Friday, April 3, 2015

ESAT ኢሳት ዜና

"ከቦሌ አውሮፕላን ማረፊያ የንግድ ድርጅቶች ጀርባ  እየተፈጸመ ያለው ሙስና
-ከ100 ሚሊዮን ብር በላይ የት እንደገባ አይታወቅም።
ከድርጅቶቹ ጀርባ እነማን አሉ?

መጋቢት ፳፬(ሃያ አራት) ቀን ፳፻፯ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-ኢሳት ከታማኝ ምንጮች እንዳረጋገጠው በቦሌ አየር ማረፊያ በሚስጢር ስም የተመዘገቡና ባለቤታቸው ተለይቶ ያልተመዘገቡ ድርጅቶች ካለፉት 10 አመታት ጀምሮ የኮንትራት ጊዜያቸውን ሳያድሱ እና የቤት ኪራይ ክፍያቸውን ለመንግስት ገቢ ሳያደርጉ በመነገድ ላይ ናቸው።
በእነዚህ ድርጅቶች ጀርባ የከፍተኛ የመንግስት ባለስልጣናት እጅ እንዳለበትም ምንጮች ጠቁመዋል።
የኤርፖርቶች ድርጅት ፣ተከራዮችንና ሌሎች የሚመለከታቸውን የህብረተሰብ ክፍሎችን ተጠቃሚ ለማድረግ በሚል ምክንያት በየካቲት 1999 ዓም ላይ ኤሮኔቲካል ያልሆኑ የገቢ ምንጮችን ለማስተዳደር የሚል መመሪያ ያወጣ ሲሆን፣ በመመሪያው መሰረት ተከራዮቹ በየአምስት አመቱ በግልጽ ጨረታ እንደገና መወዳደር ይጠበቅባቸው ነበር።
ይሁን እንጅ ከእነዚህ መካከል፣8ት ባለቤታቸው የማይታወቅ በኮድ ስም የተመዘገቡ ድርጅቶችን ጨምሮ 15 የንግድ ድርጅቶች የኮንትራት ጊዜያቸውን ሳያድሱ ፣ የሚከፍሉት ወርሃዊ ክፍያ የት እንደገባ ሳይታወቅ ገንዘቡ በባለስልጣናት መበላቱን ምንጮች ጠቁመዋል።
ድርጅቶቹ በ1995 ዓም የኮንትራት ውል የፈረሙ ቢሆንም ፣ በ1999 ዓም በወጣው መመሪያ መሰረት እንደገና አለመመዝገባቸውን፣ ድርጅቶቹን ደፍሮ እንዲመዘገቡ የሚያደርግ አካል መጥፋቱን ምንጮች አክለዋል።
-በተርሚናል ቁጥር 2 በኮድ ቁጥር AACS 02 የተመዘገበው ድርጅት፣ የህትመት ውጤቶችን ለመሸጥ በካሬ ሜትር 8 ሺ 100 ብር ተመን  54 ካሬ ሜትር ስፋት ያለው ክፍል ተከራይቶ የሚገኝ ሲሆን፣ በአመት 437 ሺ 400 ብር  የኪራይ መጠን- የአስር አመት ጠቅላላ ክፍያ 4 ሚሊዮን 374 ሺ ብር  የት እንደገባ አይታወቅም።
-በተርሚናል ቁጥር 2 በኮድ ቁጥር AACS 07”Cultural Cuisine” በሚል የይዞታ አይነት የተመዘገበው ድርጅት በአመት በካሬ ሜትር 5 ሺ 220 ብር  ተመን  54 ካሬ ሜትር ቦታ ቢወስድም፤ የ10 አመታት የኪራይ ክፍያ 2 ሚሊዮን 818 ሺ 800 ብር የት እንደገባ አይታወቅም።
-በተርሚናል ቁጥር 2 ለሻንጣ ማሸጊያ በሚል በኮድ ቁጥር AACS 22 የተመዘገበ ድርጅት ለ12 ካሬ ሜትር በአመት በካሬ ሜትር 4 ሺ 100  ሂሳብ - በአስር አመት 492 ሺ ብር ለመክፈል ቢዋዋልም፤ ክፍያው የት እንደገባ አልታወቀም።
-በተርሚናል 2 በኮድ ቁጥር AARS 12 ለካውንተር ሰርቪስ አገልግሎት ተመዝግቦ የሚገኘው ድርጅት በካሬ ሜትር በአመት 4 ፣ 100 ብር  ለመክፈል ተስማምቶ  141.31 ካሬ ሜትር ቦታ ቢወስድም፤የ10 አመታት በአጠቃላይ  ክፍያ 5 ሚሊዮን 793 ሺ 710 ብር የት እንደገባ አይታወቅም።
-ተርሚናል በኮድ ቁጥር AACS 09 የተመዘገበው የወርቅና ጌጣጌጦች ሱቅ ፤ለያዘው 31.10 ካሬ ሜትር ቦታ በአመት በካሬ ሜትር 8 ሺ 100 ሂሳብ -አጠቃላይ የአስር አመት 2 ሚሊዮን 519 ሺ 100 ብር ክፍያ የት እንደገባ አልታወቀም።
-በተርሚናል ቁጥር 2 በኮድ ቁጥር AACS 21 ለአበባ መሸጫነት የተከራየው በ25.9 ካሬ ሜትር የሰፈረው ቦታ በአመት በካሬ ሜትር 4 ሺ 100 ብር የሚከፈልበት ቢሆንም፤ የ10 አመታት አመታዊ ክፍያው 1 ሚሊዮን 61 ሺ 900 ብር የት እንደገባ አይታወቅም።
-በተርሚናል ቁጥር AACS 06 የይዞታዉ መጠን 31.10 ካሬ ሜትር ለብር ጌጣጌጥ/Silver Shop/ የሚውለው መደብር በአመት በካሬሜትር 8 ሺ 100.00 ብር የተከራዬ ቢሆንም፤ የአስር አመታት ኪራይ  2 ሚሊዮን 519 ሺ 100 ብር ክፍያ የት እንደገባ አይታወቅም።

-በተርሚናል ቁጥር 2 በኮድ ቁጥር AACS 16 ለሱፐር ማርኬት የተከራየውና በ 33.4 ካሬ ሜትር ቦታ ላይ የሰፈረው መደብር በአመት 8 ሺ 100 ብር የሚከፈልበት ቢሆንም፤ የ አስር ዓመት ክፍያው 2 ሚሊዮን 700 ሺ ብር ከ40 ሳንቲም እንዲሁ የት እንደገባ አይታወቅም።

እነዚህን ድርጅቶች በባለቤትነት የሚያስተዳድሩዋቸው ሰዎች በግልጽ ባይታወቁም፦ የዜንስው ምንጮች፦ ” በህግ የማይጠየቁ የተወሰኑ ከፍተኛ ባለስልጣናት ዘመዶችና ቤተሰቦች ናቸው” ይላሉ።
በስማቸው ተመዝገበው የሚገኙት የንግድ ድርጅቶችም በአዲሱ መመሪያ መሰረት ውል ሳይገቡ በመነገድ ላይ ሲሆኑ፤ የሚከፍሉት ክፍያ ከወቅቱ ጋር የማይመጣጠንና ተቆጣጣሪ የሌለባቸው መሆናቸውን ምንጮች ገልጸዋል።

በአዲሱ ውል መሰረት ውል ሳይዋዋሉ ለ5 አመታት ያክል በአውሮፕላን ማረፊያ ውስጥ በመነገድ ላይ ካሉት ድርጅቶች መካከል፦
- ለንደን ካፌና ሳተላይት ሬስቶራንት- 109.9 ካሬ ቦታ በአመት ብር 138 ሺ 474
- አልፋራጅ ትሬዲንግ ሃላፊነቱ የተወሰነ የግል ማህበር ፣ የይዞታ መጠን 631 ካሬ ሜትር፣ አመታዊ ክፍያ በካሬ ሜትር 8 ሺ 100 ብር
- ላሊበላ ወርቅ ቤት፣ 31.10 ካሬ ሜትር፣ አመታዊ የክፍያ መጠን በካሬ ሜትር 8 ሺ 100 ብር 
-ሲቲ ቢዝነስ ኮምፒዩተር ፣ 104 ካሬ ሜትር -አመታዊ የክፍያ መጠን በካሬ ሜትር 8 ሺ 100 ብር 
-ድሬ ኢንዱስትሪ ሃ/የተወሰነ የግል ማህበር 54 ካሬ ሜትር አመታዊ የክፍያ መጠን በሄክታር 8 ሺ 100
- ህይወት ለማ ትሬዲንግ 31.10 ካሬ ሜትር የክፍያ መጠን በካሬ ሜትር 8 ሺ 100 ብር
 ሲማት ትሬዲንግ 31.10 ካሬ ሜትር የክፍያ መጠኑ ባከሬ ሜትር 8 ሺ 100 ብር ይገኙበታል።

በአጠቃላይ አዲስ በወጣው መመሪያ መሰረት ህጋዊ ውል ሳይፈርሙ በመስራት ላይ የሚገኙት ድርጅቶች የ10 አመታት የኪራይ ዋጋ ከ100 ሚሊዮን ብር በላይ ሲሆን፣ ኤርፖርቶች ድርጅት እስካሁን እርምጃ ለመውሰድ አለመድፈሩን ምንጮች ገልጸዋል።

ጉዳዩ በተደጋጋሚ ለድርጅቱ ቢቀርብም ምላሽ መጥፋቱን ምንጮች አክለው ይገልጻሉ። በጉዳዩ ዙሪያ የኢትዮጵያ ኤርፖርት ኢንተርፕራይዝን አስተያየት ለማካተት ያደረግነው ጥረት አልተሳካም።"

ከቦሌ አውሮፕላን ማረፊያ የንግድ ድርጅቶች ጀርባ እየተፈጸመ ያለው ሙስና

ጉዳዩ በተደጋጋሚ ለድርጅቱ ቢቀርብም ምላሽ መጥፋቱን ምንጮች አክለው ይገልጻሉ። በጉዳዩ ዙሪያ የኢትዮጵያ ኤርፖርት ኢንተርፕራይዝን አስተያየት ለማካተት ያደረግነው ጥረት አልተሳካም።

No comments:

Post a Comment