Monday, April 20, 2015


Isil ለምን ኢትዮጵያዊያንን መረጠ?
የትላንትናውን እጅግ አሣዛኝ አደጋ ተከትሎ የኢትዮጵያ መንግስት የተምታታ ሀሳብ እየሰጠ ይገኛል ይህም በሕዝቡ ዘንድ ብዙ አነጋግሮ ማምሻውን መንግሥት ነገ የሐዘን ቀን እንደሚያውጅ ይፋ አድርጓል።
በመንግሥት አሰራር የተናደዱ በርካታ ኢትዮጵያዊያን በማህበራዊ ድህረ ገፆች ገዢውን ፓርቲ ሲያብጠለጥሉ ውለዋል መንግሥት ግን መስሚያ የለውም ምክንያቱም "ምንም ማድረግ የማይችል ደካማ፣ አቅመቢስ እና ደንታ የሌለው መሆኑን ቀድሞ በሳውዲ አሳይቷል።
ገዢዎቻችን የታረዱት ዜጐች የኛ መሆናቸውን አላረጋገጥንም ብለዋል ቢያረጋግጡስ ምን ሊፈይዱ ይችላሉ ሐገሪቱ እንደው አቅም አልባ ሆናለች።
አምባገነኑ መሪ ኮሎኔል መንግሥቱ ሐይለማሪያም አንድ ኢትዮጵያዊ ከ50 ሱዳናዊ እኩል ነው ብሎ ነበር አሁን ግን አንድ የውጭ ዜጋ ከ50 ሚሊየን ኢትዮጵያዊ ዜጋ በላይ ክብር አለው ህዝቡም ከለላ የሚሆነው መንግሥት የለውም ስለዚህም የትኛውም ህዝብ ኢትዮጵያዊ ላይ ጥቃት ቢፈፀም ምንም አይነት የአፀፋ ምላሽ ከኢትዮጵያ መንግሥት እንደማይደርስበት ያውቀዋል።
ISIL ጥቃት እየሰነዘረባቸው ያሉትን ሐገራት ተመልከቱ 
ሶሪያ ጦርነት ውስጥ ያለች ሐገር 
ኢራቅ ጦርነት ውስጥ ያለች ሐገር
ግብፅ የተረጋጋ መንግሥት የሌላት ሐገር 
የመን መንግሥት አልባ ሀገር
ኢትዮጵያ መንግሥት ከሕዝቡ በተቃራኒ የቆመባት ሐገር።
ታድያ ISIL ሊቢያ ውስጥ በርካታ የሌሎች የአፍሪካ ሐገራት ስደተኞች እያሉ ኢትዮጵያውያን ላይ እርምጃ ለምን ወሰደ መልሱ ቀላል ነው ኢትዮጵያውያን የኔ የሚሉት መንግሥት የላቸውም።
የትላንትናው ጥቃት የብሔራዊ ውርደታችን አካል ነው።

No comments:

Post a Comment