Sunday, July 9, 2017

የሰማያዊ ፓርቲ ብሔራዊ ሸንጎ በቅርቡ አዲስ አበባ ከተማን በተመለከተ በሚኒስትሮች ምክር ቤት የተዘጋጀው ረቂቅ አዋጅ በህዝብ ላይ እንዳይጫን ተከታታይ ስራ እንደሚሰራ አስታወቀ


(በሰማያዊ ብሔራዊ ሸንጎ የህዝብ ግንኙነት ንዑስ ኮሚቴ)
የሰማያዊ ፓርቲ ብሔራዊ ሸንጎ ዛሬ ሀምሌ 02 ቀን 2009 ዓ.ም ባደረገው ስብሰባ በወቅታዊ ሀገራዊ ጉዳዮች ላይ ውይይት ያደረገ ሲሆን በተለይም አገዛዙ በቅርቡ ባዘጋጀው ረቂቅ አዋጅ ላይ ሸንጎው ያለውን አቋም ግልፅ ማድረጉን ተከትሎ ጉዳዩ መነጋገሪያ አጀንዳ መሆኑ እንደተጠበቀ ሁኖ ህወሃት/ኢህአዴግ አሁን ባለበት ተክለ ቁመና በስልጣን ላይ የመቆየት እድሉ ከጊዜ ወደ ጊዜ እየተመናመነ በመምጣቱ በህዝብ ላይ ጥርጣሬንና አለመተማመንን ለመፍጠር ሲል አዋጁን ለማፅደቅ እንደሚፈልግ ስለሚታመን ይህንን ለሀገር ህልውና አደጋ የሆነ አዋጅ ከመፅደቁ በፊት መላው የለውጥ ፈላጊ ኃይሎች በተለይም የገፈቱ ቀማሽ የሆነው የአዲስ አበባ ህዝብ የዜግነት መብቱን በመጠቀም ይህ አዋጅ እንዳይጫንበት በተደራጀ መልኩ ትግሉን አጠናክሮ እንዲቀጥል የበኩላችንን መወጣት ይገባናል በማለት ሸንጎው አቋሙን ገልጧል፡፡በተጨማሪም የስርዓቱ መዳከም በሙስና ላይ የቆመውን የተንዛዛ ቢሮክራሲ እና የስርዓቱ ጠባቂ የሆነውን የደህንነት ሃይል ወጪ ለመሸፈን የሚያስፈልገው ገንዘብ ከጊዜ ወደ ጊዜ እያደገ ስለሚሄድ ወጭውን ለመሸፈን መሬት መሸጥ የግድ ስለሚሆንበት ይህንን አዋጅ ሊያፀድቀው እንደሚችል ይታመናል፡፡ስለሆነም ይህንን አዋጅ መቃዎም የስርዓቱን እድሜ ማሳጠር መሆኑን ተገንዝቦ ሁሉም የለውጥ ሃይል ተከታታይ ትግል ማድረግ እንዳለበት በማሳሰብ የዕለቱን ውይይት አጠናቋል፡፡

No comments:

Post a Comment