Wednesday, July 26, 2017

የመከላከያ ሰራዊትና ሚናው ክፍል 2 (አርበኞች ግንቦት7)

July 25, 2017
ከዚህ ጋር ተያይዞ ሰራዊቱ የሱማሊያን ህዝብ የጀምላ ጭፍጨፋ በማድረግ፣ሴቶችን አስገድዶ በመድፈርና ኢ-ሰባዊ ድርጊቶችን በመፈጸም ህዝቡ ከአልሸባብ ጎን እንዲሰልፍ መሰረት ጥለዋል። የሱማሊያ ህዝብ ለኢትዮጵያውያን ጥላቻ እንዲኖረው የወያኔ ሹማምንት እየሰሩ ይገኛሉ። የሱማሊያ ህዝብ የመከላከያ ሰራዊቱ ለቆ እንዲወጣ እየተማጸኑ ይገኛል።Bilderesultat for የወያኔ ከፍተኛ የጦር ባለስልጣን
በዚህ በ10 አመት  የሱማሊያ ተልኮ ከ10,000 በላይ ኢትዮጵያዊያን አልቀዋል። ቤተሰቦቻቸው እንኳን በሃገር ወግ ባህል ዋይ ብለው እርማቸውን እዳያወጡ ተደርገዋል። የጦር መሃንዲሶች 10,000 ሰራዊት አልቋል ሲሉ ግምታቸውን አስቀመጡ እንጂ በመንግስት ደረጃ በጦርነቱ ምንያክል ወታደር እንዳለቀ አልተነገረም። በህወሃት ጄነራሎች የሚመራው 43ኛ እና 44ኛ ክ/ጦር ሙሉ በሙሉ ተደምስሶ ሰራዊቱ እንደቅጠል መርገፉ ይታወቃል። ይህን ጦርነት ሲመሩ የነበሩ አዛዦች ማንም ሳይጠየቅ፣ በስልጣን ላይ ስልጣን እየጨመሩ ዛሬ ከፍተኛ የወታደራዊ የአዛዥነት ማማ ላይ ሊቀመጡ ችለዋል። ከዚህ ውስጥ ከሚጠቀሱት አንዱ የ43ኛ ክ/ጦር አዛዥ የሆነውና አሁን በመከላከያ የወታደራዊ መረጃ ዋና መምሪያ ሃላፊ የሆነው ሜ/ጄነራል ገብሬ አድሃነ ይገኝበታል።
ዛሬም የኢትዮጵያ እናቶች ልጆቻችን ይመጡ ይሆን እያሉ  በር በሩን እያዩ በተስፋ እየጠብቁ ይገኝእሉ።ግን ልጆቻቸው በሶ
ማሊያ አሽዋ ተድፍነው ቀርተዋል። ሟቹ ጠቅላይ ሚንስተር በፓርላማ ስለ ሱማሊያው ተልኮ እና በተልኮው ሳቢያ ምንያክል ወታደር እንደ እንደሞተ ሲጠየቅ እብሪት በተሞላበት መልስ “እሱን የመግለጽ ግዴታ የለብንም” ሲል ተደምጧል።በእርግጥ ሰውየው ከነበረው ስብእና እና ተከለ-ቁመና አንጻር መልሱ የሚጠበቅ ነበር። ምክኒያቱም በሰው ደም መነገድ ከለመደ፣ በስልጣን ከባለገ አንድ አምባገነን የሚጠበቅ ነውና።
ወደ ሱማሊያ የተማገደው ሰራዊት ከፍተኛ ኪሳራ እንደ ደረሰበት ሁሉም ሰው ያውቃል። እንደ ኢትዮጵያ አቆጣጠር በ1999 ዓ.ም ሰራዊቱ ወደ ሱማሊያ እንደገባ ሰሞን በኪስማዮ፣ በባይዳዋ፣ በሞቃዲሾ፣በጋልካዮና በመሳሰሉት የሱማሊያ ኣካባቢዎች የገባው ሰራዊት እንዳለ አልቋል። በዚህም አስከሬኑ በኦራል ወታደራዊ  መኪና እና በMI-17 የትራንስፖርት ሄሊኮፕተር በየቦታው ታፍሶ በኢትዮጵያ ሱማሌ ዶሎ ላይ በግሪደር ተጭሮ በጀምላ ተቀብሯል። የተረፈውን አሞራ በልቶት፣አውሬ ተጫውቶበት ቀርቷል።
ታዲያ ይህ ሁሉ እልቂት ለምን ለኢትዮጵያ ህዝብ እና ለአለም አቀፉ ማህበረሰብ ተዳፈነ? ጥያቄው ይሄነው። ምክንያቱም የእልቂቱ መጠን  በሃገር ቤት ከተሰማ ከፍተኛ የህዝብ ተቃውሞ ያስነሳል በሚል፣ እንዲሁም አልሻባብን አጠፋነው፣ ደመሰስነው እያሉ የሚዘላብዱትን ፕሮፓጋንዳ ፉርሽ ስለሚያደርግባቸው ነው። ይህን በማድረጋቸው በየበርሃው ያለቀውን ሰራዊት አስታዋሽ እንዳያገኝ አድርጎታል።  መስዋእትነቱ ከንቱ ሆኖ እንዲቀር ተፈርዶበታል። ለእያንዳንዱ መስዋእትነት ለከፈለ የሰራዊት አባል የተባበሩት መንግስታት የሚሰጠውን የመስዋዕትነት ካሳ የሆነውን 150ሺ ዶላር ውጦ ለማስቀርትና ገንዘቡን በራሳቸው የግል አካውን ስላስገቡት እውነቱን ተዳፍኖ እንዲቀር አድርገውታል።
በኢትዮ ኤርትራ ጦርነት ወቅት የህወህት የጫካ አዛዞች ምንም አይነት  የጦር መሃንዲስነት እውቀት እንደ ሌላቸው በተግባር ታይተዋል። በጾረና ግንባር 27 ታንክ በአንድ ሳምንት እንዲወድም አድርገዋል። በዚሁ ግንባር ብቻ ወደ አርባ ሺ ወጣት እንደ ቅጠል እንዲረግፍ ሁኗል። ግንባሩ ሲያዙ የነበሩት መሪ ተብየዎች በህግ መጠይቅ ሲገባቸው ከሹመት ላይ ሹመት፣ ከሃብት ላይ ሃብት ተጨምሮላቸዋል።
በአጠቃላይ በኢትዮ ኤርትራ ጦርነት ካለቀው 92,000 በላይ ወጣት አርባ ሺው  ያለቀው በጾረና ግንባር ነው። የሚያሳዝነው ለዚህ እልቂት ተጠያቂ የሆነ የህወሃት የጦር አዛዦች አንድም የለም።
ዛሬ ህወሃት ሃገሪቱን እየመራ ሳይሆን እያደናበረ ባለበት ዘመን የመከላከያ ተቋሙ እንደተቋም ከመቼውም ጊዜ በባሰ መልኩ የገዛ ወገኑን በመጨፍጨፍ ላይ ተጠምዷል። ከላይ ለማሳየት እንደ ተሞከረው በአጼውም ሆነ በወታደራዊው መንግስት የጦር ሰራዊት ተቋሙ እንደ ተቋም ህዝባዊነቱ  ለጥያቄ ምልክት የሚገባ አይደለም። ግን በሰራዊቱ ውስጥ እውነተኛ የህዝብ ልጆች ነበሩበት። ግደሉ ሲባሉ “ለምን?’’ ብለው የሚጠይቁ አያሌዎች ይገኙበት ነበር። በዚህ አቋማቸው እስከ ህይወት መስዋዕትነት ከፍለዋል። በህዝባዊ ወገንተኝነታቸው ምክንያት የሃገር ቤዛ ለመሆን በቅተዋል። ለዚህ አባባል አስረጂ መሆን ሳያስፈልግ የ“ታህሳሱን∙∙∙” እና የ“ግንቦት ስምንቱን” የመፈንቅለ መንግስት ሙከራ መጥቀስ ብቻ ይበቃል።
ከህወሃት በፊት በነበሩት መንግስታት ስር የነበረው የጦር ሰራዊት ተቋም ዘረኛ በሆነ አሰራር ፈጽሞ አይታማም። በተቋሙ ውስጥ ከአራቱም የአገሪቱ ማእዘናት የመጡ የጦር ሰራዊት አባላት እስከ ከፍተኛ ወታደራዊ ማእረግ የደረሱ፤ ብቃት ያላቸው ወታደራዊ መኮንኖች ነበሩበት። የመከላከያ ሰራዊቱ አወቃቀር እንደ ዛሬው ጎሳ ተኮር ሳይሆን ሃገር በቀል ነበር። የትናቶቹ ወታደራዊ አዛዦች ለስልጣንም ሆነ ለማእረግ የሚበቁት እንደ ዛሬዎቹ በጥርስ ቆጠራ ወይም ሃረግ መዘዛ ላይ ተመርኩዞ አሊያም አጎብድዶ ወይም ጫማ ልሶ አይደለም። ዋናው መስፈርቱ ዲሲፒሊን፣ እወቀት፣ ሃገር ወዳድነት፣ ብቃት፣ ወታደራዊ ጀብዱ በመስራት ላይ የተመሰረት ነበር። በየትኛውም የሙያ ዘርፍ እውቀት ያለው፣ በራሱ የሚተማመን አገሩንና ህዝቡን የሚወድ ሰው በአብዛኛው የህሊና ሰላም ከሚነሱ ስራዎች ይርቃል። በራስ የመተማመኑ መጠንም እንደ አለሎ የጠጠረ ነው። አገር ስትጎዳና ህዝብ ሲበደል አብሮ ከመጨቆን ወይንም “ጆሮ ዳባ ልበስ” ከማለት ይልቅ ለምን? የሚል ጥያቄ ያነሳል። በሚያነሳቸውም ጥያቄዎች ሳቢያ ሊያስከትሉበት የሚችሉትን መዘዞች በሙላ ቀድሞ ያውቃቸዋል። ቢሆንም ግን ህሊናን ሽጦ የቁም በድን ሆኖ ከመኖር  ለህዝብና ለሚያምንበት አላማ መስዋዕትነት ይከፍላል።
ዛሬ ባለው የመከላከያ ሰራዊት ውስጥ ያሉ አዛዦች ግን ከላይ የጠቅስናቸው ወታደራዊ ስነ-ምግባሮች ጨርሶውኑ አልደረሱባቸውም። የህወሃት-መራሹ የጦር መኮንን ተብዬዎች ምንም አይነት መሰረታዊ የውትድርና ሳይንስ እውቀት የሌላቸው ከመሆኑም በላይ በአንዴ ከጫካ ተንስተው እስከ ጀነራልነት የደረሱ ከአንድ ብሄር ተጠራርተው የወጡ መንደርተኞች እና በእብሪት ያበጡ  የእውቀት ድኩማን ናቸው። በዚህም ምክንያት ነው መከላከያ ሰራዊቱ ህዝባዊነት እንዳይኖረው የሆነው። እነኝህ ጫካዊ የልሙጥ እሳቤ ባለቤቶች ሰራዊቱን ከህዝብ በመነጠል ለእነሱ የታሰረ ውሻ አድርገውታል። ተኛ ሲባል ጅራቱን ቆልምሞ ለሽ የሚል፣ ያዝ ሲባል ደግሞ አባሮ የሚዘነጥል ሁኗል። ህዝቡን የሚጨርስ፣የሚያስለቅስ ተደርጓል።
እነኝህ ሽርፍራፊ እንኳን የሃገር ፍቅር ስሜት ያልፈጠረበቸው የእውቀት ድኩማኖች የሃገሪቱን አንጡራ ሃብት በመዝረፍ ላይ ይገኛሉ። በዚህም የተነሳ የመከላከያ ሰራዊቱ እና የደህንነት መስሪያ ቤቱ አጠቃላይ በጀት ኦዲት እንዳይደረግ በፓርላማ ሳይቀር አሳውጀዋል። በእርግጥ ፓርላማው የራሳቸው ተቀጥያ እንደሆነ ይታወቃል። በመሆኑም በሚዘርፉት የህዝብ ሃብት የቄንጥ ኑሯቸውን ፈልሰስ ብለው እየኖሩ ይገኛሉ። ኢትዮጵያውያን ግን የስቃይና የመከራ ህይወት እንዲገፉ ተፈርዶባቸዋል። ከዚህ በተጨማሪም እነኝህ ከርስ አምላኪዎች በስልጣናችን እና በሆዳችን መጣብን የሚሉትን የመብት ጥያቄዎችን ያነገቡ ዜጎችን ግንባር ግባራቸውን እያሉ በህዝቡ ላይ ጭፍጨፋ ይፈጽማሉ።
የሙርሌ ጎሳ አባላት ከደቡብ ሱዳን ተነስተው ድንበር ተሻግረው ጋንቤላ በሚገኙ ንጹሃን ኢትዮጲያዊያን ዜጎች ላይ ተደጋጋሚ ጥቃቶችን ሲፈጽሙ መከላከያ ሰራዊቱ የት ነበር? ብለን ብንጠይቅ ለሃገርና ህዝብ የሚያስብ የመከላከያ ሰራዊት መች አለና የሚል መልስ እናገኛለን። የወያኔ የጦር ሹማምንት በስልጣናቸው ለመጣ ካልሆነ የህዝብ እና የሃገር ጥቅም የሚባል ነገር አያውቁም። ህዝቡም በውጪ ሃይል ጥቃት ሲደርስበት አለሁልህ ብሎ ከጎኑ የሚቆም የመከላከያ ሰራዊት እንደሌለ ካወቀ ዘመናት ተቆጥረዋል።
በተለያዩ ቦታዎች የሰፈረው የመከላከያ ሰራዊት ተግባሩ ምንድነው? ለሚለው ጥያቄ የማያሻማ መልስ ሰጥተን እንለፍ። ይህ መከላከያ ሰራዊት ተግባሩ የሆነው የዜጎችን ሰላም እንዳይናወጥ መሰረቱን ለማጽናት ሳይሆን የህዝብን ሰላም ለማወክ፣ የማህበረሰቡን ጥያቄ በማፈንና የወያኔን ስልጣን አደላድሎ በማስቀጠል ተልኮ ላይ የተጠመደ ነው። ለዚህም ነው የጋምቤላ ህዝብ በሙርሌ ጎሳ ጥቃት ሲፈጸምበት ጥቃቱን ከመመከት ይልቅ መከላከያ ሰራዊቱ በኦሮሚያና በአማራ ክልል ህዝብን ሲጨፈጭፍ የነበረው። በዚህም ሳቢያ ብዙዎችን ለእስራት፣ በጣም የሚልቁትን ለስደት፣ አያሌዎችን ለሞት ተዳርገዋል።  ሃገሪቱንም ወገባቸውን ታጥቀው ጦራቸውን ሰብቀው ሰው አልባ አገር ለማድረግ ቆርጠው የተነሱ ይመስላል።
ለዚህም ነው ዛሬ ለመብቱ የሚጮኸውን ህዝብ የሚጮህበትን ልሳኑን በጥይት እየዘጉት የሚገኙት።አገራችን በአሁኑ ወቅት ከአምባገነን ሲቪላዊ አገዛዝ ወጥታ በሙሉ ወታደራዊ ቁጥጥር ስር ተጨምድዳ ትገኛለች። ሰላምና መረጋጋት የጠፋባት፣ ሰዎች ወታደራዊ ዩኒፎም የለበሰ ሰው ባዩ ቁጥር የሚደነብሩባት አገር ሆናለች። ማህበረሰባችን ከቤቱ ወጥቶ በሰላም ተመልሶ መግባት ያልቻለበት፤ ከሊቅ እስከ ደቂቅ በዚያው እንደወጣ የሚቀርባት አገር ሆናለች።
በሃገራችን የተነሳውን ህዝባዊ ተቃውሞ ተከትሎ በሺዎች የሚቆጠሩ ዜጎች በጸጥታ አካላት ተብየዎች በተተኮሰባቸው ጥይት አልቀዋል። ከ60 ሺ በላይ የሚጠጉ ዜጎች ወደ ወህኒ ተወርውረዋል። ይህን ድርጊት አለም አቅፍ የሰብአዊ መብት ተሟጋቾች በተደጋጋሚ ቢያወግዙም ሰሚ አላገኑም። ይልቁንም የአገዛዙ ዘዋሪዎች ሪፖርቱን በደፈናው ከእውነት የራቅ ብቻሳይሆን ፍጹም ውሸት ነው ማለቱን ተያይዘውታል።ሲያክሉበትም ሪፖርቱን የሚያወጡ ሰዎች የአንድን ወገን አቋም ብቻ የሚያንጸባርቅ ምናምን እያሉ ሲኮንኑ ይደመጣሉ። ይባስ ብለውም ሪፖርቱን የሚያወጡትን የሰባዊ መብት ተቆርቋሪ ተቋማትን፣ በቦታው ተግኝተው ተጫባጩን ዕውነታ ያላንጸባርቁ፤ የመንግስትን ወገን አስተያየት ያላከሉ፤ ሸገር ብለውም ሪፖርቱ የተጻፍበትን ወረቅትና እስክብሪቶ ያክል እኳን ዋጋ እንደ ማያወጣ በጎልዳፋ አንደበታቸው ሊያስረዱን ይውተረተራሉ።
ዛሬም ለህዝብ የሚያስቡ በመከላከያ ሰራዊት ውስጥ ያሉ የሰራዊቱ አባላት እንደሚገኙ ማንሳቱ ተገቢ ነው። እነዚህ አካላት በስርአቱ ውስጥ ሆነው ስርአቱን ከውስጡ መንግሎ ለመጣል በሚደረገው ህዝባዊ አሻጥር ተግባራት ውስጥ ከፍተኛ ሚና እንደሚኖራቸው ይታወቃል። የመከላከያ ሰራዊት አፈሙዙን ወደ አዛዦቹ የሚያዞርበት ቀን እሩቅ እንዳልሆነ ከሰራዊቱ ውስጥ የሚሰማው እሮሮ እያስተጋባ ይገኛል። ሰራዊቱ በአዛዦቹ ተቀፍድዶ የተያዘ ከመሆኑም በላይ የሌላ ብሄር የሆኑ የሰራዊቱ አባላት ከምንግዜውም በላይ እየተገፉ እንደሚገኙ ይታወቃል።
ሰራዊቱ በዘረኛ አስተሳሰብ ተሸብቦ የሚገኝ በመሆኑ በሰራዊቱ ውስጥ የታመቀው እሳተ ጎመራ ሲፈነዳ ከላይ ያሉትን ዘረኛና አምባገነን አዛዦችን ጠራርጎ እንደሚሄድ ይታወቃል።
በአጠቃላይ ይህን የከፋና የከረፋ ድርጊታቸውን ተርባርበን ማስቆም ካልቻልን ጉዟችን የቁልቁለት ይሆናል። መከላከያ ሰራዊቱም ከህዝብ አብራክ ወጥቶ የህዝብ ወገን መሆን የሚችለው ህዝባዊ ስርዓት ሲመሰረት ብቻ ነው። ህዝባዊ ስርዓት ለመመስረት መሰረት ለመጣል  ደግሞ ሁላችንም የሚጠበቅብንን ሃላፊነት መወጣት እንዳለብን ግድ ይለዋል።

No comments:

Post a Comment