Thursday, September 7, 2017

ትኩረት ለጎንደር (ጋዜጠኛ መሳይ መኮንን)

የአማራው ብአዴን የድል ብስራት ያሰማል። የትግራዩ ህወሀት ይፎክራል። እንደመንደር ምላሰኛ፡ ነገረኛ ''እርር ቅጥል በሉ'' ብሏል ህውሀት። ሁለቱም በየፊናቸው አሸናፊነታቸውን አውጀዋል። ድራማው አልተጠናበትም። ልምምድ ሳያደርጉ ዘለው ወደሾው ገብተዋል። ህውሀት ለጎንደር የደገሰላትን ሸንሸናና ህዝበውሳኔ የፈጠረውን ሙቀት ለማቀዝቀዝ የግጨውን ካርድ መዟል። ገዱ አንዳርጋቸው ባንድ ራስ ሁለት ምላስ መሆኑ የተረጋገጠበት ቃለመጥይቅን ላዳመጠ ብአዴን ከባርነት መውጣት እንደማይችል ይረዳል። ቅማንትና አማራን መለያየት አንድን ሰው ለሁለት መክፈል እንደማለት ነው ሲል የነበረው ገዱ፡ 180ዲግሪ ተሽከርክሮ ስለልዩነትና መነጣጠል ቅዱስነት ማውራት ጀምሯል። የወልቃይትን የማንነት ጥያቄ ሊደፈጥጥ ይችላል፡ ትኩረት ያስቀይሳል በሚል በህውሀት በኩል ዲዛይን የተደረገው የግጨው ጉዳይ እልባት ተገኘ ተብሎ ከበሮ እየተደለቀለት ነው። ድንቁርና ማስተዋልን ስለሚጋርድ ህወሀቶች ሁልጊዜ እነሱ የሚሉትን ሰዉ ሳያላምጥ የሚውጥ ይመስላቸዋል። የግጨው ጉዳይ ተፈታ ማለት የወልቃይት ፋይል ተዘጋ እንደማለት አድርገን እንድንወስድላቸው መከጀላቸው ጅልነታቸውን እንጂ ሌላ የሚነግረን ነገር የለውም። እናም ትልቁን አጀንዳ ለመሸፈን እንጭፍጫፊውን እያራገቡት ነው። ቀልብ ለመሳብም ሁለቱ ጌታና ሎሌው ''ድል ቀናን'' ብለው በየፊናቸው ዋንጫ አንስተዋል።
የትግራይ ኮሚኒኬሽን ቢሮ ያወጣት መግለጫ ግን የምር ናት? It is really funny ''......ጥያቄው የአማራ ህዝብ ጥያቄ እንዳልሆነም ስምምነት ላይ ተደርሷል" ...... :D :P
@ጋዜጠኛ መሳይ መኮንን

No comments:

Post a Comment