Friday, July 21, 2017

የአርበኞች ግንቦት 7 ድምፅ ሬዲዮ


የነጋዴዎች አድማ መላ አገሪቱን እየሸፈነ ነው
በምስራቅ ሃረርጌ የተጀመረው የነጋዴዎች አድማ በአምቦ፣ ወሊሶ፣ ደምቢዶሎ፣ ነቀምት፣ ሆለታ፣ ጊንጪ፣ ሱሉልታ፣ ሻሸመኔ፣ ዶዶላ ተጠናክሮ ሲካሄድ ከሰነበተ በኋላ፣ ወደ መዲናዋ አዲስ አበባ በመሸጋገር በሳሪስ፣ ከኮልፌ አጠና ተራ፣ ታይዋን ሰፈር፣ ዘነበወርቅ፣ አዲስ ጎማ አቦ ወርቁ ሰፈር ፣ ንፋስ ስልክና ሌሎችም ቦታዎች የንግድ ድርጅቶች እየተዘጉ ተቃውሞው በመካሄድ ላይ ነው ነው። ዛሬ ሃምሌ 14 ቀን 2009 ዓም ደግሞ አድማው አባይን ተሻግሮ በምስራቅ ጎጃሟ ሸበል በረንታ ወረዳ የዱሃ ከተማ ተጠናክሮ በመካሄድ ላይ ሲሆን፣ የዱሃ የአድማውን ችቦ በመለኮስ የመጀመሪያዋ የአማራ ክልል ከተማ ሆናለች ። 
በአዲስ አበባ የአገዛዙ ካድሬዎች ለነጋዴዎች የተለያዩ ተስፋዎችን በመስጠት አድማው እንዲቀር ለማግባባት ከፍተኛ የቅስቀሳ ስራ ሲሰሩ ታይተዋል። አንዳንድ ቦታዎች ላይ ማስፈራሪያዎች የደረሱዋቸው ነጋዴዎች ድርጅቶቻቸውን ቢከፍቱም አብዛኛው ነጋዴዎች ግን የንግድ ድርጅቶቻቸውን እንደዘጉ ናቸው። አድማውን በተጠናከ ሁኔታ ለማካሄድ ወረቀቶች እየተበተኑ ሲሆን፣ በተለይም በአዲስ አበባ አዋሳኝ ከተሞች በሱሉልታ፣ ጫንጮ፣ ሙከጡሪ፣ ፊቼ፣ ገብረጉራቻ ፣ ቡራዩ እንዲሁም ጅማ አርጆ ወረዳ አድማውን በተጠናከረ ሁኔታ ለማስኬድ እንቅስቃሴዎችን ጀምረዋል። 
በሸበል በረንታዋ የድውሀ ከተማ ምንም አይነት እንቅስቃሴ የማይታይ ሲሆን፣ ህዝቡ አሁን የተጣለው ግብር ተቀንሶ እስካልመጣ ድረስ ድርጅታችንን አንከፍትም በማለት በአንድነት ተማምሏል። 
የወረዳው ባለስልጣናት ህዝቡን ለማነጋገር ስብሰባ ቢጠሩም ፣ ነጋዴዎች “ እስካሁን ታገስናችሁ ከአሁን በሁዋላ ግን ትግስታችን አልቋል፣ ጉሮሮ ለጉሮሮ እንተናነቃለን እንጅ እናንተ በወር 10ሺ ና ከዛ በላይ እየበላችሁ እኛ ፈትሃዊ ያልሆነ ግብር አንከፍልም” በማለት አዳራሹን ለቀው ሲወጡ አዛውንቶች ወጣት ነጋዴዎች በመለመን ስብሰበውን እንዲቀጥሉ አድርገዋቸዋል።
ነጋዴዎች ገበያ ውስጥ በመሰብሰብ “ከመካከላችን አንድ ነጋዴ ቢታሰርብን አንድ በመሆን የማያዳግም እርምጃ እንወስዳለን” በማለት ቃለመሃላ ፈጽመዋል በሰሜን ሸዋ በሸሾ፡ሰላድንጋይ፡ዘመሮ፡ሞላሌ፡መሀልሜዳ፡ጓሳ፡ የመሳሰሉት አነስተኛ ከተማዋች ላይ እስከ ሰኞ የሚቆይ የነጋዴዎች አድማ ይደረጋል ተብሎ ይጠበቃል። 
በምዕራብ ጎጃም ዞን የሚትገኘው የአዴት ከተማ ነጋዴዎችም የግብር አወሳሰኑ ከፍተኛ መድልዎ የታየበት እንደሆነ በስብሰባ ላይ ተናግረዋል። 
ነጋዴዎች ፣ ግብር ወሳኝ ኮሚቴዎች በዕውቅና፣በዝምድናና ከነጋዴዎች ጋር በሚያደርጉት የጥቅም ግንኙነት በመነሳት ከፍተኛ ግብር መክፈል ለሚገባቸው ነጋዴዎች ዝቅተኛ ግብር ሲወስኑ፤በተቃራኒው ዝቅተኛ ግብር መክፈል የነበረባቸውን ነጋዴዎች ከፍተኛ ግብር በመወሰን ነጋዴውን ማህበረሰብ እንዲማረር እያደረጉ ነው በማለት ገልጸዋል። አምና የታየውን ህዝባዊ ተቃውሞ ተከትሎ የክልሉ ነዋሪ ህዝብ ለአገዛዙ ግብር የመክፈል ፍላጎት የለውም። የክልሉ ምክር ቤት ሰሞኑን ባካሄደው ስብሰባ ላይም የክልሉ ባለስልጣናት፣ ህዝቡ ግብር ለመክፈል ፍላጎት የለውም፣ ህዝቡን የማሳመን ስራ ካልሰራን ብዙ ነገሮቻችን ይበላሻሉ ብለዋል 
በምስራቅ ጉጂ ዞን ደግሞ ትናንት ሃሙስ የግብሩ መጠን ይፋ ሲሆን ነጋዴዎች ወደ አስተዳደር ጽ/ቤት በመሄድ አቤቱታቸውን አሰምተዋል። መንገድ ዳር ቡና የሚሸጡ ነጋዴዎች እስከ 30 ሺ ብር ክፈሉ መባላቸውን ነዋሪዎች ይናገራሉ። አንድ በረንዳ ላይ ቁጭ ብለው ቡና የሚሸጡ እናት 17 ሺ ብር ግብር እንዲከፍሉ በመጠየቃቸው ራሳቸውን ስተው ወደ ሆስፒታል መወሰዳቸውን ነዋሪዎች ይገልጻሉ

No comments:

Post a Comment