Monday, September 4, 2017

የኦብነግ ስራ አስፈጻሚ ተላልፎ መሰጠት የፈጠረውን ቁጣ ለማብረድ ህወሃት የተወሰኑ የኦብነግ አመራሮች ተፈቱ (ኢሳት ዜና ፣ ነሃሴ 29 ቀን 2009 ዓም)


የኦጋዴን ብሄራዊ ነጻ አውጭ ግንባር ( ኦብነግ) የስራ አስፈጻሚ አባል የሆነው ኮማንደር አብዲከሪም ሼክ ሙሴ በሰማሊያ መንግስት ተላልፎ ለኢትዮጵያ የደህንነት አባላት ከተሰጠ በሁዋላ፣ በመላው አለም የሚገኙ ሶማሊያውን ተቃውሞአቸውን መግለጻቸው ለፕሬዚዳንት ሙሃመድ አብዱላሂ መንግስትም ሆነ ለህወሃት አገዛዝ ያልተጠበቀ አደጋ ይዞ መጥቷል። Bilderesultat for ኦብነግ
ሶማሊያውያን ፕሬዚዳንቱና ጠ/ሚኒስትሩ ስልጣናቸውን እንዲለቁ እና በአገር ክዳት እንዲጠየቁ እየጠየቁ ነው። የግለሰቡ መያዝ በኢትዮጵያ ሶማሊያውያን ዘንድ የፈጠረው ንዴት ለማብረድ በኦብነግ አባልነት ስም ለአመታት ታስረው ሲሰቃዩ የነበሩ ከ10 ያላነሱ የኦብነግ አባላት ሰሞኑን እንዲፈቱ ተደርጓል። 
የህዝቡን ቁጣ ተከትሎ የሶማሊያ ባለስልጣናት እርስ በርሳቸው መከፋፈላቸውም ታውቋል። በርካታ የፓርላማ አባላት ፕሬዚዳንቱ ማብራሪያ እንዲሰጡ እየጠየቁ ነው። 
በሶማሊያ ውስጥ ያለውን ጉዳይ ከሚከታተሉ የህወሃት ባለስልጣናት መካከል አንዱ የሆነውና የኢጋድ አማካሪ በመሆን የሚሰራው ጄኔራል ገብራይ፣ ኮማንደር አብዲከሪም ተላልፈው እንደተሰጡ የኢሳትን ዜና በፌስቡክ ገጹ ላይ በመለጠፍ ደስታውን የገለጸ ሲሆን፣ ግለሰቡ ተላልፎ እንዲሰጥ ከአንድ ወር በላይ ለሆነ ጊዜ መድከሙን ገልጿል። ጄኔራል ገብሬ ለሶማሊያ ፕሬዚዳንት ፋርማጆ፣ ለጠ/ሚኒስትርሃሰን አሊና ለሶማሊያ የደህንነት ሃላፊ ሳንባሎልሼ እንዲሁም ለፑንትላንድ ፕሬዚዳንት እና በሂደቱ ላይ ለተሳተፉት ሁኑሉ ምስጋናውን ገልጿል። 
ይህ የህወሃት ባለስልጣን የሶማሊያ መንግስት ኮማንደር አብዲከሪምን አሳልፎ ከመስጠቱ በፊት በቲውተር አካውንቱ የሶማሊያን ፕሬዚዳንትንና ጠ/ሚኒስትሩን ሽብረተኞችን የሚረዱ ናቸው በማለት ከሷቸው ነበር።

No comments:

Post a Comment