Thursday, November 30, 2017

Support ESAT by Signing Up for Monthly Subscription - Ethiopia

Tarik Yifreden ሻምበል በላይነህ

የዛሬ የዕለተ ሓሙስ ህዳር 21 ቀን 2010 ዓ.ም ፕሮግራማችን ዜና .(አርበኞች ግንቦት 7 ድምፅ ሬዲዮ)

* በተለያዩ የኦሮሚያ አካባቢዎች የተቃውሞ ሰልፎች እንደቀጠሉ መሆኑ ተዘገበ
* ህወሓት የሥልጣን ሹም ሽር ማድረጉ በይፋ ተገለጸ
* በኦሮሚያና ኢትዮጵያ ሶማሌ ክልል እንደገና ባገረሸው ግጭት የመከላከያ ሠራዊት አባላት ተሳታፊ መሆናቸው ታወቀ
፠የፊታችን ቅዳሜ ህዳር 23 - 2010 ዓ/ም አውሮፓ ቤልጅም ውስጥ ኢትዮጵያ ወድየት በሚል ርዕስ ስር ድልድይ በአውሮፓ የኢትዮጵያ ማህበር አንድ የመወያያ መድረክ አዘጋጅቷል ይህንን መድረክ አስመልክቶ ከተሳታፊዎቹ አንዱ የሆነውን አቶ አናንያ ሶሪ አነጋግረነዋል እንደሚከተለው እናቀርብላችኋለን፡፡
www.patriotg7.org
Image may contain: sky and outdoor

መሀል ኢትዮጵያ- አዲስ አበባ (ጋዜጠኛ መሳይ መኮንን)


ፍርድ ቤት ውስጥ ህዝቡ በእንባ ይራጫል። አንድ ሰውነቱ በግርፋት የተዘለዘለ እስረኛ ልብሱን አውልቆ ''እዩት ሰውነቴን። አኮላሽተውኛል። ዘር እንዳይኖረኝ አድርገውኛል።'' እያለ ሲቃና ለቅሶ ባሸነፈው ድምጽ ይማጸናል። ''የኢትዮጵያ ህዝብ ይፍረደኝ''ም አለ። ፍርድ ቤቱ በሀዘን ክው ብሎ ቀረ። ሁሉም ተላቀሰ። አሁንም እዚያው አዲስ አበባ ወጣቷ ንግስት 10ሩም የእጆቿ ጥፍሮች ተነቅለው በኪሶቿ ይዛለች። የደረሰባት ቶርቸር መልኳን አገርጥቶታል። በጉጠት የተነቀሉት ጥፍሮቿን እንድትይዛቸውም አልተፈቀደም። በኋላም በህወሀት ገራፊዎች ተነጥቃለች። የሻሸመኔዋ ሸጊቱም ትናገራለች ''ጆሮዬ እስኪደማ ድረስ ተደብድቤ ተጎድቷል።ግራ እጄ ታሟል። በእግራቸው ነበር የሚረግጡኝ። ጸጉሬን እየጎተቱ ነበር የሚደበድቡኝ።''
ሁለቱ የዋልድባ መናኞች በማዕከላዊ የደርሰባቸው ስቃይና ድብደባ ቃላት አይገልጸውም። የህወሀት ደህንነቶች ሌሊትን አልፈዋቸው አያውቁም። እኚህን ዓለምን የተጠየፉትን መናኞች ዘቅዝቀው በመደብደብ፣ በመዝለፍ፣ በማንቋሸሽ ይህ ነው የማይባል ስቃይ እያደረሱባቸው ነው። ልብሰ ተክህኖአቸውን፡ ቆባቸውን እንዲያውልቁና የእስረኛ ዩኒፎርም እንዲለብሱ ነው ግርፊያውና ስቃዩ። ከዚህ ቀደም አበበ ካሴ አስሩንም ጥፍሮቹን በጉጠት ተነቅለዋል። ወ/ሮ እማዋይሽ ጡታቸው በኤሊክትሪክ ሽቦ ተተልትሏል። ብዙ የኢትዮጵያ ልጆች በማዕከላዊ ተኮላሽተዋል። ተቀጥቅጠዋል። የስቃይ መዓት ቆጥረዋል። ከትላንት እስከ ዛሬ።
ሰሜን ኢትዮጵያ- መቀሌ
ዝሆኖቹ ረጅሙን ስብሰባ ተቀምጠዋል። የሚያስጨንቃቸው የኢትዮጵያ ጉዳይ አይደለም። ጓዛቸውን አስጠቅልሎ ለሁለት ወራት መቀሌ የከተታቸው ስለኢትዮጵያውያን ተጨንቀው ተጠበው አልነበረም። የትግራይን የበላይነት ለተጨማሪ ዓመታት አስጠብቀን እንዴት እንቆያለን? የሚለው ላይ በአካሄድ ተለያይተው እንጂ። 77ቢሊየን ብር ዱቄት ያደረገውን አባይ ጸሀዬን መርቀው፡ አባይ ወልዱን ረግመው ዝቅ አድርገዋል። የማዕከላዊ ሰቆቃ እስር ቤት አዛዥ፡ ናዛዥ፡ ገራፊ አስገራፊ፡ የሆነውን ጌታቸው አሰፋን ሸልመው አዜብን ሸኝተዋል። በየነ ምክሩን አዋርደው፡ ጌታቸው ረዳን ከፍ አድርገዋል። ጉልቻ ቀያይረው፡ ከዝንጀሮ መሀል አንዱን ሊቀመንበር መርጠው፡ ወንበር ተለዋውጠው ከጨረሱ በኋላ ለኢትዮጵያ ህዝብ ''የምስራች፡ ምስር ብላ'' ሊሉት ተዘጋጅተዋል።

Wednesday, November 29, 2017

ESAT Daily News Amsterdam November 29,2017

Ethiopia: Thousands of university students left campus as protest continues ESAT News (November 28, 2017)

Protest by university students against the regime in Ethiopia continued as about 35,000 students of the Haromaya University left their campuses.
The students of Haromaya University had left their campuses a week ago but returned as the Aba Gedas, traditional leaders of the Oromos, promised to broker a deal and obtain a favorable response from authorities.
The students demand that the spy network of the regime in their campus should be abolished. Students say the “peace forum” as it is euphemistically called, is a group set up by the regime to spy on students.
Meanwhile, security forces locked down Jimma University to prevent students from leaving their campus.
In another development residents of Sawla town in Gamu Gufa Zone had burnt down the local tax office in protest against tax hikes. The locals say they would not give their money to a regime that tortures and kills citizens.
In the eastern commercial town of Aweday, residents blocked highways while in Wollega, in the towns of Mendi and Bigg, protesters demand regime’s army to leave their towns. They accused that the army had carried out extrajudicial killings.

Monday, November 27, 2017

ህወሀት ጉልቻ እየቀያየረ ነው። (ጋዜጠኛ መሳይ መኮንን)


የፊት ለውጥ ይዞ ሊመጣ መሆኑ ታውቋል። አዜብ መስፍን ባፋንጉሎ ተብላለች። የኢትዮጵያን ህዝብ ደም የመጠጠው ኢፈርት የተሰኘው ድርጅት የንትርኩ ማጠንጠኛ ይመስላል። እነአዜብና በየነ ምክሩ ከዚሁ ድርጅት ጋር በተያያዘ አይናቸው ደም በለበሰባቸው በእነስብሃት ነጋ ብጫና ቀይ ካርድ ተሰጥቷቸዋል። እነስብሃት ለጊዜው በለስ ቀንቷቸዋል። የመለስ ሌጋሲን ከመለስ ጋር እንዲቀበር የፈለጉት እነስብሃት የሌጋሲውን አቀንቃኞች በጠረባ እያሏቸው ነው። ስብሰባ ሳይጠናቀቅ መግለጫው መቅደሙ ግን ገና ጦርነቱ ያላበቃ መሆኑን ያሳያል።
እነኣዜብ ኢፈርትን ለነስብሃት አስረክበው ቤታቸው ይገባሉ? የመለስ ዜናዊ አምላኪ የሆነው ሳሞራ የኑስ ምን ብሎ ይሆን? ኢፈርትን የተቆጣጠረ ሻምፒዮን ይሆናል። የኢኮኖሚ ጡንቻ የሚሰጠው ኢፈርት ለፖለቲካው የበላይነት የጀርባ አጥንት መሆኑን አቦይ ስብሃት ልቅም አድርገው ያውቁታል። እናም የመለስን ሌጋሲ ከነአስጠባቂዎቹ መንግሎ ለመጣል መንገዱን በኢፈርት ጀምረውታል። በፖለቲካው ቀጥለዋል። እነአዜብ እጃቸውን አጨብጭበው ኢፈርትን ካስረከቡ የመልስን ሌጋሲ ብቻ ታቅፈው ይቀራሉ።
ፈረንጆቹ the bottom line ይላሉ። ዋናው ጉዳይ እንደማለት ነው። እናም ዋናው ጉዳይ የአዜብ መወገድና የስብሃት ማንሰራራት አይደለም። ጉልቻ ቢቀያየር ትርጉም የለውም። ወጥ አያጣፍጥም። ኢትዮጵያን አይቀይርም። ሌሎችንም ቱባ ባለስጣናት በማባረርና በእስር የሚገኙ ተቃዋሚዎችን በመፍታት ይህቺን የምጥ ጊዜ ለመሻገር ህወሀት ተዘጋጅቷል። ፊት በመቀየር፡ ጉልቻ በመለወጥ ህወሀት የሚድን ከመሰለው ተሳስቷል። ህወሀት ከነግሳንግሱ፡ ከነኮተቱ፡ ከራስ ጠጉሩ እስከ እግር ጥፍሩ፡ አንድም ትራፊ ሳያስቀር ካልተወገደ በቀር ለውጥ አይኖርም። የኢትዮጵያ ህዝብ የሚናፍቀው ያንን ነው።Image may contain: 1 person

Bekebero Gudguad ሻምበል በላይነህ

Enough hereafter by Hanisha Solomon

Sunday, November 26, 2017

የአማራ ክልል ምክር ቤት አባላትና የብአዴን ማአከላዊ ኮሚቴ ጽ/ቤት ኃላፊ አለምነው መኮነን መካከል ግጭት መፈጠሩ ታወቀ፡፡ (የአርበኞች ግንቦት 7 ድምፅ ሬዲዮ)

የአማራ ክልል ምክር ቤት 5ተኛ ዙር 3ተኛ ዓመት የስራ ዘመን 8ተኛ መደበኛ ጉባዔ በትናንትናው ዕለት በባህርዳር የተጀመረ ሲሆን ከጅምሩ አፈ ጉባኤው ከአቀረቡት አጀንዳ በተጨማሪ የምክር ቤት አባላት በአጀንዳነት መያዝ አለባቸው በማለት በርካተ ርዕሰ ጉዳዬችን በማንሳታቸው በተለይም በኢትዮ ሱዳን ድንበር ፡ በትግራይ እና በሰሜን ጎንደር በኩል ያለው የአማራ ድንበር ፡ በትግራይ እና በወሎ በኩል ያለው የአማራ ደንበር ፡ በእኩል ተጠቃሚነት በኩል ከኢንዱስትሪዎች እና ኢንቨስትመንቶች ፡ እንዲሁም ከህወሐት የበላይነት ወዘተ ጋር የመሳሰሉት በአጀንዳነት ሊያዙ ይገባል የሚሉ ጉዳዬች በመነሳታቸው በስብሰባው አዳራሽ ከፍተኛ ውዝግብ ተነስቷል ፡፡ ከዚያም የብዓዴኑ ሹም ገዱ አንዳርጋቸው ጣልቃ በመግባት መጀመሪያ በቀረቡት የስራ ክንውኖች ላይ እንወያይና በቀጣይ በቀረቡት ነጥቦች እንመክራለን በሚል በሰነዘረው ሀሳብ ስብሰባው መጀመር ከነበረበት ሰዓት እጅግ ዘግይቶ ተጀመረ እንዲያም ሆኖ በትምርት ዙሪያ በቀረበው ሪፖርት ላይ አለመግባባት በመፈጠሩ ፡ ይሄን መረጃ ለሌላ ጊዜ እናቆየውና በምክር ቤቱ አባላትና በአለምነው መኮነን መካከል ግጭት ወደ ተፈጠረበት መረጃ እንለፍ በማለት ተስማምተው ፡ የምክር ቤቱ የቀን ውሎ እንዳበቃ 12:00 ሰዓት ሲሆን ከሰሜን ጎንደር ዞን ፡ ከሰሜን ወሎ ዞን እና ከዋግ ህምራ ዞን የመጡትን የምክር ቤት አባላት ከአዳራሹ እዲቆዩ በማድረግ አፈ ጉባኤውና ገዱ አንዳርጋቸው ከመድረኩ ወርደው በመድረክ ወንበር ላይ አለምነው መኮነን እና ምግባሩ ከበደ በብአዴን ውስጥ የብሔራዊ መረጃና ደህንነት ወኪል ሆኖ እየሰራ ያለው ተቀመጡ ፡፡ ከዚያም አለምነው እናንተን ነጥለን ወደ ኃላ እድትቆዩ ያደረግነው በጥዋቱ የምክር ቤት ጉባኤ መክፈቻ ላይ ከድርጅታችን ብአዴን አቋም ውጭ የሆኑ ሀሳቦችን ስታነሱ ሰምተናል ፡ እናንተ ወደ እዚህ ምክር ቤት የመጣችሁት ብአዴንን ወክላቹሁ እና ህዝቡም ለብአዴን ድምፅ ሰጥቶ ስለመረጣቹሁ ነው በመሆኑም በድርጅታችን የዲስፕሊን መመሪያ መሰረት ነው ልትንቀሳቀሱ የምትችሉት ፡ በትግራይ ክልል እና በአማራ ክልል ባሉ ድንበሮች የነበሩ ችግሮች ሁለቱ ድርጅቶች እና የአካባቢው ህብረተሰብ ተወያይቶ መፍትሔ የሰጠበትን አሁን ከዚህ ምክር ቤት ስብሰባ ላይ ማንሳት ተገቢ አይደለም ፡ ከሱዳን ጋር ያለውም ቢሆን ፀረ ሰላም ኃይሎች ከሚያራግቡት ውጭ ነው ሰላማዊ ነው ወዘተ እያለ እነዚህን የምክር ቤት አባላት ለማሳመን ቢሞክርም የምክር ቤት አባላቱ ንግግሩን አቋርጠው አንድ የምክር ቤት አባል ድንበርን በተመለከተ የትኛው ህዝብ ነው የተወያየውና የተስማማው ? ህወሓት ይዞት የቀረበውን አጀንዳ ካልተቀበልንም በአርበኞች ግንቦት ሰባት ተፈርጀን በአሸባሪነት እንጠየቃለን ፡ በዚህ ሁኔታ የሁለቱ ድርጅቶች ግንኙነት መሻከር የለበትም ፡ወዘተ... ተብሎ ማስፈራሪያ ቢሰጥም ይሄን ማስፈራሪያ ወደ ጎን በመተው የተከራከሩትን በማሰር በኃይል የተሰጠ ነው በማለት ተናገሩ ሌላም የምክር ቤት አባል በወሎ በኩል ምን መፍትሔ ሰጥታቹሁ ነው እንደዚህ የምትሉት ? እኛ እኮ ከህዝብ ጋር ነው ያለነው ህዝቡ የሚለውን ነገር በሙሉ በቅርበት የምንሰማው እኛ ነን በማለት ሲናገሩ ጉዳዩ ወደ ስድብና ንትርክ ሲያመራ ምግባሩ ከበደ ደግሞ " ይሄ አይነት ሀሳብ ከናንተ የመጣ አይደለም ሁላቹሁም የምትሉት የአርበኞች ግንቦት ሰባት አሸባሪው ቡድን ሀሳብ እና የትምክህተኞች ሀሳብ ነው ይሄ ደግሞ በህግ ያስጠይቃል " በማለት ሲናገር እኛ የምንለውን እናውቃለን እስከ መቼ ባሪያዎች ሆነን እንቀጥላለን ማስፈራራቱን እናየዋለን በማለት ቀድሞም ወደ ኃላ ቅሩ ብላቹሁ እኛን ነጥላቹህ ማስቀረታችሁ ህገ ወጥ ነው እኛ ተጠሪነታችን ለመረጠን ህዝብ እንጂ ለናንተ አይደለም በማለት መድረኩን ረግጠው ወጥተዋል ፡ አሁን ባለው ሁኔታ ውጥረቶች በርትተዋል፡፡

Support ESAT by signing up for monthly Subscription

Saturday, November 25, 2017

ESAT Latest News Sat 25 NOv 2017

በመከላከያና በደህንነቱ ዋና መስሪያ ቤት መካከል ያለው አለመግባባት ከፍተኛ ደረጃ ላይ መድረሱ ተሰማ (የአርበኞች ግንቦት 7 ድምፅ ሬዲዮ)


በአቶ ጌታቸው አሰፋ የሚመራው የብሄራዊ መረጃና ደህንነት መስሪያቤት እና በጄነራል ሳሞራ የሚመራው መከላከያ መካከል የተፈጠረው ያለመግባባት በግልጽ የሚታይበት ደረጃ ላይ መድረሱ ታውቋል። በመከላከያ ውስጥ ያሉ ከፍተኛ የጦር አዛዦች የደህንነቱ መስሪያ ቤት የሚያቀርበው መረጃ፤ ታእማኒነት የሌለው ነው በማለት በተደጋጋሚ ሲገልጹ ይሰማል። አቶ ጌታቸው አሰፋ በመከላከያ ውስጥ ያለውን ተሰሚነት ለማስፋት በሚል የሚወስዳቸው እርማጃዎች ቀጥታ ከጄነራል ሳሞራ ጋር እንዳጋጨው መረጃዎች ያመለክታሉ። Image may contain: 2 peopleጄነራል ሳሞራና የእሱ ደጋፊ የሆኑ የጦር አዛዦችን ለመቆጣጠር በሚል አቶ ጌታቸው አሰፋ በመከላከያ ውስጥ ለሱ የሚታዘዝ መረቦችን ለመዘርጋት ያደረገውን ሙከራ ተከትሎ በሁለቱ የህወሃት ቁንጮዎች መካከል ከፍተኛ የሆነ ያለመግባባት ተፈጥሯል። በመከላከያ ውስጥ ለአቶ ጌታቸው አሰፋ ጥሩ ምልከታ አላቸው የሚባሉ ከፍተኛ የጦር አዛዦች ላይ በመከላከያ የወታደራዊ መረጃ ዋና መምሪያ ስር የሚገኘው በመከላከያ ጸረ መረጃ መምሪያ አማካኝነት ከፍተኛ ክትትል እየተደረገባቸው ይገኛል። በአቶ ጌታቸው አሰፋ እና በጄነራል ሳሞራ መካከል ያለውን አለመግባባት ለመቅረፍ በሚል ዶ/ር ደብረጺዮን ገብረሚካኤል እና ሌ/ጄነራል ዮሃንስ ገ/መስቀል ለማሸማገል ያደረጉት ሙከራ አለመሳካቱን ከመከላከያ የተገኘው መረጃ ያመለክታል። ሌ/ጄነራል ዮሃንስ ገ/መስቀል አቶ ጌታቸው አሰፋ ከሚመራው የደህንነቱ ዋና መስሪያቤት ጋር ጥብቅ ቁርኝት እንዳለው ይታወቃል። ሌ/ጄነራል ዮሃንስ ገ/መስቀል አሁን በመከላከያ የወታደራዊ መረጃ ዋና መምሪያ ሃላፊ ከሆኑት ሜ/ጄነራል ገብሬ ዲላ በፊት በመከላከያ የወታደራዊ መረጃ ዋና መምሪያ ሃላፊ እንደነበሩ ይታወሳል። ሌ/ጄነራል ዮሃንስ ገ/መስቀል ከጄነራል ሳሞራ ጋር ባላቸው አለመግባባት ምክንያት ነው ከዚህ ሃላፊነታቸው እንዲነሱ የተደረገው። ሌ/ጄነራል ዮሃንስ፤ አቶ ጌታቸው አሰፋና ጄነራል ሳሞራን ለማስታረቅ ያደረጉት ሙከራም የከሸፈው መጀመሪያውኑ ሌ/ጄነራል ዮሃንስ ገ/መስቀል እና ጄነራል ሳሞራ የሚግባቡ ባለመሆኑ ነው። አቶ ጌታቸው አሰፋ በመከላከያ ውስጥ የሚኖረውን ተጽኖ ለማስፋት ከሚጠቀምባቸው ሰዎች አንዱ ሌ/ጄነራል ዮሃንስ ገ/መስቀል እንደሆነ ይነገራል። ጄነራል ሳሞራ ሌ/ጄነራል ዮሃንስ ከደህንነቱ ዋና መስሪያቤት ጋር ያላቸውን ቅርርብ ጠንቅቆ እንደሚያውቀው ጉዳዩን በቅርብ የሚከታተሉ አካላት ይገልጻሉ። ከዚሁ ጋር ተያይዞ አቶ ጌታቸው አሰፋ በመከላከያ ውስጥ ያለውን ተሰሚነት ለማስፋት በሚል ከዶ/ር ደብረጺዮን ገ/ሚካኤል ጋር በቅርበት እንደሚሰራ ከደህንነቱ መስሪያ ቤት የተገኘ መረጃ ያመለክታል። አቶ ደብረጺዮን መከላከያው ውስጥ ባለው በጎ ግንኙኑነት የተነሳ፤ አቶ ጌታቸው አሰፋ በዶ/ር ደብረጺዮን በኩል ነው፤ በመከላከያ ውስጥ ያለውን ፍላጎት ለማስጠበቅ የሚንቀሳቀሰው ሲሉ በደህንነት ውስጥ ያሉ አካላት ይገልጻሉ። ዶ/ር ደብረጺዮን በመከላከያ ውስጥ ያለውን ተሰሚነት ምክንያት በማድረግ አቶ ጌታቸው አሰፋን እና ጄነራል ሳሞራን ለማግባባት ያደረገው ሙከራ አለመሳካቱ ታውቋል። ጄነራል ሳሞራ አቶ ጌታቸው አሰፋ መከላከያን ለመቆጣጠር የሚያደርገውን ሙከራ እንዲያቆም በሃይለ ቃል መናገሩ ጉዳዩን በቅርበት የሚከታተሉ አካላት ይገልጻሉ። በተጨማሪም የደህንነቱ ዋና መስሪያ ቤት የሚያቀርበው ሪፖርቶች በአብዛኛው በውሸት የተሞሉ በመሆናቸው ከደህንነቱ መስሪያ ቤት የሚመጣን ማንኛውም ሪፖርት በጥንቃቄ እንዲታይ ጄነራል ሳሞራ ትእዛዝ ማስተላለፉን ተከትሎ አቶ ጌታቸው አሰፋን ያስቆጣ ጉዳይ ሆኗል። በአሁን ሰአት ከፍተኛ የጦር አዛዦች ከደህንነቱ ዋና መስሪያ ቤት የሚመጣን ማንኛውንም የመረጃ ሪፖርት ከመጠቀም ይልቅ በመከላከያ ስር ባለው የወታደራዊ መረጃ ዋና መምሪያ በኩል የሚመጡ መረጃዎች ላይ እምነት እንዲያሳድሩ ሆኗል። በመከላከያ የወታደራዊ መረጃ ዋና መምሪያ፤ የደህንነቱ ዋና መስሪያ ቤት የስራ ክልል በሆነው በሲቪል መረጃ ስራዎች ውስጥ መግባቱ በሁለቱ ተቋማት መካከል ለተፈጠረው ያለመግባባት አንዱ ምክንያት እንደሆነ ይነገራል። በመከላከያና በደህንነቱ ዋና መስሪያ ቤት መካከል ያለውን ያለመግባባት ለመፍታት በሚል ተደጋጋሚ ጥረቶች ቢደረጉም እስካሁን ድረስ በጄነራል ሳሞራና በአቶ ጌታቸው አሰፋ መካከል ያለው ግንኙነት እንደሻከረ ይገኛል።

Thursday, November 23, 2017

በኮማንደር ደሳለኝ ላይ ለተፈጸመው ግድያ አርበኞች ግንቦት7 ሃላፊነቱን ወሰደ (ኢሳት ዜና፣ ህዳር 14 ቀን 2010 ዓም )

በባህርዳር ከተማ የፌደራል ፖሊስ አዛዥ በሆነው ኮማንደር ደሳለኝ ልጃለም ላይ ህዳር 12 ቀን 2010 ዓ/ም ከምሽቱ 4:45 በመኖሪያ ቤቱ ግቢ ውስጥ ለተፈጸመው ግድያ ንቅናቄው ሃላፊነቱን ወስዷል። ግንባሩ ባወጣው መግለጫ የፖሊስ አዛዡ በከተማው ተካሂዶ በነበረው ህዝባዊ ተቃውሞ ላይ ከህወሀት የተሰጠውን መመሪያ በማስፈጸም ለበርካቶች ግድያና ስቃይ ተጠያቂ ነበር።
የኮማንደሩ አስከሬን ከፈለገ ህይወት ሆስፒታል ምርመራ ቢደረግለትም እጅግ ጥበብ በተሞላበት ድምፅ በሌለው መሳሪያ ጭንቅላቱ ላይ ሁለት ቦታ ተወግቶ ሊሞት ችሏል ። ኮማንደሩ በ ብአዴን 37ኛ ዓመት የምስረታ በዓል ላይ ከልዩ እንግዶች ጋር የራት ግብዣ ላይ ተገኝቶ ካመሸ በሁዋላ የስንብት እርምጃ እንደተወሰደበት ግንባሩ ገልጿል።
ግንባሩ አክሎም፣ የመከላከያ የደህንነት የከተማ ምድብ ኃላፊ ሆኖ ሲሰራ የነበረ፣ የህወሓት የደህንነት አባል ህዳር 12 ቀን 2010 ዓ/ም ከምሽቱ 4:15 ሲሆን በባህርዳር ከተማ ቀበሌ 04 ከአንድ ጭፈራ ቤት ሲዝናና በነበረበት ሰዓት በአርበኞች አባላት ታፍኖ ከተወሰደ በኃላ በባህርዳርና በመሸንቲ ከተማ መሃል የግድያ እርምጃ እንደተወሰደበት አስታውቋል። ይህ የህወሓት ወታደራዊ መረጃ መኖሪያውን ባህርዳር አየር ኃይል ምድብተኛ ግቢ በማደረግ ለአለፉት 3 ዓመታት በባህርዳር ከተማ የመረጃ ኃላፊ ሁኖ በርካቶችን ያስገደለ እና በተለይ በአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ የጄኔራል ፍሳሀ እና የጄኔራል ተስፋዬ ዋና አማካሪ በመሆን በርካታ ግፎችን መፈጸሙንም ጠቅሷል። ግንባሩ ተመሳሳይ እርምጃዎችን መውሰድ እንደሚቀጥልም አስታውቋል።
ግንባሩ ባወጣው መግለጫ ዙሪያ የክልሉን ፖሊስ ለማናገር ያደረግነው ጥረት አልተሳካም።

ESAT Zegabi Modern Ethiopia Full Version 23 November 2017

ESAT Efeta Nov 22 2017

Tuesday, November 21, 2017

- ሰበር ዜና - በረከት ስምኦን - ሰለ አማራ ክልል ጠገዴ ምስጥር አወጡ !! Nov.. 21/2017

Jacky Gosee 2017 coming soon - Menalegn yenate - ምን አለኝ የናቴ

ሜቴክ ከተቋቋመበት ስልጣን ውጪ በአቶ አርከበ እቁባይ ውሳኔ ከኢሉ አባቦራ ያዩ ወረዳ የድንጋይ ከሰል እያወጣ መሸጡ...

ሮበርት ሙጋቤ ስልጣናቸውን በፍቃዳቸዉ ለቀቁ

ለ ፫፯ ዓመታት በዙምባቡዌ ስልጣን ላይ የቆዩት ሮበርት ሙጋቤ ስልጣናቸውን በፍቃዳቸዉ መልቀቃቸውን አሥታዉቀዋል። የአገሪቱ ም/ቤት ሙጋቤን በሕግ ለመጠየቅ እየመከረ ባለበት ሠዓት ነበር ሙጋቤ የመልቀቂያ ደብዳቤያቸዉን ለአፈ ጉባኤዉ ያስገቡት።
ዝርዝር ይኖረናል።
Image may contain: 1 person

የአማራ ክልል የደህንነት መዋቅር እንደገና ቀየሩ (ኢሳት ዜና ህዳር 11 ቀን 2017 ዓም)

በባህርዳር ከተማ በ ዳግማዊ ዮሃንስ ሆቴል ላይ የቦንብ ጥቃት መድረሱን ተከትሎ አቶ አለምነው መኮነን በከተማዋ ላይ ተደጋጋሚ ጥቃት የሚደርስበት ምክንያት ምንድነው በማለት የደህንነት አባላቱን ሰብስበው ጥያቄ ማቅርባቸውን የገለጹት ምንጮች፣ ችግሩ ያለው በደህንነቱ አባላት ላይ ነው በማለት አንዳንድ አባላቱን በማንሳት ሌሎችን ሹመዋል። Image may contain: 1 person
አቶ አለምነው “የአማራ ደህነት ቢሮ ብዙ መዋቅራዊ ለውጥ ቢደረግበትም ምንም ለውጥ ማምጣት አልቻለም፣ በዚህ ከተማ ፀረ ሰላም ሀይሉ በተደጋጋሚ እንደልቡ እየፈነጨበት ነው፣ የዚህ ከተማ ችግር ከጊዜ ወደ ጊዜ እየሰፋ ነው” በማለት የክልሉን የደህንነት አባላት አጥብቀው የወቀሱ ሲሆን፣ እርሳቸውና አስተዳደራቸው በደህንነት ተቋሙ ላይ እምነት ማጣታቸውን ተናግረዋል።
በአስተዳደርና ፀጥታ ጉዳይ ቢሮ የመረጃ ክፍል ሃላፊ የነበረውን አቶ አየለ አናውጤን በማንሳት በምትኩ አቶ የማነ ታደሰ የተባለ የህወሃት አባል ሀላፊ አድርገው መሾማቸውን ምንጮች ገልጸዋል። አቶ አለምነው በቅርቡ አቶ ፍሰሃ ወ/ሰንበትን በማንሳት አቶ እዘዝ ዋሴን የክልሉ የደህንነት ቢሮ ሀላፊ አድርገው ሾመው ነበር። አቶ አለምነው በደህንነት መዋቅሩ ውስጥ ያሉ የአማራ ተወላጆችን እያስወጡ ቦታውን ህወሃቶች እንዲይዙት እያደረጉ ነው የሚል ከፍተኛ ወቀሳ እየቀረበባቸው ነው።

ESAT Special Interview with Professor Birhanu Nega Part two November 2017

ESAT Menalesh Meti, Mimi Sebhatu radio on Azeb Mesfin and Al - Amoudi

አርበኞች ግንቦት 7 ለአንድነትና ለዴሞክራሲ ንቅናቄ ሊቀመንበር የሆኑት ፕሮፌሰር ብርሃኑ ነጋ (አርበኞች ግንቦት 7 ድምፅ ሬዲዮ)


የዛሬ የዕለተ ማክሰኞ ህዳር 12 ቀን 2010 ዓ.ም ፕሮግራማችን
ዜና .... 
* የአርበኞች ግንቦት 7 ታጋዬች የህወሐት ወታደራዊ ካምፕ ውስጥ ሰርገው በመግባት ጥቃት ፈፀሙ፡፡
* በሻኪሶ ሰሞኑን ትልቅ ህዝባዊ ተቃውሞ መካሄዱ ታወቀ፡፡
* የደቡብ ክልል የጸጥታ አካላት ለደህንነት አካላት ቀጥታ ሪፖርት እንድያደርጉ ታዘዙ፡፡
ከዕለቱ ዜና በማስቀጠል፡-
የድርጅታችን አርበኞች ግንቦት 7 ለአንድነትና ለዴሞክራሲ ንቅናቄ ሊቀመንበር የሆኑት ፕሮፌሰር ብርሃኑ ነጋ ለአርበኞች ግንቦት 7 ድምፅ ሬዲዮና ለኢሳት አፋን ኦሮሞ እንዲሁም ለኢሳት የትግረኛ ፕሮግራም በወቅታዊ የሃገራችን ጉዳዮች ላይ የሰጡትን ቃለ ምልልስ እናቀርባለን ፡፡ ትከታተሉን ዘንድ ግብዣችን ነው፡፡

Image may contain: 5 people, people sitting

Sunday, November 19, 2017

አርበኞች ግንቦት 7 ለአንድነትና ለዴሞክራሲ ንቅናቄ ከፍተኛ አመራርና የውጭ ጉዳዮች አስተባባሪ የሆኑትን አቶ ነዓምን ዘለቀን "ወቅታዊ የሃገራችንን ሁኔታ (አርበኞች ግንቦት 7 ድምፅ ሬዲዮ)

በዛሬ የዕለተ ዕሁድ ህዳር 10 ቀን 2010 ዓ.ም ፕሮግራማችን
ትንታኔ መሰረት ያደረገ የፀጥታ ዕቅድ" የሚል ሰነድ ከወያኔ ሾልኮ ወጥቷል በዚህ ሰነድ ላይ በተዘረዘሩ በርካታ ርዕሶች ላይ ሰፋ ያለ ማብራሪያ ሰጥተዋል ፡፡
በመጨረሻም ተባብረን ማድረግ ብንችል አገዛዙን መጣል፣ ከዚህ አፋኝ ስርዓት መላቀቅ እንችላለን ብለው ያመኑትንም ተናግረዋል ትከታተሉ ዘንድ ግብዣችን ነው፡፡
www.patriotg7.org

Image may contain: 1 person, suit and beard

Friday, November 17, 2017

የጸጥታ ሀይሎች እና ማህበረሰብ በብሔራዊ ደህንነት ምክር ቤት የተወሰኑ ውሳኔዎች በጌታቸው አሰፋ የሚመራው የድህንነቱ መ/ቤት ፍላጎቶች ለማሳካት በሚል የቀረበ መሆኑ ታወቀ።

የአርበኞች ግንቦት 7 ታጋዬች የህወሐት ወታደራዊ ካምፕ ውስጥ ሰርገው በመግባት ጥቃት ፈፀሙ፡፡ (የአርበኞች ግንቦት 7 ድምፅ ሬዲዮ)

ህዳር 7 ቀን 2010 ዓ/ም ንጋት 10:55 ሲሆን ጎንደር አዘዞ ወታደራዊ ካምፕ በአርበኞች ግንቦት 7 ታጋዮች ጥቃት ተፈፀመበት ፡፡ ከመስከረም ወር 2010 ዓ/ም ጀምሮ ካምፑን ቀደም ሲል ከነበረው 24ኛ ክፍለ ጦር የተረከበው የ42ተኛ ክፍለ ጦር የጦር መጋዝን ንጋት ላይ እጅግ ጥንቃቄ በተሞላበት መልኩ በተፈፀመው ጥቃት መጋዝኑ በከፊል የተቃጠለ መሆኑ ታውቋል፡፡ ከዚያም የአየር መንገድ እና የጎንደር ከተማ እሳት አደጋ ደርሰው በከፍተኛ ርብርብ ሙሉ በሙሉ ከመቃጠል ሊድን ችላል ፡ ይህ ጥቃት ህዳር 6 ቀን 2010 ዓ.ም. ምሽት ከካርቱም ወደ መቀሌ ነዳጅ ጭኖ ሲመጣ በነበረው ተሽከርካሪ ላይ ጥቃት የተፈፀመ ሲሆን ይሄን ጥቃት በፈፀሙ ታጋዮች ላይ ለክትትል ወታደሮች ሲወጡ ነው የጦር መጋዝኑ ላይ ጥቃት የተፈፀመው ፡ ከጥቃቱ ጋር በተያያዘ ተረኛ መኮነን የነበረው ምክትል መቶ አለቃ ደረጄ ጉደታ እና የበር ዘብ የነበረው ምክትል አስር አለቃ የኔሁን ጥላዬ በቁጥጥር ስር ውለው ሲታሰሩ በካምፑ ጭልጋ በር በተባለ ማማ ላይ የነበሩ ሁለት ወታደሮች ከነ ሙሉ ትጥቃቸው ተሰውረዋል፡፡
ምስል ከፋይል
Bilderesultat for አርበኞች ግንቦት 7

ESAT Special Interview with Prof Birhanu Nega Part 1 Nov 2017

አርበኞች ግንቦት 7 ለአንድነትና ለዴሞክራሲ ንቅናቄ ሊቀመንበር የሆኑት ፕሮፌሰር ብርሃኑ ነጋ (በአርበኞች ግንቦት 7 ድምፅ ሬዲዮ)

የዛሬ የዕለተ አርብ ህዳር 08 ቀን 2010 ዓ.ም ፕሮግራማችን
ዜና .... 
ከዕለቱ ዜና በማስቀጠል፡-ለአርበኞች ግንቦት 7 ድምፅ ሬዲዮና ለኢሳት አፋን ኦሮሞ እንዲሁም ለኢሳት የትግረኛ ፕሮግራም በወቅታዊ የሃገራችን ጉዳዮች ላይ የሰጡትን ቃለ ምልልስ ሶስተኛው ክፍል እናቀርባለን ፡፡ ትከታተሉን ዘንድ ግብዣችን ነው፡፡

www.patriotg7.orgImage may contain: 5 people, people sitting

የአርበኞች ግንቦት 7 ታጋዬች ከሱዳን ነዳጅ ጭኖ ይጓዝ በነበረ የህወሓት ተሽከርካሪ ላይ ጥቃት ፈፀሙ፡፡ (የአርበኞች ግንቦት 7 ድምፅ ሬዲዮ)


ህዳር 7 ቀን 2010 ዓ/ም ከምሽቱ 12 :48 ሲሆን በሰሜን ጎንደር ዞን ጭልጋ ወረዳ ጓንግ ወንዝ ድልድይ ከመድረሱ በፊት 100 ሜትር ሲቀረው መታጠፊያ ቦታ ላይ በህወሓት ወታደሮች ከፊትና ከኃላ ታጅቦ ሲጓዝ በነበረ ነዳጅ በጫነ ቦቴ መኪና ላይ በተፈፀመ ጥቃት ተሽከርካሪው ሙሉ በሙሉ አስከ ተጫነው ነዳጅ ሲወድም በአሽከርካሪው እና በሚያጅቡት ወታደሮች ላይ ከፍተኛ ጉዳት ደርሷል ፡፡ ከአሁን ቀደም እንደሚታወቀው ወያኔ የአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ በአወጀበት ወቅት "ቀይ ዞን" በማለት በአደገኛ ቀጠና ከፈረጃቸው ቦታዎች አንዱ ከጎንደር መተማ ፡ ሱዳን ያለውን መስመር ነው፡፡ በመሆኑም ከዚያ ጊዜ ጀምሮ ከንጋት 12:00 አሰከ ቀን 11:00 ብቻ ተሽከርካሪዎች እንደሚያልፉ እና ከዚህ ሰዓት በኃላ አይደለም ማንኛውም ተሽከርካሪዎች ይቅርና ወታደራዊ ተሽከርካሪዎችም በመንገድ አያልፉም ፡፡ በመሆኑም የህወሓት ወታደሮች አጅበውት ከሱዳን በኩል የመጣው ይሄ ነዳጅ የጫነ ተሽከርካሪ ከነጋዴ ባህር ማደር ሲገባው ከዚያ እንደማያድር ቢመሽም እንኳን ጎንደር መግባት እዳለበት ነዳጁ ለአስቸኳይ ግዳጅ ስለተፈለገ ታጅቦ እደሚሄድ መረጃው የደረሳቸው በአካባቢው የሚንቀሳቀሱ የአርበኞች ግንቦት 7 ታጋዬች ከጓንግ ወንዝ ባለው አቅጣጫ ደፈጣ በመጣል ይሄን በአጀብ ሊያልፍ የነበረን ወያኔ ለልዩ ግዳጅ ሊያውለው ያቀደውን ነዳጅ እስከነ ተሽከርካሪው ሙሉ በሙሉ በማውደም በሹፌሩና በአጃቢ ወታደሮች ላይ ጉዳት አድርሰዋል፡፡ በአሁኑ ሰዓት ይሄ ጥቃት በተፈፀመበት አካባቢ ውጥረት የነገሰ እና ፍተሻም በእጅጉ ተጠናክሮ የቀጠለ መሆኑ ታውቋል፡፡ ይህ በእንዲህ እዳለ ወያኔ ህዳር 7 ቀን 2010 ዓ/ም ከቀኑ 8:00 ሰዓት ጀምሮ ወደ ጎንደር ከተማ በሚያስገቡ 3 መግቢያዎች ላይ ኬላዎችን ማለትም ከሁመራና ከደባርቅ በኩል ወደ ጎንደር መግቢያ ፣ ከባህር ዳር በኩል ባለው መግቢያ እና ከመተማ በኩል ባለው መግቢያ ከፍተኛ ፍተሻዎችን እያደረገ ይገኛል ፡ይሄ የሆነበትም ምክንያት ወያኔ በህዝብ ስም የህወሓት ካድሬዎችን እና የእሱ ተላላኪ የሆኑ የብአዴን ካድሬዎችን "የሰላም ኮንፈረንስ" ብሎ የጠራውን ስብሰባ በጎንደር የሚያካሂድ ሲሆን የአርበኞች ግንቦት 7 ታጋዮች ወደ ከተማዋ ገብተው ጥቃት ይፈፅሙብኛል የሚል ስጋት በመኖሩ ነው ሲሉ የመረጃ ምንጮቻችን ገልፀውልናል ፡፡ በአሁኑ ሰዓት በጎንደርና በባህር ዳር ከተሞች እንዲሁም በደሴ ከተማ ከፍተኛ ውጥረት ነግሶ ይገኛል፡፡

Thursday, November 16, 2017

ESAT Special Interview with Prof Birhanu Nega Part 1 Nov 2017

ESAT Yesamintu Engeda Captain Mamo Habtewold p2 November 16 2017

የሕወሃት ማዕከላዊ ኮሚቴ ስብሰባ በከፍተኛ ውዝግብና ቀውስ መቀጠሉ ተሰማ (ኢሳት ዜና–ሕዳር 6/2010)

 ከአንድ ወር በላይ የዘለቀው የሕዝባዊ ወያኔ ሀርነት ትግራይ ማዕከላዊ ኮሚቴ ስብሰባ በከፍተኛ ውዝግብና ቀውስ ውስጥ መቀጠሉን የሕወሃት ደጋፊዎች ይፋ አደረጉ።
የቀድሞው ጠቅላይ ሚኒስትር መለስ ዜናዊ ባለቤት ወይዘሮ አዜብ መስፍን ስብሰባውን ረግጠው መውጣታቸውም ታውቋል።
ውዝግቡ በሰላም እንዲቋጭ የሕወሃት ደጋፊዎች ተማጽኖ በማቅረብ ላይ ናቸው።
ጥቅምት ወር የመጀመሪያ ሳምንት በመቀሌ እንዲሁም በሶስተኛውና በአራተኛው ሳምንት በአዲስ አበባ ያደረጉት ስብሰባ ሊቋጭ አልቻለም የወያኔ ሀርነት ትግራይ መሪዎች።Bilderesultat for የሕወሃት ማዕከላዊ ኮሚቴ ስብሰባ
የመሪዎቹ ስብሰባ ወደ ስምምነት ሊያመራ ባለመቻሉም ከ10 ቀናት በፊት እንደገና በመቀሌ የተቀመጡት የሕዝባዊ ወያኔ ሀርነት ትግራይ መሪዎች አሁንም በከፍተኛ ውዝግብ ውስጥ መገኘታቸውን የጻፉት ሁለት የሕወሃት ደጋፊ ድረገጾች ናቸው።
ጥቅምት 10/2010 መቀሌ በተጀመረው የሕወሃት ስራ አስፈጻሚ ኮሚቴ ስብሰባ ላይ ባለሃምሳ ዘጠኝ ገጽ የግምገማ ሪፖርት ለውይይት መቅረቡን “ሆርን አፌርስ” የተባለው የሕወሃት ደጋፊ ድረገጽ ገልጿል።
ይህንን ሰነድ በስብሰባው ከተገኙት ከ8ቱ የሕወሃት ስራ አስፈጻሚ ኮሚቴ አባላት 5ቱ ሲቀበሉት ሶስቱ እንደተቃወሙት ምንጮቹን ጠቅሶ ጽፏል።
ከተቃወሙት ውስጥ አንዷ የቀድሞው ጠቅላይ ሚኒስትር መለስ ዜናዊ ባለቤት አዜብ መስፍን መሆናቸው ታውቋል።–ከተቃወሙት ሁለቱ ግን እነማን እንደሆኑ ይፋ አልሆነም።

Wednesday, November 15, 2017

ESAT Daily News Amsterdam November 15,2017

የብሄራዊ ደህንነት ዕቅድ ወይስ የህወሀት የስንብት ደብዳቤ? (ጋዜጠኛ መሳይ መኮንን)

መቀሌ
ይህን ጽሁፍ በማዘጋጅበት ሰዓት መቀሌና ሀራሬ ሁነኛ የፖለቲካ ክስተት ተፈጥሯል። የመቀሌው ይፋ የወጣ አይደለም። በህወሀት አፍቃሪያን ድረገጾች የተተነፈሰ ወሬ ነው። ወ/ሮ አዜብ መስፍን የመቀሌውን ህንፍሽፍሽ ረግጠው ወጡ የሚለው ከውስጥ አዋቂ ያፈተለከው ዜና በቀላሉ የሚታይ አይደለም። በትክክል ከሆነ የሀራሬው ዓይነት መፈንቅለ መንግስት ልናይ የምንችልበት እድል ሰፊ ነው። የጄነራል/ፕሮፌሰር ሳሞራ የኑስ ቡድን በመቀሌው ስብሰባ ከተሸነፈ እጁን አጣጥፎ የሚቀመጥ አይሆንም። በአቶ ስብሃት ነጋ የሚመራው የአዲስ አበባው ህወሀት በአንዳች ተአምር መከላከያውን ከሳሞራ የኑስ እጅ ፈልቅቆ ካልወሰደ በቀር የወ/ሮ አዜብ መስፍን ኩርፊያና ረግጦ መውጣት የሚያስከትለው መዘዝ ለህወሀት ፍጻሜው ሊሆን ይችላል።Bilderesultat for mesay mekonnen
ትያትሩን አድፍጦ መከታተሉ ጥሩ ነው። ያም መጣ፡ ይሄም ሄደ ልዩነት የለውም። ለኢትዮጵያ ህዝብ የትኛውም የህወሀት አንጃ አይበጀውም። ህወህት ቢከፈልም፡ ቢሰነጣጠቅም ያው ህወሀት ነው። ከነስሩ ተመንግሎ፡ ተጠራርጎ መወገድ ያለበት እንጂ ክፋዩ፡ ስንጣቂው ቢተርፍና በስልጣን ላይ ቢቆይ ለኢትዮጵያና ህዝቧ ተውሳክ፡ ነቀርሳ መሆኑ የማይቀር ነው።
ሀራሬ
የዙምቧቡዌ ሰማይ ያልተለመደ አየር ነፍሶበታል። የ40 ዓመቱ የሙጋቤ ስዩመ እግዚያብሄር አገዛዝ ፍጻሜውን አግኝቷል። በስልጣን ላይ በመቆየት የዓለምን ክብረወሰን የጨበጡት ሽማግሌው ሙጋቤ ከነሚስታቸው በወታደሩ ክፍል ለጊዜው በማቆያ ይገኛሉ። ብሄራዊው ቴሌቪዥን ላይ የዚምቧቡዌ ጦር መሪዎች መግለጫ እየሰጡ ነው። በአጭሩ መፈንቅለ መንግስት ተካሂዷል። ለዚምቧቡዌ አዲስ ታሪክ ተመዝግቧል። ሰውዬው በአጥንታቸው ሳይቀር ጨምድደው እየገዟት ያለችው ሀገር በአዲስ የታሪክ ምዕራፍ ላይ ወጥታለች። ሁኔታዎች በፍጥነት በሚለዋወጡባት ዚምቧቡዌ የሚሆነው ነገር አይታወቅም። ታሪክ ግን ተቀይሯል።
ዚምቧቡዌ በአንድ ስልጣኑን እስከመቃብሩ ድረስ ላለመልቀቅ በወሰነ ሽማግሌ የስንግ ተይዛ ለ40 ዓመታት ቆይታለች። ኢትዮጵያ በዘርና ጎሳ በተቧደኑ፡ በዘረፋና ሌብነት ሀገሪቱን ለመጋጥ በተሰለፉ የአንድ መንደር ልጆች ከሩብ ክፍለዘመን በላይ ደሟ እየተመጠጠ ያለች ሀገር ናት። የዚምቧቡዌ ጦር የዚምቧቡዌ ነው። የኢትዮጵያ ጦር የኢትዮጵያ አይደለም። በዚምቧቡዌ መፈንቅለ መንግስት ቢካሄድ አዲስ ስርዓት በተስፋ ይጠበቃል። በኢትዮጵያ ግን መፈንቅለ መንግስት የህወሀትን አገዛዝ በመሳሪያ ሃይል የሚያስጠብቅ ሌላ የጨለማ ዘመን የሚያመጣ እንጂ ለውጥ አይኖረውም።

ህዝቡ ትግሉን አጠናክሮ እንዲቀጥል አርበኞች ግንቦት ሰባት ጥሪ አቀረበ

Asazagni qale mililis part one እንዲህ አይነት ነገርም አሳልፍፈናል።

Tuesday, November 14, 2017

ህዝቡ ትግሉን አጠናክሮ እንዲቀጥል አርበኞች ግንቦት ሰባት ጥሪ አቀረበ (ኢሳት ዜና–ሕዳር 5/2010)

በህወሀት መንግስት የብሄራዊ ደህንነት ምክር ቤት የወጣው ዕቅድ የስርዓቱ የመጨረሻው ሙከራ በመሆኑ ህዝቡ ትግሉን አጠናክሮ እንዲቀጥል አርበኞች ግንቦት ሰባት ጥሪ አቀረበ።
ንቅናቄው ለኢሳት እንደገለጸው በስልጣን ላይ ያለው ስርዓት በውድቀት አፋፍ ላይ የሚገኝ በመሆኑ በተለያዩ የሀገሪቱ ክፍሎች የሚደረጉት ሁለገብ ትግሎችን ለማፋፋም ተዘጋጅቷል።
የህወሃት መንግስት በዕቅዱ ላይ በአሸባሪነት ከወነጀላቸውና ስርዓቱን በማስጨነቅ ብርቱ ፈተና እንደደቀኑ ከተጠቀሱት ድርጅቶች አንዱ አርበኞች ግንቦት ሰባት ንቅናቄ መሆኑ ይታወቃል።
ሾልኮ የወጣውና በመንግስት የቀረበው ወቅታዊ ሁኔታን የሚዘረዝረው ዕቅድ ሀገሪቱ ያለችበትን አደጋ በጥልቀት የሚያሳይ ነው።
የህወሀት መንግስት በፖለቲካ፣ በኢኮኖሚ፣ በጸጥታና ደህንነት የገጠሙ አደጋዎች ህዝቡን ተስፋ እንዳስቆረጡት የገለጸበት ዕቅድ ግብጽንና ኤርትራን ድጋፍ በመስጠት የሚከስ ነው።

ጠቅላይ ሚኒስትር ኃይለ ማርያም ደሳለኝ ከስልጣናቸው እንዲነሱ የእንግሊዝ የደህንነት ባለስልጣናት መጠየቃቸው ተሰማ

 በቅርቡ ወደ ኢትዮጵያ የተጓዙት የእንግሊዝና የአሜሪካ የደህንነት ባለስልጣናት የልኡካን ቡድን በሀገሪቱ የተፈጠረው ያለመረጋጋት በአስቸኳይ መፍትሄ ካልተገኘለት ውሎ አድሮ የከፋ አደጋ እንደሚያስከትል ለኢትዮጵያው የብሄራዊ መረጃና ደህንነት ባለስልጣናት ማስጠንቀቃቸው ተሰማ፡፡የታሸጉ ቆዳ ፋብሪካዎች እንዲከፈቱ ጠቅላይ ሚኒስትሩ አዘዙ
በተለይ የእንግሊዝ የደህንነት ባለስልጣናት ከአቶ ጌታቸው አሰፋ የብሄራዊ መረጃና ደህንነት ሀላፊ ጋር ባደረጉት ምክክር ሀገሪቱ የገባችበት ችግር ዋንኛው ምክንያት ጠንካራና ተጻእኖ ፈጣሪ ጠ/ሚኒስትር ማጣትና ጠ/ሚኒስትር ሀ/ማርያም የተፈጠረውን ሁኔታ መቆጣጠርም ሆነ በተለያዩ አካላት ላይ ተጽእኖ ፈጠሮ ሀገሪቱን መምራት የተሳናቸው እንደሆኑ መጠቆማቸውን ኢሳት የጸጥታ ሀይሎችና ማህበረሰቡ በሚለው የዜና ፕሮግራሙ አስደምጧል።
በምትካቸውም ጠንካራ የፖለቲካ መሪ መሆን የሚችል ሰው
ማስቀመጥ አስፈላጊ መሆኑን እንዲሁም የጠቅላይ ሚንስትር ቦታውን ከሳቸው የሚረከበው ሰው ከሌላ ብሄር እንዲሆን
ከእንግሊዞቹ ጥያቄ መቅረቡም በፕሮግራሙ ተዘግቧል።
አቶ ጌታቸው በበኩላቸው በጉዳዩ ላይ እየሰሩበት ያለ ጉዳይ
ስለመሆኑና ይልቁንም ለቦታው ያጩት ሰው ስለ መኖሩ፤
ያጩትንም ሰው ለረጅም ጊዜ የሚያውቋቸውና አብረውም የሰሩ መሆኑን ተናግረው የታጨውን ሰው ስምን ግን ከመግለጽ መቆጠባቸውን ዜናው ያስረዳል፡፡

አቶ ጌታቸው ከእንግሊዝ የደህንነት ባለስልጣናት የቀረበላቸውን ጥያቄና እሳቸውም ያጩትን አዲሱ ጠ/ሚኒስትር ለስልጣን የማብቃት ስራን ተግባራዊ ለማድረግ ይቻላቸው ዘንድ ከእንግሊዝ የደህንነት ባለስልጣናት ጠንካራ ድጋፍ እንደሚሹ የጸጥታ ሀይሎችና ማህበረሰቡ የተባለው ፕሮግራም በዝርዝር አስደምጧል ።
የህወሀት ባለስልጣናትን እንዲሁም የጦር ጀነራሎችን
በማግባባትና ለተግባራዊነቱ ተባባሪ እንዲሆኑ ለማድረግ
የአሜሪካ መንግስት የማግባባቱንና የማደራደሩን ስራ እንድትሰራ እንግሊዝ ግፊት እንድታደርግ አቶ ጌታቸው አጠብቀው መጠየቃቸውን በፕሮግራሙ ተደምጧል።
በህወሃት ድርጅት ውስጥ ጠ/ሚኒስትር ሃይለማርያምን
በመቀየሩ ሀሳብ ላይ ቢስማሙም በሚተካው ሰው ላይ እስካሁን መስማማት ያለመቻላቸወም በዜናው ተዘግቧል፡፡

የድርጅታችን አርበኞች ግንቦት 7 ለአንድነትና ለዴሞክራሲ ንቅናቄ ሊቀመንበር የሆኑት ፕሮፌሰር ብርሃኑ ነጋ (በአርበኞች ግንቦት 7 ድምፅ ሬዲዮ)

 የዛሬ የዕለተ ማክሰኞ ህዳር 05 ቀን 2010 ዓ.ም ፕሮግራማችን
ዜና .... ከዕለቱ ዜና በማስቀጠል፡-
ለአርበኞች ግንቦት 7 ድምፅ ሬዲዮና ለኢሳት አፋን ኦሮሞ እንዲሁም ለኢሳት የትግረኛ ፕሮግራም በወቅታዊ የሃገራችን ጉዳዮች ላይ የሰጡትን ቃለ ምልልስ እናቀርባለን ፡፡ ትከታተሉን ዘንድ ግብዣችን ነው፡፡
www.patriotg7.orgImage may contain: 5 people, people sitting

Sunday, November 12, 2017

የብሔራዊ ደህንነት ምክር ቤት በሀገሪቱ ያሉትን ችግሮች ይፈታል የተባለ አዲስ እቅድ አወጣ (ኢሳት ዜና–ህዳር 1/2010)

በኢትዮጵያ ያለውን ወቅታዊ ሁኔታ መነሻ በማድረግ ከፍተኛ ባለስልጣናት የተካተቱበት የብሔራዊ ደህንነት ምክር ቤት በሀገሪቱ ያሉትን ችግሮች ይፈታል የተባለ አዲስ እቅድ አወጣ።
የብሔራዊ ደህንነት ምክር ቤቱ ያወጣውን አዲስ እቅድ በተመለከተ የመከላከያ ሚኒስትሩ ሲራጅ ፈርጌሳ በሰጡት መግለጫ እንዳሉት የጸጥታ ሃይሎች ከእንግዲህ የሚካሄዱ ህገ ወጥ ሰልፎችን ለማስቆም እንዲችሉ መመሪያ ተሰጥቷቸዋል።Image may contain: 9 people, people sitting
እስካሁን ለጠፋ ህይወትና ንብረት የሚጠየቁና ለሕግ የሚቀርቡ አካላት እንደሚኖሩም አቶ ሲራጅ ገልጸዋል።
ዜጎች በተለያዩ የሀገሪቱ አካባቢዎች የሚያካሂዱት አመጽ እንዲቆም ይደረጋልም ብለዋል።
በኢትዮጵያ የተከሰተውን ሕዝባዊ አመጽ አንዴ በሀይል ሌላ ጊዜ ደግሞ ያልተፈጠረ በማስመሰል ለመከላከል ሲማስን የነበረውና በሕወሃት የሚመራው አገዛዝ ብዙ ሙከራዎችን ሲያደርግ ቆይቷል።
በአስቸኳይ አዋጁ ጭምር የሕዝብን ጥያቄ ለማፈን ያልቻለው አገዛዝ ሁሉም ነገር በቁጥጥር ስር ውሏል፣የሀገሪቱ ሰላምም አስተማማኝ ነው ሲልም ነበር።
አሁን ደግሞ በኢትዮጵያ የተለያዩ አካባቢዎች ያለውን የሕዝብ ቁጣ ለማፈን አዲስ እቅድ ነድፌያለሁ እያለ ነው።
አዲስ እቅድ ደግሞ ተነደፈ የተባለው በብሔራዊ ደህንነት ምክር ቤት መሆኑን የመንግስት መገናኛ ብዙሃን ዘግበዋል።
የብሔራዊ ደህንነት ምክር ቤት የሚባለው በጠቅላይ ሚኒስትር ሃይለማርያም የሚመራ ሆኖ በውስጡ የሀገር መከላከያ ሚኒስትርን፣የፌደራል ፖሊስ ኮሚሽንን፣የመረጃ ደህንነት መስሪያ ቤትን፣የኢህአዴግ ጽህፈት ቤትንና ሌሎች የጸጥታ አላካትን ያካተተ ነው።
በአሁኑ የብሔራዊ ደህንነት ምክር ቤት ስብሰባ ደግሞ የክልል ርዕሰ መስተዳድሮችና የክልሎች የጸጥታ አካላትም ተሳትፈውበታል።
እናም የብሔራዊ ደህንነት ምክር ቤቱ በሀገሪቱ በአሁኑ ወቅት ያለውን ቀውስ በዘላቂነት ለመፍታት በሚል የተለያዩ ርምጃዎችን እንደሚወስድ ገልጿል።
የምክር ቤቱን ውሳኔ አስመልክተው የመከላከያ ሚኒስትሩ አቶ ሲራጅ ፈርጌሳ እንዳሉት ከአሁን በኋላ የሚካሄዱ ሰልፎች የሚያስከትሉትን ችግር ለመከላከል የጸጥታ አካላት ተቀናጅተው ርምጃ ይወስዳሉ።
እስካሁን የሚካሄዱ ሰልፎችም ሕገወጦች ናቸው ብለዋል።
በኦሮሚያና ሶማሌ እንዲሁም በተለያዩ የሀገሪቱ አካባቢዎች በተፈጠሩ ግጭቶች ለጠፋው ሕይወትና ንብረትም ተጠያቂ የሚሆኑ አካላት እንደሚኖሩ አቶ ሲራጅ ፈርጌሳ ገልጸዋል።
ከኦሮሚያና ሶማሌ የተፈናቀሉት ከ7 መቶ ሺ በላይ የሚሆኑ ሰዎችም ወደነበሩበት ይመለሳሉ ብለዋል።
በኬላዎች፣በአውራጎዳናዎች እንዲሁም ከክልል ክልል በሚደረጉ ዝውውሮች ሰላም ጠፍቷል ያሉት የመከላከያ ሚኒስትሩ የብሔራዊ ደህንነት ባወጣው አዲስ እቅድ በዘላቂነት ይፈታል ሲሉ ተናግረዋል።
አቶ ሲራጅ በአዲሱ እቅድ የሚታሰር ሰው እንዳለ ፍንጭ ሰጥተዋል።
የጸጥታ ሃይሎች ይወስዳሉ ስላሉ ርምጃ ግን ማብራሪያ ከመስጠት ተቆጥበዋል።

በሕወሐት አዝጋሚ ወታደራዊ መፈንቅለ መንግስት ሴራ የኢትዮጵያ ህዝብ የነፃነት ትግል አይቀለበስም!!! (ከሰማያዊ ብሔራዊ ሸንጎ የተሰጠ መግለጫ)


ሕወሐት/ኢሕአዴግ በአስቸኳይ ጊዜ አዋጅና ጥልቅ ተሃድሶ የኢትዮጵያን ህዝብ በወታደራዊ አገዛዝ አፍኖ ለህዝብ ጥያቄዎች ተገቢ ምላሽ ለመስጠት ሳይሞክር ለአለፉት ሁለት ዓመታት በተለያዩ ጊዚያት በሰላማዊ መንገድ ተቃውሟቸውን የሚገልፁ ዜጎችን መግደልና በጅምላ ማሰር የእለት ከዕለት ስራው አድርጎ ቆይቷል፡፡Image may contain: 2 people
ገዥው ቡድን ለጊዜውም ቢሆን በአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ ሊያዳፍን የሞከረው የህዝብ የነፃነትና የእኩልነት ጥያቄ በአስቸኳይ ጊዜ አወጁ ወቅትና አዋጁም ከተነሳ በኋላ ተጠናክሮ ቀጥሏል፡፡ አገዛዙ ጥያቄ ያነሱ ዜጎችን በአደባባይ በጥይት መረሸኑን ቀጥሎበታል፡፡ ለ26 ዓመታት ኮትኩቶ ያሳደገው የዘር ጥላቻ ፍሬ አፍርቶ ዜጎች በማንነታቸው ምክንያት በአደባባይ እየታረዱ ቤት ንብረታቸው እየተቃጠለ በኢትዮጵያ ምድር የንፁሃን ደም እየጮኸ ነው፡፡ የሀገራችን ዩኒቨርሲቲዎችም የአገዛዙ የዘር ጥላቻ በረጨው መርዝ ምክንያት የታዳጊ ወጣቶች ህይወት አደጋ ላይ ወድቋል፡፡ 
በስልጣን ላይ ያለው የአራት የጎሳ ድርጅቶች ግንባር የሆነው ኢህአዴግ የየጎሳው መንግስታት የሚፈጥሩት የእርስ በእርስ ግጭትና አለመተማመን ለብዙ ኢትዮጵያውያን ሞትና መፈናቀል ምክንያት ሆኗል፡፡
ሕወሐት በህዝብ የተቀጣጠለውን የህዝብ ተቃውሞ ተከትሎ በግንባሩ ውስጥ በተፈጠረው መከፋፈል ምክንያት ሀገራችንን እራሱ በፃፈው ህገ መንግስት አስቸኳይ ጊዜ አዋጅ ማወጅን ጨምሮ ቢጠቀምም የህዝቡን ተቃውሞም ሆነ የድርጅቶችን የውስጥ ሽኩቻ ማስቆም አልቻለም፡፡ በሁሉም መመዘኛዎች አቅመ ቢስ የሆነው ሕወሐት ደህንነቱንና መከላከያውን ቢቆጣጠርም አሁን ያለውን የህዝብ ተቃውሞንና የድርጅት ሽኩቻ አሁን ያለው የሲቪል አገዛዝ እስካለ ድረስ ተንፋሹን ማስቀጠል እንደማይችል አረጋግጧል፡፡ 
አሁን ካለው የዓለም ፖለቲካ አንፃር የለየለት ወታደራዊ መፈንቅለ መንግስት ማድረግ ኪሳራ እንደሚያስከትልበት የተገነዘበው ሕወሐት አሁን ያለውን ህገ መንግስት ሙሉ በሙሉ በመተው ለወታደሩ ትልቅ ስልጣን የሚሰጥና በሂደትም ሙሉ በሙሉ የሲቪል አስተዳደሩን ስልጣን ነጥቆ በወታደሩ እጅ እንዲገባ የሚያደርግ "የብሔራዊ ደህንነት ምክር ቤት" በሚል አካል ስም "አዝጋሚ ወታደራዊ መፈንቅለ መንግስት" በተግባር ደንግጓል፡፡ በመሰረቱ ይህ የብሔራዊ ደህንነት ምክር ቤት የተባለው አደረጃጀት ዓላማው በሀገር ደህንነት ጉዳይ ለአስፈፃሚው አካል ምክር ከመስጠት ውጭ በራሱ እርምጃ የመውሰድ ምንም ስልጣን የሌለው አካል ነው፡፡ ገዥው ቡድን በዚህ የብሔራዊ ደህንነት ምክር ቤት በተባለው አደረጃጀት ስም ሊወስደው ያቀደው እርምጃ አገዛዙ ያለው የመጨረሻ በትር ሲሆን የሚወስደው የመደናገጥና የተስፋ መቁረጥ እርምጃ ሀገራችንንና ዜጎቻችንን ብዙ ዋጋ እንደሚያስከፍል ብንገነዘብም የኢትዮጵያን ህዝብ የነፃነት ጥያቄ ሊቀለብሰው እንደማይችል በፅኑ እናምናለን፡፡ 
በዓለም ታሪክ አገዛዝ ህዝብን ለዘለቄታው አሸንፎ አያውቅም፡፡ አሁን በአገዛዙ እየተወሰዱ ያሉ የጭካኔ እርምጃዎች የሚያረጋግጡልን የህዝብ ትግል ወደ ነፃነት እየተቃረበና አገዛዙ እየሞተ መሆኑን ነው፡፡ 
በመሆኑም ይህንን ከባድ ፈተና ለመወጣትና ትግሉን በአሸናፊነት ለማጠናቀቅ ሁሉም ኢትዮጵያውያን ለመራራው ትግል በቆራጥነት እንዲነሱ ጥሪያችንን እናስተላልፋለን፡፡ በመጨረሻም ሕወሐት ችግሮችን ከማወሳሰብና ሀገራችንን በትኖ ወደ እርስ በእርስ ጦርነት ማምራት ለሁላችንም የኢትዮጵያ ልጆች የማይበጅ ከባድ የታሪክ ጠባሳ መሆኑን በመገንዘብ ከተያያዘው የአውዳሚነትና የተስፋ መቁረጥ እርምጃ ተቆጥቦ ስልጣን ለህዝብ እንዲያስረክብና ሁሉን አቀፍ የባለ አደራ መንግስት እንዲቋቋም ያለበትን ታሪካዊ ሃላፊነት እንዲወጣ ጥሪያችንን እናስተላልፋለን፡፡
ህዳር 03 ቀን 2010 ዓ.ም
አዲስ አበባ

ESAT Menalesh Meti, TPLF rubber-stamp parliament

የኢሳት 7 ኛ ዓመት ትናንት ቅዳሜ በአምስተርዳር በልዩና በደማቅ ሁኔታ ተከብሯል። በአምስተርዳም የኦሮሞ ኮሙኒቲ አባላት ለበዓሉ ድምቀት ላሳያችሁት አስገራሚ ተሳትፎ ምስጋናችን ታላቅ ነው።

"ኢትዮጵያ የኛም ሀገር ናት፣ ኢሳት የኛም ነው" በማለት በዝግጅቱ ቦታ በመገኘታችሁ " ኢትዮጵያ ሀገሬ፣መመኪያ ጋሻዬ" በሚለው ሙዚቃ መድረክ ላይ ተጋብዛችሁ በልዩ ደስታ የተጫወታችሁ የጅቡቲ ሶማሌዎች ለእናንተም ምስጋናችን ይድረሳችሁ። ከሁሉም በላይ የመድረኩ ፈርጥና ድምቀት ለነበራችሁት ለአርቲስት ሃኒሻ ሰሎሞንና ለአርቲስት ቱሉ ምስጋናችን ወደር የለውም።
በመጨረሻም የአምስተርዳምና አጠቃላይ የሆላንድ የኢሳት ድጋፍ አስተባባሪ ኮሚቴዎች፣ የሥራችሁን ስኬት አምሮ ስላገኛችሁት እንኳን ደስ ያላችሁ፣
Image may contain: 7 people, people smiling, people standing and suit
Image may contain: 3 people, people smiling

የኢሳት 7 ኛ ዓመት ትናንት ቅዳሜ በአምስተርዳር በልዩና በደማቅ ሁኔታ ተከብሯል። በአምስተርዳም የኦሮሞ ኮሙኒቲ አባላት ለበዓሉ ድምቀት ላሳያችሁት አስገራሚ ተሳትፎ ምስጋናችን ታላቅ ነው።

"ኢትዮጵያ የኛም ሀገር ናት፣ ኢሳት የኛም ነው" በማለት በዝግጅቱ ቦታ በመገኘታችሁ " ኢትዮጵያ ሀገሬ፣መመኪያ ጋሻዬ" በሚለው ሙዚቃ መድረክ ላይ ተጋብዛችሁ በልዩ ደስታ የተጫወታችሁ የጅቡቲ ሶማሌዎች ለእናንተም ምስጋናችን ይድረሳችሁ። ከሁሉም በላይ የመድረኩ ፈርጥና ድምቀት ለነበራችሁት ለአርቲስት ሃኒሻ ሰሎሞንና ለአርቲስት ቱሉ ምስጋናችን ወደር የለውም።
በመጨረሻም የአምስተርዳምና አጠቃላይ የሆላንድ የኢሳት ድጋፍ አስተባባሪ ኮሚቴዎች፣ የሥራችሁን ስኬት አምሮ ስላገኛችሁት እንኳን ደስ ያላችሁ፣

Image may contain: 7 people, people smiling, people standing and suit

Demere Legesse & Asrebeb Tadege - Bela Libelha | በላ ልበልሃ - New Ethiopian...

Tensae Radio Nov 11 2017

(የአርበኞች ግንቦት 7 ድምፅ ሬዲዮ)

በዛሬ የዕለተ እሁድ ጥቅምት 03 ቀን 2010ዓ.ም ፕሮግራማችን የድርጅታችን አርበኞች ግንቦት 7 ከፍተኛ አመራር የሆኑት ዶ/ር ታደሰ ብሩ በወቅታዊ የሃገራችን ጉዳዮች ላይ ያላቸውን ምልከታና ይበጃል የሚሉትን ሃሳቦችም በአርበኞች ግንቦት 7 ድምፅ ሬዲዮ አካፍለውናል ተከታተሉት.............. 
www.patriotg7.org

Image may contain: 1 person, smiling, standingImage may contain: sky and outdoor

Saturday, November 11, 2017

አጭር መልዕክት ለብሔራዊ ደህንነትና መረጃ አገልግሎት ባልደረቦች በሙሉ! (በዶ/ር ታደሰ ብሩ)

የብሔራዊ ደህንነትና መረጃ አገልግሎት ሥራቸውና ስማቸው ለየቅል ከሆኑባቸው ተቋማት አንዱ ነው። ይህ ተቋም እንደ ስሙ የሚሠራ ቢሆን ኖሮ ለብሄራዊ ደህንነት የሚጠቅሙ መረጃዎችን የሚሰበስብ በሆነ ነበር፤ ግን አልሆነም።
አሁን ባለሁ ሀቅ መሠረት የብሔራዊ ደህንነትና መረጃ አገልግሎት፣ ህወሓትን የሚቃወሙ ዜጎችን ሁሉ በጠላትነት ፈርጆ ለማጥፋት “ህጋዊ ፈቃድ” የተሰጠው ተቋም ነው። የዚህ ተቋም አባላት በአገር ደህንነት ስም የዜጎችን የግል መኖሪያ ቤት፣ ቢሮ፣ የስልክና የኢሜል ግኑኝነቶች ይበረብራሉ። “የዓይኖቻቸው ቀለም” ያላማሩዋቸውን“ ዜጎች ያዋክባሉ፣ ይገርፋሉ፣ ያሳድዳሉ፣ ይገላሉ። ከፍተኛ መጠን ያለው የሀገር ሀብት የህወሓት ሽማምንትን ደህንነት ለመጠበቅ ያባክናሉ። ውሎና አዳራቸው ዜጎችን ማሳደድ ነው። ከዚህም አልፎ ሕዝብ ከሕዝብ፤ የአንድ እምነት ተከታዮች ከሌላ እምነት ተከታዮች ጋር የሚያጋጩ አሻጥሮችን ይሠራሉ። ዘወትር ወንጀሎችን እየሠሩ በሌሎች ላይ ይደፈድፋሉ። ፍርድ ቤቶች ፍርደገምል ውሳኔ እንዲሰጡ ያደርጋሉ። ... ብዙ እጅግ ብዙ ለዓይንና ጆሮ የሚቀፉ ተግባራትን ይፈጽማሉ።
ኢትዮጵያዊያን በገዛ አገራችን ተሸማቀን እንድንኖር፤ አሊያም አገር ለቀን እንድንሰደድ የሚያደርጉን የዚህ ተቋም ባልደረቦችና ተባባሪዎች ናቸው።
ይሁን እንጂ የተቋሙ ባልደረቦች በሙሉ አንድ ዓይነት እንዳልሆኑ እገነዘባለሁ። በሆነ ምክንያት ገብተው መውጣት ያልቻሉ፤ ከዛሬ ነገ እለቃለሁ እያሉ የሰነበቱ፤ አሊያም ”የእንጀራ ጉዳይ” ሆኖባቸው ባያምኑበትም የታዘዙትን በመፈፀም ላይ የሚገኙ ወገኖች እንዳሉ አውቃለሁ። እነዚህ ወገኖች በሚሠሯቸው ወንጀሎች መሸማቀቃቸው ለራሳቸውም ሆነ ስቃዩ ለሚደርስብን ወገኖች የሚፈይደው ነገር የለም። እነዚህ ወገኖች ይሰሙኛል ብዬ በማሰብ አንዳንድ ነገሮችን ላነሳ እፈልጋለሁ።Bilderesultat for የብሔራዊ ደህንነትና መረጃ አገልግሎት፣
ሥራችሁን ሳትለቁ ለገዛ ራሳቸው ህሊና፤ ለልጆቻችሁ፣ ለሀገራችሁ እና ለሕዝብ ጠቃሚ የሆኑ ተግባራትን መፈፀም ትችላላችሁ። ህወሓትን ከስልጣን በማስወገድ ሂደት አስተጽዖ በማድረግ የለውጡ አካል የመሆን እድል አላችሁ። የለውጡ እንቅፋት ብትሆኑ የጊዜ ጉዳይ ካልሆነ በስተቀር መወገዳችሁ አይቀርም፤ ስማችሁና ክብራችሁ እንደጎደፈ ይኖርል። የለውጡ አካል ከሆናችሁ ግን ራሳችሁ ነፃ ታወጣላችሁ፤ ስማችሁና ክብራችሁን ታድሳላችሁ፤ የለውጡን መልካም ፍሬ ከሕዝብ ጋር ትቋደሳላችሁ። ይህንን ለማድረግ የአሁኑ ሥራችሁን መልቀቅ አያስፈልጋችሁም።
ሰብዓዊ ህሊና እና የሀገር ፍቅር ያላችሁ የብሔራዊ ደህንነትና መረጃ አገልግሎት ባልደረቦች ጠላት ጉያ ውስጥ ሆናችሁ ጠላትን የማዳከም ከፍተኛ አቅም አላችሁ። የህወሓት የስለላ ድርጅት ውስጥ ሆናችሁ ራሱ ህወሓትን ሰልሉት፤ ደካማና ጠንካራ ጎኖቹን አጥኑ፤ ያገኛችሁትን መረጃ ደግሞ ሥርዓቱን ለሚቃወሙ ኃይሎች አካፍሉ። ክፉ ሥርዓት ልብ ውስጥ መሆናችሁ፤ ከማንም በላይ ይህን ክፋት ለማስወገድ በተመቸ ቦታ ላይ ያላችሁ መሆናችሁን ተገንዘቡ ! እጃችሁ ውስጥ ያለውን ኃይል ረብ ላለው ነገር አውሉት፤ እድሜ ልካችሁን የምትኮሩበት ታሪክ ትፈጽማላችሁ። ልጆቻችሁና ወገኖቻችሁ በእናንተ ይኮራሉ።
ህወሓት እንዲህ በተዋከበትና በተዳከመበት ወቅት የራሳችሁን እና የቤተሰቦቻችሁን ታሪክ የማደስ እድል አታስመልጡ።

(የአርበኞች ግንቦት 7 ድምፅ ሬዲዮ)


የዛሬ የዕለተ አርብ ህዳር 01 ቀን 2010 ዓ.ም. መሰናዷችን በቅድሚያ ዜና ፡-
* ሁለተኛ ቀኑን በያዘው የምንጃር ሸንኮራና የጨፌ ዶንሳ ከተማ ተቃውሞ ህዝቡ ለውጥ እንፈልጋለን የሚሉ ጥያቄዎችን እያቀረበ መሆኑ.
* የብሄራዊ መረጃና ደህንነት አገልግሎት በኮረኔል ደመቀ ዘውዱ ላይ ያቀረበውን ሪፖርት አልተረጋገጠም መባሉ
* በምስራቅ ዕዝ በመካሄድ ላይ ባለው የመኮንኖች ስብሰባ ላይ የዕድሜና የትምህርት ጥያቄ መነሳቱ
፠በዛሬው የአርበኞች ማስታወሻ መሰናዷችን፡ ያዶሎሮሳ (የነጻነት ጎዳና) በሚል ርዕስ የተዘጋጀ ጽሁፍ በአርበኛ ታጋይ ፊደል ዳንኤል ይቀርብላችሃል።
ሙሉ ፕሮግራሞቻችንን በ www.patriotg7.org/ ላይ መከታተል የምትችሉ መሆኑን በአክብሮት እንገልፃለን፡፡Image may contain: sky and outdoor

ESAT YETSETETA HAYILOCHINA MEHABERESEB NOVEMBER 11 2017

የመጨረሻው መጀመሪያ (ጋዜጠኛ መሳይ መኮንን)

የኢኮኖሚ ቀውስ ህወሀትን በአፍጢሙ ሊደፋው ተቃርቧል። የፖለቲካ ግለቱ ከቤተመንግስቱ አፋፍ ተጠግቷል። የኢኮኖሚና የፖለቲካ ቀውሶች አንድ ላይ ሲከሰቱ ደግሞ አይጣል ነው። አንዳቸው በተናጠል ቢመጡ እንኳን የመንግስት ለውጥ የማምጣት አቅማቸው ከፍተኛ ነው። እያየን ያለነው ደግሞ ሁለቱም ተያይዘውና ተደጋግፈው በፍጥነት እየገሰገሱ መሆናቸው ነው። ሌላም ቀውስ ከአጠገባቸው አለ። ማህበራዊ መናጋት። ይህም ቀውስ ስር ይዞ አድፍጧል። ለብዙዎች ይህ ወቅት የደርግን የፍጻሜ ዘመን ያስታውሳቸዋል። ወደ ኋላ ራቅ ላለው ትውልድ ደግሞ የ66ቱ አብዮት ኮፒ ሆኖባቸዋል።Image may contain: 6 people, people standing and outdoor
የኢኮኖሚ ቀውስ
ለኢኮኖሚ ባለሙያዎች አሁን የሚታየው ቀውስ አላስገረማቸውም። ቀድሞውኑ የታመመ፡ የተበላሸ፡ በእርዳታና ብድር የተጠጋገነ፡ በሪሚተንስ ስጋና አጥንት ለብሶ የቆመ ኢኮኖሚ እንጂ በራስ አቅምና ትጋት የተገኘ የኢኮኖሚ እድገት አይደለም። የኤድመንተኑ ነዋሪ ኢኮኖሚስት ዶ/ር ሽፈራው አዲሎ እንደሚሉት በእርዳታና ብድር ተደግፎ የቆመው ኢኮኖሚ አሁን የሚደገፈው ሲያጣ ወድቋል። ብድርና እርዳታ ደርቀዋል። እዳ መክፈል የማይችለው ኢኮኖሚ ሀገሪቱን አበዳሪ አሳጥቷታል። ለህወሀት የልብ ወዳጅ የሆኑት እነቻይና ፊት መንሳት መጀመራቸው ይሰማል። የምዕራቡ ዓለምም ለእርዳታ እጁን መሰብሰብ ጀምሯል። በተለይ የትራምፕ አስተዳደር በከፍተኛ መጠን የእርዳታ ገንዘብ እንዲቀንስ በማድረጉ በሌሎች ሳምባ የሚተነፍሰው የህወሀት ኢኮኖሚ ከሞቱ አፋፍ ይጠጋ ዘንድ ግድ ሆኗል። ኢትዮጵያውያን ከባህር ማዶ ወደ ሀገር ቤት የሚልኩት የውጭ ምንዛሪም አደጋ ላይ ነው። ለታዋቂው የኢኮኖሚ ባለሙያ ፕ/ር ጌታቸው በጋሻው የህወሀት ኢኮኖሚ ሁልጊዜም ''ግራ የሚያጋባ፡ ከኢኮኖሚክስ ፍልስፍና ውጭ የሆነ፡ ለኢኮኖሚስቶችም ለመረዳት እጅግ ያዳገተ ውስብስብ'' ኢኮኖሚ ነው።

Friday, November 10, 2017

ESAT Efeta Fri 10 Nov 2017

የአርበኞች ግንቦት 7 ተልዕኮ ራዕይ

የአርበኞች ግንቦት 7 ንቅናቄ፣ እያንዳንዱ ኢትዮጵያዊ ዴሞክራሲያዊና ሰብአዊ መብቱ የተከበረበት፣ የኢኮኖሚ ብልፅግናና ማኅባራዊ ፍትህ የሚያገኙበት፣ የዜጎች ህይወት፣ ደህንነትና ጥቅም የተከበረበት ሃገር እንዲኖረው ማድረግ ነው።
ተልዕኮ
የአርበኞች ግንቦት 7 ንቅናቄ፣ ቀዳሚ ተልዕኮ የመንግስትና የፖለቲካ ስልጣን በሠላማዊና ዴሞክራሲያዊ ሂደት የሚያዝበትንና የሃገሪቱ ዜጎች ምርጫ በተግባር የሚገለፅበትን ብሄራዊ ሥርአት እንዲገነባ ማገዝ ነው።
መሰረታዊ ዕሴቶችና መርሆዎች
የግለሰቦችና የህዝብ መብቶች መከበር የአዲሱ ፖለቶቲካዊ ሥርአት የሚዕዘን ድንጋይ ነው፣
የአዲሱ ፖለቲካዊ ስርአት የጀርባ አጥንት በመሆን የአምባገነን መንግስታትንም ሆነ ፓርቲዎችን፣ እንዲሁም ፖለቲከኞችን መረን ያጣ ሥልጣን ለመቆጣጠር፣ ነፃ መንግስታዊ የሆኑና ያልሆኑ ተቋማት ምሥረታና መጠናከር አስፈላጊነቱን በማመን፣ ነፃ የፖሊስና የመከላከያ
ሃይል፣ ነፃ የምርጫ ቦርድና ነፃ ፕሬስ እንዲመሰረቱና እንዲጠናከሩ መታገል፣
የሃይማኖት፣ የዘውግ፣ የባህልና የመልክአ ምድራዊ አቀማመጥ ልዩነቶች የሚያደምቁን ውበቶቻችን እንጂ፣ የርስ በርስ መጠቃቂያ መሳሪያዎች አለመሆናቸውን በማመን፣ ይህንን ውበት ያላበሱን ልዩነቶቻችንን የሚያከብር በሃገራዊ አርበኛነት ላይ የቆመ ጠንካራ ህብረተሰብ መገንባት፣
ዜጎች ከሚጋሩት ህይወት፣ ህልምና ተስፋ እንዲሁም በታሪክ ካዳበሩት የጋራ ትስስር ይልቅ፣ የዘውግ፣ የሃይማኖትና ባህላዊ ልዩነቶቻቸውን ለአጭር ጊዜ የፖለቲካ ጥቅም የሚቆምሩ ፖለቲካዊና ተውፊታዊ ጎታች ሃይሎችን መታገል፣
ዜጎች በዘውግ ጀርባቸው፣ በሃይማኖታቸው፣ በቋንቋቸው፣ በባህላቸው፣ በእድሜያቸው፣ በጾታቸው ወይም በመልክአ ምድራዊ ልዩነቶቻቸው ወይም በግላዊ አቅመ-ደካማነታቸው የተነሳ አድልኦ የማይፈጸምባቸውና የዜግነት የእኩልነት መብታቸው የሚከበርበት ፖለቲካዊ ሁኔታ ማመቻቸት፣
ሃገሪቱን ለማገልገል የቆረጡ፣ ታታሪ፣ ብሩህ፣ አርቆ አሳቢና ሆደ-ሰፊ፣ ለዜጎች አርአያ የሚሆኑ መሪዋች እንዲፈጠሩ ማገዝ፣
የመልካም አስተዳደር፣ የተጠያቂነትና የግልፅነት መርሆዎች፣ ህዝብን ማዕከል ካደረገ የውሳኔ አሰጣጥ ጋር ተሳስረው በተግባር የሚተረጎሙበትን ሥርአት መመሥረት፣
በጥረት የሚገኝ ውጤት የሚከበርበት፣ ሃገርን ማገልገል ድንቅ የሚባልበት፣ ችሎታና ታታሪነት ብቻ የሽልማት መስፈርቶች የሆኑበት፣ ዜጎች በፖለቲካ ትስስራቸውና በዘውግ ማንነታቸው ሳይሆን በአበርክቶአቸው የድካማቸውን ውጤት የሚያገኙበትና የሚወደሱበት ፖለቲካዊ ሥርአት መመሥረት፣
ከሌሎች የፖለቲካ ፓርቲዎችና ህዝባዊ ግንባሮች ጋር ቅንብርና ትብብር በመፍጠር፣ በመሃላቸው ያለውን ውጥረት ማርገብ፣ ብሎም፣ ሁሉን በአካተተ፣ ሰፊ የፖለቲካዊ ስርአት አማካይነት ብሄራዊ ሰላምና መረጋጋት መፍጠር፣
ማንኛውም የፖለቲካ ፓርቲ፣ የህዝብ ግንባርና እንዲሁም መብትና ጥቅሜ አልተጠበቀም የሚል ቡድን፣ በፖለቲካ ዕምነቱም ሆነ ፕሮግራሙ የተነሳ የማይገለልበትን፣ ሁሉን አቀፍ የፖለቲካ ሥርአት ማቋቋም ነው።

ESAT EFETA November 8 2017

ESAT DC DAily NEws Thur 09 Nov 2017

Gedion Daniel - Bewedat | ብወዳት - New Ethiopian Music 2017 (Official Video)

Wednesday, November 8, 2017

ESAT Zare with Kassahun Yilma 07 Nov 2017

ESAT Daily News Amsterdam November 08,2017

ESAT Yesamintu Engeda Captain Mamo Habtewold November 8 2017

Must Watch! Prof. Berhanu Nega speech at PG7 Meeting in Las Vegas

ESAT Daily News Amsterdam November 07,2017

የደቡብ ምእራብ እዝ ከሃረሪ ክልል መሪ ጎን እንደሚቆም አስታወቀ (ኢሳት ዜና ጥቅምት 28 ቀን 2010 ዓም)


በይፋ ባልተገለጸ ሁኔታ የአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ የታወጀበት የሃረሪ ክልል በወታደራዊ መሪዎች እየተመራ ሲሆን፣ ወታደራዊ መሪዎቹ ሰሞኑን በተለያዩ ቀበሌዎች እየዞሩ ህዝቡን እና ካድሬዎችን ካነጋገሩ በሁወላ የውይይቱ ውጤት ነው ያሉትን ለክልሉ መሪ ለአቶ ሙራድ አብዱላሂ አቅርበዋል። 
በክልሉ ያለው ችግር የመሪዎች ችግር መሆኑን የገለጸት ወታደራዊ ባለስልጣናቱ፣ የመሪዎች አለመግባባት ህዝቡን አሸፍቶታል ብለዋል። የደቡብ ምዕራብ እዝ ምክትል የኦሮፕሬሽን አዛዡ ጄኔራል አማረ፣ በገጠር የሚገኙ አንዳንድ ኦሮሞዎች ሸፍተው ጫካ የገቡ በመሆኑ እርምጃ ሊወሰድባቸው ይገባል ብለዋል። ፕሬዚዳንቱን በሚወሰዱት እርምጃ ከጎናቸው እንደሚቆሙም አስታውቀዋል። Image may contain: 1 person
በኤረር ወረዳ ውስጥ ህገወጥ የጦር መሳሪያ የተበራከተ በመሆኑ ፣ ሰራዊቱ መሳሪያውን ለማስፈታት መዘጋጀቱንም አዛዡ ተናግረዋል። ጄኔራል አማረ ክልሉን በጣምራ የሚመሩትን የኦህዴድ አመራሮችን በክልሉ ውስጥ ችግር እየፈጠሩ እንደሆነና መከላከያ ከሃረሪ ብሄራዊ ሊግ ጎን እንደሚቆም አስታውቀዋል። 
በሌላ በኩል በሁንደኔ ወረዳ የሚገኙ የኦሮሞ ተወላጆች በሃረሪ ክልል ባለስልጣናት እየደረሰባቸው ያለውን የመብት ጥሰት በማንሳት ከክልሉ እንዲወጡ ያቀረቡት ጥያቄ መልስ ባላገኘበት ሁኔታ አካባቢውን በህግ ወደ ሃረሪ ክልል ለማጠቃለል አዲስ አዋጅ እየወጣ ነው። 
ሁንደኔ ወረዳ ለሃረሪ ክልል በይሁንታ የተለገሰ መሆኑን የሚናገሩት የአካባቢው ነዋሪዎች ፣ በወረዳው የሚኖረው የኦሮሞ ህዝብ ባለፉት 26 ዓመታት በሃብሊ ባለስልጣናት ከፍተኛ ጭቆና ሲደርስበት መቆየቱን ተከትሎ የመብት ጥያቄዎችን አንስቷል። አሁን ደግሞ አካባቢውን በህግ ወደ ሃረሪ ክልል ለማስገባት አዲስ አዋጅ መረቀቁን ምንጮች ረቂቅ አዋጁን በማያያዝ ከላኩን መረጃ ለመረዳት ተችሎአል።
በጉዳዩ ዙሪያ የወረዳውን ባለስልጣናት ለማናገር ያደረግነው ሙከራ አልተሳካም።

Sunday, November 5, 2017

የኢትዮጵያ ሕልውና እዲጠበቅ የጥላቻ ሰነድ ይቀደድ፤የዜጎች መስተጋብር ይጠበቅ የጋራ አጀንዳ ለጋራ ሁለንተናዊ ነፃነት!!! (ከሰማያዊ ብሔራዊ ሸንጎ የተሰጠ መግለጫ)


ዛሬ ኢትዮጵያ ከመቸውም ጊዜ በላይ ከአገዛዝ ለውጥ ዋዜማነት ባለፈ ብዙ ፈተናዎች ከፊቷ ተደቅነዋል፡፡ የአገዛዙ የጎሳ ድርጅት አባሎች ተስማምተው አገዛዛቸውን ማስቀጠል አቅቷቸው በእርስ በእርስ ሽኩቻ ተጠምደው ገመናቸው በአደባባይ እየዋለ የአገዛዙ ማርጀትና መበስበስ በብዙ ማሳያዎች እየተገለፀ ነው፡፡ 
1ኛ. በመንግስት ኮሚኒኬሽን ሚኒስቴር እና በብሮድካስት ባለስልጣን እንዲሁም በብሮድካስት ባለስልጣንና በክልል የጎሳ መንግስታት የሚዲያ ተቋማት መካከል የሚታየው መፈራረጅና አለመደማመጥ
2ኛ. በቅርቡ ለፓርላማ ይቀርባል የተባለውን የትራንስፖርት ረቂቅ አዋጅ በተመለከተ በፌደራልና በክልል የጎሳ መንግስታት መካከል የተፈጠረው የስልጣን ይገባኛል ጥያቄና አለመደማመጥ
3ኛ. በቅርቡ ለፓርላማ ይቀርባል የተባለውን የአሰሪና ሰራተኛ ጉዳይ አዋጅ በተመለከተ የሰራተኛ ማህበራት ያነሱት ያልተለመደ ጠንካራና ሊቀጥል የሚችል ተቃውሞ
4ኛ. በአገዛዙ አቅመ ቢስነትና ሃላፊነት በጎደለው ሁኔታ በባዶ እጃቸው ለተቃውሞ አደባባይ የወጡ ወጣቶች በመከላከያ ጥይት ተደብድበው ህይወታቸው ማለፉና ዜጎች አሰቃቂ በሆነ ሁኔታ እየታረዱ ውድ ህይወታቸውን ማጣታቸው
5ኛ. በአንድ ወቅትና ባልተጠና ሁኔታ በተደረገ የዶላር ምንዛሬ ማሻሻያ ምክንያት በዜጎች የእለት ከእለት ኑሮና አጠቃላይ በሀገር ኢኮኖሚ ላይ የፈጠረው ምስቅልቅል
6ኛ. ይህ አስደንጋጭ ሁኔታ ከአገዛዙ ቁጥጥር ውጭ መሆኑን የሀይማኖት ተቋማት ሁሉ እየተገነዘቡት በመምጣታቸው የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተ ክርስቲያን ሀገር አቀፍ ምህላ ማወጇ
ከላይ ከብዙ በጥቂቱ የጠቀስናቸው ማሳያዎች ሀገራችን ያለችበትን ውስብስብ ችግርና የዜጎቿን ትብብርና ቅንነት የምትሻበት ከባድ ፈተና ላይ መሆኗን ያሳያል፡፡ አሁን ለተጋረጠብን ሀገራዊ የብተና አደጋ ዋናው መሰረቱ በልዩነትና በጥላቻ ላይ የተመሰረተው የጎሳ አስተዳደር ነው ብለን እናምናለን፡፡ ስለሆነም ከዚህ ከአንዣበበብን የብተና አደጋ ለመዳን አሁን ያለውን በዘር ላይ የተመሰረተ አገዛዝ በመለወጥና ጊዚያዊ የባላደራ መንግስት በማቋቋም ሁሉን አቀፍ በዜግነት ላይ የተመሰረተ ህጋዊ አስተዳደር ለመመስረት ሁሉም የኢትዮጵያ ልጆች ቀዳሚ አጀንዳችን አድርገን ትግላችንን እንድናስተባብር ጥሪያችንን እያቀረብን በሰራተኛ ማህበራትና በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተ ክርስቲያን ሀገራችን ያለችበትን ሁኔታ ተገንዝበው የወሰዱት አቋም በሌሎች ተቋማትም ተጠናክሮ እንዲቀጥል እናሰስባለን፡፡ 
በመጨረሻም የሀገራችን ችግር ከአንድ ፓርቲ አቅም በላይና በጥገናዊ ለውጥ የማይሰተካከል መሆኑን ተገንዝበናል፡፡ ነገር ግን ምንም ዓይነት የህብረተሰብ ውክልና የሌላቸው ተቃዋሚ ፓርቲ ነን ባዮች የሀገራችንን ሁኔታ ላለማቀፍ ማህበረሰብ ድርድር በሚሉት ማጭበርበሪያ አቃለው በማሳየት ችግሩን የሚመጥን መፍትሔ በሁሉም ባለድርሻ አካላት እንዳይወሰድ ከባድ እንቅፋት እየፈጠሩ ይገኛሉ፡፡ በመሆኑም በኢትዮጵያ መፃኢ እድል ላይ እየፈጠሩት ያለው ጠባሳ ታሪክ ይቅር የማይለው ሀገራዊ ክህደት ስለሆነ ይህንን አውቀው ከድርጊታቸው እንዲቆጠቡ በጥብቅ እያሳሰብን እነዚህ አካላት ከድርጊታቸው እንዲቆጠቡ የለውጥ ሃይሎች ሁሉ ተገቢውን ጫና እንዲያደርጉ ጥሪያችንን እናስተላልፋለን፡፡
ጥቅምት 26 ቀን 2010 ዓ.ም
አዲስ አበባImage may contain: 10 people, people standing and outdoor

Cabinet reshuffle, crackdown on corruption in latest Saudi purge


ባላገር ማለት ያልሰለጠነ
ሗላቀር ፣ ያልዘመነ ፣ ማለት አይደለም
ትርጉሙን የሚሰጡት
እራሳቸው ያልሰለጠኑ ፣ ያላወቁ ሰዎች ናቸው ፡፡ 
ባላገር ማለት ሀገሩ የራሱ
የሆነ ፣ ሀገር ያለው ፣ ማንነቱን ያለወጠ ፣ ራሱን ያልሸጠ ፣ በማንነቱ የሚኮራ ፣ ኢትዮጵያዊነቱን ፣ ያላደበዘዘ ፣ ክብር ያለው ፣ ቀትረ ቀላል ያልሆነ ሰው ማለት ነው!
አንድ ሰው ያልሰለጠነ
መሆኑን ልትነግረው ባላገር ብለህ
የተሳደብክ እለት አላዋቂ እንደሆንክ
እወቅ! ያኔ ያልሰለጠንከው አንተ
ያልዘመንከው አንተ ሗላ ቀር አንተ
መሆንህን እወቅ! ባላገሮች ሗላ ቀር
አይደሉም! እንዲያውም የፊተኞች
ስልጣኔ ጀማሪዎች ፣ የጥበብ
ቀዳሚዎች ፣ ሰው የመሆን ሚስጥሮች ናቸው! ልዩነቱ አንተ መሰልጠንን ሌላ ከመምሰል ጋር ስታያይዝ ለባላገሮች
መሰልጠን እራስን መቻል መሆን ነው!
አንተ ሗላ ቀር የምትላቸው ባላገሮች ናቸው ዘመን የሚላቸው አለም ሊሰራቸው ቀርቶ ሊያስባቸው እንኳን የማይችላቸው እነ ላሊበላ ፣ አቅሱም ፣ ፋሲለደስ ፣ ጉዛራ
የመሳሰሉ ድንቅ ቅርሷች
ያስቀመጡልህ! አንተ አልዘመኑም
የምትላቸው ባላገሮች ናቸው ዘመናዊ ባልተባለ መሳርያ ታጅቦ የመጣን ፈረንጅ አንበርክኮ ሀገር ነፃ ማንነት የሰጡህ !ባላገር ማለት እውነተኛ የስልጣኔ መገኛ ሀገር ማንነት ያለው ማለት ነው!!!
ማወቅ መልካም ነው
ያወቁትን ማሳወቅ ደግሞ ፍፁም
በጎነት ነው ። በምድር ላይ
የምናደርጋቸው መልካም ነገሮች ሁሉ በሰማይ ላይ የዘላለም ደመወዝ ሆነው ይከፈሉናል ።
ስለዚህ አንተም ወዳጄ
ይህ አሁን ያነበብከው መጣጥፉ
ከተመቸህ ወዳጅ ዘመድዎም
እንዲማርባቸው #ሼር#ላይክ -
#ኮሜንት አድርጉላቸው ።
ሰናይ ቀን ተመኘሁ
#Dereje Alebachew

በሳኡዲ አልጋ ወራሽ ትዕዛዝ በሙሰና ሰበብ የታሰሩት የሳኡዲ የንጉሳዊያን ቤተሰቦችና ባለስልጣን እንዲሁም ባለ ሀብቶች እነዚህ ናቸው።


ሼህ መሀመድ ሁሴን አል አሙዲ በሙስና ተጠርጥረው ታሰሩ።
ኒው ዮርክ ታይምስ እንደዘገበው አል አሙዲንን ጨምሮ በርካታ ሰዎች በሳኡዲ መንግስት በሙስና ተጠርጥረው ታስረዋል። 11 ልኡላን እና ሚኒስትሮች፣ እንዲሁም ቢሊየነር ነጋዴዎች ከታሳሪዎቹ ውስጥ ተካተዋል። ከታሳሪዎች መካከል የሚከተሉት ይገኙበታ፦
ልኡል አልዋሌድ ቢን አብዱላህ 
ልኡል አልዋሌድ ቢን ታላል 
ልኡል ሚተብ ቢን አብዱላህ
ልኡል ቱርኪ ቢን አብዱላህ
ካሊድ አል ትዋይጂሪ
አደል ፋኬህ
ኢብራሂም አል አሳፍ
አብዱላህ አል ሱልጣን
ባክር ቢን ላደን
መሀመድ አል ቶባሺ
አምር አል ዳባግ
መሀመድ ግሁሴን አል አሙ።

Saturday, November 4, 2017

ESAT YETSETETA HAYILOCH DASESA PART ONE NOVEMBER 04 2017

Open letter to His Excellences Crown prince Håkon and Crown princess Mette Marit of Norway

Your Excellences Crown Prince Håkon and Crown Princess Mette Marit of Norway

We Ethiopians and Norwegians of Ethiopian origin, living in Norway have heard that you are travelling to Ethiopia during the coming few days of time. We are happy that you got the time to visit that historic and ancient country in Africa.
Your Excellences,
We believe that you are aware of the current political situation in Ethiopia. The Country is ruled by the regime TPLF/EPRDF for the last 26 years. The political atmosphere in the country is deteriorating over time during the past 26 years of TPLF’s rule, and now it is transforming to chaotic situation. Today, anti-government demonstrations costing human lives are a day-by-day phenomenon in many parts of the country.
The regime incites conflict between the various ethnic groups as part of its long-standing ‘divide and rule’ strategy to stay in power. These conflicts become out of control even for the regime itself. Ethiopians face killing, imprisonment, eviction from their holdings on a daily bases.
Ethiopia is standing at a cross road and crying for help. This help is not material investment, but distancing from the current regime that prohibit Ethiopians coexist peacefully and in harmony in Ethiopia.  TPLF is the driving force of the regime in Ethiopia. As its name tells, the Tigray People’s Liberation Front (TPLF) stands for a minority ethnic group in Ethiopia and promoting dangerous ethnic based politics that leads the country into disintegration.
Your Excellences,
We are well aware that the Norwegian government is one of those who has good relationship with the regime in Ethiopia. Norway as a peace-loving country would not have created a friendship with a regime that mercilessly kill and deny basic human rights to its people.
A country, like Norway, known for its long tradition of conflict resolution and maintenance of peace and stability, should stand with the Ethiopian people, but not with the ethnocentric corrupt dictators.
Ethiopia today need countries, institutions, government officials and individuals, like Your Excellences, who advocate Human Rights and rule of law.
Your Excellences,
If Your Excellences are travelling to Ethiopia to encourage business and investment under the current brutal regime in Ethiopia, you are making a historic mistake. Ethiopians consider investment in Ethiopia at this moment is not only unsafe but also unethical.
The regime in Ethiopia has evicted millions of farmers, pastoralists and urban dwellers and sold their farmland and holdings for the so-called foreign investors. Selling/leasing farmland to foreign investors without properly compensating poor owners was described as one of the alarming land grab in Africa. Land grab in Ethiopia is condemned by many international organizations.
We hope the scheduled visit of your Excellences to Ethiopia may focus on issues of Human Rights and stabilization of a better political atmosphere in the country rather than business and investment with a corrupt and murderous regime.
Yours faithfully,
Ethio-Norwegians in Norway,

ህወሀቶች በማያቋርጥ ስብሰባ ውስጥ ናቸው (ጋዜጠኛ መሳይ መኮንን)

ልዩነታቸው ከመጥበብ ይልቅ እየሰፋ መጥቷል። የበላይነት ይዟል የተባለው በስብሃት ነጋ የሚመራው ቡድን ከሳሞራ የኑስ ላይ ወታደሩን የመንጠቅ ሙከራው የተሳካ ባለመሆኑ አንዳቸውም አንጃ ገዝፎ መውጣት ተስኖት በር ዘግተው መጠዛጠዛቸውን ቀጥለዋል። መጨረሻቸው አጓጊ ይመስላል። ቦታ እየቀያየሩ የቀጠሉት ህንፍሽፍሽ ለኢትዮጵያ መፍትሄ ለማምጣት እንዳልሆነ ይታመናል። ከችግር ፈጣሪ መቼም የመፍትሄ ሀሳብ አይፈልቅም። የመለስ ዜናዊ አይነት ብልጣብልጥና ሴረኛ መሀላቸው ባለመኖሩ አንደኛው አንጃ ነጥሮ የመውጣትና ሌላኛው ደፍልቆ ለማንበርከክ ያለው እድል እጅግ ጠባብ ነው። ዝሆኖች ሲጣሉ ጥሩ ነው።Bilderesultat for መሳይ መኮንን
የህወሀቶች ህመም መድሃኒት ያለው አይደለም። ፈውስ የለውም። ጠራርጎ ሊወስዳቸው ከሚችል ጽኑ ህመም ጋር እየሰቃዩ ለመሆናቸው በርካታ ክስተቶችን ማሳየት ይቻላል። አንዱና ዋና የኦህዴድ ሰሞንኛ እንቅስቃሴ ነው። አንዳንዶች ቲያትር ነው፡ ያለህወሀት ፈቃድ ኦህዴድ ስንዝር መራመድ አይችልም የሚል አስተያየት ይሰጣሉ። እኔም ይህን አስተያየት ሙሉ በሙሉ ውድቅ የማደርገው አይደለም። ነገር ግን ህወሀት ከገባበት ማጥ፡ ከተዘፈቀበት አረንቋ፡ ከሚያሰቃየው ጽኑ ህመም፡ ስር ከሰደደው የእርስ በእርስ ፍጥጫ አኳያ ከተወሰደ ህወሀት ለማሴር፡ ቲያትር ለመስራት አቅም ያለው አይመስለኝም። ህወሀት ተዝረክርኳል። ሀገሪቱ ዝናብ እንዳበላሸው ሰርግ መላ ቅጧ የጠፋባት የሆነችው ያለምክንያት አይደለም።
ለህወሀት መዳከም ትልቁ ማሳያ አባወራው መብዛቱም ነው። ለውጭ ዲፕሎማቶች ግራ እስኪያጋባ ድረስ የትኛው አለቃ፡ የትኛው አዛዥ እንደሆነ አይታወቅም። የአራት ኪሎው ቤተመንግስት ያዘዘውን የካዛንቺሱ መንግስት የሚሽርበት፡ የመቀሌው አለቃ የወሰነውን፡ የአዲስ አበባው ቡድን የሚያፈርስበት ሁኔታ ከተፈጠረ ሰንብቷል። የውጭ ሀገራት ዲፖሎማቶች ስለኢትዮጵያ ጉዳይ ከየትኛው አካል ጋር እንደሚነጋገሩ አያውቁትም። ባለፈው የቃሊቲን እስር ቤት ለመጎብኘት አዲስ አበባ የገቡት ዲፕሎማቶች ከአቶ ሃይለማርያም ፍቃድ አግኝተው ቃሊቲ ሲደርሱ በሌላኛው ቡድን ቀጭን ትዕዛዝ ጉብኝታቸው ተከልክሏል። የቅርብ ጊዜው የአቶ በቀለ ገርባ የዋስ መብት ውሳኔ የተሻረውና በኋላም የታገደው በዚሁ ምክንያት ነው።
አረናዎች ዛሬ በመቀሌ ያደረጉት ሰላማዊ ሰልፍም የህወሀትን አቅም ማጣት ከሚያሳዩ ክስተቶች አንዱ ነው የሚል እምነት አለኝ። ህወሀት የትግራይ ህዝብ አማራጭ እንዲኖረው ፈጽሞ አይፈቅድም። ''መስመሪ ህወሀት መስመሪ ህዝበ ትግራይ እዩ'' የሚለው የእነመለስ ዜናዊ ዶክትሪን በትግራይ ምድር መቼም ህወሀትን የሚቀናቀን ፓርቲ እንዲኖር የሚፈቅድ አይደለም። የትግራይ ህዝብ ሌላ ነገር እንዲያስብ ከቶም አይፈለግም። ህወሀትን እንደብቸኛ አዳኝ እንዲቀበል የህወሀት መዝገብ ውስጥ በስውር ተጽፏል። ከሌላው የኢትዮጵያ አከባቢ ይልቅ ትግራይ ለብዝሃነት ፊት ተነፍጓታል። ለአማራጭ ሀሳቦች እድል አልተሰጣትም። ህወሀትና ህወሀት ብቻ ትግራይ ምድርን ይሞሏት ዘንድ የህወሀት መጽሀፍ ቅዱስ ይደነግጋል። እናም አረናዎች ከነችግሮቻቸው ለትግራይ ህዝብ ያልተለመደ ድምጽ ለማሰማት የሚፍጨረጨሩት የህወሀትን መዳከም ተከትሎ ነው። ዛሬ በመቀሌ አረናዎች ይዘው የወጡት መፈክር የህወሀትን ዶክትሪን የሚወግዝ ነው። ''ህወሀትን ህዝቢ ትግራይን ዝተፈላለዮ 'ዮም'' - የትግራይ ህዝብና ህውሀት አንድ አይደሉም ነው ትርጉሙ።

ESAT Bezhisamint November 4 2017 Gizaw Legesse,Semahagn Gashu,Deres Geta...

በህወሀት ላይ አምፆ የሰነበተው ኦህዴድ መለሳለስ ማሳየቱ እየተነገረ ነው Wazema ONAIR 110417

Friday, November 3, 2017

በኢትዮጵያ የተከሰተው የኑሮ ውድነት ህዝቡን እያማረረ መሆኑ ተሰማ። (ኢሳት ዜና–ጥቅምት 24/2010)

 በኢትዮጵያ የተከሰተው የኑሮ ውድነት ህዝቡን እያማረረ መሆኑ ተሰማ።
ኢሳት ወደ ተለያዩ የኢትዮጵያ አካባቢዎች በመደወል ያነጋገራቸው ኢትዮጵያውያን እንደሚሉት የኑሮ ውድነቱ የመኖር ህልውናቸውን አደጋ ውስጥ ከቶታል።
በተለይ በዝቅተኛ የኑሮ ደረጃ ላይ የሚገኙ ኢትዮጵያውያን የዕለት ጉርሳቸውን መሸመት አቅቷቸው አደጋ ውስጥ መውደቃቸውን ነው የተናገሩት።
በሌላ ዜና በሀዋሳ ነጋዴዎችና ባለሀብቶች ምሬት ላይ መሆናቸው ተሰምቷል።Image may contain: one or more people, crowd and outdoor
ከዋጋ ግሽበትና ከብር የመግዛት አቅም መቀነስ ጋር በተያያዘ ነጋዴው ለከፍተኛ ኪሳራ በተዳረገበት በዚህን ወቅት ለአባይ ቦንድ አዲስ ዙር ገንዘብ አምጡ በሚል በመንግስት በኩል ጫና እየተደረገባቸው መሆኑን የደረሰን መረጃ አመልክቷል።
የኑሮ ውድነቱ ከምን ጊዜው በላይ እየከፋ በመምጣቱ የሀገር ውስጥ ስደት መጨመሩን መረጃዎች ያሳያሉ።
የምግብ ሸቀጦች ዋጋ በሶስትና ከዚያ በላይ እጥፍ በመጨመሩ ህዝቡ መኖር እንዳቃተው እየገለጸ ነው።
መሰረታዊ የሆኑ የምግብ ሸቀጦች ዋጋቸው ከመጨመሩም በላይ አንዳንዶቹ ከገበያ ውስጥ በቀላሉ የማይገኙ በመሆናቸው ከፍተኛ አደጋ ውስጥ መግባታቸውን ያነጋገርናቸው ገልጸዋል።

በተለይም ጤፍ፣ ስኳር፣ ቲማቲምና ዘይት ላይ የተከሰተው የዋጋ ጭማሪ ህዝቡ ሊቋቋመው ከሚችለው በላይ በመሆኑ በቀን አንድ ጊዜ መብላት የማይችለው ኢትዮጵያዊ ቁጥር በከፍተኛ መጠን እየጨመረ መምጣቱንም መረጃዎች ይጠቁማሉ።
በተለይ በዝቅተኛ የኑሮ ደረጃ ላይ የሚገኙ ኢትዮጵያውያን የዕለት ጉርሳቸውን መሸመት አቅቷቸው አደጋ ውስጥ መውደቃቸውን ነው የተናገሩት።
ለሕጻናት የእለት ተእለት ምግብ የሆነውን ወተት እንኳን መስጠት ብርቅ የሆነበት ደረጃ ላይ መደረሱን ነው ነዋሪዎቹ በምሬት የሚገልጹት።
በሌላ በኩል የአባይ ዋንጮ በዙር ሀዋሳ መግባቱን ተከትሎ ነጋዴዎችና ባለሀብቶች ከፍተኛ መጠን ያለው ገንዘብ እንዲያዋጡ መወሰኑ ታውቋል።
የኢሳት ምንጮት እንደገለጹት የሀዋሳ ነጋዴዎች በተደራራቢ ጫናዎች መስራት ከማይችሉበት ደረጃ ላይ ናቸው።
በቅርቡ የተጣለባቸው ከአቅም በላይ ግብር በርካታ ነጋዴዎች ለኪሳራ ከመዳረጉም በላይ ጥቂት የማይባሉት ፍቃዳቸውን መመለሳቸውን ለማወቅ ተችሏል።
በየጊዜው እየጨመረ የመጣው የዋጋ ግሽበትም በሀዋሳ ነጋዴዎች ላይ ያመጣው ጉዳት ቀላል የማይባል ሲሆን በተያዘው ወር መጀመሪያ ላይ በመንግስት ርምጃ የተቀነሰው የብር የመግዛት አቅምም ለነጋዴው ብርቱ አደጋ ማምጣቱ ይነገራል።
በእነዚህ ምክንያቶች ለኪሳራ ተዳርጎ ከጨዋታ ውጪ በሆነው የሀዋሳ ነጋዴ ማህበረሰብ ላይ ለአባይ ግድብ ገንዘብ እንዲያዋጡ መገደዱ ከፍተኛ ምሬት ማስከተሉን ከምንጮቹ መረጃ ለመረዳት ተችሏል።
በዙር ሀዋሳ የደረሰው የአባይ ዋንጫ በየአከባቢው ህዝቡን ለስገዳጅ መዋጮ በመዳረግ እያማረረ መሆኑን የገለጹት ምንጮች በቅርቡ በሲዳማ ዞን በጭኮ መምህራን አናዋጣም በማለት የስራ ማቆም አድማ ማድረጋቸው የሚታወስ ነው።
አንዳንድ ነጋዴዎች እንደሚሉት ስራ በጠፋበት፣ ኢኮኖሚው በወደቀበት፣ ግብር ያለአቅም ተቆልሎ ነጋዴው ሀገር ጥሎ ለመሰደድ በቋፍ ላይ ባለበት በዚህን ወቅት ከፍተኛ መጠን ያለው ገንዘብ ለአባይ መዋጮ እንዲያቀርቡ በመንግስት ታዟል።
ከዚህ ቀደም በተደጋጋሚ ያዋጡት ገንዘብ ሳይመለስላቸው ሌላ ዙር መምጣቱ ግራ እንዳጋባቸውም ተናግረዋል።
የአባይ ግድብ በገንዘብ እጥረት ስራው ከቆመ ወራት የተቆጠሩ ሲሆን የአባይ ዋንጫ በየክልሉ እየዞረ ከፍተኛ መጠን ያለው ገንዘብ እንዲሰበሰብ ከአባይ ግድብ ብሄራዊ ምክር ቤት በተወሰነው መሰረት ህዝቡን ለምሬት የዳረገ መዋጮ በአስገዳጅነት እየተከናወነ ይገኛል።