ/ቤቱ የቃሊቲ ማ/ቤት አስተዳደር ቀደም ሲል በንግስት ይርጋ አቤቱታ ላይ የተላለፈውን የፍ/ቤቱን ትዕዛዝ ለምን እንዳላከበረ በቀጣይ ቀጠሮ ቀርቦ እንዲያስረዳ በድጋሜ ትዕዛዝ ሰጥቷል፡፡
የመጨረሻው መጀመሪያ (በኤርሚያስ ለገሰ)
የሕውሓት አገዛዝ የመጨረሻውን መጀመሪያ ጐዳና ጀምሮታል። ይህ ምዕራፍ እውነተኛው የስርአቱ ባህሪ በማያወላዳ መንገድ የሚገለጥበት ሆኗል ። በተለይም የትግራይ ተወላጆችን በፍራቻ በመሸበብ ከሌሎች ኢትዬጲያውያን ጋር ደም እንዲቃቡ የማይቆፍረው ጉድጓድ እንደማይኖር በግልፅ የታየበት ነው። የሰሞኑ አስደንጋጭ ክስተቶች ዝም ብለው የመጡ ሳይሆን ከአገዛዙ ውስጣዊ ባህሪ የሚመነጩ ናቸው።
ሰለሆነም የኢትዮጵያ ህዝብ የሚያደርገው የስርአት ለውጥ ትግል ህውሓት ትግሉን ወደ ሌላ አቅጣጫ በመውሰድ እንዳይቀለብሰው የሚያደርጉ ስትራቴጂ እና ስልቶችን መከተል እንደሚያስፈልግ ግላጭ የወጣበት ሆኗል። ለዛሬው በኦሮሚያ እየተካሄዱ ያሉ ሕዝባዊ ትግሎችን ለማገዝ ይረዳሉ የምላቸውን ጥቂት ቁምነገሮች ለመጠቆም እፈልጋለሁ።
# የቅድሚያ ቅድሚያው ህዝባዊ እምቢተኝነቱንና ተቃውሞውን አጠናክሮ መቀጠል ይሆናል። ሰልፎችን አለማቋረጥ፣ መንገድ መዝጋት፣ የቀበሌና ወረዳ እንዲሁም የመንግስት ቢሮዎችን ማጨናነቅ፣ የፓርቲ ጽሕፈት ቤቶችንና ኩባንያዎችን ማገት ያስፈልጋል። ከህውሓት/ ኢህአዴግ ጋር ባላቸው የጥቅም ትስስር የሚንቀሳቀሱ ባለሃብቶችን ንብረት ቆጠራ ማካሄድና ከአገዛዙ ጋር ያላቸውን ትስስር ፍቺ እንዲፈጽሙ ማስጠንቀቅ ያስፈልጋል። የኤፈርት ምርቶችን የሚቀበሉ ነጋዴዎች ውላቸውን እንዲያቋርጡ ማስጠንቀቂያ መላክ ያስፈልጋል። የጉና ኢንተርፕራይዝ የጅምላ እና ችርቻሮ ሱቆች ተለይተው መዘጋት ይኖርባቸዋል። የአንበሳ፣ ወጋገን ባንክና የአፍሪካ ኢንሹራንስን ህዝቡ እንዳይጠቀም ማድረግ ያስፈልጋል። እንደዚህ አይነት እርምጃዎች ተጠናክረው መቀጠል ያለባቸው ነው። በተከታታይ ተጠናክረው መቀጠል ካልቻሉ ህውሓት ትንፋሽ የመሰብሰቢያ ጊዜ እንዲያገኝ ያደርገዋል። ከዚህ በተጨማሪም ከህውሓት ጋር አብረው አገር ማፍረሻ አሳብና መሳሪያ ሲያቀብሉ የነበሩት እነ ለማ መገርሳ ከሁሉም የበለጠ ከሃዲዎች ሊሆኑ እንደሚችሉ መገንዘብ ያስፈልጋል። በሕዝባዊ ማዕበል ተወጥረው ካልተያዙና የሚወስዷቸው አስገዳጅ እርምጃዎች የሚያመላክቱ የተቆጠሩ እቅዶች ካላቀበልናቸው አስደንጋጭ ሁኔታ አጭር ጊዜ ውስጥ ሊከሰት ይችላል። በውስጣቸው ያለው አድርባይነት የወለደው ደካማ አቋም አገንግኖ የህዝቡን ትግል ለማጨናገፍ ሊሯሯጡ ይችላሉ። በመሆኑም በህዝባዊ ተቃውሞ እንዲናጡና ወገባቸው እስኪጐብጥ ማስጨነቅ ያስፈልጋል።
# ሕዝባዊ ተቃውሞው እንዲቀዘቅዝ የሚያደርጉ ማንኛውም አካላት ፀረ ለውጥ መሆናቸውን ተገንዝቦ ሊጋለጡ ይገባል። በግራ እጁ ከተቃውሞ ወደ አብዬት ተሸጋግረናል የሚል ነጋሪት ጐስሞ ሲያበቃ በቀኝ እጁ የሌለበትን የሕዝብ ማእበል ሊደፍቅ የሚመጣ ቡድን ታሪክና ህዝብ ሊወቅሰው ይገባል። የትግሉ ባለቤት ማንም ሳይሆን ህዝቡ ነው። ትግሉ ደግሞ የስርአት ለውጥ እስኪያመጣ ተጠናክሮ ያለማቋረጥ ይቀጥላል። ትግሉ ያለማቋረጥ ባይቀጥል ኖሮ ኦቦ በቀለ ገርባ አይፈታም ነበር።
ነገሮች በፍጥነት እየተለዋወጡ ነው። (ጋዜጠኛ መሳይ መኮንን)
ነግቶ በመሸ ቁጥር አዲስ ነገር ይሰማል። አዲስ ቀን አዲስ ክስተት ይዞ ብቅ እያለ ነው። ባለፉት ሁለት ወራት በኢትዮጵያ የፖለቲካ ገጽ ላይ የተፈጠሩት ክስተቶች ባለፉት 25 ዓመታት ከሆኑት አንጻር ፈጣንና አይቀሬ ለውጥ በቅርበት እንዳደፈጠ የሚጠቁሙ ናቸው። ለውጡ ምን እንደሆነ አሁን ላይ መተንበይ ሊያስቸግር ይችላል። ጽልመትና ተስፋው ከፊት ተደቅነዋል። ጨለማው በእጅጉን የጠቆረውን ያህል በጭላንጭል የሚታይ ብርሃንም አለ። ጽልመቱ እንዳያሸንፍ፡ ለውጡ የመጥፎ እንዳይሆን ከጸሎት ባሻገር ትንፋሽ ወስዶ፡ ቁጭ ብሎ መመካከር ያስፈልጋል።
ህወሀት በአጭሩ ደክሞታል። ሲፈጠር ጀምሮ ያጣውን የኢትዮጵያ ህዝብ ልብ ሳያገኝ ወደ መቃብሩ ጉዞ የጀመረ ይመስላል። በውስጣዊ የሃይል መሳሳብ ጉልበቱ ዝሎ፡ አቅሞ ተሟጦ፡ ሞተሩን እንደነከሰ አውቶሞቢል መንተፋተፍ ከጀመረ ሰንብቷል። ህወሀት ከእርጅናው ጋር ተዳምሮ የገባበት ውጥንቅጥ የቋመጣትን 100 ዓመት የመግዛት ህልሙ እንዲጨናገፍበት አድርጎታል። የህልሙን ሲሶ እንደኖረ በታሪክ ጥቁር መዝገብ ላይ ሰፍሮ ሊሰናበት 11ኛው ሰዓትን ተጠግቷል።
በእርግጥ የስብሃትና የሳሞራ ቡድኖች በር ዘግተው በህንፍሽፍሽ ሲሞዣለቁ ከከረሙ በኋላ በስብሃት ቡድን አሸናፊነት ግብግቡ ማብቃቱም ይነገራል። ሆኖም ህወሀት የትኛውም አንጃ ነጥሮ ቢወጣ ደካማ ህወሀት መሆኑ አይቀርም። ከእንግዲህ ሳሞራም ያሸንፍ ስብሃት ህወህትን የሚታደግ አንጃ አይኖርም። ህወሀት ጥይቱን ጨርሷል። ተልፈስፍሷል። ምስጥ የጨረሰው ኩይሳ ሆኗል። መለስ ዜናዊ በቁሙ ህወሀት ሲፈርስ ሳያይ ሞት ስለቀደመው እድለኛ ነው። እንደ ጋዳፊ በጥፊ እየተመታ፡ በውርደት ከመሞት አምልጧልና።
እንደሰማነው ህወሀት የሽግግር መንግስትን እንደሁለተኛ አማራጭ ይዟል። በአጥንቱም ቢሆን ረግጦ መግዛት የማይችል ከሆነ መከላከያውና ደህንነቱ ከእጁ ሳይወጡ የሽግግር መንግስት ለማቋቋም ፍላጎት እንዳለው የኢሳት የመረጃ ምንጮች ገልጸዋል። ይህ ካልሆነም ኢትዮጵያውያን መሃል በየቦታው የቀበረውን ፈንጂ እንዲፈነዳ በማድረግ ወደ መቀሌ ገብቶ የትግራይን ሪፑብሊክ ለመመስረት በፕላን C ይዞታል። ለዚህም አጀንዳውን ቀስቅሶ በአንዳንድ ቦታዎች ተጋሩዎች ውይይት ማድረግ ጀምረዋል። ሰሞኑን የአዲስ አበባ ተጋሩዎች በትግራይ መገንጠል ዙሪያ አጀንዳውን እንደመከሩበት ተሰምቷል። የጨነቀው እርጉዝ ያገባል ሆነና ህወሀት ከማይቀረው ሞቱ ለማምለጥ የትኛውንም ሙከራ ከማድረግ ወደ ኋላ አይልም። ኢትዮጵያ ጠፍታ ህወሀት የሚተርፍ ከሆነ ያደርገዋል። ውዷን ሀገራችንን ከማጥፋቱ በፊት እንዲጠፋ ማድረጉ የዚህ ትውልድ ትልቁ የቤት ስራ ሆኗል።
የትግራይ ህዝብ ወሳኝ የታሪክ ምዕራፍ ላይ ይገኛል። ከሰሞኑ የሚሰሙት ነገሮች ለትግራይ ህዝብ የማንቂያ ደውል ሊሆኑ ይገባል። የሆኑትና ሊሆኑ እያንዣበቡ ያሉት አደጋዎች ያስፈራሉ። ለኢትዮጵያችን የማይገቧት ናቸው። የትግራይ ህዝብ ላለፉት 27 ዓመታት በስሙ ከነገደው፡ በስሙ ከዘረፈው፡ በስሙ ከገደለውና በመጨረሻም ብቻውን ወደ መቃብሩ እየገሰገሰ ካለው ህወሀት ጋር ፍቺ የሚፈጽምበት ጊዜ ቢዘገይም አሁንም ይጠበቃል። በግልጽ ለመናገር የትግራይ ህዝብ ከህወሀት ጋር የሚፈጽመው ፍቺ ለኢትዮጵያ ፈውስ ይሆናል።
እናም የትግራይ ህዝብ ለኢትዮጵያዊ ወገኑ ሊቆም ይገባል። ትላንት አልፏል። ዛሬ ግን በትግራይ ህዝብ እጅ ነው። ሌላው የኢትዮጵያ ህዝብ እንደሆነ ግልጽ መልዕክት እያሰማ ነው። ይህ ጸረ ህዝብ የሆነው ስርዓት ስልጣን ላይ የቆየበት ዘመን ለትግራይ ህዝብ መጥፎ ዘመን ላይሆን ይችላል። ለኢትዮጵያውያን ግን የመከራ፡ የፍዳና የስቃይ ዘመን መሆኑን የትግራይ ወገኖቻችን ሊረዱትና ህወሀትን በቃ! ሊሉት ይጠበቅባቸዋል። ዛሬ ሳይሆን አሁኑኑ!!!!
Monday, October 30, 2017
Sunday, October 29, 2017
በሕወሐት/ኢሕአዴግ ከተሰነዘረብን የሁለት ስለት ሰይፍ ሀገራችንን ለመታደግ ሑሉም በያለበት ዘብ ይቁም!!! (ከሰማያዊ ብሔራዊ ሸንጎ የተሰጠ መግለጫ)
ዛሬ ሀገራችን ኢትዮጵያ በሕወሐት/ኢሕአዴግ ባለ ሁለት ሰይፍ የጥፋት ተልዕኮ በደም እየዋኘች ትገኛለች፡፡
የመጀመሪያውና ዋነኛው የሕወሐት/ኢሕአዴግ ሰይፍ ስለት በጥላቻና በልዩነት ላይ ኢትዮጵያን ዘልዝሎና አዳክሞ ለመግዛት የተዘረጋው የአገዛዝ ዘይቤ ሲሆን ይህም ፍሬውን አፍርቶ የኢትዮጵያን ልጆች አባቶቻቸው ሀገራቸውን ከጠላት ለመከላከል ከአንተ እኔ ቀድሜ ልሙት እየተባባሉ በገነቧትና ባቆዩዋት ሀገር ዛሬ ላይ በሕወሐት/ኢሕአዴግ አገዛዝ የአንድ መንደር ሰው(ብሔረሰብ) ለሌላው ባዕድ ሆኖ ወንድሙን በጥላቻ ተነሳስቶ አረመኒያዊና ዘግናኝ በሆነ መንገድ ሲገለውና ንብረቱን ሲያወድመው በአይናችን እያየን በጆሯችን እየሰማን ነው፡፡ በዚህ ድርጊት በወንድሞቻቸው እጅ ህይወታቸው ያለፉ ወገኖቻችን ጉዳይ እጅግ ልብ የሚሰብርና የሚዘገንን ተግባር ከመሆኑም ባሻገር እንደ ሀገርና እንደ ትውልድ ደግሞ የሚያሳፍርና አንገት የሚያስደፋ ተግባር ነው፡፡ ሰሞኑን በኦሮሚያ ክልል ኢሉባቦር ዞን እና በቤንሻንጉል ጉመዝ ክልል ካማሽ ዞን በአማሮች ላይ የደረሰው ጭፍጨፋ ይህንኑ የሚያረጋግጥ ነው፡፡
ሁለተኛው የሕወሐት/ኢሕአዴግ ሰይፍ ስለት ደግሞ በግብር ከፋይ ዜጎች ሀገርን ለመከላከል የተቋቋመው ሰራዊት መለዮውን ለብሶ በባዶ አጃቸው ሰልፍ የወጡና በድንጋይና በእንጨት መንገድ የዘጉ ታደጊ ወጣቶችን ግንባር ግንባራቸውን እያለ ሲገድል እያየን እየሰማን ነው፡፡ በዚሁ ሳምንት በአምቦ ከተማ የተደረገው ድርጊት የሚያረጋግጥልን ሕወሐት/ኢሕአዴግ ማንኛውንም ለስልጣኔ ስጋት ነው ያለውን ሰላማዊ እንቅስቃሴ በጠመንጃ ለመፋለም ያለ ሐፍረት መወሰኑን በተግባር ያየንበት ነው፡፡
በአጠቃላይ ሕወሐት/ኢሕአዴግ በስልጣኑ ለመቆየት ሁለቱንም የጥፋት ዘዴዎች ማለትም እርስ በእርስ ማባላትና ከዛ የተረፈውንና በሰላማዊ መንገድ መብቱን የሚጠይቀውን በጥይት ለመቁላት መወሰኑን ከላይ በገለፅናቸው ድርጊቶቹ አረጋግጦልናል፡፡ስለሆነም ሀገራችንን ከዚህ የጥፋት አደጋ ለመታደግና ትግሉን በአሸናፊነት ለመወጣት ሁሉም የበኩሉን እንዲወጣና በያለበት ዘብ እንዲቆም ጥሪያችንን እናስተላልፋለን፡፡ በመጨረሻም በአገዛዙ መሰሪ ሴራና ጥይት ህይታቸውን ላጡ ወገኖቻችን የተሰማንን ጥልቅ ሀዘን እንገልፃለን፡፡
ጥቅምት 19 ቀን 2010 ዓ.ም
አዲስ አበባ
Saturday, October 28, 2017
Friday, October 27, 2017
Thursday, October 26, 2017
Wednesday, October 25, 2017
Tuesday, October 24, 2017
የኦዴግ አመራሮች ወደ ሱዳን ካርቱም ለኤክስፐርቶች በተዘጋጀው መድረክ ላይ ለመሳተፍ እንደሄዱ ገለጹ (ኢሳት ዜና–ጥቅምት 14/2010)
የኦዴግ ሊቀመንበር አቶ ሌንጮ ለታና ምክትል ሊቀመንበሩ ዶክተር ዲማ ነገዎ ወደ ሱዳን ካርቱም ያመሩት ከኢትዮጵያ መንግስት ጋር ለመደራደር ሳይሆን የአፍሪካ ሕብረት ባቀረበላቸው ግብዣ መሰረት መሆኑን አረጋገጡ።
አመራሮቹ በተለይ ከኢሳት ጋር ባደረጉት ቆይታ ህብረቱ ግብዣውን ያደረገላቸው በአፍሪካ ቀንድ ላይ ያደረጉትን ጥናት መነሻ በማድረግ በሱዳን ካርቱም ለኤክስፐርቶች በተዘጋጀው መድረክ ላይ ማብራሪያ እንዲሰጡ መሆኑን ተናግረዋል።
ከኢትዮጵያ መንግስት ጋር በሚስጥር በሱዳን ካርቱም ድርድር ማድረጋቸው የተገለጸው የኦሮሞ ዲሞክራሲያዊ ግንባር ኦዴግ አመራሮች አቶ ሌንጮ ለታና ዶክተር ዲማ ነገዎ በጉዳዩ ላይ ለኢሳት ማብራሪያ ሰጥተዋል።
የኦዴግ ሊቀመንበር አቶ ሌንጮ ለታና ምክትል ሊቀመንበሩ ዶክተር ዲማ ነገዎ ካርቱም መሔዳቸውን ለኢሳት ያረጋገጡ ሲሆን ጉዟቸው ግን ለድርድር ሳይሆን የአፍሪካ ሕብረት ባዘጋጀው ስብሰባ ላይ በተደረገላቸው ግብዣ መሆኑን ተናግረዋል።
ስብሰባው ለኤክስፐርቶች የተዘጋጀ በመሆኑ ሁለቱም በአፍሪካ ቀንድ ላይ ያደረጉትን ጥናት መነሻ በማድረግ መጋበዛቸውንም አስረድተዋል።
በስብሰባው ስፍራ አንድም የኢትዮጵያ መንግስት ባለስልጣን ወይንም ልውጥ እንዳልነበር የገለጹት አቶ ሌንጮ ለታና ዶክተር ዲማ ነገዎ ግብዣው በግል በባለሙያነት የመጣላቸው ቢሆንም የተጓዙት ግን ፓርቲያቸውን አሳውቀው መሆኑን ጠቁመዋል።
ስልጣን ላይ ያለው የኢትዮጵያ መንግስት መደራደር ከፈለገ በቅድሚያ ያሰራቸውን ፈቶ ከነሱ ጋር ይደራደር ሲሉም አቶ ሌንጮ ለታ ተናግረዋል።
ዶክተር ዲማ ነገዎ በበኩላቸው በሰጡት አስተያየት የኢትዮጵያ ችግር ሰፊና ውስብስብ በመሆኑና ከአንድ ወገን ጋር በመደራደር ስለማይፈታ በተናጠል ግብዣም ለመሳተፍ ፈቃደኛ አይደለንም ብለዋል።
በኦሮሚያ የተቀሰቀሰውን ተቃውሞ ተከትሎ የደህንነት መስሪያ ቤቱ የብሄር ግጭቶችን ለማስነሳት እየሰራ ይገኛል፡፡ (የአርበኞች ግንቦት 7 ድምፅ ሬዲዮ)
በኦሮሚያ ኤሊባቦር ዞን የሚደረገውን ተቃውሞ ተከትሎ በተቀሰቀሰ ግጭት የበርካታ ሰዎች ህይወት መጥፋቱ ይታወቃል። ከብሄራዊ መረጃና ደህንነት አገልግሎት የተገኘው መረጃ እንደሚያሳየው የደህንነት ተቋሙ በተለያዩ ቦታዎች የሚደረጉ ተቃውሞዎችን ወደ ብሄር ግጭት እንዲያመሩ የሚያስችል ስራዎችን እያከናወኑ መሆኑን ነው። በዚህ መሰረት በኤሊባር የተፈጠረው የአማራ ማህብረሰብን ኢላማ ያደረገ ጥቃት በደህንነቱ የተከናወነ እንደሆነ ለማወቅ ተችሏል። በሃገር ውስጥ ደህንነት ዋና መምሪያ ውስጥ ከፍተኛ ስልጣን ያላቸው የኦህዴድ አባላት የሆኑ አቶ አዲሱ በዳዳ እና አቶ ተስፋዬ ኡርጌ የተባሉ የኦሮሚያን ክልል የደህንነት ጉዳዮች በበላይነት የሚከታተሉ ግለሰቦች አማካኝነት ነው በአማራውና በኦሮሚያ ክልል ተወላጆች መካከል የብሄር ግጭት እንዲነሳ ለማድረግ የሚጥሩት። እንደ አንድ ኦፕሬሽን ተይዞ እየተሰራበት ባለ በዚህ ጉዳይላይ የኦሮሚያ ክልል የአስተዳደርና ጸጥታ ቢሮ ሃላፊ የሆነው ረዳት ኮሚሽነር ደመላሽ ገ/መስቀል በዋና ተሳታፊነት እንደሚገኝ ታውቋል። ይህን ኦፕሬሽን የደህንነቱ ቁንጮ ከሆነው አቶ ጌታቸው አሰፋ ትእዛዝ እየተቀበለ በበላይነት እየመራ የሚገኘው የህወሃት አባል የሆነው የሃገር ውስጥ ደህንነት ዋና መምሪያ ሃላፊ አቶ አማኑኤል ኪሮስ የተባለ ግለሰብ ነው። እንዲሁም አቶ ደርበው ደመላሽ የተባሉ በደህንነቱ ውስጥ በከፍተኛ ሃላፊነት የሚገኙ ግለሰብ በረዳትነት ብሄሮችን ከብሄር የማጋጨት ኦፕሬሽኖችን ከአቶ አማኑኤል ኪሮስ ጋር በመሆን ያከናውናሉ። የደህንነቱ መስሪያቤት በአቶ አዲሱ በዳዳ እና በአቶ ተስፋዬ ኡርጌ አማካኝነት አሁን ያለውን የኦሮሚያ ክልል ሃላፊዎችን ይቃወማሉ የሚባሉ ሰዎችን እየመለመሉና እያደራጁ እንደሆነ ከደህንነት መስሪያ ቤት የተገኘው መረጃ ያመለክታል። የኦህዴድ አባል የሆኑት በኦሮሚያ ገጠር መንገድ በሃላፊነት እየሰሩ ያሉት አቶ ጀማል አባሶ የዚህ በደህንነቱ ለሚደረገው ኦፕሬሽን በዋና ተሳታፊነት እያገለገሉ ይገኛሉ። በአቶ ለማ መገርሳና በዶ/ር አቢይ አህመድ የሚመራው የኦሮሚያ ክልላዊ መንግስት በደህንነቱ መስሪያ ቤት ከፍተኛ አሻጥር እየተሰራበት እንደሆነና እነዚህ የኦህዴድ መሪዎች በሌላ መካከለኛ ላይ ባሉ የኦህዴድ አመራሮች ለመተካት የሚያስችሉ ዝግጅቶች እየተደረጉ እንደሆነ ለማወቅ ተችሏል።
በኦሮሚያ የተቀሰቀሰውን ተቃውሞ ተከትሎ ከፍተኛ የጦር አዛዦ ከሃላፊነታቸው እየተነሱ ነው (የአርበኞች ግንቦት 7 ድምፅ ሬዲዮ)
በኦሮሚያ የተቀሰቀሰውን ተቃውሞ ተከትሎ መከላከያ ውስጥ የሚገኙ ከፍተኛ ኦሮሞ የሆኑ የጦር አዛዦች ቀጥታ ሰራዊቱን ከሚያዙበት ምድቦች እየተነሱ ምንም ስራ በሌለባቸው ቦታዎች እየተመደቡ እንደሆነ ታውቋል። በኦሮሚያ ክልል የተነሳውን ተቃውሞ ተከትሎ ኦሮሞ የሆኑ የሰራዊቱ ከፍተኛ መኮንኖች ተቃውሞውን ይደግፋሉ የሚል ምልከታ በህወሃት የጦር አዛዦች መያዙን ለመረዳት ተችሏል። ታችኛው ላይ ያለው አብዛኛው ሰራዊት ከሌላ ብሄር የመጡ በመሆናቸው እነዚህ የኦሮሞ ከፍተኛ መኮንንኖች ኦሮሚያ ውስጥ የተቀሰቀሰውን ተቃውሞ ምክንያት አድርገው ታች ላይ ያለውን ሰራዊት በማንቀሳቀስ ህወሃት ላይ አደጋ እንዳያመጡና የተቃውሞው አካል እንዳይሆኑ በማለት ቀጥታ ሰራዊት ማዘዝ የማይችሉባቸው ቦታዎች ላይ እንዲመደቡ ተደርጓል። በዚህ መሰረት የ24ኛ ክ/ጦር ዋና አዛዥ የነበሩት ብ/ጄነራል ሹማ አብደታ ከሃላፊነታቸው ተነስተው በሹመት ስም ምንም ጦር ማዘዝ በማይችሉበት ቦታ በሆነው የደቡብ ምስራቅ እዝ ም/ል አዛዥና የሰው ሃብት ልማት ሃላፊ በማለት እንዲመደቡ ተደርገዋል። በብ/ጄነራል ሹማ አብደታ ምትክ የ24ኛ ክ/ጦር ዋና አዛዥ በመሆን ኮ/ል የማነ ገ/ሚካኤል የተባሉ የህወሃት የጦር አዛዥ ተመድበዋል። የ13ኛ ክ/ጦር ዋና አዛዥ የሆኑት ብ/ጄነራል ከድር አራርሳ ቀጥታ ጦሩን ከሚያዙበት ሃላፊነታቸው እንዲነሱ ተደርጎ በሹመት ስም ምንም ጦር ወደ ማይመሩበት የማዕከላዊ እዝ ም/ል አዛዥና የሰው ሃብት ልማት ሃላፊ በመሆን ተመድበዋል። የ6ኛ ሜካናይዝድ ክ/ጦር ዋና አዛዥ የሆኑት ብ/ጄነራል ከፍያለው አምዴ እንዲሁ ከሃላፊነታቸው እንዲነሱ ተደርጓል። የ21ኛ ክ/ጦር ዋና አዛዥ የሆኑት ብ/ጄነራል ዋኘው አማረ ከሃላፊነታቸው ተነስተው በመሃንዲስ ዋና መምሪያ ውስጥ እንዲቀመጡ ተደርጓል። የአጋዚ ኮማንዶና ልዩ ሃይሎች ጠቅላይ መምሪያ ም/ል አዛዥና የኦፕሬሽን ሃላፊ የሆኑት ብ/ጄነራል ሙላት ጀልዱ ከላፊነታቸው ተነስተው በመከላከያ የስነምግባር መከታተያ ዳይሬክተር በማድረግ ከሰራዊቱ ጋር ቀጥታ ከሚያገናኛቸው ስራዎች እንዲገለሉ ተደርጓል። በርካታ የአማራና የኦሮሞ ከፍተኛ መኮንኖች በሰላም ማስከበር ሰበብ ከሰራዊቱ እንዲገለሉ የማድረግ ስራዎች እየተሰሩ እንደሆነ መከላከያ ውስጥ ያሉ ምንጮቻችን ገልጸዋል። በኦሮሚያ ክልል የተነሳውን ተቃውሞ ተከትሎ ሰራዊቱ ተቃውሞውን እንዳይቀላቀል በህወሃት በኩል ከፍተኛ ስራዎች እየተሰሩ ያሉ ሲሆን ለህዝብ ወገኝተኝነት ያሳያሉ የሚባሉ የጦር አዛዦችን ከሃላፊነታቸው በማንሳት ምንም ወደ ማይሰሩበት ቦታዎች በሹመት ስም እየተዛወሩ መሆኑ ታውቋል።
ምስል ከፋይል
Monday, October 23, 2017
ከኢትዮጵያ አገራዊ ንቅናቄ በኢሉባቦር አካባቢ የተከሰተውን አሳሳቢና አሳዛኝ ሁኔታ አስመልክቶ የተሰጠ መግለጫ
በአገራችን ውስጥ የተለያዩ ማህበረሰቦች ለዘመናት ተቻችለውና ተቀራርበው መኖራቸውንና እየኖሩም እንደሆነ ህዝቡ ራሱና ታሪክ ምስክር ናቸው። እነኚህ ማህበረሰቦች አብሮ ከመኖር ባሻገር የተጋቡና የተዋለዱ፤ ደስታና ሃዘናቸውን ሲጋሩ የኖሩም ናቸው። ይህ የአብሮነትና የመቻቻል መንፈስ ከትውልድ ትውልድ ሲሸጋገር የመጣ እና ወደፊትም የሚቀጥል ነው።
ይህንን የህዝባችንን የመቻቻልና አብሮ የመኖር የቆየ ሥርዓት ለራሱ የፖለቲካ ህልውና እንደ አደጋ የቆጠረው የህወሃት አገዛዝ፤ የአገዛዝ ዕድሜውን ለማራዘም ሲል ወገንን ከወገን የማጋጨት ሴራ እየሸረበ መገዳደልንና ደም መፋሰስን እንደ ህልውና ማቆያ ስልት እየተጠቀመበት ይገኛል።
የህወሃት አገዛዝ ላለፉት 26 አመታት በህዝባችን ላይ የፈጠረውን አፈና ፤ ጭቆናና ብዝበዛ ለመቃወም ሰሞኑን በኢሉባቦር ዞን በቡኖ በደሌ ከተማና አካባቢው ተደርጎ በነበረው የተቃውሞ ሰልፍ ላይ አገዛዙ ሆን ብሎ ያሰማራቸው ሃይሎች የኦሮሞንና አብረውት የሚኖሩትን የሌሎች ብሄረሰብ አባላት በማጋጨት ግጭቱ ወደ እርስ በርስ እንዲዞር እና የአስራ አንድ ንጽሃን ዜጎች ህይወት እንዲቀጠፍ አድርጓል። በቅርቡ በሱማሌና በኦሮሞ ፡ በሲዳማና በኦሮሞ እንዲሁም በአፋርና በአማራ ህዝብ መካከል ፈጥሮት የነበረውን ግጭት ማስታወስ ተገቢ ነው።
ህወሃት እንዲህ አይነት እኩይ ተግባር የሚፈጽመው ህዝባችንን በመከፋፈል ቆሞበት የነበረው የፖለቲካ መሠረት ስለተናጋበትና ቀደም ሲል የራሱን ጥቅም ለማስጠበቅ ሲጠቀምባቸው የነበሩት የኢህአደግ አባል ድርጅቶች በተለይም ኦህዴድና ብአዴን ከተገፋው ህዝባቸው ጎን የመቆም ዝንባሌ ማሳየት በመጀመራቸው የሥልጣን ዕድሜው እያጠረ መሆኑን በመገንዘቡ እንደሆነ መረዳት አያዳግትም። ከዚህም በተጨማሪ እራሱ በሚቀሰቅሰው ግጭት የሚፈጠረውን የሰላምና መረጋጋት እጦት በመጠቀም የለመደውን የአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ በመጠቀም አገሪቱን ወደ ወታደራዊ አገዛዝ የመመለስ ዕቅዱን ለማሳካት ነው።
የኢትዮጵያ አገራዊ ንቅናቄ ህወሃት የሥልጣን ዕድሜውን ለማራዘም ሲል እየተጓዘበት ያለውን ይህን እኩይ ተግባር አጥብቆ ያወግዛል። ግጭት በመቀስቀስ ለፈሰሰው የዜጎች ደም ህወሃት ብቸኛ ተጠያቂ እንደሆነም ያስገነዝባል።
እንዲህ አይነት ሃላፊነት የጎደለው እርምጃ ተፋቅሮና ተቻችሎ የሚኖረውን ህዝብ ወደ እርስ በርስ ብጥብጥ በመውሰድ ወደ ማያባራ ጦርነት አገሪችንን ሊወስዳት እንደሚችል ህዝባችን አውቆ በህወሃት ሴራ ሳይጠለፍ ከአሁን ቀደም ሲያደርግ እንደቆየው ሁሉ እራሱን ፡ ቤተሰቡንና አካባቢውን ከእርስ በርስ ግጭት ተግቶ እንዲከላክል ንቅናቄያችን ወገናዊ ጥሪውን ያቀርባል።
ከዚህ በተጨማሪ በኦሮሚያ እና አማራ አካባቢዎች የተጀመረውን ህዝባዊ ተቃውሞ በተቀረው የአገራችን ክፍሎች ሁሉ በማዳረስ አፈናና ጭቆና የሚያበቃበት ጊዜ እንዲመጣ መላው ህዝባችን የዚህ ህዝባዊ ትግል አካል እንዲሆን የኢትዮጵያ አገራዊ ንቅናቄ ተግቶ እንደሚሠራ ማስታወቅ ይወዳል።
በህወሃት የአፈና ተቋማት ውስጥ የምትሰሩ በተለይም የመከላክያ፡ የፖሊስና የደህንነት አባላት የሆናችሁ ኢትዮጵያውያን በሙሉ በዚህ የመከራ ወቅት ከነጻነት ጠያቂው ወገናችሁ ጎን እንድትሰለፉ ጥሪያችንን እናቀርብላችኋለን።
ፍትህ እና ነጻነት ለኢትዮጵያ ህዝብ !
Sunday, October 22, 2017
በሕወሐት፣ኦህዴድና ኦነግ በተቀነባበረ ሴራ በንፁሐን ዜጎች ላይ የሚደርሰው ተደጋጋሚ ጭፍጨፋ ታሪክ ይቅር የማይለው አረመኒያዊ ተግባር ነው!!! (ከሰማያዊ ብሔራዊ ሸንጎ የተሰጠ መግለጫ)
አገዛዙ እያረጀና የመውደቂያ ዘመኑ መቃረቡን ተከትሎ የአገዛዙን ግብዓተ መሬት ለማፋጠን በሐገራችን በተለያዩ አካባቢዎች የተቀሰቀሱ አመፆች ቀጥለው አሁን በአንዳንድ አካባቢዎች ሕዝባዊ እንቅስቃሴዎቹ መልካቸውን እየቀየሩ ከአገዛዙ ጋር ግንኙነት የሌላቸውን ዜጎችን በአሰቃቂ ሁኔታ ወደ መግደልና ማሳደድ ተቀይረዋል፡፡ በተለያዩ የመገናኛ ብዙሃን እንደተገለፀው የተነሳውን ሕዝባዊ እንቅስቃሴ ተክትሎ በኦሮምያ ክልል ቡኖ በደሌ ዞን ጮራና ዴጋ ወረዳዎች በሚኖሩ አማሮች ላይ በተሰነዘረ ጥቃት ብዙ ዜጎች በገጀራ አንገታቸው እየተቀላ በአሰቃቂ ሁኔታ እንደተገደሉ፣ቤት ንብረታቸው እንደተቃጠለና ከጥቃቱ የተረፉትም ህይወታቸውን ለማዳን በቤተ ክርስቲያን እንደተጠለሉና ገሚሶቹም በጫካ ውስጥ ተጠልለው እንደሚገኙ ታውቋል፡፡
ሕወሐት/ኢሕአዴግ በተከለው የዘረኝነትና የጥላቻ ፖለቲካ በተለያየ ጊዜ በተለያዩ የሐገራችን አካባቢዎች የኢትዮጵያውያን ሞት፣የንብረት መውደምና ከቀዬቸው መፈናቀል በየጊዜው የምንሰማው መርዶ ነው፡፡ ይህ የአገዛዙ የጥላቻ መርዝ ቀስቱ ከመነሻው ጀምሮ በአማራ ላይ ያነጣጠረ መሆኑን እራሱ አገዛዙ በአዘጋጃቸው ሰነዶች ላይ በግልፅ ተቀምጧል፡፡ አገዛዙ ይህንን በዚህ ህዝብ ላይ የጥፋት ተልዕኮውን ለማስፈፀም በሕወሐት የሚዘወር ኢሕአዴግ የሚባል ሽፋን እየተጠቀመ ተደጋጋሚ የሆነ የግድያና የማፈናቀል ተግባሩን ተያይዞታል፡፡
ብአዴን የሚባለው የሕወሐት ጉዳይ አስፈፃሚ ድርጅት አውክለዋለሁ የሚለውን ህዝብ ከመፈረጅና ከማጥላላት አልፎ የአማራ ህዝብ ለሚደርስበት ግድያ፣መፈናቀልና የንብረት ውድመት ምንም ዓይነት ተግባራዊ እርምጃ ያልወሰደና በዝምታ የሕወሐት የጥፋት ተልዕኮ ተባባሪ በመሆን የአገልጋይነት ተግባሩን ቀጥሎበታል፡፡
ኦህዴድና ኦነግም የአማራን ህዝብ ለኦሮሞ ህዝብ ጠላት አድርጎ ፕሮፓጋንዳ በመንዛትና የጥላቻ ሀውልት በማቆም የአማራን ህዝብ በየጊዜው ለግድያ፣ለንብረት ውድመትና መፈናቀል እንዲዳረግ አድርገውታል፡፡
አንዳንድ ወገኖች በተለያዩ ጊዚያት በአማራ ህዝብ ላይ የሚደርሰውን ጭፍጨፋ በአማራና ኦሮሞ ህዝብ ተራ ዜጎች መካከል የተፈጠረ በሁለቱም በኩል ያለ ጥላቻ አድርገው ለመሳል ይሞክራሉ፡፡ ነገር ግን ይህ አመለካከት ከእውነት የራቀና መሬት ላይ ያለውን ሀቅ የማይወክል መሆኑን ለማረጋገጥ በኦሮሚያ ክልል መንግስት የተሰራውን የጥላቻ ሀውልት እና የአማራ ህዝብ በተደጋጋሚ ጊዜ ግድያና መፈናቀል የሚደርስበት በኦሮሚያ ክልል ሲሆን በአማራ ክልል ውስጥ የሚኖሩ የኦሮሞ ህዝብ ግን የግድያም ሆነ የማፈናቀል ተግባራት ተፈፅሞባቸው አያውቅም፡፡ ስለሆነም በአማራ ህዝብ ላይ እየተፈፀመ ያለው ፍጅት በንቃት በድርጅት በተለይም በሕወሐት፣በኦህዴድና በኦነግ የተቀነባበረ ፀረ አማራ ተግባር ነው፡፡ በመሆኑም ሀገር አስተዳድራለሁ በማለት ኃላፊነት የወሰደው ሕወሐት/ኢሕአዴግ እስካሁኗ ሰዓት ድረስ በአማራ ህዝብ ላይ ለደረሰው ጥፋት በህግም ሆነ በታሪክ ከተጠያቂነት አያመልጥም፡፡ የቅርብ ጊዜ ታሪካችንን ብንመለከት በጨቋኙ የደርግ አገዛዝ ዘመን ዜጎች እርስ በእርስ በጥላቻና በመናናቅ ተነሳስተው የተፈፀመ የጎላ ግጭት አልነበረም፡፡ እንዲህ አይነት አረመኒያዊ ተግባር ተጠንስሶና ተሰርቶበት ያደገው በሕወሐት/ኢሕአዴግ የአገዛዝ ዘመን ነው፡፡
በመሆኑም ይህንን ችገር ከመሰረቱ ለመንቀል የኢትዮጵያ ህዝብ ሕወሐት፣ኦህዴድና ኦነግ በሚረጩት የጥላቻ መርዝ ሳይፈታ የቀደመ ጨዋነት፣ሆደሰፊነትና መከባበር እሴቶችን በመጠበቅ ከሚደርስበት የመጠፋፋት ተግባር እራሱን እንዲከላከል እያሳሰብን የችግሮች ሁሉ ምንጭ የሆነውን ሕወሐት/ኢሕአዴግን ለማሶገድና ህዝባዊ አስተዳደር ለመትከል የጀመረውን ትግል አጠናክሮ እንዲቀጥል ጥሪያችንን እናስተላልፋለን፡፡
ጥቅምት 12 ቀን 2010 ዓ.ም
አዲስ አባባ
ህወሓትና አሻጥር (Dr.Tadesse Biru Kersmo)
ህወሓት ለ27 ዓመታት የገዛው በአሻጥር ነው።
ከቁጥር ከሚያታክቱ የህወሓት አሻጥሮች በቅድሚያ አዕምሮዬ ውስጥ የሚመጣው በረሀ በነበረት ጊዜ ከላይ ስንዴ በተን በተን የተደረገባቸው በአሸዋ የተሞሉ ከረጢቶችን ለየዋህ ለጋሾች የሸጠበት አጋጣሚ ነው። ይህ አዕምሮዬ ውስጥ ይቀረጽ እንጂ ከዚያ በኋላ ከፈፀማቸው አሻጥሮች አንፃር ሲታይ ይኸኛው የዕቃ ዕቃ ጨዋታ ነው።
የመንግሥት መዋቅር ከተቆጣጠረ በኋላ ህወሓት አሻጭረኛነቱ ባሰበት። ቁጥር ማምታት፤ ሕዝብን ከሕዝብ በተጠና መንገድ ማጋጨት፤ የአንድ እምነት ተከታዮችን ከሌሎች ጋር ማጣላት፤ ድርጅቶችን ውስጣቸው ሰርጎ በመግባት ማበጣበጥ፤ ሕዝብን በሽብር ጥቃት ገድሎ በሌሎች ማሳበብ .... ወዘተ ... ወዘተ
ህወሓት በአሻጥር ተወልዶ፤ በአሻጥር አድጎ ፤ በአሻጥር ጎልብቶ፤ በአሻጥር እያረጀ ነው።
ዛሬ፣ አሁን እነዚህን ዓረፍተ ነገሮች በምተይብባቸው ደቂቃዎች፣ የጌታቸው አሰፋ እና ገብሬ ዲላ የአሻጥር ኤክስፐርቶች ብርቱ ሥራ ላይ ናቸው።
በዚህ ወቅት የምመክረው አንድ ነገር ነው። ለህወሓት አሻጥሮች መንገድ አንስጥ። ሲያጣሉን ከተጣላንላቸው አሻጥሩ ግቡን መታ ማለት ነው። ስሜቶቻችንን ተቆጣጥረን ዓይኖቻችንን በግባችን ሳንነቅል መንገዳችን ከቀጠልን አሻጥሩን አከሸፍን።
የህወሓትን አሻጥሮች ማክሸፍ የሚቻለው በመካከላችን መተማመንን ስንገነባ ነው። የጋራ ጠላት መኖር መተማመንን ይፈጥል። ህወሓት የኢትዮጵዊያን ሁሉ የጋራ ጠላት ነው። ይህን አምነን ከተቀበልን የህወሓት አሻጥሮች ውጤት አይኖራቸውም።
ኢትዮጵያ ለዘላለም ትኑር!
ድል ለኢትዮጵያ ሕዝብ !!!
ከቁጥር ከሚያታክቱ የህወሓት አሻጥሮች በቅድሚያ አዕምሮዬ ውስጥ የሚመጣው በረሀ በነበረት ጊዜ ከላይ ስንዴ በተን በተን የተደረገባቸው በአሸዋ የተሞሉ ከረጢቶችን ለየዋህ ለጋሾች የሸጠበት አጋጣሚ ነው። ይህ አዕምሮዬ ውስጥ ይቀረጽ እንጂ ከዚያ በኋላ ከፈፀማቸው አሻጥሮች አንፃር ሲታይ ይኸኛው የዕቃ ዕቃ ጨዋታ ነው።
የመንግሥት መዋቅር ከተቆጣጠረ በኋላ ህወሓት አሻጭረኛነቱ ባሰበት። ቁጥር ማምታት፤ ሕዝብን ከሕዝብ በተጠና መንገድ ማጋጨት፤ የአንድ እምነት ተከታዮችን ከሌሎች ጋር ማጣላት፤ ድርጅቶችን ውስጣቸው ሰርጎ በመግባት ማበጣበጥ፤ ሕዝብን በሽብር ጥቃት ገድሎ በሌሎች ማሳበብ .... ወዘተ ... ወዘተ
ህወሓት በአሻጥር ተወልዶ፤ በአሻጥር አድጎ ፤ በአሻጥር ጎልብቶ፤ በአሻጥር እያረጀ ነው።
ዛሬ፣ አሁን እነዚህን ዓረፍተ ነገሮች በምተይብባቸው ደቂቃዎች፣ የጌታቸው አሰፋ እና ገብሬ ዲላ የአሻጥር ኤክስፐርቶች ብርቱ ሥራ ላይ ናቸው።
በዚህ ወቅት የምመክረው አንድ ነገር ነው። ለህወሓት አሻጥሮች መንገድ አንስጥ። ሲያጣሉን ከተጣላንላቸው አሻጥሩ ግቡን መታ ማለት ነው። ስሜቶቻችንን ተቆጣጥረን ዓይኖቻችንን በግባችን ሳንነቅል መንገዳችን ከቀጠልን አሻጥሩን አከሸፍን።
የህወሓትን አሻጥሮች ማክሸፍ የሚቻለው በመካከላችን መተማመንን ስንገነባ ነው። የጋራ ጠላት መኖር መተማመንን ይፈጥል። ህወሓት የኢትዮጵዊያን ሁሉ የጋራ ጠላት ነው። ይህን አምነን ከተቀበልን የህወሓት አሻጥሮች ውጤት አይኖራቸውም።
ኢትዮጵያ ለዘላለም ትኑር!
ድል ለኢትዮጵያ ሕዝብ !!!
Saturday, October 21, 2017
Friday, October 20, 2017
Thursday, October 19, 2017
Wednesday, October 18, 2017
አሁን የደረሰን ዜና ፦ በገብረጉራቻ ተቃውሞ ተባሶ ቀጥሏል፡፡ (የአርበኞች ግንቦት 7 ድምፅ ሬዲዮ)
ዛሬ ማምሻውን በርካታ ቤቶች እየተቃጠሉም ይገኛሉ ፡፡የመንግስት ተሸከርካሪዎችና የስርአቱ ደጋፊ የሆኑ ባለሃብት ንብረቶች እየተለዩ በመቃጠል ላይ መሆናቸውም ታውቋል ፡፡ የህዝብ ምሬትና አገዛዙን ከሹመቱ ለማውረድ ህዝብን ነፃ ለማውጣት ያለው መደጋገፍና መረዳት አገዛዙን ግራ ያጋባው ሲሆን አሁን የህዝቡም ቁጣ ከአገዛዙ ቁጥጥር ውጭ በመሆኑ ህዝቡ ሙሉ በሙሉ አደባባይ ወጥቶ ብርድ ጨለማ ሳይበግረው ስለ ወገኑ ድምፁን በማሰማት ላይ ይገኛል፡፡ ዛሬ ቀኑን ሙሉ በገብረጉራቻ በነበረው ህዝባዊ አመፅ በርካታ ሰዎች በወታደሮች መገደላቸውና መቁሰላቸው ታውቋል፡፡ ህዝቡ በወሰደው ጥቃት ከ4 መኪኖች በላይ መቃጠላቸው ታውቋል፡፡የመንግስት ንብረቶች እንዲወድሙም ተደርገዋል፡፡ ከአዲስ አበባ ወደ ባህርዳና ጎንደር የሚወስደው መንገድም ተዘግቶ ውሏል ፡፡
Tuesday, October 17, 2017
Monday, October 16, 2017
#ESAT· ሰበር ዜና
ኢሳት በአረብ ሳት ወደ አየር ተመልሷል።
ዝርዝር መረጃዎች
Satellite : Arabsat Badr6
Position : 26°E
Transponder : 2
Downlink Polarisation : Vertical
Downlink Frequency : 11747 MHz
Modulation : DVB-S
Symbol rate 27500 and Dec 3/4
ዝርዝር መረጃዎች
Satellite : Arabsat Badr6
Position : 26°E
Transponder : 2
Downlink Polarisation : Vertical
Downlink Frequency : 11747 MHz
Modulation : DVB-S
Symbol rate 27500 and Dec 3/4
Sunday, October 15, 2017
የማህበራዊ መገናኛ ብዙሃን ዳሰሳ (የአርበኞች ግንቦት 7 ድምፅ ሬዲዮ)
የዕለተ እሁድ ጥቅምት 05 ቀን 2010ዓ.ም. ፕሮግራም
*የማህበራዊ መገናኛ ብዙሃን ዳሰሳ .ከአርበኞች ግንቦት 7 ከፍተኛ አመራር ዶ/ር ታደሰ ብሩ ጋር የተደረገ ውይይት ይከታተሉት ዘንድ ግብዣችን ነው፡፡
ሙሉ ፕሮግራሞቻችንን በ www.patriotg7.org/ ላይ መከታተል የምትችሉ መሆኑን በአክብሮት እንገልፃለን፡፡
*የማህበራዊ መገናኛ ብዙሃን ዳሰሳ .ከአርበኞች ግንቦት 7 ከፍተኛ አመራር ዶ/ር ታደሰ ብሩ ጋር የተደረገ ውይይት ይከታተሉት ዘንድ ግብዣችን ነው፡፡
ሙሉ ፕሮግራሞቻችንን በ www.patriotg7.org/ ላይ መከታተል የምትችሉ መሆኑን በአክብሮት እንገልፃለን፡፡
Saturday, October 14, 2017
Friday, October 13, 2017
Thursday, October 12, 2017
ኢሳት የተመሰረበትን 7ኛ ዓመት በኖርዌይ ኦስሎ October 14/2017 በደማቅ ሁኔታ ሊያከብር ዝግጅቱን አጠናቆ እየጠበቆት ነው!!!
የኢሳት ኢዲቶሪያል ሐላፊ ጋዜጠኛ ፋሲል የኔ ያለም በመሀከላችን ተገኝቶ የኢሳትን የ7ዓመት ጉዞ የሚያስዳስሰን ሲሆን ተወዳጅዋ ድምፃዊት ሐኒሻ ሰለሞን ከኦርጋኒስት መርሶ ወንድማገኝ ጋር በመሆን በዓሉን በጣመ ዜማ እስከ እኩለ ሌሊት ታደምቀዋለች።
Tuesday, October 10, 2017
Monday, October 9, 2017
የሰሞኑ ንፋስ (ጋዜጠኛ መሳይ መኮንን)
ነገሮች ጥሩ አይመስሉም። ንፋሱ ወዴት አቅጣጫ እንደሆነ ለመተንበይ የሚቸግር ግን አይደለም። የሆነ መስመር ግልጽ እየሆነ የመጣ ይመስላል። አሰላልፍ ላይ ማን ከማን እንደቆመ ምልክት መታየት ጀምሯል። የወታደሩ ክፍልና በፌደራል መንግስት ላይ ሃይለማርያምን የሚመራው የህወሀት ቡድን ሚናቸውን ለመረዳት የሚያስችል ክስተቶችን ከሰሞኑ እየታዘብን ነው። በተለይም በሁለቱ ክልሎች(ኦሮሚያና ኢትዮጵያ ሶማሌ) መሃል ተነሳ የተባለው ውዝግብ ማን ከማን እንደተሰለፈ በብልጭታ ደረጃ የሚያሳይ ነገር አለው። የአባዱላ ገመዳ የስራ መልቀቂያና ለኢቢሲ የሰጡት መግለጫ ላይ ''ለጊዜው ሆድ ይፍጀው'' ያሉበት ምክንያታቸው ይህንኑ ጥርጣሬአችንን የሚያጠናክር ነው። የመንግስት ኮሚኒኬሽን ጽ/ቤት የዛሬው ቆንጠጥ፡ መረር ያለው ማስጠንቀቂያም የሚያመላካተን አሰላልፉ ግልጽ እየሆነ መምጣቱን ነው።
ሁኔታዎች ሊቀያየሩ ቢችሉ የሚለውን ከግምት በማስገባት አሰላልፉን ለመግለጽ ያህል የህወሀት ጄነራሎች ከሶ
Sunday, October 8, 2017
የፊንፊኔ ደላላ- ኧረ የገዥ ያለህ፣ ሞጃዎች ሊኮበልሉ ይመስላል (ለዋዜማ ራዲዮ)
ጤና ይስጥልኝ ጌታዬ!
ገረመው እባላለሁ፡፡ እሳት የላስኩ የፊንፊኔ ደላላ ነኝ፡፡ ምስጉን ጉዳይ ገዳይ ስለመሆኔ እግዜርም ሰይጣንም ያውቃሉ፡፡ ኪራይ ሰብሳቢ መሆኔን ድሪባም ኩማም ያውቃሉ፡፡ ዉሎ-አዳሬ ብሔራዊ፣ አመሻሼ አብዮታዊ ሃሃ፣ ላየን ባር ቤቴ፣ ቴሌ ባር ግዛቴ፡፡
እውነት ነው! ጥሎብኝ አልረጋም፡፡ ካዛንቺስ ነው ሲሉኝ ሳሪስ፣ ቀበና ነው ሲሉኝ ባምቢስ ደላላ ምን ቀልብ አለው ብለው ነው፤ጌታው!
እንዴት ነዎት ግን እርስዎ?
አይጠይቁኝ፡፡ ይኸው ይህን ሳምንት እንድቺው፡፡ ለምወዳት ዱለት እንኳ ጊዜ ልጣ!
ምንላርግ ብለው ነው….ከጥቃቅን ሚኒስትር እስከ ከፍተኛ ነጋዴ “ንብረቴን ሽጥልኝ” ብሎ ሰንጎ ይዞኝ…፡፡ ላይ ብወጣ ገረመው ነው፣ ታች ብወርድ ገረመው ነው፡፡ መካኒሳ “ሽጥልኝ ነው” ሰሚት ብወርድ “ሽጥልኝ” ነው፡፡ አጋዛኝ የሚል እኮ ጠፋ፡፡ ሻጭና ገዢ እንዲህ ያልተመጣጠነበት ዘመን በድለላ ዘመኔ ገጥሞኝም አያውቅ፡፡
የአባዱላ ነገር (D'r Tadesse Biru Kersmo)
የአቶ አባዱላ ገመዳ የሥራ መልቀቂያ ማቅረብ ፓለቲካዊ እንድምታ ከነገ ጀምሮ የሚታይ ነገር ይሆናል። የህወሓት ሰዎች ከሚከተሉት አንዱን ይመርጣሉ ብዬ አስባለሁ።
ሀ) ምንም እንዳልተፈጠረ ማስመሰል።
ቀድሞውኑ ጥያቄው አልቀረበም ይባል ይሆናል። ጥያቄው መቅረቡ ማስተባበል ካስቸገረ ደግሞ በጤና እክል ምክንያት የተጠየቀ መሆኑ፤ በዚህም ምክንያት የአባዱላ ማመልከቻ ተራ ነገር አድርገው ሊያቀርቡት ይሞክሩ ይሆናል። ከቅርብ ጊዜ ወዲህ የህወሓት ሰዎች ከነባራዊ እውነታ እየራቁ በቅዥት ዓለም የሚንሳፈፉ ሰዎች ሆነዋል። ስለሆነም ይህ ቢሆንስ (scenario) የማይመስል የሚባል አይደለም።
ለ) ማተራመስ።
ህወሓቶች አምርረው ሹም ሽሮችን በማከታተል ሁሉንም (የእውነቱን ብቻ ሳይሆን የይስሙላ ስልጣኖችንም) ጠቅልሎ ወደመያዝ ሊያመሩ ይችላሉ። የስልጣን ሽግግጉ ትግራይም ውስጥ ሊኖር ይችላል። ይህ ተግባራዊ ከሆነ ህወሓት ብአዴንና ኦህዴን አፍርሶ እንደገና ሊፈጥራቸው ይሞክራል፤ የሚሳካለት ግን አይመስለኝም።
ምንም ይሁን ምን የአባዱላ ገመዳ ውሳኔ የአቶ ለማ መገርሳን ክንድ አጠንክሯል። የኦህዴድ መሪዎች ህወሓት የማይወደውን ውሳኔ መወሰን የሚደፍሩ መሆናቸውን አስመስክሯል። አባዱላ ገፍቶ፣ ደፍሮ ከወጣ ብቻውን አይሆንም። ከነገ ጀምሮ የሚኖሩ የሸንጎ ስብሰባዎች የኦህዴድ ሰዎች በንቃት የሚሳተፉበት ይሆናሉ። ብአዴንም በዚህ መበረታታቱ አይቀርም። ደኢህዴንም ከእንቅፉ ለመንቃት መገላበጡ አይቀርም።
ህወሓት “ኢህአዴግ” የተባለውን ቀፎ ምን እንደሚያደርገው አይታወቅም። በአሁኑ ሰዓት የህወሓት የቅርብ ወዳጆች ሶህዴፓ፣ ሀብሊ፣ አብዴፓ፣ ቤጉሕዴፓና ጋብዴፓ እንጂ ኦህዴድ፣ ብአዴንና ደኢህዴን አይደሉም። የኢትዮጵያ ፓለቲካ የምትከታተሉ ሰዎች እነዚህን ድርጅቶች እወቋቸው - ሶህዴፓ፣ ሀብሊ፣ አብዴፓ፣ ቤጉሕዴፓና ጋብዴፓ። ህወሓት እነዚህን ድርጅቶች አቅፎ ኢትዮጵያን ለመግዛት ያልም ይሆናል።
Saturday, October 7, 2017
(የአርበኞች ግንቦት 7 ድምፅ ሬዲዮ)
ውድ አድማጮቻችን በዛሬው የአርበኞች ማስታወሻ መሰናዷችን አንድ አርበኛ ታጋይን እንዘክራለን። ይህ አርበኛ ታጋይ ከወጣትነት ዕድሜው ጀምሮ በኢትዮጲያ የ70ዎቹ ፖለቲካ ውስጥ በንቃት ሲሳተፍ የነበረና በጎልምስና ጊዜውም ቢሆን በሃሳብ፣ በገንዘብና በጉልበት ከወያኔ ጋር የሚደረገውን የነጻነት ትግል ሲያግዝ የነበረ ነው። በተለይም ደግሞ ይህን አርበኛ ልዩ የሚያደርገው በርካታ ኢትዮጲያዊያን እንደ ምድረ ገነት በሚያዩዋት ሃገረ አሜሪካ ሲያትል በተባለ ከተማ ይኖር የነበረና ተደራራቢ የቤተሰብና የስራ ሃላፊነቱን በትጋት ከመወጣት ባሻገር በኢትዮጲያ ህዝብ አርበኞች ግንባር በኋላም በአርበኞች ግንቦት 7 ለአንድነትና ለዲሞክራሲ ንቅናቄ ውስጥ በመቀላቀል ትግሉን በተለያየ መንገድ ሲያግዝ የነበረ ጠንካራ ኢትዮጲያዊ ስለነበርም ነው። ድርጅታችን አርበኞች ግንቦት 7 በሚያደርጋቸው የህዝባዊ እምቢተኝነቶችም ሆኑ ሌሎች ተሳትፎዎች ላይ ማድረግ የሚችለውን ሁሉ ካደረገና ከልጆቹ ጉሮሮ እየቀነሰ ትግሉን በገንዘብም ሲረዳ ከቆየ በኋላ ይህ ሁሉ ጥረቱ ለልቡ ደስታ ለህሊናው እርካታ አልሰጥ ብሎት ዱር ቤቴ ብሎ የአርበኞች ግንቦት 7 ህዝባዊ ሃይልን ኤርትራ በረሃ ወርዶ ተቀላቀለ። መሬት ላይ ያለውንም ትግል እንደ ማንኛውም አርበኛ ታጋይ የበሉትን በልቼ የጠጡትን ጠትቼ በዱር በገደሉ ከጓዶቼ ጋር ጠላታችንን ወያኔን እንዋጋለን በማለት ወደ በረሃ ቆርጠው ከወረዱ እንደ አንዳርጋቸው ጽጌ፣ ሻለቃ መሳፍንት ጥጋቡ ወይንም ገብርዬ፣ ፕሮፌሰር ብርሃኑ ነጋ፣ ገበየሁ አባጎራው፣ ኤፍሬም ማዴቦ፣ አበበ ቦጋለ፣ ነአምን ዘለቀ፣ ዕዝራ ዘለቀ፣ ሽባባው ዋዩና ከመሳሰሉት ጥቂት ብርቅዬ የኢትዮጲያ ዳያስፖራዎች ተርታ ስሙ በታሪክ ማህደር ውስጥ ተመዝግቧል። ይህ ሰው ተስፋ ላቀው አስረስ ወይንም በትግል ስሙ አርበኛ ታጋይ ተከዜ ይባላል።
አርበኛ ታጋይ ተከዜ እጅግ በጣም መልካም ስነምግባር የነበረው፣ በንቅናቄው አመራር አባላትም ሆነ በትግል ጓዶቹ ዘንድ የተወደደና የተከበረ ታጋይ ነበር። በበረሃ ቆይታው ውስጥ በማሰልጠኛ ካምፕም ውስጥ ሆነ ከዚያ ውጪ በሚከናወኑ ማናቸውም አይነት እንቅስቃሴዎች ውስጥ ቀድሞ የሚገኝ፣ ከሚናገረው በላይ የሚሰራ፣ በዕድሜው ከአብዛኛዎቹ ወጣት ታጋዮች የገፋ ቢሆንም አንድም ቀን ቢሆን የድካምና የመሰልቸት ስሜት ሳይታይበት የታገለ ጀግና ነበር። የሚገርም ትህትናን የተላበሰ፣ በታጋዬች መካከል ለሚፈጠሩ አለመግባባቶች የሽምግልናና የማስታረቅ ሚናን ይጫወት የነበረ፣ የሰራዊቱን የአካልና የስነ ልቦና ደህንነት ለመጠበቅ በጤና መኮንንነት ያገለገለና በተምሮ ማስተማር ሂደት ውስጥ በርካታ አርበኞችን መሰረታዊ የማንበብና የመጻፍ ትምህርትን ይሰጥ የነበረ አርበኛ ብቻ ሳይሆን ወንድምም አባትም የነበረ ትክክለኛ አገር ወዳድና ለኢትዮጵያ ህዝብም አጥብቆ የሚቆረቆር የዳያስፖራው አምባሳደር ነበር።
ለረዥም ጊዜ ከአሜሪካን የሕይወት ልምዱ ያገኘውን በነጻነትና በድፍረት ሃሳብን የመግለጽ ባህል በሚገባ የተላበሰው አርበኛ ታጋይ ተከዜ ይህንን የግልጽነትና የቀጥተኛነት ባህርይ በትግል ሜዳም ሆኖ ሲያስተላልፍ የነበረ የሰራዊቱ ድምጽ ነበር ማለት ይቻላል። የታገለለትና የተሰዋለትም ይህንን የነጻነትና የዲሞክራሲ ባህል በኢትዮጲያ ውስጥ ለመተግበር ንቅናቄአችን ያስቀመጠውን ራዕይ ለማስፈጸም ሲል ነውና ይህንን የሱን ትግል ከዳር የማድረስ ታሪካዊ ሃላፊነት በትከሻችን ላይ ጥሎብን ሄዷል።።
ሰበር ዜና
የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት አፈ ጉባዔ አባዱላ ገመዳ ሥልጣናቸውን በፈቃዳቸው ለመልቀቅ ደብዳቤ ማስገባታቸውን አዲስ ስታንዳርድ ዘገበ።
ለአባዱላ ሥልጣን መልቀቅ ዋነኛው ምክንያት ከ150 ሺህ በላይ የኦሮሞ ተወላጆች የተፈናቀሉበት በምስራቅ ኢትዮጵያ የተከሰተው የሰሞኑ ግጭት መፍትሄ ሊያገኝ አለመቻሉ ነው ተብሏል።
በዚህ ምክንያት ባለፉት ሳምንታት አፈ ጉባዔው ከሌሎች ከፍተኛ የመንግስት ሹመኞች ጋር ከፍ ያለ መካረር ውስጥ ገብተው መሰንበታቸውብም ጋዜጣው አስነብቧል።
በተያዘው ሳምንት የጠቅላይ ሚኒስትሩ ፕሮቶኮል ሹምና አንድ ብርጋዲየር ጀነራል ስርአቱን መክዳታቸው ይታወቃል።
Sat 07 Oct 2017
ለአባዱላ ሥልጣን መልቀቅ ዋነኛው ምክንያት ከ150 ሺህ በላይ የኦሮሞ ተወላጆች የተፈናቀሉበት በምስራቅ ኢትዮጵያ የተከሰተው የሰሞኑ ግጭት መፍትሄ ሊያገኝ አለመቻሉ ነው ተብሏል።
በዚህ ምክንያት ባለፉት ሳምንታት አፈ ጉባዔው ከሌሎች ከፍተኛ የመንግስት ሹመኞች ጋር ከፍ ያለ መካረር ውስጥ ገብተው መሰንበታቸውብም ጋዜጣው አስነብቧል።
በተያዘው ሳምንት የጠቅላይ ሚኒስትሩ ፕሮቶኮል ሹምና አንድ ብርጋዲየር ጀነራል ስርአቱን መክዳታቸው ይታወቃል።
Sat 07 Oct 2017
Friday, October 6, 2017
ኢትዮጵያን ለማዳን በሚደረገው ትግል የድርሻችንን እንወጣ!! ታላቅ ጥሪ ለአርበኞች ግንቦት ሰባት ደጋፊዎች ታጋይ አርበኛ ፕሮፌሰር ብርሃኑ ነጋ እና ሌሎች ከፍተኛ የድርጅቱ አመራሮች በተገኙበት ታላቅ ህዝባዊ ስብሰባ የፊታችን ኦክቶበር 15 በሲያትል ተዘጋጅቷል። በዕለቱ ስለቀጣይ የትግል አካሄድ ፣ በቅርቡ ስለተካሄደው ጠቅላላ ጉባኤ አጠቃላይ ግንዛቤ ይሰጣል ፣ ውይይት ይደረጋል። በተባለው ቀን እና ቦታ በመገኘት የኢትዮጵያ አርበኛ ታጋዮችን እንደግፍ። አንድነት ኃይል ነው ኢትዮጵያ ለዘላለም ትኑር!!
Thursday, October 5, 2017
Wednesday, October 4, 2017
ጃሎ እንበል!!!!!
ሞትን ያህል መከራ
ባሩድን ያህል መራራ
ጠጥቶ ሃገሩን ሊያኮራ
ቅንጣት ለነፍሱ ሳይፈራ
በሞቱ ታሪክ ሊሰራ
ይህ ነበር የጀግና ትውፊት ሃገር ትውልድን ያኮራ
………
የሃገሩን ሞት ሞቶ የራሱን ነፍስ ሊሰጣት
የፍቅሩን ፅናት ፈትኖ በባሩድ በእቶን እሳት
ጠላቱን አይቀጡ ቀጥቶ የክብሩን ፀዳል ሊያለብሳት
ዘጠኝ ሞት ከፊቱ ቀርቦ ጨልጦ ዘጠኝኑም ሞት
ዘጠኙም ሳይገለው ቀርቶ በሺህ ልብ ህይወት ዘርቶ
ከዘላለም እስከ ዘላለም ጥግ ህያው ታሪክ ዘርቶ
እንዲህ ነበር አባት ሲያልፍ አኩሪ ስራውን ተክቶ
…………..
ልጁም ያባቱን ወኔ ቆራጥ ተግባሩን ወርሶ
ለወገቡ ዘር መራራ ደሙን ከጀግና ልቡ ቀንሶ
እሱም ተክቶ ያልፋል ያገሩን ታሪክ አውርሶ
ይህ ነበር የኛ ታሪክ ድርሳኑን ላየው
ከግሉ ቅጦት ይልቅ ያገሩን ክብር ያሳየው
እንዲህ ለሀገር በመሞት ፈቃዷን እየፈፀምነ
ጎበዝ ሲያልፍ ጎበዝ ተክቶ ከዘንድሮ ላይ ደረስነ
……………
ዘንድሮስ! ዘንድሮስ! ዘንድሮማ ምን ይወራል
እድሜ ለስልጣኔ ለለጋ ህፃናት ይብላኝ ለአገራዊ ሁሉ መጥኔ
ልጄ ኑርልኝ ስትል ሃገር በብርክ ቆማ
የዝሆን ጆሮ ይስጠኝ ብሎ የእምዬን ተማፅኖ ላይሰማ
ወላጅ ለሞት ሲጣደፍ ጨቅላ ህፃናት በትኖ
እድሜ ባዛለው ጉልበቱ አያት ከልጅ ልጅ ታምኖ
አረጋዊነት ዘመኑ ማረፍ መጦሩ ቀረና
መውለድ እርግማን ሆነ ፀጋ መሆኑ አበቃና
………………..
ሌጣ ሆኖ እንደበቀለ ሳያስብ ለእናት አባቱ
ለግሉ ደስታ ሲማስ ሲታደፍ ለእሳት ጉልበቱ
ወላጁን በሃዘን ማግዶ ሲሰበር በለጋነቱ
ወዴት አቤት ይባላል መጥኔ ለዚያች እናቱ
የልጇን መረታት አይታ ሰፍሳፋ ልቧ ሲባባ
አንጀቷ ሁለት ተከፍሎ ፊቷ ሲታጠብ በእምባ
ላፍታ እንኳ ይህ ቢታወሰው ዘሎ ከእሳቱ ባልገባ
…………..
ጉድ ነው ጉድሽን ስሚ እማማ ከነእርምሽ መኖሩ ይብቃ
የጉድ ዘመን ትውልድሽ የአውሮፓ የላቲን መጢቃ
ክብሩን ሞራሉን ሸጦ እንኳን ለልጁ ሊተርፍ ለራሱም ገና ሳይበቃ
መች እንደአባቱ ሊያኖርሽ ለራሱም መኖር አቅቶት
20 30 ኬላውን አርባ መድፈን ተስኖት
በደዌ በትር ሲመታ ቡቃያው ጅምሩ ቀርቶ
ወፌ ቆመች እንዳላል የእምቦሳው ተስፋ ገርጥቶ
ጥናቱን ይስጥሽ እማማ አሳርሽ መከራሽ በዝቶ
እንደአሸን የፈላው ዘርሽ እንደአሸን ልርገፍ ካለ
ጎህ ሲቀድ የፈላው ዘርሽ ጀንበርን ማለፍ ካልቻለ
መገን ከማለት በቀር ከንግዲህ ሌላ ምን አ ለ
………………………………
ሽምግልና ላይገኝ ከእንግዲህ በተረት ይፃፍ
የእድሜ በረከት ስጦታው ሲዘጋ በደዌ ምዕራፍ
ጃሎ እንበል ጎበዝ እንፎክር የመኖር ገዳችን ቢመጣ
ወኔአችን ግሎ ተነስቶ ሞትን ካገሩ ሊያስወጣ
ያኔ ሃገር ስትጠራን በጭንቅ በጣር ተይዛ
ድረሱ አድኑኝ ስትል በጠላት አዝና ተክዛ
በቀረርቶ ፍርሃትን ገድለን በሽለላ ሞትን ደፍረን
የሀገርን መደፈር ላናይ በፈቃዳችን ሞተን
ታንኩን መትረየስ መድፉን ጎራዴን ታጥቀን ማርከናል
ጠላትን አይቀጡ ቀጥተን ወደመጣበት ልከናል
አንዴ አይደል ደርዘን ተዋግተን የወንዱን ሱሪ ፈተናል
ያኔም የነበር እኛ! አንሁን ያለን እኛ! እንዴት ያን ሁሉ ወኔ ለደዌ ሰተን እንተኛ
ጃሎ በል ጎበዝ እንፎክር የመኖር ገዳችን ይምጣ
ወኔአችን ግሎ ተነስቶ ሞትን ካገር ቢያስወጣ
ዱብ ዱብ ባይ እንደበረዶ በልጅነቱ በረሃ ለምዶ
እጥፍጥፍ እንደ ኩታ ልብስ አተኳኮሱ አንጀት የሚያርስ
እዚህ አጉርሶ እዚያ ቢልከው አንጀት ጉበቱን አዝለከለከው
ገና ወጣቱ የነበር ጣቱ
ያ ጎበዝ ጀግና ጠረፍ ነው ሞቱ
አትንኩኝ! አትንኩኝ! አትንኩኝ እያለ ታልፋለች ህይወቱ
አታታታታታታታታታታ እምምምምምምመምምምም……..
ባሩድን ያህል መራራ
ጠጥቶ ሃገሩን ሊያኮራ
ቅንጣት ለነፍሱ ሳይፈራ
በሞቱ ታሪክ ሊሰራ
ይህ ነበር የጀግና ትውፊት ሃገር ትውልድን ያኮራ
………
የሃገሩን ሞት ሞቶ የራሱን ነፍስ ሊሰጣት
የፍቅሩን ፅናት ፈትኖ በባሩድ በእቶን እሳት
ጠላቱን አይቀጡ ቀጥቶ የክብሩን ፀዳል ሊያለብሳት
ዘጠኝ ሞት ከፊቱ ቀርቦ ጨልጦ ዘጠኝኑም ሞት
ዘጠኙም ሳይገለው ቀርቶ በሺህ ልብ ህይወት ዘርቶ
ከዘላለም እስከ ዘላለም ጥግ ህያው ታሪክ ዘርቶ
እንዲህ ነበር አባት ሲያልፍ አኩሪ ስራውን ተክቶ
…………..
ልጁም ያባቱን ወኔ ቆራጥ ተግባሩን ወርሶ
ለወገቡ ዘር መራራ ደሙን ከጀግና ልቡ ቀንሶ
እሱም ተክቶ ያልፋል ያገሩን ታሪክ አውርሶ
ይህ ነበር የኛ ታሪክ ድርሳኑን ላየው
ከግሉ ቅጦት ይልቅ ያገሩን ክብር ያሳየው
እንዲህ ለሀገር በመሞት ፈቃዷን እየፈፀምነ
ጎበዝ ሲያልፍ ጎበዝ ተክቶ ከዘንድሮ ላይ ደረስነ
……………
ዘንድሮስ! ዘንድሮስ! ዘንድሮማ ምን ይወራል
እድሜ ለስልጣኔ ለለጋ ህፃናት ይብላኝ ለአገራዊ ሁሉ መጥኔ
ልጄ ኑርልኝ ስትል ሃገር በብርክ ቆማ
የዝሆን ጆሮ ይስጠኝ ብሎ የእምዬን ተማፅኖ ላይሰማ
ወላጅ ለሞት ሲጣደፍ ጨቅላ ህፃናት በትኖ
እድሜ ባዛለው ጉልበቱ አያት ከልጅ ልጅ ታምኖ
አረጋዊነት ዘመኑ ማረፍ መጦሩ ቀረና
መውለድ እርግማን ሆነ ፀጋ መሆኑ አበቃና
………………..
ሌጣ ሆኖ እንደበቀለ ሳያስብ ለእናት አባቱ
ለግሉ ደስታ ሲማስ ሲታደፍ ለእሳት ጉልበቱ
ወላጁን በሃዘን ማግዶ ሲሰበር በለጋነቱ
ወዴት አቤት ይባላል መጥኔ ለዚያች እናቱ
የልጇን መረታት አይታ ሰፍሳፋ ልቧ ሲባባ
አንጀቷ ሁለት ተከፍሎ ፊቷ ሲታጠብ በእምባ
ላፍታ እንኳ ይህ ቢታወሰው ዘሎ ከእሳቱ ባልገባ
…………..
ጉድ ነው ጉድሽን ስሚ እማማ ከነእርምሽ መኖሩ ይብቃ
የጉድ ዘመን ትውልድሽ የአውሮፓ የላቲን መጢቃ
ክብሩን ሞራሉን ሸጦ እንኳን ለልጁ ሊተርፍ ለራሱም ገና ሳይበቃ
መች እንደአባቱ ሊያኖርሽ ለራሱም መኖር አቅቶት
20 30 ኬላውን አርባ መድፈን ተስኖት
በደዌ በትር ሲመታ ቡቃያው ጅምሩ ቀርቶ
ወፌ ቆመች እንዳላል የእምቦሳው ተስፋ ገርጥቶ
ጥናቱን ይስጥሽ እማማ አሳርሽ መከራሽ በዝቶ
እንደአሸን የፈላው ዘርሽ እንደአሸን ልርገፍ ካለ
ጎህ ሲቀድ የፈላው ዘርሽ ጀንበርን ማለፍ ካልቻለ
መገን ከማለት በቀር ከንግዲህ ሌላ ምን አ ለ
………………………………
ሽምግልና ላይገኝ ከእንግዲህ በተረት ይፃፍ
የእድሜ በረከት ስጦታው ሲዘጋ በደዌ ምዕራፍ
ጃሎ እንበል ጎበዝ እንፎክር የመኖር ገዳችን ቢመጣ
ወኔአችን ግሎ ተነስቶ ሞትን ካገሩ ሊያስወጣ
ያኔ ሃገር ስትጠራን በጭንቅ በጣር ተይዛ
ድረሱ አድኑኝ ስትል በጠላት አዝና ተክዛ
በቀረርቶ ፍርሃትን ገድለን በሽለላ ሞትን ደፍረን
የሀገርን መደፈር ላናይ በፈቃዳችን ሞተን
ታንኩን መትረየስ መድፉን ጎራዴን ታጥቀን ማርከናል
ጠላትን አይቀጡ ቀጥተን ወደመጣበት ልከናል
አንዴ አይደል ደርዘን ተዋግተን የወንዱን ሱሪ ፈተናል
ያኔም የነበር እኛ! አንሁን ያለን እኛ! እንዴት ያን ሁሉ ወኔ ለደዌ ሰተን እንተኛ
ጃሎ በል ጎበዝ እንፎክር የመኖር ገዳችን ይምጣ
ወኔአችን ግሎ ተነስቶ ሞትን ካገር ቢያስወጣ
ዱብ ዱብ ባይ እንደበረዶ በልጅነቱ በረሃ ለምዶ
እጥፍጥፍ እንደ ኩታ ልብስ አተኳኮሱ አንጀት የሚያርስ
እዚህ አጉርሶ እዚያ ቢልከው አንጀት ጉበቱን አዝለከለከው
ገና ወጣቱ የነበር ጣቱ
ያ ጎበዝ ጀግና ጠረፍ ነው ሞቱ
አትንኩኝ! አትንኩኝ! አትንኩኝ እያለ ታልፋለች ህይወቱ
አታታታታታታታታታታ እምምምምምምመምምምም……..
አበባው መላኩ
Monday, October 2, 2017
ከባህርዳር ዩኒቨርሲቲ ፖሊ ቴክኒክ ካምፓስ ተማሪዎች ያለ አግባብ እየተባረሩ መሆኑ ታወቀ (የአርበኞች ግንቦት 7 ድምፅ ሬዲዮ)
የባህር ዳር ዩንቨርስቲ ፖሊ ቶክኒክ ካምፓስ የአራተኛ አመት የኢንጅነሪንግ ተማሪዎች መብታቸውን በመጠየቃቸው ምክንያት 1500 ከዩኒቨርሲቲው ግቢ እንዲባረሩ ተደርጓል፡፡ ተማሪዎችም ያለአግባብ አንወጣም በማለታቸው ምክንያት በፌደራል ፖሊሶች እየተዋከቡ ይገኛሉ፡፡ አብዛኞቹ ተማሪዎች ከሌላ ክፍለሃገር የመጡ በመሆናቸው ምክንያት በእጃቸውም ምንም ገንዘብ የሌላቸው በመሆኑ ወደ ቤተ ክርስቲያን እና መስጊድ ለመጠጋት ቢሄዱም የወያኔ ቅጥረኛ ወታደሮች እየተከታተሉ ክልከላ እያደረጉባቸው ይገኛሉ፡፡ተማሪዎች ማደሪያ ስለሌላቸው በአካባቢው ወደ ሚገኘው ጊዮርጊስ ቤተክርስትያን ለማደርና እቃቸውን ለማስቀመጥ ወደ ቤተክርስቲያኑ ሲደርሱ የወያኔ ልዩ ሀይል ወታደር ከቦ ጠበቃቸው እናም ክልከላ በመፈፀም ከቤተክርስቲያኑ አካባቢ እንዲርቁ በማስገደድ ላይ ናቸው፡፡ በዚህ ግራ የተጋቡት ተማሪዎቹ ጉዟቸውን ወደ ሌላ ቤተክርስቲያን አድርገዋል ስለሆነም የባህርዳር ህዝብ እዲያስጠጋቸውና እዲደርስላቸው በመማፀን ላይ ይገኛሉ፡፡
Mon 02 Oct 2017
H.RES 128 በኢትዮጵያ መንግስት ሎቢስቶች አማካኝነት ከድምፅ አሰጣጥ ስነስርአት እንዲዘገይ መደረጉ ታወቀ
ለኦክቶበር 2 , 2017 ሊደረግ የነበረው ኢትዮጵያን የሚመለከተው ህግ H.Res 128 መተላልፉን አስመልክቶ የኮንግረስ አባላት አዲስ ኢንፎርሜሽን ለኢትዮ አሜሪካን ሲቪክ ካውንስል መኖሩን ለኮሚቴው አስታውቀዋል። ጉዳዩን በቅርበት የሚከታተሉት የኢትዮጵያውያን አሜሪካን ሲቪክ ካውንስል እና ኢትዮጵያን አድቮከሲ ኔትወርክ እንደገለፁልን ከሆነ የተላለፈበት ምክንያት ባለፈው ሳምንት ከአሜሪካን ባለስልጣናት የተነገራቸው የጊዜ ጥበት ሳይሆን፤ የኢትዮጵያ መንግስት በቀጠራቸው ሎቢስቶች አማካኝነት ከድምፅ አሰጣጥ ስነስርአት ለጊዜው እንዲወጣ ማስደረጋቸውን ለመረዳት መቻላቸውን አስታውቀዋል። [ 29 more words ]
http://hr128.org/h-res-128-ለኦክቶበር 2 , 2017 ሊደረግ የነበረው ኢትዮጵያን የሚመለከተው ህግ H.Res 128 መተላልፉን አስመልክቶ የኮንግረስ አባላት አዲስ ኢንፎርሜሽን ለኢትዮ አሜሪካን ሲቪክ ካውንስል መኖሩን ለኮሚቴው አስታውቀዋል።
http://hr128.org/h-res-128-ለኦክቶበር 2 , 2017 ሊደረግ የነበረው ኢትዮጵያን የሚመለከተው ህግ H.Res 128 መተላልፉን አስመልክቶ የኮንግረስ አባላት አዲስ ኢንፎርሜሽን ለኢትዮ አሜሪካን ሲቪክ ካውንስል መኖሩን ለኮሚቴው አስታውቀዋል።
Sunday, October 1, 2017
አርበኝነት (የአርበኞች ግንቦት 7)
July 10, 2017
አርበኝነት ማለት ለወገኑ የተሻለ ህይወት ጊዜዉን ጉልበቱን እዉቀቱን ገንዘቡን ክቡር ህይወቱን መስዋትነት ለመክፈል የተዘጋጀ ሰዉ ወይም የህብረተስብ ክፍል ማለት ነዉ።
ከዚህም በመነሳት ዛሬ ላይ እየተካሄደ ባልዉ የአርበኝነት ትግል አላማችን እንዲሳካ እራአያችን እንድያብብ የምንሻ ሁሉ የግድ ያለዉን ነባራዊ ሁኔታ ማጤንና መገንዘብ ያስፈልጋል። የአርበኝነት አላማ ደግሞ ዉጤታማ የሚሆነዉ በእቅድ የሚመራ በተግባር የሚታይና በድርጊት የሚገለጽ የጥርት ዉጤት ሲሆን ነዉ።
በመሆኑም ድሮ አርበኛ አባቶቻችን በአዋጅ ተሰባስበዉ በራሶችና በደጃዝማቾች የጦር አጋፋሬዎች እየተመሩ ለሃገራቸዉ በነበራችዉ ጥልቅ የሃገራዊ የፍቅር ስሜት አርበኝነትን ተላብስዉ በባዶ እግራቸዉ ወንዝና ሽነተረሩን አቋርጠዉ ዳገት ቁልቁልቱን ወጥተዉ ወርደዉ ከጦርነቱ አዉድማ ሲደርሱ ነጋሪት እየተጎሰመ እንቢልታዉ እየተንፋ ንጉስ ከፈረስ ሳይወርዱ በጦርነተ መሃል ዉስጥ ሆነዉ አዋጅ እያስነገሩ የፊዉታራሬ ጦር ግባ ተብለሃል፥ የቀኝ አዝማች ጦር ግባ ተብለሃል፥የግራዝማች ጦር ግባ ተብለሃል በሚል የአዉደ ዉጊያ የእዝ ሰንሰለት ጊዜዉ በፈቀደዉ የጦርነት ስልት ነበር በጦር በጎራዴ ተዋግተዉ ደማቸዉን አፍሰዉ ሃገራችን ኢትዮጵያን ከወራሪ ቅኝ ገዥዎች ያዳኗት።
በዛሬው የኢሬቻ በዓል የተሳተፉ ወጣቶች በከፍተኛ ድምጽ የተቃውሞ መፈክሮች ሲያሰሙ ነበር። DW (Amharic)
ከመፈክሮቻቸው ውስጥ "ዶ/ር መረራ፣ በቀለ ገርባ ይፈቱ" ፣ "ኦሮሞዎችን መግደል ይቁም" የሚሉ ይገኙበታል። በበዓሉ ከተደመጡ መፈክሮች መካከል "ጭቆና በቃን፣ ለኦሮሞዎች ከሶማሌ ክልል መፈናቀል ምክንያት የሆኑ ለፍርድ ይቅረቡ፣ ነፃነት ለኦሮሚያ" የሚሉ ነበሩበት። የበዓሉ ታዳሚ ወጣቶች ተቃውሟቸውን በመፈክር እና በዘፈን ከማሰማታቸው ባሻገር ባለፈው ዓመት ህይወታቸውን ያጡ ዜጎችን ለማስታወስ ተንበርክከው፣ እጃቸውን በ"X" ምልክት በማጣመር ሀዘናቸውን ገልጸዋል። በስፍራው የነበሩ የኦሮሚያ ክልል ፖሊሶች ተቃውሞውን በዝምታ አልፈውታል። ጸጥታ ለማስጠበቅ ከተሰማሩ ወጣቶች ጋር በመሆንም ሁኔታውን ለማረጋጋት እና በዓሉ በሰላም እንዲጠናቀቅ በድምጽ ማጉያ መልዕክት ሲያስተላልፉ ታይተዋል። (ፎቶ- ከተስፋለም ወልደየስ ማኅደር)
እንኳን ለእሬቻ በአል አደረሳችሁ (አርበኞች ግንቦት7)
September 29, 2017
የእሬቻ በአል ብዙ ብዙ ቁስሎችን ጥሎብን አልፏል፡፡ ብዙ ወንድሞቻችንን እህቶቻችንን እናት አባቶቻንንና ህፃናት ልጆችን በአገዛዙ የጭካኔ አገዳደል አጥተናል፡፡ ገንዘብ ከመለመንና ህይወትን ከቁሳዊ ትርፉ በቀር የሰው ልጅ በራሱ ሃብት መሆኑ ያልገባው ቢገባውም ለማሽመድመድ የሚሞክረው አገዛዙ ባለፈው አመት የእሬቻ በአል አከባበር ላይ ብዙዎችን ለሞትና ለአካል ጉዳት በሺዎች የሚቆጠሩትን ደግሞ ለእስርና ለስደት ዳርጓል፡፡ የሚገርመው ያንን ሁሉ ሃዘን ሰቆቃና እንግልት ማለፋችን ሳያንስ ዛሬ ደግሞ ያኔ ጉዳት ለደረሰባቸው ዜጎች በድንገት የሞቱ የሚል ሃውልት በመገንባት ዛሬም ቀልዱን ቀጥሏል ፡፡ በእራሱ በአገዛዙ ወታደሮች የጥይት አረር እንደወጡ ሳይመለሱ የቀሩ ሮጠው እንኳን ያልጠገቡ ለጋ ህፃናት በድንገት የሞቱ ተብሎ ተፅፎ ሲቀለድባቸው ማየትን የመሰለ ከባድ ህመም የለም፡፡
በመሰረቱ ይህ ሃውልት ከጅምሩስ ለምን ተሰራ? ምንን ለማሳየትስ ተፈልጎ ነው? ሃውልቱ የተሰራው ብለን ስናስብ አሁን የሚከበረው የእሬቻ በአል ላይ ህዝቡ አገዛዙ በፈፀመው ግፍ ተፀፅቷል ብሎ እንዲያምን መሆኑ ግልፅ ነው ፡፡ ይህን ሃሳቡን ያወቀበት ህዝቡ ደግሞ ከዚህ ሃውልት ላይ በድንገት የሞቱ የምትለዋን ማጭበርበሪያ ጭንብልህን አውልቃት ብለው ስለሞገቱት ሳይወድ በግዱ ሊፍቃት ችሏል፡፡
ሌላው ደግሞ ለህዝብ የሚቆረቆርና እንደ መንፈሳዊ አባት ሆኖ ህዝብ ሲያጠፋም አጠፋህ መንግስትም ሲበድል በደልክ የሚል አባት አጥተን በእየ እስር ቤቱ እየዞሩ በውሸት መስክሩ ልማቱን አታደናቅፉ የሚሉ አድር ባይ አባቶች በሞሉባት ሃገር ላይ እንደ ኦሮሚያ አባገዳዎች ለሃገሩና ለህዝቡ የሚቆረቆር አባት ማግኘታችን ኢትዮጲያዬ እውነትም ተስፋ አለሽ እንድንል ያደርገናል ፡፡ እንግዲህ እሁድ በሚከበረው የእሬቻ በአል ላይ የኦሮሚያ ቄሮዎችና አባገዳዎች በአሉን ለማክበር እንዲህ መሆን አለበት ያሉትን በመግለጫም ጭምር አስቀምጠዋል፡፡ ይኸውም በእሬቻ በአል ላይ ማንም የዚህ አምባገነን ስርአት ሹም የሆነ ሰው ሁሉ በአሉ ላይ ተገኝቶ ምንም የሚያደርገው ንግግር እንዳይኖር ፣ የልማት ማስታወቂያ እንዳይነገር ፣ ዜጎች በሚራቡባት ብዙዎች በሚታሰሩባት በሚገደሉባትና በሚሰደዱባት ሃገር ውስጥ እየኖርን ልማቱ ምጥቀቱ የሚል ውዥንብር አንፈልግም ! ስለዚህ ማንም የአገዛዙ አካል ወይም ወኪል በአላችን ላይ ንግግር ማድረግ አይችልም ሲሉ በግልፅ አስቀምጠዋል፡፡እንዲሁም ቄሮዎቹ የማንም ድርጅት ይሁን ክልል ባንዲራ አይውለበለብም የሚል አቋምም ወስደዋል፡፡ ይህ ደግሞ ለሁሉም ኢትዮጲያዊ ትልቅ ድል ነው፡፡
አገዛዙ 50 የሚሆኑ ሰዎች በድንገት ሞቱ ቢልም እኛ የምናውቀውና ከጉያችን የተለዩን ከ500 በላይ የሚሆ
Subscribe to:
Posts (Atom)