Saturday, April 25, 2015

በሜልበርን የሚገኙ ኢትዮጵያዊያን በደቡብ አፍሪካና በሊቢያ በወገኖቻችን ላይ የተፈጸመውን ኢሰባዊ ጥቃት በመቃወም ከፍተኛ የተቃውሞ ሰልፍ አደረጉ

April 25, 2015
ሳምሶን አስፋው – ከሜልቦርን አውስትራልያ
Ethiopians protested in Melbourne, Australia

የሜልበርን ኢትዮጵያዊያን ኮሚኒቲና ዲሞክራሲ ለኢትዮጵያ ድጋፍ ቡድን በህብረት ባስተባበሩት የተቃውሞ ሰልፍ እጅግ ከፍተኛ ቁጥር የነበረው ኢትዮጵያዊ ተሳትፎ ቁጣውን በመረረና እልህና ቁጭት በተንጸባረቀበት መልክ ሲገልጽ አርፍዷል።
በደቡብ አፍሪካ ደርባን ከተማ ጥቃት የደረሰባቸውን ወገኖች ዘግናኝ ምስልና ልዩ ልዩ መፈክሮችን አንግቦ ከጠዋቱ 11 ኤም ጀምሮ በደቡብ አፍሪካ ቆንስል ጽ/ቤት የተገኘው ሰልፈኛ ስሜት ይህን ይመስል ነበር። (ቪዲዮውን ይመልከቱ)
Ethiopians protested in Melbourne, Australia
ከኢትዮጵያዊ ሰልፈኛ ጋር አብራ የታደመች የደቡብ አፍሪካ ተወላጅ የሆነች ወጣት ያደረገቺው ንግግር የሰልፈኝውን ስሜት የገዛ ነበር።
ወጣቷ በንግግሯ በደቡብ አፍሪካ ደርባን ከተማ በአፍሪካዊያን ላይ የተፈጸመው ጥቃት አስቃቂ፤ ዘግናኝና አሳፋሪ ነው ካለች በኋላ ማንዴላ አረጋግቶ የያዘውን ደቡብ አፍሪካ ጃኮብ ዙማ እየገደላት ነው ማንም ሰው አንድ ቦታ ላይ የውጭ ዜጋ ነው። እኔም እናተም የውጭ ዜጎች ነን በመሆኑም በውጭ ዜግነትን ምክንያት አድርጎ የሚሰነዘር ጥቃት አሳፋሪ ነው፡፤ ስትል በወገኖቻችን ላይ የተፈጸመውን እንስሳዊ ጥቃት አውግዛለች።
Ethiopians protested in Melbourne, Australia
Ethiopians protested in Melbourne, Australia
አንድ እህት ያቃረበቺው ግጥምም የሰልፍኛውን ስሜት በሃዘን ያስደመመ ነበር።

በሰልፉ ላይ የተለያዩ ወገኖች ንግግር ያደረጉ ሲሆን የኦርቶዶክስ ሃይማኖቶት ካህን ቂም በቀልና ጥላቻ ዘላቂ ሰላም እንደማያመጣ በመግለጽ አሁንም ልባችን ለፍቅርና ለይቅርታ ክፍት ይሁን ሲሉ አስገንዝበዋል።
የሙስሊም ማህበረሰቡ ተወካይም በተለይ በአይሲስ የተፈጸመውን ግድያ አስመልክቶ ባደረገው ንግግር አይሲስ ተግባርም ሆነ ምንነት ከእስልምና ሃይማኖት ጋር ምንም ግንኙነት እንደሌለው አስረግጠው ተናግረዋል።
ሌሎችም ተናጋሪዎች ወገናችንን ለስደት የሚዳርገው ዘረኛው የወያኔ መንግስት ከኢትዮጵያ ህዝብ ጫንቃ ላይ እስካተወገደ በወገናችን ላይ እየደረሰ ያለው ጥቃት አያቆምም። አስተዳድረዋለሁ ለሚለው ህዝብ ደህንናትና የሃገር ሉዋላዊነት ደንታ ቢስ የሆነው ህዋት መራሹን መንግስት በጽናት መታገል እንደሚያስፈልግ አጽኖት ሰጥተው ተናግረዋል።
ሰልፈኛው በዚሁ መልክ ቁጣውን ሲግልጽ ቆይቶ ለቆንሲሉ ጽቤት የተዘጋጀውን መልዕክት አስተላልፎ ሰልፉ ተጠናቋል።
Ethiopians protested in Melbourne, Australia
Ethiopians protested in Melbourne, Australia

No comments:

Post a Comment