Monday, September 18, 2017

አርበኞች ግንቦት7 ንቅናቄውን ለሚቀጥሉት 3 ዓመታት የሚመሩትን መሪዎችን ይፋ አደረገ (ኢሳት ዜና መስከረም 08 ቀን 2009 ዓም)


ንቅናቄው በኤርትራ ሲያደርግ የነበረውን ጉባኤ ሲያጠናቅቅ ድርጅቱን ለሚቀጥሉት 3 ዓመታት የሚመሩትን መሪዎች በ4 ዘርፎች ከፋፍሎ ይፋ አድርጓል። እነዚህ ተመራጮች የስራ አስፈጻሚዎች ይሆናሉ።
ፕ/ር ብርሃኑ ነጋ በሊቀመንበርነት በሚመሩት በዚህ የሃላፊነት ተዋረድ፣ ኮማንደር አሰፋ ማሩ የህዝባዊ ተጋትሮ ዘርፍን በአዛዥነት፣ አርበኛ ታጋይ ገበየሁ አባጎራውና አርበኛ ታጋይ ታደለ ወንድም በምክትል አዛዥነት ይመሩታል። በፖለቲካው ዘርፍ ደግሞ አርበኛ ታጋይ ኤፍሬም ማዴቦ በዘርፍ ሃላፊነት፣ አርበኛ ታጋይ ንአምን ዘለቀና አርበኛ ታጋይ አበበ ቦጋለ በምክትል ዘርፍ ሃላፊነት ይመራሉ። የህዝባዊ እምቢተኝነቱን ዘርፍ ዶ/ር ታደሰ ብሩ የሚመሩት ሲሆን፣ አርበኛ ታጋይ ቸኮል ጌታሁንና አርበኛ ታጋይ አብርሃም ልጃለም በምክትል ሃላፊነት ያገለግላሉ። የንቅናቄውን ጽ/ቤት ደግሞ አርበኛ ታጋይ መኳንንት አበጀ በሃላፊነት እንዲሁም አርበኛ ጃንከበድ ዘሪሁን እና አርበኛ ታጋይ መላኩ ተሾመ በምክትል ሃላፊነት እንደሚመሩት ንቅናቄው ገልጿል።

No comments:

Post a Comment