Monday, July 10, 2017

የምታገለው አርበኞች ግንቦት 7 ለቆመለት ዓላማ ነው ።


ኢትዮጵያ ውስጥ እውነተኛ የሆነ የስርዓተ ለውጥ እንዲመጣ እስከመጨረሻው ድረስ እታገላለሁ ። ይህንንም ስል እንደከዚህ ቀደሞቹ አንድን ስርዓት በሌላ ሃይል ለመተካት ሳይሆን ። ኢትዮጵያ ውስጥ እውነተኛ የሆነ የዲሞክራሲ ተቋም እንዲፈጠር ነው ። ይህንንም ለማሳካት የሚቻለው ደግሞ ከአሁኑ ጀምሮ እንጂ ከነገ ጀምሮ ወይም ደግሞ ከነፃነት በኋላ ሊሆን አይገባም ።
ብዙውን ጊዜ ሁላችንም የምናተኩረው ጠላታችንን እንዴት ታግለን እንደምንጥለው እንጂ ጠላታችንን ታግለነው ከጣልነው በኋላ በምን አይነት ሁኔታ እንደምንቀይረው አናስብም ። ለዚህም ነው አሁን በበረሃ ያሉት የነፃነት ሃይሎች ኢትዮጵያ ውስጥ መሰረታዊ የሆነ ለውጥ እንዲመጣ የሚታገሉት ። ለዚህም ማስረጃ እንዲሆነኝ የድርጅቱ ሊቀመንበር የሆኑት አርበኛ ፕሮፌሰር ብርሃኑ ነጋ ስለዚህ ጉዳይ ሲናገሩ ኢትዮጵያ ውስጥ ወያኔን መጣል ቀላል ነው ነገር ግን ከወያኔ ስርዓት በኋላ ሊመጣ የሚችለውን ነገር መስራቱ ነው ከባዱ ብለው ነበር ። ይህንንም ለማድረግ በአሁኑ ሰዓት ተግተው እየሰሩና በዚህም ሁኔታ ብዙ ሁኔታዎች እየተስተካከለ እያየን የመጣንበት ወቅት ላይ ደርሰናል ።
ለዚህም ነው ታዲያ እኔም የለውጡ አካልና የትግሉ ባለቤት ነኝ ብዬ የማስብ ከሆነ ከአሁኑ ጀምሬ ኢትዮጵያ ውስጥ ስር ነቀል የሆነ የስርዓት ለውጥ እንዲመጣ መታገልና ስር ነቀል ለውጡ የሚፈልገውን እውነተኛውን ስርዓት ለመተካት እንደታጋዮቹ ከወዲሁ አባጣና ጎርባጣ የሆነውን የዲሞክራሲ ስርዓት እንቅፋት የሆኑትን አሰራሮች በማስተካከልና ለህዝቢም እውነተኛ የሆነውን የዲሞክራሲ መንገድ በማሳየት ብሎም እንዲሳተፍና እርሱም የትግሉ አካል ሆኖ ወደ ትግሉ እንዲቀላቀል በማድረግ የበኩሌን ድርሻ በመወጣት ትግሉ የመላው ኢትዮጵያዊ ትግል እንዲሆን መስራት ይጠበቅብኛል ።
ይህንንም ሳደርግ ታዲያ ከአሁኑ ጀምሮ ለዲሞክራሲ ስርዓት እንቅፋት የሆኑትን ነገሮች ፊትለፊት በመጋፈጥ በቁርጠኝነት ልዋጋው ያስፈልገኛል ይህንንም መንፈስ ደግሞ ቀሪውም ወገኔ እንዲያምንበት እራሴ ታማኝ ሆኜ መቅረብ ብቻ ሳይሆን እርሱም እንዴት ሆኖ መዋጋት እንዳለበትና በፅናት እንዲቆም እራሴ በፅናት ቆሜ ላሳየው ይገባኛል ። ይህንን የማደርግ ከሆነ ከታጋይ ወገኖቼ ጎን መቆሜን አስመሰክራለሁ ይህንን የማላደርግ ከሆነ ደግሞ ኢትዮጵያን እንደምጎዳት አምናለሁ ።
በአጠቃላይ የለውጥ አካል ለመሆን ከፈለግን እኛ ብቻ ሳንሆን መላውን ኢትዮጵያዊ አስተባብረን ልንሰራና እውነተኛ የሆነው የዲሞክራሲ ስርዓት እንዲፈጠር በንቃት ልንታገል ግድ ይለናል ።
እግዚአብሔር ለሁሉም ነገር መሳካት ይርዳን ።
ኢትዮጵያ በክብር ለዘላለም ትኑር !!!!!
@ዘነበ ዘ ቂርቆስ

No comments:

Post a Comment