ጅማ ከተማ ውስጥ የሚገኘው ህዝብ ኢህአዴግን የሚደግፍ ሰላማዊ ሰልፍ እንዲያደርግ በስርዓቱ ካድሬዎች ትእዛዝ ቢሰጠውም እንዳልተቀበለው ተገለጸ፣
በምንጮቻችን መረጃ መሰረት። በጅማ ከተማ የሚገኘውን ህዝብ የስርዓቱ ካድሬዎች በኢህአዴግ ላይ ያላችሁን ድጋፍ በሰላማዊ ሰልፍ መግለፅ አለባችሁ ተብለው። መጋቢት 18/ 2007 ዓ/ም ሊያስገድዱት በሞከሩበት ግዜ። ነዋሪው ህዝብ ግን እኛን የሚወክል ድርጅት ይሁን መንግስት እስካላገኘን ድረስ አንደግፍም ማለቱን የገለጸው መረጃው። በዚህ መልስ የተደናገጡ የስርዓቱ ካድሬዎችም። ያሰቡትን ለማስፈጸም ግንጪ ከተባለ ቦታና ሌሎች የገጠር አካባቢዎች ሰዎችን በመኪና ጭነው በማስመጣት። የድጋፍ ሰላማዊ ሰልፍ እንደተካሄደ አስመስለው መናገራቸውን ከቦታው የደረሰን መረጃ አስታወቀ፣
የከተማው ነዋሪ ህዝብ። መንግስት ለምንድን ነው የማደናገር ተግባርት የሚፈፅመው፤ እስከ መቼ ድረስ ይህ ስርዓት ህዝቡን እያታለለ ስልጣን ላይ ይቀጥላል በማለት። በስርዓቱ ላይ ጥላቻ የወለደው ከፍተኛ ስሜት ይዞ እንደሚገኝና። የክልሉ ባለስልጣኖችም ተቃውሞ ይነሳል የሚል ስጋት ስላደረባቸው። ፌደራል ፖሊስ አሰማርተው በተጠናከረ ጥበቃ ላይ እንደሚገኙ መረጃው አክሎ አስረድቷል፣
No comments:
Post a Comment