Tuesday, September 12, 2017

የወያኔ/ኢህአዴግ የወታደር ምንጭ መንጠፍ አለበት። ዶ/ር ታደሰ ብሩ

የህወሓት አገዛዝ 2010ን ለመሻገር ከሚፈልጋቸው ነገሮች ቀዳሚው የአዳዲስ ወታደሮች ምልመላ ነው።
ኢትዮጵያዊያን ወጣቶች የገዛ ራሳቸው ወላጆችን፣ ወንድምና እህቶቻቸውን ወይም የሌሎች ሰዎች ወላጆችን፤ የሌሎች ሰዎች ወንድምና እህቶችን መግደል የማይፈልጉ መሆኑን ማሳያ ጊዜዓቸው አሁን ነው። በዘመነ ኢህአዴግ “ወታደር” ማለት ሰላማዊውን ሰው ገዳይ ፈሪ ማለት እንጂ የአገር ጠላት ተከላካይ ማለት አለመሆኑ በግልጽ መታወቅ አለበት። ወጣቶች፣ የኢህአዴግ መንግሥት ወታደር መሆን የዘራፊና ገፋፊ አሽከር መሆን ማለት መሆኑን ተረድተው “እንቢኝ!” የሚሉት ጊዜ አሁን ነው።
ወጣቶች ለወያኔ የውትድርና ቅጥር ጥሪ ምላሻቸው እንቢታ እንዲሆን በተቻለ ሁሉ እንርዳቸው። የወያኔ/ኢህአዴግ የወታደር ምንጭ ዛሬውኑ መንጠፍ አለበት።

No comments:

Post a Comment