Tuesday, September 5, 2017

የገዢው ፓርቲ አጋር ባለሐብቶች ወጪ በዝቶባቸዋል (ዋዜማ ሬዲዮ)


አዲሱን ዓመት ‹‹የከፍታ ዘመን›› በሚል በልዩ ሁኔታ ለመቀበል ከሚሰናዳው ዝግጅት ጋር ተያይዞ መንግሥት አጋር ባለሐብቶችን ከመዋጮ ጋር በተያያዘ እያስጨነቃቸው ይገኛል፡፡ መዋጮ እየተጠየቁ ከሚገኙ 250 የሚገጠጉ ባለሐብቶች መሐል ለአዲስ ዓመት አገር ቤት የገቡት ቢሊየነሮቹ አቶ ሳቢር አርጋውና አቶ በላይነህ ክንዴ ይገኙበታል፡፡Image may contain: 1 person, standing
እነዚህ ባለሐብቶች መዋጮውን እየተጠየቁ የሚገኙት በተለያየ መንገድ ሲሆን አንዱ በሚሰናዱ የመድረክ፣ የሬዲዮና የቴሌቪዥን ዝግጅቶች ላይ የድርጅቶቻቸውን ምርት እንዲተዋወቅላቸው በማድረግ በማስታወቂያ ስም የተጋነኑ ክፍያዎችን እንዲከፍሉ በማበረታት፣ ሁለተኛው መንገድ ደግሞ በቀጥታ ለፓርቲው ድጋፍ እንዲያደርጉ በደብዳቤ የሚጠየቁበት ዘዴ እንደሆነ ታውቋል፡፡ ከዚህም በተጨማሪ የባለሐብቶቹ የግል መኖርያ ቤቶች የሚገኙባቸው ክፍለከተሞችም ሆነ ወረዳዎች ለስብሰባ፣ ለበዓል ማድመቂያ፣ ለልምድ ልውውጥ፣ ለሠራተኞች ዓመታዊ የሕዳሴ ጉዞ ወዘተ. በሚል ከኢህአዴግ ጽሕፈት ቤቶች በሚመጡ ግለሰቦች ገንዘብ እንዲያበረክቱ በተደጋጋሚ ይጠየቃሉ፡፡ 
የአልሳም ባለቤት አቶ ሳቢር አርጋው ባለፈው ሳምንት መጨረሻ ላይ ለአዲሱ ዓመት ክብረ በአልና ተያያዥ ወጪዎች በሚል 8 መቶ ሺህ ብር በቼክ ገቢ ማድረጋቸው ታውቋል፡፡ የብአዴን የቁርጥ ቀን አጋር እንደሆኑ የሚነገርላቸው አቶ በላይነህ ክንዴም መጠኑ ያልታወቀ ገንዘብ ለድርጅቱ ገቢ አድርገዋል፡፡
=======
-ግርማ ብሩ ተመለሱ
በአሜሪካ የኢትዮጵያ አምባሳደር የነበሩትና ወደ ሀገር ቤት እንዲመለሱ ሲጠሩ በተለያዩ ምክንያቶች ጆሮ ዳባ ልበስ ብለው የነበሩት ግርማ ብሩ በመጨረሻ ወደ ሀገር ቤት ተሳፍረዋል። 
አምባሳደር ግርማ ወደ አዲስ አበባ የመመለሻ ጊዜያቸውን ሁለት ወራት ያህል አራዝመው የቆዩ ሲሆን አሁንም አንዳንድ አስገዳጅ ሁኔታዎች ስለተፈጠሩ ወደ ሀገር ቤት እንደተመለሱ የቅርብ ምንጮች ይናገራሉ። 
አምባሳደር ግርማ ብሩ በሀዋሳ በሚደረገው የአምባሳደሮች የምክክር ጉባዔ ላይ የመገኘት ዕቅድ እንዳላቸውና በጥቂት ሳምንታት ውስጥ ወደ አሜሪካ እንደሚመለሱ ተነግሯል። 
አምባሳደር ግርማ የኦሮሞ ህዝብ ዴሞክራሲያዊ ድርጅት አባል ሲሆኑ ሚንስትር በነበሩባቸው ተቋማት ጋር በተነሳ የሙስና ክስ ስማቸው መነሳቱ አልቀረም። አምባሳደሩ የህክምና ጉዳያቸውንም የሚከታተሉት አሜሪካ በመሆኑ ወደ ሀገር ቤት ከመመለስ ሳያዘገያቸው እንደልቀረ ይገምታሉ።

No comments:

Post a Comment