Friday, July 28, 2017

ገዢው ፓርቲ በነጋዴዎች እየቀረበ ያለውን ጥያቄ ወደ ጎን በማለት “የበቀል እርምጃ” እየወሰደ ነው ሲሉ ነጋዴዎች ተናገሩ

በአገር ሽማግሌ ስም መቀሌ ከሄዱት መካከል 4ቱ የተባረሩ የአርበኞች ግንቦት አባላት የነበሩ ናቸው

ከድርጅቱ ያገኘነው መረጃ እንደሚያመለክተው የአማራ እና የትግራይን ህዝብ እናስታርቃለን በማለት ወደ መቀሌ ከተጓዙ የአገር ሽማግሌ ስም ከተሰጣቸው ሰዎች መካከል አራቱ በአርበኞች ግንቦት7 ስር ተደራጅተው ሲሰሩ የነበሩና በሁዋላ ላይ ህወሃት በሰላይነት እንዲያገለግሉት እንደመለመላቸው ሲታወቅ የተባረሩ ናቸው። አቶ ታያቸው ጥሩነህ፣ አቶ ሞላ መኮንን፣ አሰማራው መኮንን እና ሻንቆ ሽባባው የተባሉትን በመድረክ ላይ ይናገሩት የነበሩት በመጀመሪያ ለነጻነት ትግሉ ዋና ተዋናይ ሆነው ከቀረቡ በሁዋላ የተሰጣቸውን ህዝባዊ አደራ በመተውና የድርጅት ዲሲፕሊን በመጣስ ለህወሃት መረጃ ሲያቀብሉ የነበሩ መሆናቸውና ሲደርስባቸው በማምለጥ ከድርጅቱ የተባበሩ መሆናቸውን ንቅናቄው ገልጿል።
Bilderesultat for አርበኞች ግንቦት 7
 ግለሰቦቹ በአሁኑ ሰአት ከፍተኛ ገንዘብ ተመድቦላቸው ከደህንነት አባላት ጋር “ምህረት እናሰጣላን” በማለት ታጋዮችን በማታለል ለአገዛዙ እጃቸውን እንዲሰጡ ለማድረግ እየሰሩ ነው ብሎአል። 

Thursday, July 27, 2017

በኢትዮጵያ ያለው መንግስት በሙስና የተዘፈቀ ጨካኝና የዘረፋ መጠኑም ድንበር የማይገታው ነው ተባለ

በአሜሪካ የህግ መወሰኛ ምክር ቤት የካሊፎርኒያ ተወካይ የሆኑት ዳና ሮራባከር እንዳሉት እሳቸው በግል የሚያውቋቸው ትውልደ ኢትዮጵያውያን የመንግስት ደጋፊ ባለመሆናቸው ብቻ ንብረታቸው እንደተወረሰ አስታውሰው እንዲህ ያለ የሰብአዊ መብትን ቀርቶ የግል ንብረትን እንኳ የማያከብር አገዛዝ ከአሜሪካ መንግስት ጋር ወዳጅና ተባባሪ ለመሆን መሞከሩ በጣም ይገርመኛል ብለዋል።
ባጭሩ አሉ የምክር ቤቱ አባል በኢትዮጵያ ያለው አገዛዝ ፈላጭ ቆራጭና ለምንም ነገር ገደብ የሌለው ነው ብለዋል።
በኢትዮጵያ ጉዳይ ላይ የተረቀቀው የዚህ ህግ ዋና አርቃቂ የሆኑት የኒውጀርሲው ተወካይ ክሪስ ስሚዝ በበኩላቸው በኢትዮጵያ እየቀጠለ ያለው የሰብአዊ መብት ጥሰት በፍጹም ተቀባይነት የሌለው ነው ብለዋል።
ካለፍርድ ቤት ትእዛዝ መታሰር፣ግድያ፣ሰቆቃ በተቃዋሚ ፖለቲከኞችና ጋዜጠኞች ላይ እየቀጠለ ነው ብለዋል።
ክሪስ ስሚዝ እንዳሉት በቅርቡ ለአንድ  አሁን በአሜሪካ ለሚገኝ ኢትዮጵያዊ አትሌትን ጉዳይ በተመለከተ ለአሜሪካ የዜግነትና ስደተኞች ጉዳይ ቢሮ የድጋፍ ደብዳቤ መጻፋቸውንና ጥያቄያቸውም ደምሰው አበበ የተባለው ሯጭ ቤተሰቦች ወደ አሜሪካ መጥተው እንዲያገኙት ነው ብለዋል።
ደምሰው ተቃዋሚ በመሆኑ ብቻ ተይዞ ውስጥ እግሩ ክፉኛ ተገርፎ እንዳይሮጥ የተደረገና ሌሎች ከፍተኛ ሰቆቃዎች የተፈጸመበት ግለሰብ ነው ብለዋል።
ሚስተር ስሚዝ ሲቀጥሉም አባ ጉያ የተባለ የአካል ጉዳተኛና የሀገሪቱ የአካል ጉዳተኞች ማህበር መሪን ትቃወመናለህ በሚል የአገዛዙ ደህንነቶች በእስር ካሰቃዩት በኋላ ደብድበው ጫካ ውስጥ ጥለውት በበጎ አድራጊዎች እርዳታ ከሞት መትረፉን ተናግረዋል።
አባ ጉያም ከአራት ወር በፊት በዚህ ምክር ቤት ቀርቦ ምስክርነት መስጠቱን አስታውሰዋል።
ይህ የተረቀቀው ህግ አሉ ሚስትር ስሚዝ በኢትዮጵያ ያለው አገዛዝ እንደ መስታወት ራሱን የሚያይበትና ለለውጥም እራሱን የሚያዘጋጅበትን እድል ይፈጥርለታል።
ኤች አር 128 በሚል ምህጻረ ቃል የሚጠራው ረቂቅ ህግ የአሜሪካ የህግ መወሰኛ ምክር ቤት በኢትዮጵያ ያለው የአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ እንዲነሳ፣የታሰሩ የሰብአዊ መብት አቀንቃኞች፣ጋዜጠኞችና የተቃዋሚ መሪዎች እንዲፈቱ፣ህገ መንግስታዊ መብታቸውን በመጠቀማቸው ብቻ ለሞትና ለስቃይ የተዳረጉ ሰዎች ጉዳይ እንዲታይና የድርጊቱ ፈጻሚዎችም ለፍርድ እንዲቀርቡ ይጠይቃል።
ህጉ በተጨማሪም በኢትዮጵያ እየተፈጸመ ያለው የሰብአዊ መብት ጥሰት በተባበሩት መንግስታት ድርጅት በኩል እንዲጣራ ይጠይቃል።
ረቂቅ ህጉ በሌሎች የምክር ቤቱ አባላት ዛሬ የድጋፍ አስተያየት ተሰጥቶበታል።ለምክር ቤቱም ተመርቶ በቅርቡ እንድሚጸድቅ ይጠበቃል።
ኢሳት ዜና -ሐምሌ 20/2009

የአርበኞች ግንቦት 7 ድምፅ ሬዲዮ


የሐምሌ 20 ቀን 2009 ዓ.ም.
ዜናዎች

* በህወሃት የሚዘወረው በሙስና የተጠረጠሩ ከ30በላይ ከፍተኛ የመንግስት የስራ ሃላፊዎች እና ነጋዴዎችን በቁጥጥር ስር አውያለሁ ሲል ገለፀ፡፡
* በኢትዮጵያ በ ተለያዩ ከተሞች እየተካሄደ ያለው የነጋዴዎች አድማ እንደቀጠለ መሆኑ ታወቀ፡፡
* የአማራ ክልል ሰላ ከቁጥጥር ውጭ እየሆነ መጥቷል ሲል ብአዴን በዝግ በመከረበት ስብሰባ ላይ ገለፀ፡፡
* በሽብር የተከሰሰው ወጣጥ ህክምና ተከልክሎ እንደሞተ ተገለፀ፡፡
* በአርባ ምንጭና በሃዋሳ የተለያዩ ቦታዎች በራሪ ወረቀቶች ሲበተኑ ማደራቸው ታወቀ፡፡
የሚሉትን ዜናዎችና ሙሉ ፕሮግራሞቻችንን በ www.patriotg7.org ላይ መከታተል የምትችሉ መሆኑን በአክብሮት እንገልፃለን፡፡

Wednesday, July 26, 2017

ግፈኛው፣ ሸረኛው፣ ዘራፊውና ገፋፊው የህወሃት/ኢሕአዴግ ሥርዓት በግብር ስም የሚያደረግብንን ዘረፋ በጋራ ለመቃወም ከሀምሌ 23 ቀን እስከ ሀምሌ 25 ቀን 2009 ዓ.ም የሚቆይ የሥራ ማቆም አድማ ጠርተናል። በእነዚህ ቀናት አንዳችም ሽያጭ ሆነ አገልግሎት አይቀርብም።

#ሀገር አቀፍ
Image may contain: 1 person, textImage may contain: 1 person, text

በላባችን ለፍተን፣ ጥረን፣ ግረን የምናድር ለፍቶ አደሮችን ለማደህየት አቅማችን የማይችለውን የግብር ሸክም ተጭኖብናል። በጉልበት ለተጫነብን ገዢ መገበር አንገሽግሾናል !!!
ግፈኛው፣ ሸረኛው፣ ዘራፊውና ገፋፊው የህወሃት/ኢሕአዴግ ሥርዓት በግብር ስም የሚያደረግብንን ዘረፋ በጋራ ለመቃወም ከሀምሌ 23 ቀን እስከ ሀምሌ 25 ቀን 2009 ዓ.ም የሚቆይ የሥራ ማቆም አድማ ጠርተናል። በእነዚህ ቀናት አንዳችም ሽያጭ ሆነ አገልግሎት አይቀርብም።
ህወሃት/ኢህአዴግ በዘፈቀደ የ

የመከላከያ ሰራዊትና ሚናው ክፍል 2 (አርበኞች ግንቦት7)

July 25, 2017
ከዚህ ጋር ተያይዞ ሰራዊቱ የሱማሊያን ህዝብ የጀምላ ጭፍጨፋ በማድረግ፣ሴቶችን አስገድዶ በመድፈርና ኢ-ሰባዊ ድርጊቶችን በመፈጸም ህዝቡ ከአልሸባብ ጎን እንዲሰልፍ መሰረት ጥለዋል። የሱማሊያ ህዝብ ለኢትዮጵያውያን ጥላቻ እንዲኖረው የወያኔ ሹማምንት እየሰሩ ይገኛሉ። የሱማሊያ ህዝብ የመከላከያ ሰራዊቱ ለቆ እንዲወጣ እየተማጸኑ ይገኛል።Bilderesultat for የወያኔ ከፍተኛ የጦር ባለስልጣን
በዚህ በ10 አመት  የሱማሊያ ተልኮ ከ10,000 በላይ ኢትዮጵያዊያን አልቀዋል። ቤተሰቦቻቸው እንኳን በሃገር ወግ ባህል ዋይ ብለው እርማቸውን እዳያወጡ ተደርገዋል። የጦር መሃንዲሶች 10,000 ሰራዊት አልቋል ሲሉ ግምታቸውን አስቀመጡ እንጂ በመንግስት ደረጃ በጦርነቱ ምንያክል ወታደር እንዳለቀ አልተነገረም። በህወሃት ጄነራሎች የሚመራው 43ኛ እና 44ኛ ክ/ጦር ሙሉ በሙሉ ተደምስሶ ሰራዊቱ እንደቅጠል መርገፉ ይታወቃል። ይህን ጦርነት ሲመሩ የነበሩ አዛዦች ማንም ሳይጠየቅ፣ በስልጣን ላይ ስልጣን እየጨመሩ ዛሬ ከፍተኛ የወታደራዊ የአዛዥነት ማማ ላይ ሊቀመጡ ችለዋል። ከዚህ ውስጥ ከሚጠቀሱት አንዱ የ43ኛ ክ/ጦር አዛዥ የሆነውና አሁን በመከላከያ የወታደራዊ መረጃ ዋና መምሪያ ሃላፊ የሆነው ሜ/ጄነራል ገብሬ አድሃነ ይገኝበታል።
ዛሬም የኢትዮጵያ እናቶች ልጆቻችን ይመጡ ይሆን እያሉ  በር በሩን እያዩ በተስፋ እየጠብቁ ይገኝእሉ።ግን ልጆቻቸው በሶ

ፕ/ር ብርሃኑ ነጋ ዛሬ ከሰጡት መግለጫ የተቀነጨበ: -



“የሕዝብ አመጽ በተደራጀ መንገድ እንዲካሄድና ለትግሉም የሚያስፈልገውን አቅርቦት በማዘጋጀት በኩል ለአመጽ ከተደራጀነው ኃይሎች የሚጠበቀውን ሁሉ እንደምናደርግና እያደረግንም እንደሆነ እንዲታወቅ እንፈልጋለን። የዚህ ዓይነቱ እንቅስቃሴ በሰሜኑ የሀገራችን ክፍል ብቻ ሳይሆን በሁሉም የሀገራችን ክፍሎች እንዲስፋፋ ለማድረግ እየሠራንበት ያለው አብይ ሥራችን ነው። በዚህ መስክ የሚደረገው እንቅስቃሴ ዝግጅቱን በቶሎ አጠናቆ ሊደበቅ በማይችልበት ሁኔታ በግልጽ የሚወጣበት ግዜ ሩቅ እንዳልሆነ አረጋግጥላችኋለሁ። ይህ እንቅስቃሴ ብዙ ሕይወት ሳያስገብር ከዳር እንዲደርስ በወያኔ ስር ተጠርንፎ የሚገኘው የኢትዮጵያ ወታደር አሁንም በትንሽ በትንሹ እንደጀመረው በሰፊው ተንቀሳቅሶ ከሥርዓቱ ጋር ሳይሆን ከሕዝቡ ጎን እንዲቆም የምናደርገው ጥረትም ተጠናክሮ ይቀጥላል።”Image may contain: 1 person, closeup

Friday, July 21, 2017

አርበኛ ታጋይ ብርሃኑ ጀግኔ July 21, 2017

በዚህ በዛሬው የአርበኞች ማስታወሻ መርሃ ግብራችን ውስጥ አንድ ጀግና አርበኛን እናስተዋውቃችኋለን።Image may contain: 1 person, outdoor
በ3 ሺህ ዘመን ታሪኳ ውስጥ ማህጸኗ መቼም ቢሆን የቁርጥ ቀን ልጆች ከመጸነስ፣ ከመሸከምና ከመውለድ አቋርጣ የማታውቀው እናታችን ኢትዮጲያ ዛሬም እንዲሁ ጀግና ወልዳልናለች። ይህ ጀግና አርበኛ የተፈጠረበትን፣የመጣበትን ዋና ተልዕኮ ፈጽሞ፣ ሩጭውንም ጨርሶ ወደማይቀረው አለም በክብርና በነጻነት ሄዷል።

የአርበኞች ግንቦት 7 ድምፅ ሬዲዮ


የነጋዴዎች አድማ መላ አገሪቱን እየሸፈነ ነው
በምስራቅ ሃረርጌ የተጀመረው የነጋዴዎች አድማ በአምቦ፣ ወሊሶ፣ ደምቢዶሎ፣ ነቀምት፣ ሆለታ፣ ጊንጪ፣ ሱሉልታ፣ ሻሸመኔ፣ ዶዶላ ተጠናክሮ ሲካሄድ ከሰነበተ በኋላ፣ ወደ መዲናዋ አዲስ አበባ በመሸጋገር በሳሪስ፣ ከኮልፌ አጠና ተራ፣ ታይዋን ሰፈር፣ ዘነበወርቅ፣ አዲስ ጎማ አቦ ወርቁ ሰፈር ፣ ንፋስ ስልክና ሌሎችም ቦታዎች የንግድ ድርጅቶች እየተዘጉ ተቃውሞው በመካሄድ ላይ ነው ነው። ዛሬ ሃምሌ 14 ቀን 2009 ዓም ደግሞ አድማው አባይን ተሻግሮ በምስራቅ ጎጃሟ ሸበል በረንታ ወረዳ የዱሃ ከተማ ተጠናክሮ በመካሄድ ላይ ሲሆን፣ የዱሃ የአድማውን ችቦ በመለኮስ የመጀመሪያዋ የአማራ ክልል ከተማ ሆናለች ። 
በአዲስ አበባ የአገዛዙ ካድሬዎች ለነጋዴዎች የተለያዩ ተስፋዎችን በመስጠት አድማው እንዲቀር ለማግባባት ከፍተኛ የቅስቀሳ ስራ ሲሰሩ ታይተዋል። አንዳንድ ቦታዎች ላይ ማስፈራሪያዎች የደረሱዋቸው ነጋዴዎች ድርጅቶቻቸውን ቢከፍቱም አብዛኛው ነጋዴዎች ግን የንግድ ድርጅቶቻቸውን እንደዘጉ ናቸው። አድማውን በተጠናከ ሁኔታ ለማካሄድ ወረቀቶች እየተበተኑ ሲሆን፣ በተለይም በአዲስ አበባ አዋሳኝ ከተሞች በሱሉልታ፣ ጫንጮ፣ ሙከጡሪ፣ ፊቼ፣ ገብረጉራቻ ፣ ቡራዩ እንዲሁም ጅማ አርጆ ወረዳ አድማውን በተጠናከረ ሁኔታ ለማስኬድ እንቅስቃሴዎችን ጀምረዋል። 
በሸበል በረንታዋ የድውሀ ከተማ ምንም አይነት እንቅስቃሴ የማይታይ ሲሆን፣ ህዝቡ አሁን የተጣለው ግብር ተቀንሶ እስካልመጣ ድረስ ድርጅታችንን አንከፍትም በማለት በአንድነት ተማምሏል። 
የወረዳው ባለስልጣናት ህዝቡን ለማነጋገር ስብሰባ ቢጠሩም ፣ ነጋዴዎች “ እስካሁን ታገስናችሁ ከአሁን በሁዋላ ግን ትግስታችን አልቋል፣ ጉሮሮ ለጉሮሮ እንተናነቃለን እንጅ እናንተ በወር 10ሺ ና ከዛ በላይ እየበላችሁ እኛ ፈትሃዊ ያልሆነ ግብር አንከፍልም” በማለት አዳራሹን ለቀው ሲወጡ አዛውንቶች ወጣት ነጋዴዎች በመለመን ስብሰበውን እንዲቀጥሉ አድርገዋቸዋል።
ነጋዴዎች ገበያ ውስጥ በመሰብሰብ “ከመካከላችን አንድ ነጋዴ ቢታሰርብን አንድ በመሆን የማያዳግም እርምጃ እንወስዳለን” በማለት ቃለመሃላ ፈጽመዋል በሰሜን ሸዋ በሸሾ፡ሰላድንጋይ፡ዘመሮ፡ሞላሌ፡መሀልሜዳ፡ጓሳ፡ የመሳሰሉት አነስተኛ ከተማዋች ላይ እስከ ሰኞ የሚቆይ የነጋዴዎች አድማ ይደረጋል ተብሎ ይጠበቃል። 

ኢሳት- ሰበር ዜና በአዲስ አበባ በሚገኝው የሰላም ባስ ጋራዥ ላይ ማምሻውን የቦምብ ጥቃት ተፈጸመ።

የአርበኞች ግንቦት 7 ድምፅ ሬዲዮ

ከፍተኛ የግብር ጭማሪን ተከትሎ በአዲስ አበባ ኮልፌ፡ ሳሪስ፡ አዲስ ሰፈር፡ ንፋስ ስልክ፡ አዲስ ጎማ፡ አቦ እና ወርቁ ስፈር አከባቢ የንግዱ ማህበረሰብ ሱቆቹን በመዝጋት የተቃውሞ አድማውን ተቀላቅለዋል። በኦሮሚያ በርካታ አካባቢዎች ዛሬም የተቃውሞ አድማ እንደቀጠለ ነው። በሌላ በኩል በአዲስ አበባ የወያኔ ስርአት ንግድ ቤታቸውን የዘጉ የንግዱ ማህበረሰብን ሱቆቻችሁን ክፈቱ በማለት እያስፈራራ እንደሚገኝም ታውቋል።

(የአርበኞች ግንቦት 7 ድምፅ ሬዲዮ)

የሐምሌ 14 ቀን 2009 ዓ.ም ዜና
* በተለያዩ ከተሞች ከግብር ጋር በተያያዘ የተጀመረው አመጽና አድማ እንደቀጠለ መሁኑ ታወቀ
* በእነ ንግስት ይርጋ ላይ የሚቀርቡት ምስክሮች እንዲታለፉ ብይን ተሰጠ

* የጣናን ሃይቅ በቆሻሻ ፍሳሽ እየበከሉት ያሉት የመንግስት ተቋማትና ሆቴሎች ችግሩን አሁንም እያባባሱት መሆኑን ታወቀ
የሚሉትን ዜናዎችና


የአርበኞች ማስታወሻ በተሰኘው መሰናዷችን ደግሞ የጀግናውን አርበኛ ታጋይ ብርሃኑ ጀግኔ ታሪክ እንዘክራለን
ሙሉ መሰናዶዎቻችንን በ http://www.patriotg7.org/ መከታተል እንደምትችሉ እንገልፃለን፡

Tuesday, July 18, 2017

የአርበኞች ግንቦት 7 ድምፅ ሬዲዮ


* በሰሜን ጎንደር ዞን በሚገኙ ሁለት ከተሞች ላይ አርበኞች ግንቦት 7 የተሳካ ዘመቻ መፈፀሙ ታወቀ
* ከግብር ጋር ተያይዞ ነጋዴዎች የሚያደርጉት ተቃውሞ እንደቀጠለ መሆኑ ታወቀ
* በቆላድባ ከፍተኛ ቁጥር ያላቸው የስርአቱ አገልጋይ ወታደሮች ተሰማርተው ህዝብ ላይ ጥቃት እየፈፀሙ ነው
* በሶማሌ ክልል በዶሎ ዞን ባለፈው ወር ብቻ በርሃብ ምክንያት 68 ሕጻናት መሞታቸውን ድንበር የለሽ የሃኪሞች ቡድን አስታወቀ፡፡
የሚሉትን ዜናዎችና ሙሉ መሰናዷችንን በ www.patriotg7.org መከታተል እንደምትችሉ እንገልፃለን፡

የመከላከያ ሰራዊትና ሚናው (ከአርበኞች ግንቦት 7)

July 18, 2017

ለአንዲት አገር በሁለንተናዊ መልኩ ከሚያስፈልጓት መሰረታዊ ተቋማት መካከል ወሳኙና የአንበሳውን ድርሻ የሚወስደው የጸጥታው አካል ነው። አገሪቱ ዳር ድንበራ ተከብሮ፣ ዜጎቿ ያለስጋት በሰላም ወጥተው እንዲገቡ በማድረግ ደረጃ የጸጥታ አካላት የሚወጡት ሚና እጅግ የላቀ እንደ ሆነ አሌ የማይባል ሃቅ ነው።
Relatert bilde
በዚህ የጸጥታ አካል እየተባለ በሚጠራው ተቋም ዋና ዋና ተብለው ከሚጠቀሱት ውስጥ የመከላከያ ሰራዊት፣ የፖሊስ ሰራዊት እና የመረጃና ደህንነት መስሪያ ቤቶች ይገኙበታል።

Sunday, July 16, 2017

Sweden_Radio_about_ESCFE.mp3

Yehunie Belay - Tana |ጣና - New Ethiopian Music 2017 (Official Video)

የአርበኞች ግንቦት 7 ድምፅ ሬዲዮ


የአርበኞች ግንቦት 7 ሰራዊት በሁለት የሰሜን ጎንደር ከተሞች የተሳካ ዘመቻ አደረገ። 
በሰሜን ጎንደር ዞን ችንፋዝ ስላሬ በተባለ ከተማ እና በበለሳ ጉሃላ ከተማ ከሀምሌ 6 ቀን 2009ዓም እስከ ሀምሌ 8 ለ9 ለሊት 2009ዓ/ም ድረስ በተጠቀሱት ሁለት ከተሞች ላይ በስርአቱ ሹማንቶችና የስርአቱ ቅጥረኛ ወታደሮች ላይ ጥቃት ተሰንዝሯል፡፡ 
በመሆኑም በስላሬ ከተማ በአንድ ቀን ውጊያ የስርዓቱ ወታደሮች እና መዋቅሩ ላይ ጉዳት በማድረስ ከተማውን መቆጣጠር የተቻለ ሲሆን በጉሃላ በግማሽ ቀን ውጊያ ከተማውን መያዝ ተችሏል፡፡ በጉሃላ የአስተዳዳሪው ጽ/ቤት እና የገቢዎች ጽ/ቤት በቦንብ የተመቱ ሲሆን። ለአጭር ጊዜ ከተማዋን የተቆጣጠሩት አርበኛ ታጋዮች በሰላም ወደ መጡበት ተመልሳዋል፡፡ በአሁኑ ስዓት አካባቢው ላይ ከፍተኛ ውጥረት ነግሷል፡፡ ታጣቂዎችም የገዢውን ሃይል በመክዳት ከነፃነት ኃይሎች ጋር በመቀላቀል ላይ ይገኛሉ።

Thursday, July 13, 2017

ልዩ ዜና በኦሮሚያ ክልል አምቦ ከተማ ዛሬ ተቃውሞ ተቀስቅሷል። በመላ ሀገሪቱ የተጣለው የቀን ገቢ ግብር ያስነሳው ተቃውሞ ዛሬ በአምቦ ከፍተኛ ግጭት እንዲቀሰቀስ ማድረጉን የኢሳት ምንጮች ከስፍራው ያደረሱን መረጃ ያመለክታል።

አሁን የደረሰን ዜና-ኢሳት

በአዳማ(ናዝሬት) ተቃውሞ ተቀስቅሷል። ከግብር ጋር በተያይዘ የነጋዴው ማህበረሰብና ህብረተሰቡ የሚያሰማው ቅሬታ ወደ ተቃውሞ ተቀይሮ ቁጣ መነሳቱን የደረሰን መረጃ ያመለክታል። በቱሉ ቦሎም ተመሳሳይ ተቃውሞ መቀስቀሱን ለማወቅ ተችሏል።

Patriotic Ginbot 7 'Adera Band' New Afaan Oromo Song (Hinkaature - Adera)

የአርበኞች ግንቦት 7 ድምፅ ሬዲዮ


የአምቦ ከተማ ተቃውሞ እንደቀጠለ ነው፡፡
ለተቃውሞው ምክንያት የሆነው በቅርቡ ተገቢ ያልሆነ ግብር ነጋዴው ላይ መጨመሩ ሲሆን። ስርአቱ የህዝቡን ጥያቄ በሰላማዊ መንገድ ከመመለስ ይልቅ ሃይልን መፍትሄ አድርጎ መንቀሳቀሱ በተፈጠረው ግጭት አንድ የፌደራል ፓትሮል መኪና ሲቃጠል ሌላ ተሰባብሯል፡፡ እንዲሁም አንድ አውቶብስ ላይ የመሰባበር አደጋ ደርሶበታል፡፡ ከፍተኛ ተኩስ እንዳለና ወደ ወለጋ የሚወስደው መንገድም እስካሁን እንዳልተከፈተ ለማወቅ ተችሏል፡፡ በከተማው ያሉ አገልግሎት የሚሰጡ ተቋማት ሙሉ በሙሉ ተዘግተዋል። ከፍተኛ የግብር ጭማሪን ተከትሎ በሌሎች አካባቢዎች የተቃውሞ እንቅስቃሴ ሊኖር እንደሚችል አስተያየት ሰጪዎች ይናገራሉ

የአርበኞች ግንቦት 7 ድምፅ ሬዲዮ


- በተለያዩ ከተሞች ፀረ መንግስት የሆኑ በራሪ ወረቀቶች መበተናቸው ተገለጸ 
የአግ7 ድምፅ ስርጭት ዘወትር ማክሰኞ ፡ ሓሙስ፡ አርብና እሁድ ይከታተሉ
የዕለተ ሓሙስ ሐምሌ - 06 - ቀን ፡ 2009 ዓ/ም የሬድዮ ስርጭት

ሰበር ዜና

#ESAT
ከግብር ጋር በተያያዘ በአምቦ የተጀመረው ተቃውሞ ቀጥሎአል። የፌደራል ፖሊስ መኪና ተቃጥሎአል፣ በርካታ መኪኖችም ተሰባብረዋል።

Monday, July 10, 2017

የምታገለው አርበኞች ግንቦት 7 ለቆመለት ዓላማ ነው ።


ኢትዮጵያ ውስጥ እውነተኛ የሆነ የስርዓተ ለውጥ እንዲመጣ እስከመጨረሻው ድረስ እታገላለሁ ። ይህንንም ስል እንደከዚህ ቀደሞቹ አንድን ስርዓት በሌላ ሃይል ለመተካት ሳይሆን ። ኢትዮጵያ ውስጥ እውነተኛ የሆነ የዲሞክራሲ ተቋም እንዲፈጠር ነው ። ይህንንም ለማሳካት የሚቻለው ደግሞ ከአሁኑ ጀምሮ እንጂ ከነገ ጀምሮ ወይም ደግሞ ከነፃነት በኋላ ሊሆን አይገባም ።
ብዙውን ጊዜ ሁላችንም የምናተኩረው ጠላታችንን እንዴት ታግለን እንደምንጥለው እንጂ ጠላታችንን ታግለነው ከጣልነው በኋላ በምን አይነት ሁኔታ እንደምንቀይረው አናስብም ። ለዚህም ነው አሁን በበረሃ ያሉት የነፃነት ሃይሎች ኢትዮጵያ ውስጥ መሰረታዊ የሆነ ለውጥ እንዲመጣ የሚታገሉት ። ለዚህም ማስረጃ እንዲሆነኝ የድርጅቱ ሊቀመንበር የሆኑት አርበኛ ፕሮፌሰር ብርሃኑ ነጋ ስለዚህ ጉዳይ ሲናገሩ ኢትዮጵያ ውስጥ ወያኔን መጣል ቀላል ነው ነገር ግን ከወያኔ ስርዓት በኋላ ሊመጣ የሚችለውን ነገር መስራቱ ነው ከባዱ ብለው ነበር ። ይህንንም ለማድረግ በአሁኑ ሰዓት ተግተው እየሰሩና በዚህም ሁኔታ ብዙ ሁኔታዎች እየተስተካከለ እያየን የመጣንበት ወቅት ላይ ደርሰናል ።
ለዚህም ነው ታዲያ እኔም የለውጡ አካልና የትግሉ ባለቤት ነኝ ብዬ የማስብ ከሆነ ከአሁኑ ጀምሬ ኢትዮጵያ ውስጥ ስር ነቀል የሆነ የስርዓት ለውጥ እንዲመጣ መታገልና ስር ነቀል ለውጡ የሚፈልገውን እውነተኛውን ስርዓት ለመተካት እንደታጋዮቹ ከወዲሁ አባጣና ጎርባጣ የሆነውን የዲሞክራሲ ስርዓት እንቅፋት የሆኑትን አሰራሮች በማስተካከልና ለህዝቢም እውነተኛ የሆነውን የዲሞክራሲ መንገድ በማሳየት ብሎም እንዲሳተፍና እርሱም የትግሉ አካል ሆኖ ወደ ትግሉ እንዲቀላቀል በማድረግ የበኩሌን ድርሻ በመወጣት ትግሉ የመላው ኢትዮጵያዊ ትግል እንዲሆን መስራት ይጠበቅብኛል ።
ይህንንም ሳደርግ ታዲያ ከአሁኑ ጀምሮ ለዲሞክራሲ ስርዓት እንቅፋት የሆኑትን ነገሮች ፊትለፊት በመጋፈጥ በቁርጠኝነት ልዋጋው ያስፈልገኛል ይህንንም መንፈስ ደግሞ ቀሪውም ወገኔ እንዲያምንበት እራሴ ታማኝ ሆኜ መቅረብ ብቻ ሳይሆን እርሱም እንዴት ሆኖ መዋጋት እንዳለበትና በፅናት እንዲቆም እራሴ በፅናት ቆሜ ላሳየው ይገባኛል ። ይህንን የማደርግ ከሆነ ከታጋይ ወገኖቼ ጎን መቆሜን አስመሰክራለሁ ይህንን የማላደርግ ከሆነ ደግሞ ኢትዮጵያን እንደምጎዳት አምናለሁ ።
በአጠቃላይ የለውጥ አካል ለመሆን ከፈለግን እኛ ብቻ ሳንሆን መላውን ኢትዮጵያዊ አስተባብረን ልንሰራና እውነተኛ የሆነው የዲሞክራሲ ስርዓት እንዲፈጠር በንቃት ልንታገል ግድ ይለናል ።
እግዚአብሔር ለሁሉም ነገር መሳካት ይርዳን ።
ኢትዮጵያ በክብር ለዘላለም ትኑር !!!!!
@ዘነበ ዘ ቂርቆስ

አርበኝነት - July 10, 2017

አርበኝነት ማለት ለወገኑ የተሻለ ህይወት ጊዜዉን ጉልበቱን እዉቀቱን ገንዘቡን ክቡር ህይወቱን መስዋትነት ለመክፈል የተዘጋጀ ሰዉ ወይም የህብረተስብ ክፍል ማለት ነዉ።Bilderesultat for ginbot 7
ከዚህም በመነሳት ዛሬ ላይ እየተካሄደ ባልዉ የአርበኝነት ትግል አላማችን እንዲሳካ እራአያችን እንድያብብ የምንሻ ሁሉ የግድ ያለዉን ነባራዊ ሁኔታ ማጤንና መገንዘብ ያስፈልጋል።  የአርበኝነት አላማ ደግሞ ዉጤታማ የሚሆነዉ በእቅድ የሚመራ በተግባር የሚታይና በድርጊት የሚገለጽ  የጥርት ዉጤት ሲሆን ነዉ።

Sunday, July 9, 2017

የሰማያዊ ፓርቲ ብሔራዊ ሸንጎ በቅርቡ አዲስ አበባ ከተማን በተመለከተ በሚኒስትሮች ምክር ቤት የተዘጋጀው ረቂቅ አዋጅ በህዝብ ላይ እንዳይጫን ተከታታይ ስራ እንደሚሰራ አስታወቀ


(በሰማያዊ ብሔራዊ ሸንጎ የህዝብ ግንኙነት ንዑስ ኮሚቴ)
የሰማያዊ ፓርቲ ብሔራዊ ሸንጎ ዛሬ ሀምሌ 02 ቀን 2009 ዓ.ም ባደረገው ስብሰባ በወቅታዊ ሀገራዊ ጉዳዮች ላይ ውይይት ያደረገ ሲሆን በተለይም አገዛዙ በቅርቡ ባዘጋጀው ረቂቅ አዋጅ ላይ ሸንጎው ያለውን አቋም ግልፅ ማድረጉን ተከትሎ ጉዳዩ መነጋገሪያ አጀንዳ መሆኑ እንደተጠበቀ ሁኖ ህወሃት/ኢህአዴግ አሁን ባለበት ተክለ ቁመና በስልጣን ላይ የመቆየት እድሉ ከጊዜ ወደ ጊዜ እየተመናመነ በመምጣቱ በህዝብ ላይ ጥርጣሬንና አለመተማመንን ለመፍጠር ሲል አዋጁን ለማፅደቅ እንደሚፈልግ ስለሚታመን ይህንን ለሀገር ህልውና አደጋ የሆነ አዋጅ ከመፅደቁ በፊት መላው የለውጥ ፈላጊ ኃይሎች በተለይም የገፈቱ ቀማሽ የሆነው የአዲስ አበባ ህዝብ የዜግነት መብቱን በመጠቀም ይህ አዋጅ እንዳይጫንበት በተደራጀ መልኩ ትግሉን አጠናክሮ እንዲቀጥል የበኩላችንን መወጣት ይገባናል በማለት ሸንጎው አቋሙን ገልጧል፡፡በተጨማሪም የስርዓቱ መዳከም በሙስና ላይ የቆመውን የተንዛዛ ቢሮክራሲ እና የስርዓቱ ጠባቂ የሆነውን የደህንነት ሃይል ወጪ ለመሸፈን የሚያስፈልገው ገንዘብ ከጊዜ ወደ ጊዜ እያደገ ስለሚሄድ ወጭውን ለመሸፈን መሬት መሸጥ የግድ ስለሚሆንበት ይህንን አዋጅ ሊያፀድቀው እንደሚችል ይታመናል፡፡ስለሆነም ይህንን አዋጅ መቃዎም የስርዓቱን እድሜ ማሳጠር መሆኑን ተገንዝቦ ሁሉም የለውጥ ሃይል ተከታታይ ትግል ማድረግ እንዳለበት በማሳሰብ የዕለቱን ውይይት አጠናቋል፡፡

የአርበኞች ግንቦት 7 ድምጽ ሬድዮ ወደ ኢትዮጵያ የሚያስተላልፈው የአጭርና የመካከለኛ ሞገድ የሳተላይት ስርጭት የቀን እና የሰዓት ለውጥ ለውጥ ስላደረገ እናንተም እንድታስተካክሉ እናሳስባለን፡፡

ማክሰኞ    ጠዋት ከ12፡00-12፡30     ምሽት ከ12፡30-1፡00
ሀሙስ     ጠዋት ከ12፡00-12፡30     ምሽት ከ12፡00-12፡30
አርብ      ጠዋት ከ12፡00-12፡30     ምሽት ከ12፡00-12፡30
እሁድ     ጠዋት ከ12፡30-1፡00       ምሽት ከ12፡00-12፡30
ወደ ኢትዮጵያ የሚያስተላልፈው የሥርጭት ሞገድ
👉 መካከለኛ ሞገድ (Medium Wave)
በ358 ሜትር ባንድ በ837 ኪሎኸርዝ
👉አጭር ሞገድ (Short Wave)
በ31 ሜትር ባንድ በ9700 ኪሎኸርዝ
በ41 ሜትር ባንድ በ7160 እና በ7120 ኪሎኸርዞች
በ49 ሜትር ባንድ በ5980 እና በ6026 ኪሎኸርዞች

👉ሳተላይት ሬድዮ (Satellite Radio) በArabSat Satellite 11980 ፍሪኩዌንሲ
የአርበኞች ግንቦት 7 ህዝብ ግንኙነት