Saturday, September 9, 2017

ዳንኤል ሺበሺ

ለሀገር የሚከፈል ዋጋ ፦
""""""""""""""""""""""""""""""""""  ሀገር ስንል ምን ማለት እንደሆነ ይገባናል፡፡ ጰውጉሜ 1ቀን፡ 2009 ዓም ዕለተ ዕሮብ ኮ/ቀ/ክ/ከ ኳስ ሜዳ ተብሎ ወደሚጠራው ሠፈር በመጓዝ የብሔራዊ አንድነት ፓርቲ ፕሬዚዳንት የአቶ #ዘሪሁን ገ/እግዚአብሔር'ን ቤተሰቦች ጎብኝቺያቸው ነበር፡፡ ምናልባት የማታውቁት ካላችሁ አቶ ዘሪሁን ገ/እግዚአብሔር ከፀረ ሽብር አዋጁ ሰለባዎች ውስጥ አንዱ ሲሆን፤ ተወልደው ያደጉት እዚሁ በመዲናችን አዲስ አበባ ከተማ ነው፤ ባለትዳርና የሁለት ሴት ልጆች አባትም ናቸው ፡፡ የኢት/ን ፖለቲካ ተረድተው ሰላማዊ ትግሉን መቀላቀላቸው ነገር፤ ነገር መዘዝ መዞባቸው ከእነ ርእዮት ዓለሙ፣ ውብሸት ታዬ እና ከሌሎቹ ጋዜጠኞችና ፖለቲከኞች ጋር በአንድ ላይ ለወኀኒ ዳርጓቸዋል፡፡ #ሰኔ12ቀን፡2003ዓም ተይዞ የታሰረ ሲሆን ከአባሪዎቹ ማለትም ከላይ ከተጠቀሱ ተከሣሾች ጋር በአንድ መዝገብ ተከሰው የ17 ዓመት ፍርድም ተሸልሟል፡፡ በአሁኑ ወቅት የ17 ዓመት ፍርደኛ ሲሆኑ የሚገኙትም ቃሊት ዞን 6 ነው ፡፡

ከእሥርና ከምርመራ ሁኔታ ጋር በተያያዘ አካሉ ላይ ጉዳት ደርሶበታል፡፡ የቀኝ እጁ ሰዓት ማሰሪያ አንጓ እና አውራ ጣቱ ላይ ስብራት ደርሶበታል፡፡ በሌላ በኩል ዘገየት ብሎ በጀመረው በጀርባ ህመምና በኩላልት በሽታ እንደሚሰቃይ ቤተሰቦቹ አጫውተውኛል ፡፡ ይህንን አካላዊ ጉዳት በተለይም የቀኝ እጁ አንጓ ስብራትን በተመለከተ እኔም ቃሊት ዞን 2 እና ታንከር ተብሎ በሚጠራው ጠባብ ክፍል ውስጥ ከእርሱ ጋር በነበርኩበት ወቅት በአይኔ አይቻለሁ፡፡ እኔ ልጎብኛቸው ወደቤታቸው ስደርስ ባለቤቱ ወ/ሮ ፎዚያ የሚታፈቅረውን ባለቤታቸውን ጥየቃና ስንቅ ለማቀበል ወደ ቃሊቲ ደርሳ ሲትመለስ ነበር የተገናኘነው ሲሆን፤ ቃሊት ደርሶ መመለስ በራሱ ከባድ እሥር መሆኑን ነበር በጨዋታው መሀል በምሬት የተናገረችው፡፡ ይህ ስሜት ለእኔም በጣም ይገበኛል፡፡ የቤተሰቦቼም ስሜት ስለነበረ፡፡
ይሁን እንጂ የአባታቸው ዓላማ የሚከፈልም/የማይከፈልም ዕዳ የሆነላቸውን፤ ጦሱ የተረፈላቸው ባለቤቱ ፎዚያንና ሁለቱን ልጆቹን ሳዋራቸው ዛሬም በጣም ጠንካራ፣ ደስተኛና ውስጣዊ ሠላም እንደሚሰማቸው አጫውተውናል፡፡ Z! እንደት ነው? ብዬ በሀዘነታ ስጠይቃት፤ Z! በጣም ሠላምም ደስተኛም ነው ብላኛለች፡፡Image may contain: 4 people, people sitting and indoor

ባጠቃላይ ታሣሪውም ከባድ የእሥር ጊዜያትን አሳልፏል፡፡ እያሳለፈም ነው፡፡ ቤተሰቦቹም እጥፍ ድርብ የመከራ ጊዜያትን እያሳልፉት ይገኛሉ፡፡ የአቶ ዘሪሁንም ሆነ የቤተሰባቸውን መከራ ቁልል እንዲሆን ያደረገው መታሠሩ ብቻም አይደለም፡፡ እሥር ቤቱ በእሱ ላይ የጣለው ዕቀባም ጭምር እንጁ፡፡ በአንድ በኩል እሱን መጠየቅ የሚችሉት ሚስትና ልጅ ብለው ከገደቡ በኀላ ይህም አላረካ ሲሏቸው ሰዓቱን በቀን ከ10-20 ደቂቃ ማድረጋቸው ነው፡፡ የዚህ አይነት እሥረኛን ከእሥረኛ ለይተው ማጥቃት (#በቀለኝነት) በእኔም ሆነ በሌሎች (በእነ አንዱዓለም፣ እስክንድር፣ ተመስጌን፣ ናትናኤል፣ በቀሌ፣ ውብሸት፣ ... ) ፖለቲካ እሥረኞች ላይም ተፈጽሟል፡፡ አሁንም እንደቀጠለ ነው፡፡ ድንቅ ነው! መቸስ ሰው ብርቱ፤ ሰው ከንቱ እንዲሉ፤ የሰው ልጅ ይህን ሁሉ ዶፍ ችለው በህይወት መኖሩ በራሱ የሚደንቅ ነው ፡፡ ከቤተሰቦቹ ጫማ ሥር ሆነን ነገር ሁላን ስናይ የቤቱ አድባር፣ የቤቱ አባትን ያጣ ቤተሰብ ምን አይነት ሥነ-ልቦና ቀውስ ሊደርስ እንደሚችልና ምን ያህል ኢኮኖሚ ድቀት ሊደርሳቸው እንደሚችል ለማስረዳት መሞከር እንዲያው ወሬ ማብዛት ይመስለኛል፡፡ የጉዳቱ መጠንና የህመሙን ልክ ለሚመለከትና ለሚያስተውል ሁሉ ግልጽ ስለሆነ ፡፡

ጥቂት ሰዎች፣ የታሣሪ ቤተሰቦች ካልሆነ በስተቀር በሀገር ጉዳይ የታሠረ ሰውን በጅምላ ለመጠየቅና ደንነቱን ከመከታተል አንፃር ደካሞች ነን፡፡ ውስጤ ያዝናል፡፡ በተለይ ሀገር ቤት በምንኖር ላይ፡፡ በከተማ ነዋሪዎች ላይ፡፡ አይደለም! ንጹኃን የሆኑ የህልና እሥረኞች ይቅርና ነፃና ፍትሐዊ ዳኝነት ቢኖረንና በዚሁ ህግ መሠረት ተዳኝተዋል፤ ወይም በፈጸሙት ድርጊታቸው፣ በወንጀላቸውና በጥፋታቸው የታሠሩ ናቸው የተባሉትንም ጭምር ሀቅምና ሁኔታ በፈቀደ መጠን መጠየቅ፣ ደንነታቸውን መከታተል ፦
#የፈጣሪ ትዕዛዝ፣
#ሕገመንግሥታዊ (በተፃፈ ሕግ ያልተከለከለ)፣ 
#የዜግነት ግደታችን፤
# ሰው'ዊ መሆኑን መዘንጋት የለብንም ፡፡ ይህንን በማድረጋችን ከፈጣሪ በስተቀር ከማንም ምላሽ/ዋጋ የማንጠብቀው ውለታ የሰራን ሲሆን፤ ለሠማዩ ለምድሩም የሚሆን፣ የውስጥ ሠላም፣ የህልና ነፃነት፣ የአዕምሮ እርካታንና የልብ ደስታን የሚሰጠን ነው፡፡

ከላም ለመጥቀስ እንደሞከርኩት በአሁኑ ወቅት የወንድማችን ዘሪሁን የጤና ሁኔታ በአንፃራዊነት የተሻለ ቢሆንም በጊዜው በቂ ህክምና ባለማግኘቱና በኀላም ህክምናው ከተፈቀደም በኀላም የእሥር ቤቱ አስተዳዳሪዎች በራሳቸው ሥልጣን የሀኪም ቀጠሮዎችን በማቋረጣቸውና ህክምና በመከልከላቸው የቀኝ እጁ አውራ ጣት ስብራቱ ሳይጠገን (Bone formation ...) እንደተሰበረ በዛው በመዳኑ ምክንያት አውራ ጣቱ እንደተጣመመ እንደቀረለት አጫውተውኛል ፡፡
ታዲያ ምን እናደርግለት? እንደት እንድረስለት? ቤተሰቦቹም ሆነ እርሳቸው ዛሬም የሕዝብ ፍቅር ፤ የፍትህ ጥማት አለባቸው፡፡ ቀናነቱና ትኩረቱ ከተሰጠበት ማድረግም መድረስም ይቻላል !Image may contain: 3 people, people sitting and indoor
በጉብኝቴ ዕለት ከተወሰኑ ቤተሰብ አባላት ጋር የማስተወሻ ፎቶግራፍ'ም ተነስተናል፡፡ ከልጆቹና ከልጆቹ እናት ጋር፡፡ ለጤናቸው ሠላም በመሆናቸው በእጅጉ ደስ እያለኝ ነው የተመለስኩት፤ ሌላ ምን እላለሁ እግዚአብሔር ይመስገን፡፡
አዎን! አሁን ላይ ሆነን የአሁን መከራችንን ወደ ውስጥም ወደ ውጭም ሲናይ ለኛ ለተገፋን፣ ብዙ ነገራችን የጨለመብን/የከሰረን ዜጎች ብመስለንም ግን ግን ምንም አትጠራጠሩ ጭጋጉ ይተናል፤ ሌሊቱ ይነጋል፤ ታሪክ ይቀየራል፤ መጪዩ ጊዜያችን ከፈጣሪያችን ጋር ብሩኀ ነው፡፡ በማንም ላይ በቀለኝነትን፣ ቂመኝነትን አንቋጥር፡፡ እኛ ከበዳዮቻችን/ከአሳሪዎቻችን በሞራል ከፍታ፣ በዲሲፕሊን፣ በሰብዓዊነት፣ በሕጋዊነት፣ በሠላማዊነት፣ በአርቆ አሳቢነት፣ ከጎሴኝነት፣ ለሐገርና ለወገን ተቆርቋርነት አንፃር በርግጥም እንደ ሰው ፍጹማን መሆን ብያቅተን እንኳ በአመዛኙ ተሽለን መገኘት አለብን፡፡
እንደ ፈጣሪያችን ፈቃድ 2010 ዓመተ-ምህረትም የምህረት-ዓመትም ይሁንልን፡፡ እየገባን ያለነው አዲሱ ዓመታችን ለሀገራችን፣ ለኔና ለእናንተ (ለሕዝባችን) በሁለንተናዊ ነገራችን ላይ የትንሳዔ ዓመት ይሁንልን፡፡ ሠላም!

No comments:

Post a Comment