Monday, July 10, 2017

አርበኝነት - July 10, 2017

አርበኝነት ማለት ለወገኑ የተሻለ ህይወት ጊዜዉን ጉልበቱን እዉቀቱን ገንዘቡን ክቡር ህይወቱን መስዋትነት ለመክፈል የተዘጋጀ ሰዉ ወይም የህብረተስብ ክፍል ማለት ነዉ።Bilderesultat for ginbot 7
ከዚህም በመነሳት ዛሬ ላይ እየተካሄደ ባልዉ የአርበኝነት ትግል አላማችን እንዲሳካ እራአያችን እንድያብብ የምንሻ ሁሉ የግድ ያለዉን ነባራዊ ሁኔታ ማጤንና መገንዘብ ያስፈልጋል።  የአርበኝነት አላማ ደግሞ ዉጤታማ የሚሆነዉ በእቅድ የሚመራ በተግባር የሚታይና በድርጊት የሚገለጽ  የጥርት ዉጤት ሲሆን ነዉ።

በመሆኑም ድሮ አርበኛ አባቶቻችን በአዋጅ ተሰባስበዉ በራሶችና በደጃዝማቾች የጦር አጋፋሬዎች እየተመሩ ለሃገራቸዉ በነበራችዉ ጥልቅ የሃገራዊ የፍቅር ስሜት አርበኝነትን ተላብስዉ በባዶ እግራቸዉ ወንዝና ሽነተረሩን አቋርጠዉ ዳገት ቁልቁልቱን ወጥተዉ ወርደዉ ከጦርነቱ አዉድማ ሲደርሱ ነጋሪት እየተጎሰመ እንቢልታዉ እየተንፋ ንጉስ ከፈረስ ሳይወርዱ በጦርነተ መሃል ዉስጥ ሆነዉ አዋጅ እያስነገሩ የፊዉታራሬ ጦር ግባ ተብለሃል፥ የቀኝ አዝማች ጦር ግባ ተብለሃል፥የግራዝማች ጦር ግባ ተብለሃል በሚል የአዉደ ዉጊያ የእዝ ሰንሰለት ጊዜዉ በፈቀደዉ የጦርነት ስልት ነበር  በጦር በጎራዴ ተዋግተዉ ደማቸዉን አፍሰዉ ሃገራችን ኢትዮጵያን ከወራሪ  ቅኝ ገዥዎች ያዳኗት።
ዛሬ ላይ ደግሞ ሃገር በቀል ወራሬ የወያኔን ቡድን ለማስወገድ የአርበኞች ግንቦት 7 አርበኛ ታጋዮች በሁለገብ የትግል ስልት ከገጠር እስከ ከተማ ሁሉንም የሃገራችነን ክፍል ባከለለ የህዝባዊ እንቢተኝነትና የህዝባዊ አመጽ እንዲጎለብት በማድረግ በቁርጠኝነት በምታገል ላይ ናቸዉ።
እንድሁም አርበኛ ታጋዮቻችን ከነጻነት ሃይሎችና ከህዝቡ ጋር በመሆን የሽምቅ ዉጊያ በማካሄድ ትግሉ ወደ ላቀ ደረጃ እንድሸጋገር ከፍተኛ ተጋድሎ በማድረግ ላይ ይገኛሉ።
ስለሆነም የአርበኞች ግንቦት 7 አርበኛ ታጋዮች እንዳ አባቶቻችን የአርበኝነትን  መንፈስ ተላብሰዉ መስዋእትነት በመክፈል ደማችዉን አፍሰዋል።
በአሁኑ ስአትም ደም ገብረዉ ሃገራችንን ከጥፋት ለመታደግ የቆረጡ የህዝብ ልጆች ከአገዛዙ ታጣቂ ሃይሎች ጋር እየተፋለሙ ናቸዉ።
በሌላ በኩል ግን ወያኔን ለማስወገድ ራሱ ወያኔ በመጣበት የትግል ስልት እና ኢህአፓና ኢድዩ የትጓዙበትን የትግል መንገድ የተከተለ አይደለም ምክኔያቱም ዘመኑ ያለፈበት የትግል መንገድ በመሆኑ።
ወይም እንዳባቶቻችን የደጃዝማች ጦር በቀኝ በኩል ግባ ተብለሃል የፊዉታራሪ ጦር በግራ በኩል ግባ ተብለሃል በሚል በአዋጅ የሚደረግ ጦርነት አይደለም ዘመኑ የቴክኖሎጅ ዘመን ነዉ።ስለዚህ አሁን ያለዉ የአርበኝነት ትግል የወቅቱን ነባራዊ ሁኔታን ባገገናዘበ በስልትና ሚስጥር በመጠበቅ የሚደረግ የአርበኝነት ትግል ነዉ ።
ይህን ተከትሎ በትጨባጭ የአርበኞች ግንቦት 7 አርበኛ ታጋዮች በመፈቃቀድ ላይ የተመሰረተ አንድነትን ለማምጣትና ዴሞክራሲን ለማስፈን ለሃገራችን ኢትዮጽያ በጎ ራእይን በመሰነቅ  የወያኔን አገዛዝ ለማስወገድ በሁሉም መስክ ትግሉን እያቀጣጠሉ ይገኛሉ።
ነገር ግን አንዳድ ወገኖች ከራሳቸዉ የግል ጥቅም በመነሳት እና አሁን ያለዉን ነባራዊ ሁኔታ በጥልቀት ባለመረዳት እንድሁም በግንዛቤ እጥረት አራንባና ቆቦ በሆነ አስተሳሰብበ በአዉሮፓና  በአሜሪካ  ካለ የፕረስ ነጻነት ጋር በማመሳሰል እቅዳችን ይሕ ነዉ፥አሁን እንደዚህ እየሰራን ነዉ ፥ወደፊት እንደዚያ ልናደርግ ነዉ የሚል ሪፖርት ወይም ጋዜጣዊ መግለጫ እንድሰጥ የሚፈልጉ የመኖራቸዉን ያክል፥ በሌላ በኩል ደግሞ የሽምቅ ዉጊያ ሚስጥራዊነቱ ተጠብቆ የሚከናወን በመሆኑ አንዳድ ብሄር ተኮር ፖለቲከኞች ለራሳቸዉ የፖለቲካ ስካራ ለግባትነት ለመጠቀም በማሰብ ሆን ብለዉ በተግባር እየተከናወነ ያለዉን ስራ ትቢያ እያለበሱ  ምንም ስራ እንዳልተሰራ በደካማ ጎን በመፈረጅ የወሬ ቋታቸዉን ሲያራግቡ ይስተዋላሉ።
በጥቅሉ  እነዚህ ግለሰቦች አብሮ ከመታገልና የስናፍጭ ቅንጣት ታክል ለትግሉ አስተዋጽኦ ከማድረግ ይልቅ ችግሮችን እየፈለጉ በስራ ላይ የሚከሰቱትን ጥቃቅን ስህተቶችን ነቅሶ በማወጣት የሚያናፍሱት ወሪ የአርበኝነት ትግሉን ወደኋላ   የሚጎትት እና የወያኔን የአገዛዝ እድሜ ሊያራዝም በሚያስችል በተሳሳተ መንገድ እየተጓዙ መሆናቸዉ ግልጽ ሆኖ እየታየ ነዉ።
ሃግርን ለምዳን በሚደረገዉ የሞት ሽረት ትግል ዉስጥ ሚና በሌለዉ ለግል ጥቅም አንጋጦ በወሬ ብቻ እራስን ከፍ አድርጎ እንደ ታጋይ በመቁጠር የሚመጣ ለዉጥ የለም ከገደል ማሚቶነት ማስተጋባት የዘለለ ሊሆን የሚችል አይደለም ።
በአንጻሩ ግን ለፖለቲካ ግባትነት ያገለግላል ከሚል መነሻነት አማራ ኦሮሞ በማለት ልዩነትን በማስፋት ትርፍን አስቦ የግል ፍላጎትን ለማሟላት የሚደርግ ሩጫ የወያኔን እድሜ ከማራዘሙም በላይ በህብረተሰቡ መካከል ቅራኒን አስፍቶ ዘመን የማይሽረዉን ጠባሳ ይተክላል ።ስለሆነም በህዝብ ደም ለመነገድ ማሰቡ ሊቆም ይገባዋል።
የዚህ አይነት አመለካከት ያላቸዉ ግለሰቦች ሊያዉቁት የሚገባዉ መሬት ላይ ያለዉ እዉነታ በርበኞች ግንቦት7 ድርጅት ጥላ ስር የትሰባሰቡ በሃገር ዉስጥም በዉጭም ያሉ አርበኛ ታጋዮች በእንቅስቃሴአቸዉ በተግባር እያከናወኑት ያለዉ የአርበኝነት ትግል አንዱን አገዛዝ አስወግዶ ሌላዉን አገዛዝ ለመተካት አይደለም  ምክኒያቱም በትግሉ ሂደት ዉስጥ ሁሉንም እይነት ፈተና በመቀበልና መስዋእትነት እየተከፈለ ያለዉ ሃግራችን ኢትዮጽያ ከገባችበት የአሮንቃ ማጥ ዉስጥ ለማዉጣት ሲባል ብቻና ብቻ ነዉ።
ስለሆነም ክቡር ህይወትን ከመገበር በላይ ሌላ ምስክርነት የሚስፈልገዉ አይደለም ።
ይልቁንም እንደኔ እምነት የሚሻለዉ መንገድ ሁላችንም ግለሰባዊ ጥቅምን ወደ ጎን በመተዉ እንደ ሃገር በጅምላ የደረሰብንን መከራና ስቃይ ዋየታና እሮሮ ለማስቆም በአንድነት ላይ ቁመን በጋራ ተባብረን በአርበኝነት በመታገል ወራሪ የህዉሃትን ቡድን ለማስወገድ ቅድሚያ ልንሰጠዉ የሚገባ ተግባር ሊሆን ይገባዋል።

No comments:

Post a Comment