Monday, April 6, 2015

የየመን ግጭት ተከትሎ የወያኔ መንቀዥቀዥ አንድም ለገንዘብ አንድም ለማጭበርበር... Minilik Salsawi (ምንሊክ ሳልሳዊ) - የአረብ ሊግ በየመኑ የተነሳውን ግጭት ለማረጋጋት በሳኡዲ አረቢያ መሪነት አስፈላጊዉን የሰላም ዋስትና

የየመን ግጭት ተከትሎ የወያኔ መንቀዥቀዥ አንድም ለገንዘብ አንድም ለማጭበርበር...
"የየመን ግጭት ተከትሎ የወያኔ መንቀዥቀዥ አንድም ለገንዘብ አንድም ለማጭበርበር...

@[291169534245718:274:Minilik Salsawi (ምንሊክ ሳልሳዊ)] - የአረብ ሊግ በየመኑ የተነሳውን ግጭት ለማረጋጋት በሳኡዲ አረቢያ መሪነት አስፈላጊዉን የሰላም ዋስትና ለማረጋገጥ ኤርትራን ጨምሮ ለተለያዩ አባል ሃገሮቹ ጦራቸውን እንዲያዘምቱ ሲጠይቅ ሆዱን የቆረጠው ወያኔ ይህንን ጥያቄ እንዳልቀረበለት ቢታወቅም የሰላም አስከባሪ ጦር ለማሰማራት እና ገንዘብ ለመሰብሰብ አስፍስፎ በመንቀዥቀዥ ላይ መሆኑን ከሃይለማርያም ደሳለኝ ጀምሮ እስከ ቃል አቀባዮቻቸው ድረስ የተለያዩ ዲስኩሮችን በማሰማት ላይ ናቸው::

እስካሁን ሰሚ ጆሮ ያላገኙት ወያኔዎች አንድ ጊዜ የአየር ድብደባውን እንደግፋለን ሌላ ጊዜ ኤምባሲያችን ተመታ ሌላ ጊዜ ያላደረጉትን ፈጸምን አደረግን ወዘተ ቢሉም እስካሁን ከነሱ በዘለለ ሌላው ኢትዮጵያዊ እና የውጪ አካል ሊያዳምጣቸው አልቻለም::የተለያዩ ሃገር ዜጎች ክናይጄሪያ እስከ ህንድ ከሱዳን እስከ ፓኪስታን ምእራባውያንን ጨምሮ ዜጎቻቸውን በአየር እና በመርከብ ሲያወጡ ወያኔ ኢትዮጵያውያንን በስልክ ሽቦ ለማውጣት መሞከሩ ምን ያህል ብሄራዊ ውርደት ላይ እንደደረስን በገሃድ እያመሰከረ ነው::በዜጎች ላይ ብሄራዊ ውርደት ማስከተሉ ያልተዋጠለት የወያኔው ጁንታ ሳኡድ አረቢያ በየመን የምታደርገውን ድብደባ እደግፋለሁ በማለት በማያገባው እና ባልተጠራበት ሌሎች አገራት ገለልተኛ በሆኑበት ጉዳይ እየተርመሰመሰ በስደት ላይ ባሉ ኢትዮጵያውያን ላይ በበደል ላይ በደል የከሳውን መግደል የሚል እጅግ አደገኛ ባህር ዘለል ፕሮፓጋንዳ በመርጨት በየመን በሚኖሩ ኢትዮጵያውያን ላይ ጥርስ እንዲነከስ በማድረግ ላይ ይገኛል::

በየመን የሰላም አስከባሪ ጦር አሰማራ ተብሎ እንዲጠየቅ ፍላጎት ያሳየው እና ዞር ብሎ የሚያየው የጠፋው ወያኔ እስካሁን ድረስ ባልተጠየቀበት እየፈተፈተ በማላዘን ላይ ሲሆን ወታደሮቹን ልኮ ዶላሮችን ለመዛቅ ሳኡድ አረቢያን እየተለማመጠ ያለበት ደረጃ ላይ መሆኑ ምን ያህል አወናባጅ እና አጭበርባሪ እንደሆነ በገሃድ አስመስክሯል:: ዜጎችን ለማስወጣት ያልተረባረበ ወንጀለኛ ስርአት በየትኛው ሞራሉ ሰላም አስከባሪ ልኮ የመኖችን ሊታደግ? የወያኔ ጥቅም ለማጋበስ የሚደረግ ሩጫ እስካሁን አልተሳካም:: አረብ ሊግ እኮ እንደማይፈልግ በተደጋጋሚ እየተናገረ ሳኡዲን መለማመጥ ለምን አስፈለገ?የወያኔ አገልጋይ የሆነው ሃይለማርያም ደሳለኝ የሳኡዲ አረቢያን የአየር ድብደባ በተመለከተ የሰጠው ድጋፍ የሰሙት የመናውያን በኤምባሲው ላይ ጥቃት እንዳደረሱ እና ኢንዲሁም ኢትዮጵያውያንን በየመንገዱ እየተሳደቡ እንደሚገኙ ከሰነአ የሚገኙ ወገኖች ጠቁመዋል::በተሳሳተ መረጃ ለማደናበር ወያኔ እየሞከረ ነው::የየመንን ግጭት ተከትሎ እንደ አንድ መንግስት ኢትዮጵያውያንን ከማዳን ይልቅ የወያኔ መንቀዥቀዥ ለብሄራዊ ጥቅም አሊያም ኢትዮጵያውያንን ለመታደግ ሳይሆን አንድም ለገንዘብ አንድም ለማጭበርበር ቢሆንም እስካሁን ጆሮ ዳባ ልበስ ተብሏል:: ይህንን አምባገነን እና ወገኖቻችንን በጥቅም የሚለውጥ ስርአት በህዝባዊ አብዮታችን በቃህ ልንለው ይገባል!! === ብሄራዊ ውርደት ይብቃ !!! === #ምንሊክሳልሳዊ"
Minilik Salsawi (ምንሊክ ሳልሳዊ) - የአረብ ሊግ በየመኑ የተነሳውን ግጭት ለማረጋጋት በሳኡዲ አረቢያ መሪነት አስፈላጊዉን የሰላም ዋስትና ለማረጋገጥ ኤርትራን ጨምሮ ለተለያዩ አባል ሃገሮቹ ጦራቸውን እንዲያዘምቱ ሲጠይቅ ሆዱን የቆረጠው ወያኔ ይህንን ጥያቄ እንዳልቀረበለት ቢታወቅም የሰላም አስከባሪ ጦር ለማሰማራት እና ገንዘብ ለመሰብሰብ አስፍስፎ በመንቀዥቀዥ ላይ መሆኑን ከሃይለማርያም ደሳለኝ ጀምሮ እስከ ቃል አቀባዮቻቸው ድረስ የተለያዩ ዲስኩሮችን በማሰማት ላይ ናቸው::
እስካሁን ሰሚ ጆሮ ያላገኙት ወያኔዎች አንድ ጊዜ የአየር ድብደባውን እንደግፋለን ሌላ ጊዜ ኤምባሲያችን ተመታ ሌላ ጊዜ ያላደረጉትን ፈጸምን አደረግን ወዘተ ቢሉም እስካሁን ከነሱ በዘለለ ሌላው ኢትዮጵያዊ እና የውጪ አካል ሊያዳምጣቸው አልቻለም::የተለያዩ ሃገር ዜጎች ክናይጄሪያ እስከ ህንድ ከሱዳን እስከ ፓኪስታን ምእራባውያንን ጨምሮ ዜጎቻቸውን በአየር እና በመርከብ ሲያወጡ ወያኔ ኢትዮጵያውያንን በስልክ ሽቦ ለማውጣት መሞከሩ ምን ያህል ብሄራዊ ውርደት ላይ እንደደረስን በገሃድ እያመሰከረ ነው::በዜጎች ላይ ብሄራዊ ውርደት ማስከተሉ ያልተዋጠለት የወያኔው ጁንታ ሳኡድ አረቢያ በየመን የምታደርገውን ድብደባ እደግፋለሁ በማለት በማያገባው እና ባልተጠራበት ሌሎች አገራት ገለልተኛ በሆኑበት ጉዳይ እየተርመሰመሰ በስደት ላይ ባሉ ኢትዮጵያውያን ላይ በበደል ላይ በደል የከሳውን መግደል የሚል እጅግ አደገኛ ባህር ዘለል ፕሮፓጋንዳ በመርጨት በየመን በሚኖሩ ኢትዮጵያውያን ላይ ጥርስ እንዲነከስ በማድረግ ላይ ይገኛል::
በየመን የሰላም አስከባሪ ጦር አሰማራ ተብሎ እንዲጠየቅ ፍላጎት ያሳየው እና ዞር ብሎ የሚያየው የጠፋው ወያኔ እስካሁን ድረስ ባልተጠየቀበት እየፈተፈተ በማላዘን ላይ ሲሆን ወታደሮቹን ልኮ ዶላሮችን ለመዛቅ ሳኡድ አረቢያን እየተለማመጠ ያለበት ደረጃ ላይ መሆኑ ምን ያህል አወናባጅ እና አጭበርባሪ እንደሆነ በገሃድ አስመስክሯል:: ዜጎችን ለማስወጣት ያልተረባረበ ወንጀለኛ ስርአት በየትኛው ሞራሉ ሰላም አስከባሪ ልኮ የመኖችን ሊታደግ? የወያኔ ጥቅም ለማጋበስ የሚደረግ ሩጫ እስካሁን አልተሳካም:: አረብ ሊግ እኮ እንደማይፈልግ በተደጋጋሚ እየተናገረ ሳኡዲን መለማመጥ ለምን አስፈለገ?የወያኔ አገልጋይ የሆነው ሃይለማርያም ደሳለኝ የሳኡዲ አረቢያን የአየር ድብደባ በተመለከተ የሰጠው ድጋፍ የሰሙት የመናውያን በኤምባሲው ላይ ጥቃት እንዳደረሱ እና ኢንዲሁም ኢትዮጵያውያንን በየመንገዱ እየተሳደቡ እንደሚገኙ ከሰነአ የሚገኙ ወገኖች ጠቁመዋል::በተሳሳተ መረጃ ለማደናበር ወያኔ እየሞከረ ነው::የየመንን ግጭት ተከትሎ እንደ አንድ መንግስት ኢትዮጵያውያንን ከማዳን ይልቅ የወያኔ መንቀዥቀዥ ለብሄራዊ ጥቅም አሊያም ኢትዮጵያውያንን ለመታደግ ሳይሆን አንድም ለገንዘብ አንድም ለማጭበርበር ቢሆንም እስካሁን ጆሮ ዳባ ልበስ ተብሏል:: ይህንን አምባገነን እና ወገኖቻችንን በጥቅም የሚለውጥ ስርአት በህዝባዊ አብዮታችን በቃህ ልንለው ይገባል!! === ብሄራዊ ውርደት ይብቃ !!! === ‪#‎ምንሊክሳልሳዊ‬

No comments:

Post a Comment