Friday, September 15, 2017

[PG7] ከአርበኞች ግንቦት 7፣ ለአንድነትና ለዴሞክራሲ ንቅናቄ፣ አንደኛ መደበኛ ጉባኤ ለኢትዮጵያ የመከላከያና የፖሊስ ሰራዊት ዓባላት በሙሉ፣

የወያኔ ዘረኛና አምባገነን ሥርዓት፤ እድሜውን የሚያራዝመው፣ መብቱንና ነጻነቱን ለማስከበር የሚታገለው ወገናችሁ ላይ በየጊዜውና በየቦታው አሰቃቂ ርምጃ እንድትወስዱ በማድረግ ሲሆን፣ በሌላው ጎኑ ይህ ሥርዓት ከአናቱ እየፈረሰ መሆኑ ደግሞ ከእናንተ የተሰወረ እንዳልሆነ ግልጽ ነው።
በቅርብ የምታውቋቸው አለቆቻችሁ ከሲቪል አቻዎቻቸው ባልተናነሰ ሁኔታ በከፍተኛ ዘረፋ በተዘፈቁበት አጸያፊ ድርጊት ምን ያህል ሀብት እንዳካበቱ የአደባባይ ሚስጥር መሆኑን ታውቃላችሁ።

ስለዚህ የእናንተ ከዚህ ከበሰበሰና ሊወድቅ እያዘመመ ካለ ሥርዓት ጋር መቆም፤ በሀገራችሁ እና በወገናችሁ ላይ ከሚያስከትለው ሰቆቃ በሻገር፤ እናንተም የስርዓቱ አሰቃቂ ርምጃዎች አስፈጻሚ እና ቀጥተኛ ተሳታፊ መሆናችሁ የተለየ ሀላፊነትን አሸክሟችኋል። በመሆኑም የወያኔን ያበቃለት የአገዛዝ ሥርዓት ዛሬውኑ ትታችሁ እና በሚቻላችሁ ሁሉ በሕዝብ ላይ የምታደርሱበትን ሰቆቃ አቁማችሁ፣ ከወገናችሁ ጎን እንድትቆሙና በምትችሉት አጋጣሚ ሁሉ ንቅናቄያችንን እያካሄደ ያለውን ትግል እንድታግዙ፤ ከተቻለም ንቅናቄያችንን እድትቀላቀሉ በራችን ክፍት መሆኑን ጉባኤያችን ያረጋግጥላችኋል።

No comments:

Post a Comment