Tuesday, September 26, 2017

እነሆ ደረሰ!!! ምኑ ትላላችሁ እንዴ? ጥቅምት 14 ነዋ የኢሳት 7ኛ ዓመት ክብረ-በዓል።

ይህንን አስመልክተን በኦስሎ ዕቱተን ስናደምቀው ልናመሽ ተዘጋጅተናል። ከእውቁ ጋዜጠኛ ፋሲል የኔ ዓለም እና እንዲሁም ቀናችንን በተስረቅራቂው ድምጿ ልታደምቀው ከስዊዲን በኪቤርድ ባለሙያው አርቲስት መርሶ ታጅባ ከዚህ በፊት ለህዝብ ባልተደመጡ ምርጥ ዝግጅቶቿ ስታስፈነድቀን ልታመሽ አርቲስት ሃኒሻ ሰለሞን ከለንደን እኛው ጋ ነች።
ኑ አብረን እንስራ አብረን እንደሰት። የኢትዮጵያ ሕዝብ ዐይንና ጆሮ ብቻ ሳይሆን እስትንፋስም የሆነውን ኢሳትን እንርዳ።ይህንን ስናደርግ በቅድሚያ የምንረዳው እኛኑ ራሳችንን ነው። በጋራ የምንሰራው ሁሌም የጋራ መሠረታችንን ነው።ለተወሰኑ ሰዎችና ድርጅቶች የሚተው ስራ አይደለም። የኢዮጵያውያንና የኢትዮጵያን ወዳጆች ሁሉ ወደዝግጅታችን ያመራሉ።
ቀኑ Oktober 14/2017 ከ15:ሰዓት ጀምሮ።
ቦታው John Collets plass 2
ወደ ሪክስ ሆስፒታል አቅጣጫ ሲጓዙ ከኡልቮል ሆስፒታል ቀጥሎ የሚገኘው የትሪክ መቆሚያ በስተቀኝ ያለው ባለ3 ፎቅ ህንፃ 2ኛው ፎቅ።
ይምጡ ይደሰቱ ኢሳትንም ይርዱ።
Image may contain: 2 people, people smiling, text

No comments:

Post a Comment