Saturday, September 2, 2017

ይድረስ ለተከበርከው ውድ ወንድሜ 50 አለቃ እሸቱ፦


ቀን 25/12/09 ዓ'ም
'
 ምንም እንኳን የበረሃ ነገር እንደ ልብ ስልክህ ቻርጅ ባይደረግ ኔት ወርክ እንቢ ቢልህና ለማነበብ በቂ ጊዜ ባይኖርህ የስሚ ስሚ መልዕክቱ መድረሱ አይቀርምና ልባዊ ሠላምታየ ይድረስህ ብያለሁ።ወንድም ጋሻየ እንደዋዛ ከተለያየን 13 ዓመት ሊሞላን ነው። 7 ዓመት የአገልግሎት ግዴታህን ስትጨርስ በፈለግከው ሰዓት እንደምትመለስ ቃል ገብተህልኝ ነበር። ቀኑ ቀን እየወለደ ድካም ልፋትህም የተመኘኸውን ለውጥ ሳያመጣ ጉልበትም ጊዜህም እየተቃጠለ ነው። ከአንተ በመቶዎት ኪሎ ሜትር እረቀት ይልቅ የእኔ በሽህዎች ኪሎ ሜትር እርቀት ለወገን ቅርብ ነው። የምሰማው ጥሩ አይደለም ።ብዙ ሰው ሞቷል፣ ብዙ ሰው ተሰዷል፣ ብዙ ሰው ታስሯል። አንተ ለማንና ለምን እንደምታገለግል ከዚህ በላይ የማሰቢያና የማንሰላሰያ ጊዜ የለህም። መወሰን ያለብህ አሁን ነው። መስከረም 2/01/2010 አገር አቀፍ የሥራ ማቆም አድማ ተጠርቷል። በአዲስ ዓመት ምክንያት አስፈቅደህም ሆነ መሳሪያህን አስረክበህ ሃገርክን ካልገባህ መሃል አገር ፈራርሶ አንተ ዳር ላይ ተቋርጠህ እንደምትቀር እወቀው። የሰናይት አባት "እኛ ኤርትራን ከሻዕቢያ ወረራ እየጠበቅን ወያኔ ግንቦት 20 ሃገሪቱን በመቆጣጠሩ መሪዎቻችን ወደ ውጭ ሲሄዱ እኛ ትራንስፖርት አጥተን ያን ሁሉ መንገድ ሌትና ቀን በባዶ እግራችን ያለ ስንቅ በልመና እንጀራና ውሃ ከዘመድ ለመገናኘት በቃን" ብሎ የሚነግረን ተረት የሚመስል ታሪክ በፍጹም እንዳትረሳው። ህዝቡ በዘር ተከፋፍሎ፣ ፍትህ አጥቶ በወሰን እየተጣላ፣ በግብር እያለቀሰ የሚኖር ሰው እንደ ሰናይት አባት አብልቶ አጠጥቶ መንገድ አሳይቶ የሚሸኝህ ሳይሆን እንደተለከፈ ውሻ በየደረስክበት ሁሉ ቀጥቅጦ እንደሚገድልህ አውቀህ ዛሬውኑ ወስን። ወንድሜ ሆይ ሰማይ እሩቅ፣ አደራ ጥብቅ ነውና አሁንም ደጋግሜ የምነግርህ ከወገን ከዘመድ ጋር ለመገናኘትና አብሮ ለመኖር ወሳኝ ሰዓት ላይ ነህና እንዳትፀፀት ዓይኖችህ አለቃዎችህን ሳይሆን ወገኖችህን ይመልከቱ። የግል ፎቶህን ለደህንነትህ ስል አላወጣሁትም። እህትህ አያንቱ ነኝ።
@ድር ቢያብር አንበሳ ያስር..Image may contain: 4 people, people standing

No comments:

Post a Comment