Friday, January 30, 2015


Golgul/ጎልጉል: የድረገጽ ጋዜጣ

ማክሰምና መሰንጠቅ – ባንዳና ባርነት
(ርዕሰ አንቀጽ)
http://www.goolgule.com/splitting-and-destroying-the-way-o…/
ህወሃት በዘረፈውና በሚዘርፈው ሃብት ተጠቅሞ ለወዳጆቹ የሚያኮራ፣ ትውልድ ለሚላቸው የሚበጅ ተግባራት እያከናወነ እንደሆነ ይነግረናል፤ ይነግሩናል። ውስን ባለሥልጣናትና አበሮቻችው በሃብት ተመንድገዋል። በንዋይ ሰከረው የሚያደርጉት እስኪጠፋቸው ናጥጠዋል። የት ጋር አንደሚያበቃ ባይታወቅም፣ የተደሰቱ፣ የተከፉ፣ የተናቁ፣ የተሰረቁ፣ የሚሰረቁ፣ እየሰረቁ ያሉ፣ የተትረፈረፈላቸው፣ በስማቸው የሚነገድባቸው፣ ባሪያዎችና ባንዳዎች፣ ቀን የሚጠብቁ፣ ጥርሳቸውን የነከሱ፣ … ወዘተ “አብረው” አሉ፡፡
የአንድነትና የመኢአድ ቢሮ በፖሊስ ተከቧል
የአንድነት ለፍትሕና ዴሞክራሲ ፓርቲ (አንድነት) ቢሮ በፖሊስና በደህንነት መከበቡን አቶ አስራት አብርሃ ለነገረ ኢትዮጵያ ገልጸዋል፡፡ ቢሮው በደህንነትና በፖሊስ በመከበቡ አባላት መውጣትና መግባት እንደማይችሉ የገለጹት አቶ አስራት ‹‹ውጭ ያለነው ወደ ውስጥ እንዳንገባ ተከልክለናል፡፡ ውስጥ ያሉትም መውጣት አይችሉም፡፡›› ብለዋል፡፡ የአንድነት አመራሮችና አባላት እንዳይወጡና እንዳይገቡ የከለከሉት ደህንነትና ፖሊሶች የከበባውን ምክንያት እንደማይናገሩ አቶ አስራት ለነገረ ኢትዮጵያ ገልጸዋል፡፡
በተመሳሳይ የመላው ኢትዮጵያ አንድነት ድርጅት (መኢአድ) ቢሮው በፖሊስና በደህንነቶች በመከበቡ አመራሮችና አባላቱ ወደ ውስጥ መግባትም ሆነ ወደ ውጭ መውጣት እንደማይችሉ ተግልጾአል፡፡

Thursday, January 29, 2015

Negere Ethiopia

የሰማያዊ አመራሮችና አባላት ቅጣት ተላለፈባቸው
ሰማያዊ ፓርቲ ሚያዚያ 19 ቀን 2006 ዓ.ም በአዲስ አበባ ሰላማዊ ሰልፍ ባደረገበት ወቅት ሰላማዊ ሰልፉን በተመለከተ በራሪ ወረቀት ሲበትኑ በቁጥጥር ስር ውለው በየካ ፖሊስ ጣቢያ በነበሩበት ወቅት ‹‹ጣቢያ ውስጥ ደንብ ተላልፋችኋል›› በሚል ክስ የተመሰረተባቸው 14 የፓርቲው አመራሮችና አባላት ዛሬ ጥር 21 ቀን 2007 ዓ.ም በቀበና ፍርድ ቤት በዋለው ችሎት በቀረበባቸው ክስ ጥፋተኛ በመሆናቸው 13ቱ እያንዳንዳቸው 200 ብር እንዲቀጡ ተወስኗል፡፡
ተስፋዬ መርኔ የተባለው ተከሳሽ ግን ‹‹ከዚህ በፊት ተመሳሳይ ሪኮርድ ያለበት በመሆኑ›› በሚል የ600 ብር ቅጣት ተጥሎበታል፡፡
14ቱ የፓርቲው አባላት በፖሊስ ጣቢያ እያሉ ‹ፍትህ የለም›፣ ‹ዴሞክራሲ የለም›፣…በማለት ጮክ ብለው ድምጻቸውን በማሰማት የጣቢያውን ደንብ እንደተላለፉ አቃቤ ህግ ያቀረበውን ክስ ማስረዳት ችሏል በሚል ፍርድ ቤቱ የጥፋተኝነት ውሳኔ ለማስተላለፍና ቅጣቱን ለመጣል ተጠቅሞበታል፡፡
በመሆኑም 14ቱም የፓርቲው አመራሮችና አባላት የተጣለባቸውን የገንዘብ ቅጣት ከፍለዋል፡፡ ሆኖም ግን የፓርቲው አመራሮችና አባላት በውሳኔው ላይ ይግባኝ እንደሚጠይቁ ገልጸዋል፡፡

“በሀገሬ ጉዳይ ያገባኛል ባይ ሰው ነኝ” – አርቲስት አስቴር በዳኔ (ቃለምልልስ ከቁምነገር መጽሔት ጋር) - See more at: http://www.zehabesha.com/amharic/archives/38553#sthash.LEKH1jiu.Aalg0BKS.dpuf

ሰሞኑን በማህበራዊ ድረገፆች እና አንዳንድ መገናኛ ብዙሃን ላይ ስሟ በተደጋጋሚ የሚነሳው አርቲስት አስቴር በዳኔ የሀገራችን ‹ታዋቂ› አርቲስቶችን ባሳተፈውና ህወሃት የተመሰረተበትን 40ኛ ዓመት ክብረ በዓል ምክንያት በማድረግ በተዘጋጀው የጉብኝት ፕሮግራም በጠየቀቻቸው ጥያቄዎች መነጋገሪያ አጀንዳ ሆና ሰንብታለች፡፡ አስቴር ለመከላከያ ሚኒስትር ጠቅላይ ኤታማዦር ሹም ለሆኑት ለጄኔራል ሳሞራ የኑስ ባቀረበቻቸው ጥያቄዎች የደነገጡ አንዳንድ የሙያ ጓደኞቿ ሳይቀሩ ‹ማግለልና መድልዎ› ለመፍጠርም ሲሞክሩ ስለመታየታቸው ይነገራል፡፡ የራሷን አቋም በግልፅና በድፍረት በዚያ መድረክ ላይ ካቀረበችው አስቴር በዳኔ ጋር አዲስ አበባ ላይ አጠር ያለ ቆይታ ከቁምነገር መጽሄት ጋር አድርጋለች – ለግንዛቤ እንዲረዳዎ ዘ-ሐበሻ እንደወረደ አስተናግዳዋለች::፡ ቁም ነገር፡- ሰሞኑን በማህበራዊ ድረ ገፆች ላይ ስምሽ በስፋት እየተነሳ ነው፤ ምንድነው? አስቴር፡- እንግዲህ ከሰሞኑ የደደቢት ጉዞ ጋር የተያያዘ ይመስለኛል፡፡ በጉዞው ላይ ለየት ያሉ ጥያቄዎች ጠይቃለች በሚል መሰለኝ የተለያየ ነገር እየተባለ ያለው፡፡ ቁም ነገር፡- አንቺስ የተለየ ጥያቄ ጠይቄያለሁ ብለሽ ታስቢያለሽ? አስቴር፡- ያሉና ሁሉም የሚያውቀውን ህዝቡ ውስጥ ያሉ ጥያቄዎችን ነው የጠየቅሁት፤ አዲስ ነገር አለው ብዬ አላስብስም፡፡ ቁም ነገር፡- በመጀመሪያ እስኪ በጉዞው ላይ እንዴት እንድትሳተፊ እንደተጠራሽ ንገሪኝ? አስቴር፡- እንደማንኛውም አርቲስት ነው

Ethiopia Bloggers to Enter Pleas in Terrorism Case Next Week - See more at: http://www.zehabesha.com/ethiopia-bloggers-enter-pleas-terrorism-case-next-week-2/#sthash.xUQg48fv.dpuf

zone 9 `

Wednesday, January 28, 2015

እንካን ለ94 ኛው አመትህ ጥር /20 2007 በሰላም.አደረሰህ ውድ እና ብርቅ በኢትዪጵያውያን ልብ ውሰጥ በክብር ላለህው ተወዳጁ አባቴ እግዚሐብሄር ረጅም እድሜና ጤና እንዲሰጥህ የዘወትር ምኞቴ.ነው ። ልጅህ የትምወርቅ ጃጋማ

በነገረ ኢትዮጵያ ሪፖርተር

ጋዜጠኞችና ጦማርያኑ ለጥር 26 ቀጠሮ ተሰጠባቸው
∙ፍርድ ቤቱ ተሻሻለ በተባለው ክስ ላይ ብይን ሰጥቷል
በነገረ ኢትዮጵያ ሪፖርተር
የዞን ዘጠኝ ጦማርያንና ጋዜጠኞች ዛሬ ጥር 20 ቀን 2007 ዓ.ም ለ16ኛ ጊዜ በፌደራሉ ከፍተኛ ፍርድ ቤት ልደታ ምድብ 19ኛ ወንጀል ችሎት የቀረቡ ሲሆን፣ ፍርድ ቤቱ ቀደም ብሎ ተሻሻለ የተባለውን ክስ አይቶ ብይን ሰጥቷል፡፡ በዚህም መሰረት ከአራቱ ነጥቦች መካከል አንዱን ብቻ ውድቅ ሲያደርግ ሦስቱን እንደተሻሻሉ ቆጥሮ በክሱ ውስጥ እንደተካተቱ እንዲቀጥሉ በብይኑ አመልክቷል፡፡
ፍርድ ቤቱ በአቃቤ ህግ የክስ ማሻሻያ ላይ የሰጠውን ብይን በንባብ አሰምቷል፡፡ በዚህ መሰረት የፌደራል አቃቤ ህግ አሻሽየዋለሁ ያለውን ክስ ከአንዱ ነጥብ በስተቀር ቀሪዎቹ ሦስት ነጥቦች ፍርድ ቤቱ በሰጠው ትዕዛዝ መሰረት አቃቤ ህግ አሻሽሏል በሚል ፍርድ ቤቱ በቀበሉን በብይኑ አመልክቷል፡፡ 
ስለሆነም በክሱ ላይ የተጠቀሰው የተከሳሾች የስራ ክፍፍል አለ በሚል የቀረበው ነጥብ ብቻ በአቃቤ ህግ እንዳልተሻሻለ በመውሰድ ፍርድ ቤቱ ውድቅ ሲያደርገው ሌሎቹ ነጥቦች፣ ማለትም ‹ቡድን› በሚል የተጠቀሰው፣ የ48000 ብሩን ጉዳይ እንዲሁም ተከሳሾቹ ስልጠና መውሰዳቸውን የሚገልጸው ነጥቦችን ፍርድ ቤቱ እንደተሻሻሉ ቆጥሮ ተሻሻለ በተባለው ክስ ውስጥ እንዲካተቱ ብይን ሰጥቷል፡፡ 

የጄነራል ጃጋማ ኬሎ የሕይወት ታሪክ/ Biography of L/General Jagama Kello (94) Happy Birth


የጄነራል ጃጋማ ኬሎ የሕይወት ታሪክ/ Biography of L/General Jagama Kello (94) Happy Birth Day

Postby MINILIK SALSAWI » 26 minutes ago

Image

Monday, January 26, 2015

የደደቢት ጉዞ መዘዝ፤ ከሰራዊት ፍቅሬ እስከ ታገል ሰይፉ (ክንፉ አሰፋ)

የደደቢት ጉዞ መዘዝ፤ ከሰራዊት ፍቅሬ እስከ ታገል ሰይፉ
(ክንፉ አሰፋ)
http://www.goolgule.com/trip-to-dedebit-serawit-to-tagel/
በመጀመርያ ዶክተር ደብረ ጽዮን ገብረ ሚካኤል የህዝባዊ ወያኔ ሃርነት ትግራይ (ህወሃት) ደጋፊና ተደጋፊ የኪነጥበብ ባለሙያዎችን በሙሉ ጠሯቸው። ሰበሰቧቸው። እንዲህም አሏቸው። “ወደ ደደቢት አብራችሁን ትሄዳላችሁ፤ እዛ እንደደረሳችሁም አመጣጣችንንና አካሄዳችንን በደንብ አድርጋችሁ ታጤናላችሁ። ከዚያ ስትመለሱ ሁሉንም ነገር ለህዝቡ ትናገራላችሁ።…”
በምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር ማዕረግ የሃገር መሪ ሆነው የሚሰሩት እኝህ ሰው መልዕክታቸውን በዚህ አላበቁም። አይናቸውን ፈጠጥ፤ ጉሮሯቸውንም ጠረግ-ጠረግ አደረጉና ንግግራቸውን ቀጠሉ “ስለረጅሙና መራራው ትግላችን፤ ከጅምራችን እስከ አያያዛችን የታዘባችሁትን ሁሉ ንገሩን። ጥሩውንም ይሁን መጥፎውን ነገር ሳትደብቁ ተናገሩ።…”

Sunday, January 25, 2015

Breaking News: UK diplomats clash over Briton on death row in Ethiopia January 24, 2015

UK diplomats clash over Briton on death row in Ethiopia: Officials’ fury after Foreign Secretary claims he couldn’t ‘find time’ to help father-of-three facing execution

  • Andargachew Tsege was snatched by officials at Yemen airport last June
  • The 59-year-old was transferred to Ethiopia where he is thought to remain
  • Father-of-three moved to London in 1979 from native African country
  • He was dubbed ‘Ethiopian Mandela’ after exposing government corruption
  • Leaked emails revealed British officials’ frustration at political inaction
  • Philip Hammond said he could not ‘find time’ for phone call on issue
UK diplomats clash over Briton on death row in Ethiopia
From left Andargachew Tsige’s wife Yemi Hailemariam, Andargachew Tsige and UK F

UDJ protest in Addis Ababa Ethiopia – January 25, 2015 (Video) - See more at: http://www.zehabesha.com/udj-protest-in-addis-ababa-ethiopia-january-25-2015-video/#sthash.yKAgukrC.dpuf


አንድነት በአዲስ አበባ የጠራው ሰልፍ በተንቀሳቃሽ ምስል (Video) ይመልከቱ
http://www.zehabesha.com/udj-protest-in-addis-ababa-ethiop…/
You may use these HTML tags and attributes: <a href="" title=""> <abbr title=""> <acronym title=""> <b> <blockquote cite=""> <cite> <code> <del datetime="">...

ከብት እየተደበደቡ ነው። እጅግ በጣም ከፍተኛ ጉዳይ ደርሷል የአንድነት ፓርቲ ሰልፎች ቀጥታ ዘገባ ይከታተሉ – ሰላማዊ ዜጎች በአገራቸውና በምድራቸው እንደ ከብት እየተደበደቡ ነው። እጅግ በጣም ከፍተኛ ጉዳይ ደርሷል - See more at: http://satenaw.com/amharic/?p=4004#sthash.maSJ6vMz.dpuf

 ሸዋ ሮቢት

በሸዋ ሮቢት ሰልፉ በጣም ደምቋል። የስርዓቱ ደህንነቶች ህዝቡ እንዳይወጣ ቢያከላክሉም ህዝቡ ግን ጥሶ ወደ ሰልፉ እየመጣ ነው። ህዝቡ በከፍተኛ መነቃቃት ድምጹ እያሰማ ነው። በደብረ ማርቆስም ብዙ ህዝብ በተገኘበት ሰልፉ እየተካሄደ ነው። በሸዋ ሮቢት  በሺሆች የሚቆጠሩ ሰልፉን ተቀላቅለዋል። ሰልፉ በጣም ደምቋል። የስርዓቱ ደህንነቶች ህዝቡ እንዳይወጣ ቢያከላክሉም ህዝቡ ግን ጥሶ ወደ ሰልፉ እየመጣ ነው። ህዝቡ በከፍተኛ መነቃቃት ድምጹ እያሰማ ነው። በደብረ ማርቆስም ብዙ ህዝብ በተገኘበት ሰልፉ እየተካሄደ ነው።

Saturday, January 24, 2015

ታገል ሰይፉ



የዚህ ሁሉ መነሻ፤ የኢ

ለኢትዮጵያ የዋልክላትን ውለታ የሚመልስልህ ሆድህ ብቻ ነው !!! 24 January 2015 at 10:02

ምኒልክ ዘጎጃም ዘመነ ትዝታ ቅፅ -  ክፍል - ፪

ፊት አውራሪ ገሞራውን ድፍን የጎጃም ሰው ያውቃቸዋል ። ገሞራው የጦር ሜዳ ስማቸው ነው እናት እና አባቶቻቸው ያወጡላቸው ስም ሸዋፈራሁ ነው ነገሩ ስምን መላእክ ያወጠዋል ነው ። ወራሪ ኢጣሊያንን አይቀጡ ቅጣት ሰጥተው በጀግንነት ጣሊያንን ድል ከነሱ አርበኞች አንዱ ናቸው ። የእነ በላይ ዘለቀ ጦር ሶማ በረሃ ላይ ኢጣሊያ ዶግ አመድ ሲያደርጉ የእነ ፊት አውራሪ ኃይለ ኢየሱስ (አባ ፍላቴ) ጦር ደግሞ የጨረቃ ላይ ኢጣሊያንን እንዳልነበር አደረገው ። በእነ ፊት አውራሪ ገሞራው የሚመራው ጦር ደግሞ ደጋ ዳሞት ላይ በእሳተ ገሞራዊ ጥቃት አጋዬው ። ፊት አውራሪ ገሞራው ከሁለት ሺ አምስት መቶ በላይ የኢትዮጵያ አርበኞችን ይዘው ነበር ለአምስት አመታት ኢጣሊያንን ተዋግተው ያሸነፉት ። ኢጣሊያን የእነ ፊት አውራሪ ገሞራው ጦር መቋቋም ከሚችለው በላይ ሁኖበታል ያለ የሌለ ኃይሉን አሰባስቦ ለማጥቃት ይነሳል ድንገት እንደ እሳተ ገሞራ የፊት አውራሪ ገሞራው ጦር በኢጣሊያን የጦር ሰፈር ላይ ጥቃት ይሰነዝራል አሁን ገሞራው ሸሸ ሲባል እንደ እሳተ ገሞራ ደንገት ይፈነዳል በዚህ የተነሳ ኢጣሊያን ፊት አውራሪ ገሞራውን ለማግባባት ሽማግሌ ይልካል ይኸኔ ፊት አውራሪ እንዴት ቢንቀኝ ነው ይህ ሶላቶ እጄን እንድሰጥ እና ሀገሬን እንድሸጥ ባንዳ ሁኜ ክብሬን እንድለውጥ የሚያግባባኝ በማለት እሳት ለብሰው እሳት ጎርሰው ለሽማግሌዎች እንድ ነገር ላስቸግራችሁ ይችን መልእክት አድርሱልኝ አሏቸው ፦

Journalist Reeyot: Prisoner of conscience continues in defiance to TPLF/EPDRF prison January 21, 2015


The recent article posted on several websites entitled ” metaram yemgebaw manew” (መታረም የሚገባው ማነው) by Journalist Reeyot Alemu caught my eyehttp://www.abugidainfo.com/amharic/index.php/16788.Reeyot Alemu is a budding Ethiopian poet, essayist, and journalist.

by Ewnetu Sime

Ethiopia: The Invention of Ethnic Politics January 24, 2015

Take a random group of Ethiopians as you find them in any public place. You will never hear them defining themselves by a single characteristic. If you ask one of them how a person is defined, he/she will say that a person is defined by age, gender, class, social role, religion, culture, ethnic background, etc. This same person is also Ethiopian, African, and human. This means that, outside a political realm, individuals see their personality as a heterogeneous unity, as the interactions, interpenetrations of multiple identities yielding a unified person, like different notes compose a musical piece. This heterogeneous self is the reality of all individuals, how they grasp their essence and existence. Be it noted that nothing is distinct or dominant in the claimed unity; rather, all the factors interpenetrate and constitute a changing and complex sense of oneself.Ethiopia, The Invention of Ethnic Politics
by Messay Kebede

ኢሳት ዜና

ኢትዮጵያን እየመሩ ያሉ ከፍተኛ ባለስልጣናት በሙሉ በጥቂት ቀናት ትምህርት ብቻ ከአንድ የውጪ ዩኒቨርሲቲ የማስተርስ ዲግሪ እንዲያገኙ መደረጋቸው ተመለከተ።
ጥር ፲፫(አስራ ሦስት ) ቀን ፳፻፯ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-ሀገሪቱ የምትመራበትን ፖሊሲ ከመጠምዘዝ ጀምሮ ድርጊቱ በሀገርና በህዝብ ላይ የከፋ ተጽእኖ እንዳለው የተገነዘቡ ኢትዮጰያውያን በዩኒቨርሲቲው ላይ የተቃውሞ ዘመቻ እያስተባበሩ ነው።
አዲስ አበባ የሚገኘው ኢንተርናሽናል ሊደር ሺፕ ኢንስቲትዩት አማካይነት የሚቀርቡለትን ባለስልጣናት በአጭር ቀናት ኮርስ በማስተርስ ዲግሪ እያንሸበሸ ያለው ፤በእንግሊዝ ሀገር የሚገኘው የግሪንዊች ዩኒቨርሲቲ ነው። በአይ ኤል አይ ድረገጽ እንደተመለከተው ጠቅላይ ሚኒስትር ሀይለማርያም ደሳለኝን ጨምሮ ሁሉም የሀገሪቱ ባለስልጣናት በቀናት ኮርስ ከአንድ ትምህርት ቤት ማለትም ከግሪንዊች ዩኒቨርሲቲ የማስተርስ ዲግሪ እንዲወስዱ ተደርገዋል።

የአርበኛው አቶ አንዳርጋቸው 60ኛ ዓመት የልደት በዓል!


Andybrithday

የነጻነትና የፍትህ ታጋዩ አርበኛው አንዳርጋቸው ጽጌ በወያኔ ትውልድ ገዳይና ሰው በላ መዳፍ እጅ ከወደቀበት ቀን ጀምሮ ኢትዮጵያውያን በእልህ፣ በቁጭትና በቁርጠኝነት ከበፊቱ በበለጠ ትግላችንን አጠናክረን እንድንቀጥል አድርጎናል።ዘረኛውና አረመኔው ወያኔ አንዳርጋቸውን በመያዝና በማሰር የነጻነት ትግሉ ወደ ኋላ ይገታል ብሎ የቅዠት ህልም ቢያልምም አገር ወዳድ ኢትዮጵያውያን በሙሉ ግን ሁላችንም አንዳርጋቸው ጽጌዎች በመሆን የቆመለትን ዓላማ ከግብ ለማድረስ ተግተን ተነስተናል።
ይህንንም ለማረጋገጥ ለኢትዮጵያ አገራችን ነጻነትና ፍትህ ለማስፈን የህይወት መስዋትነትን እስከ መክፈል ድረስ እየታገለ የሚገኘውን የነጻነት ተምሳሌት የጀግናው አንዳርጋቸው ጽጌ ፷ኛ ዓ

Friday, January 23, 2015

olgul/ጎልጉል: የድረገጽ ጋዜጣ

የመኢአድ ም/ፕሬዝደንት የፖሊስ ልብስ በለበሱ ከፍተኛ ድብደባ ተፈፀመባቸው
http://www.goolgule.com/aeup-vice-pres-beaten-badly/
የመላው ኢትዮጵያ አንድነት ድርጅት (መኢአድ) የፓርቲያቸው ምክትል ፕሬዝደንት እና የሰሜን ቀጠና ኃላፊ የሆኑት አቶ ዘመነ ምህረት እጅግ ዘግናኝ ድብደባ ደርሶባቸው ሲል ፓርቲው ጥር 15/2007 ዓ.ም በሰጠው መግለጫ አስታወቀ፡፡ አቶ ዘመነ የመኢአድን ጠቅላላ ጉባኤ አድርገው ወደ መኖሪያቸው ጎንደር ከተማ ከተመለሱ በኋላ ከፍተኛ የደህንነት ክትትልና ጫና ይደረግባቸው እንደነበር ለፓርቲያቸው አሳውቀው ነበር ያለው ፓርቲው በ10/05/2007 ዓ.ም ጎንደር ከሚገኘው መኖሪያው ቤታቸው ከባቤታቸውና ከህጻን ልጃቸው ፊት የፖሊስ ልብስ በለበሱ አካላት ከፍተኛ ደብደባ ተፈጽሞባቸው ወዳልታወቀ ቦታ መወሰዳቸውን ግልጾአል፡፡ በአሁኑ ወቅት የፓርቲው አባላት ባደረጉት ክትትል አቶ ዘመነ አዘዞ የሚገኘው የመከላከያ ካምፕ ውስጥ እንደሚኙ አረጋግጠናል ያለው መግለጫው የሰው ልጅ ላይ ይፈጸማል ተብሎ የማይገመት ከፍተኛ ስቃይና ሰቆቃ ደርሶባቸዋል ብሏል፡፡

የመከላከያ ሰራዊት

አለመተማመን ይስተዋላል።ፊሽካው እስኪነፋ የሚጠብቀዉ የመከላከያ ሰራዊት አፈሙዙን ወደ ወያኔ እንደሚያዞረዉ ታማኝ የዉስጥ ምንጮቼ ግምታቸዉን አካፍለዉኛል።የኢትዮዽያ መከላከያ ሰራዊት የወያኔ ዕድሜ አራዛሚ ላለመሆንና የጭቆና ቀንበርን ለመስበር በጣት የሚቆጠሩ ቀናቶች ብቻ ቀርተዋል።

We Need Freedom


ተነስ ተነስ ተነስተናል! አንተ ያገሬ ጀግና
ኢትዮጵያን እና ኢትዮጵያዊያንን ከምድረ ገጽ እስከ ወዲያኛው ፈጽሞ ለማጥፋት ለሴኮንዶች እና ለስንዝር ወደ ኋላ የማይሉ መርዘኛ የወንበዴ ቡድኖች እና የርኩስ ሴራቸውን ከእንግዲህ ለመታገስ ወደ ማይቻልበት ወቅት ላይ ደርሰናል፡፡
ኢትዮጵያ እና ኢትዮጵያን በረጅም የኋሊት ታሪካችንም ሆነ በመጻኢ ዘመናችን ወዲያኛው ገጥሞን በማያውቅ እና ይገጥመናልም ተብሎ በማይጠበቅ የህልውና ጥልቅ ገደል አፋፍ ላይ እናገኛለን፡፡ ለኛ ለኢትዮጵያን መራብ፣ መታረዝ፣ መደንቆር፣ መጠማት፣ በችግር መመታት፣ በወረርሽኝ ማለቅ፣ በድርቅ መመታት፣ በጦርነት ማለቅ፣ ስደት፣ ሥራ አጥነት፣ ውነብድና፣ ሴተኛ አዳሪነት፣ እስር፣ ድብደባ፣ እንግልት፣ ውርደት፣ሞት፣ መለያየት፣ ዘረኝነት፣ ጎጠኝነት፣ ሙስና፣ የፍትህና የነጻነት እጦት፣ የውሃ፣ የመብራት፣ የስልክ፣ የትራንስፖርት፣ ... ወዘተረፈ ህልቆ መሳፍርት ቀጥተኛ ተጠቂዎች የምንሆንበት ዘመን ከእንግዲህ ያከትማል፡፡
ጥቂቶች ሚሊዮኖችን የዋህ ህዝብን እርስ በእርስ በማባላት የሚቀጥሉበት ዘመን ከእንግዲህ ከህልምነት ሊዘል አይችልም፡፡ ማንኛውም ኢትዮጵየዊ በአሁኑ ወቅት ከፊቱ በስንዝር ርቀት የሚጠብቀውን በየቤቱ የሚንኳኳበት የነጻነት የትግል ችቦ ለማቀጣጠል ተነስቷል፡፡ ይህንን የመላው ህዝብ ትግል ከእንግዲህ በየትኛውም መልኩ ሊያጨናግፍ የሚችል መድራዊ ሀይል እንደማይኖር ለዘላለም መመኪያችን በሆነው ኃያል አምላክ ተስፋ እናደርጋለን፡፡ በተሰጠንም የድል አድራጊነት መንፈስ በሙሉ ልብ በቆራጥነት እና በጀግንነት ታግለን የሚያስከፍለውን መሰዋዕትነት ሁሉ ከፍለን የነጻነት አየር ለመተንፈስ ተዘጋጅናል፡፡
ክቡር የኢትዮጵያ ሕዝብ ሆይ ከእንግዲህ ለራስህ ነጻነት መቆም ያለብህ ራስህ ነህና በአንድነት ሆ ብለህ ለአንዲት ኢትዮጵያ ትንሳኤ በቆራጥነት እና ጀግንነት ተነስ፡፡

Ethiopia decimates free press – Human Rights Watch January 22, 2015

(Human Rights Watch, Nairobi) – The Ethiopian government’s systematic repression of independent media has created a bleak landscape for free expression ahead of the May 2015 general elections, Human Rights Watch said in a report released today. In the past year, six privately owned publications closed after government harassment; at least 22 journalists, bloggers, and publishers were criminally charged, and more than 30 journalists fled the country in fear of being arrested under repressive laws.The Ethiopian government’s systematic repression of independent media
The 76-page report, “‘Journalism is Not a Crime’: Violations of Media Freedom in Ethiopia,” details how the Ethiopian government has curtailed independent reporting since 2010. Human Rights Watch interviewed more than 70 current and exiled journalists between May 2013 and December 2014, and found patterns of government abuses

Negere Ethiopia 41 mins ·

የሰማያዊ አባላትና ደጋፊዎች ‹‹ካርድ አልቋል›› እየተባሉ እንደሆነ ገለጹ
በምስራቅ ጎጃም ዞን የተለያዩ የምርጫ ጣቢያዎች ላይ የመራጮች ካርድ እጥረት አልቋል እንደተባሉ የነገረ ኢትዮጵያ ምንጮች አስታወቁ፡፡ ምንጮቹ የመራጭነት ካርድ ለመውሰድ ባመሩባቸው የምርጫ ጣቢያዎች ካርድ እንደሌለ ተገልጾላቸው እንዲመለሱ መደረጋቸውን ገልጸዋል፡፡
ኢህአዴግ በተለያዩ አደረጃጀቱ በመጠቀም ኢህአዴግን ይመርጣሉ ብሎ ያሰባቸውን ዜጎች ቤት ለቤት ሳይቀር እየቀሰቀሰ ምርጫ ካርድ እንዳደላቸው የገለጹት ምንጮች፣ የተቃዋሚ ፓርቲዎችን ይመርጣሉ ተብለው የተገመቱት ዜጎች ግን ከወዲሁ ካርድ አልቋል እየተባሉ ወደ ቤታቸው እየተመለሱ መሆኑን ለማወቅ አስታውቀል፡፡

Thursday, January 22, 2015

“ጋዜጠኝነት ወንጀል አይደለም”

የሰብዓዊ መብት ጠባቂ የሆነው ድርጅት (ሂዩማን ራይትስ ዎች) “ጋዜጠኝነት ወንጀል አይደለም” በሚል ርዕስ ያወጣል ተብሎ የተጠበቀውን ዘገባ ማምሻው ላይ ይፋ አድርጓል፡፡ ከጥቂት ቀናት በፊት ጎልጉል የድረገጽ ጋዜጣ “ያለ ነጻ ሚዲያ – ምርጫ ወይስ ቁማር?” በሚል ርዕስ ባተመው ዜና ላይ ዘገባው እንደሚወጣ በተናገረው መሠረት ባለ 76 ገጽ ሪፖርቱ በሚዲያ አፈና ዙሪያ ዝርዝርና ወቅታዊ መረጃዎችን አውጥቷል፡፡
ኢህአዴግ በሚያደርስባቸው ስልታዊ አፈና፣ ማስፈራሪያ፣ ህይወት የማጥፋት ዛቻ፣ … ምክንያት በአሁኑ ጊዜ በትንሹ 22 የሚሆኑ ጋዜጠኞች በእስር ላይ እንደሚገኙ፤ ከ30 በላይ የሚሆኑ ደግሞ አገር ጥለው መኮብለላቸውን በዘገባው ተጠቁሟል፡፡ እንዲህ ያለው ገለልተኛ ሚዲያን የሚያፍን እና ከሜዳው የሚያስወጣ አሠራር ከወራት በኋላ ይካሄዳል ከሚባለው “ምርጫ” አኳያ የውድድሩን ሜዳ ከማጥበብ አልፎ እንዳይኖር እንደሚያደርገው የዘገባው ሃተታ ያስረዳል፡፡

Wednesday, January 21, 2015

Golgul/ጎልጉል: የድረገጽ ጋዜጣ የጠለምትና የወልቃይት ጠገዴ ጉዳይ የጎንደሬዎች . . .

የጠለምትና የወልቃይት ጠገዴ ጉዳይ የጎንደሬዎች . . .
http://www.goolgule.com/the-case-of-telemt-and-wolqayit-te…/
በጠለምት፣ በበየዳ፣ በጃናሞራ፣ በወልቃይት፣ በጠገዴ፣ በአርማጨኾ ነዋሪው እየተባረረ፣ ሀብቱ እየተዘረፈ፣ ያንገራገረው እየተገደለ፤ ሰው በምሬትና በሰቀቀን ኑሮውን መግፋት አቅቶት አጣብቂኝ ላይ ገብቷል። ትናንት ቡያ ነበር ክልሉ። ትናንት በሀከር ነበር ክልሉ። ቀጥሎ ራስ ደጀንን ወደነሱ አካተቱት። ጠገዴን ጠቀለሉት። ገፍተው ስሜን አውራጃን በሙሉ ጠቀለሉ። ወገራ አውራጃን ሽራርፈው ወሰዱና ጎንደር አውራጃን ተጠጉ። አሁን ዘለው የጎንደር ከተማውን ገነት ተራራ፤ የትግራይ መሬት እያሉ ለትግራይ ልጆቻቸው እያሰተማሩ ነው። ጎንደር ከምድረ ገጽ እንድትጠፋ እየተገፋ ነው። ይህ የመኖርና ያለመኖር፤ ውሎ የማደርና በ...

አቶ አንዳርጋቸው ፅጌን በጨረፍታ!

andargachew new picture
ግዛቸው አበበ
ከሁለት ሳምንት በፊት በዕለተ-እሁድ በኢትዮጵያ ቴሌቪዥን የፖሊስ ፕሮግራም ላይ ቀርቦ፣ እንደገና ከአራት ቀናት በኋላ በእለተ ሐሙስ በድጋሚ የታየው፤ አቶ አንዳርጋቸው ፅጌን የሚመለከተው ፕሮግራም፤ ጃኬትና ሸሚዝ ሳይቀር እየተቀያየረ ተበጣጥሶ የተገጣጠመ መሆኑ በግልጽ የሚታይ ነበር፡፡
ይህ ፊልም የቀረበው፡- “በኢትዮጵያ እስር ቤቶች ውስጥ ሰቆቃ አይፈጸምም” ለማለት ተፈልጎ መሆኑ ይታወቃል። በእውነት በኢትዮጵያ እስር ቤቶች፣ የምርመራ ማዕከላትና በደህንነት ጽሕፈት ቤቶች ውስጥ ግፍና ሰቆቃዎች አይፈፀሙም ወይ? ለሚለው ጥያቄ እውነተኛውን መልስ መስጠቱ ነው። ሌላው ቢቀር በኢትዮጵያ ፍርድ ቤቶች ቀርበው በምርመራ ማእከላትና እስር ቤቶች ውስጥ ሰቆቃና ግፍ እየተፈጸመባቸው መሆኑን የገለጹ በጣም ብዙ ሰዎች ስላሉ መለስ ብሎ መመርመር ተገቢ ነው።

በ‹‹ነጻነት ለፍትሃዊ ምርጫ›› የጀመርነው ነጻነታችን የማስመለስ ትግል ይቀጥላል!

ከ9ኙ ፓርቲዎች ትብብር የተሠጠ መግለጫ
ትብብራችን ‹‹ነጻነት ለፍትሃዊ ምርጫ›› በሚል መርህ እያካሄደ ያለው የጋራ እንቅስቃሴ መነሻና መሰረት የትብብሩን መግባቢያ ስምምነት ከመፈራረማችን በፊት በ14 ፓርቲዎች ‹‹የተቃውሞ ጎራው ዲሞክራቲክ ኃይሎች በትብብር ለመሥራት ያደረጉት ተደጋጋሚ ጥረት ለምን ከሸፈ?›› በሚል የተደረገው ጥናትና የጸደቀው መግባቢያ ሰነድና በእነዚህ ላይ የቆመው በትብብር አባላት የተዘጋጀው የተግባር ዕቅዳችን ነው፡፡ 
በእነዚህ ሰነዶች መሰረት የትብብሩ አባላት በሦስት መሰረታዊ ጉዳዮች ማለትም በምርጫ፣ በፖለቲካ ምህዳርና በዜጎች ሰብዓዊና ዲሞክራሲያዊ መብቶች ዙሪያ በደረሱት የጋራ ግንዛቤዎች መሰረት ካስቀመጥናቸው ሁለት ግልጽ ዓላማዎች አንዱ የፖለቲካ ምህዳሩን በማስፋትና የምርጫ ሜዳውን በማስተካከል መጪው ምርጫ ነጻ፣ ፍትሃዊ አሳታፊና ተኣማኒ የማድረግ የጋራ የተባበረ ትግል ማካሄድ እንደመሆኑ ለዚህ ተፈጻሚነት ‹‹ነጻነት ለፍትሃዊ ምርጫ›› በሚል መርህ የጋራ እንቅስቃሴ ከጀመርን ወራት መቆጠራቸው ይታወቃል፡፡

ኢሳት ዜና

http://ethsat.com/…/esat-daily-news-amsterdam-january-19-2…/
አቶ አንዳርጋቸው ጽጌ ከስድስት ወራት በሁዋላ ለመጀመሪያ ጊዜ ልጆቻቸውን ጨምሮ ከቤተሰቦቻቸው ጋር በስልክ መነጋረራቸው ተስፋ እንደሰጣቸው ባለቤታቸው ወይዘሮ የምስራች ገለጹ።
ጥር ፲፩(አስራ አንድ ) ቀን ፳፻፯ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-ወይዘሮ የምስራች በተለይ ለኢሳት ሲናገሩ፤ አቶ አንዳርጋቸው ካልታወቀ እስር ቤት ሆነው ልጆቻቸውንና የቤተሰቡን አባላት ድንገት ሲያናግሩ ደንግጠው እንደነበር በመጥቀስ፤ ድንገት የተደወለውን ስልክ ሲያነሱ በድምጻቸው ወዲያው እንደለዩዋቸው ግልጸዋል።

Tuesday, January 20, 2015

የ9ኙ ፓርቲዎች ትብብር ነፃነትን የማስመለስ ትግሉን አጠናክሮ እንደሚቀጥል ገለጸ

• ዜጎች የምርጫ ካርድ እንዲያወጡ ጥሪ አቅርቧልነገረ ኢትዮጵያ / Negere Ethiopia
9 mins · 
• ‹‹ምህዳሩ ካልተስተካከለ ምርጫው አንድ ቀን ሲቀረውም ቢሆን ከምርጫ ልንወጣ እንችላለን››
የ9ኙ ፓርቲዎች ትብብር ‹‹በነፃነት ለፍትሓዊ ምርጫ›› ዘመቻው ነፃነትን የማስመለስ ትግሉን አጠናክሮ እንደሚቀጥል ገለጸ፡፡ ትብብሩ ዛሬ ጥር 12/2007 ዓ.ም በሰጠው ጋዜጣዊ መግለጫ ኢህአዴግና ምርጫ ቦርድ አፈና እና ጫና እያደረጉ ቢሆኑም ነፃነትን ለማስመለስ የያዘውን ግብ ለማሳካት ወደኋላ እንደማይል ገልፀዋል፡፡ ‹‹የኢህአዴግ ጨካኝነትና የምርጫ ቦርድ አጋፋሪነት ሊቀጥል ይችላል›› ያሉት የትብብሩ ሊቀመንበር ኢንጅነር ይልቃል ጌትነት ሆኖም የትግሉ አላማ ኢህአዴግን ማጋለጥ በመሆኑ የሚያስፈልገውን መስዋዕትነት እየከፈሉ ትግሉን እንደሚቀጥሉ ገልጸዋል፡፡ በተመሳሳይ ‹‹ህዝቡ ካርድ እንዲያወጣ ጥሪ ስናደርግ የፖለቲካ ምህዳሩ ተስተካክሏል እያልን አይደለም፡፡ እኛ አሁንም እያነሳን ያለነው የትግል ጥያቄ ነው›› ያሉት የትብብሩ ም/ል ሊቀመንበር አቶ ኤርጫፎ ኤርዴሎ የትብብሩ የትግል አላማ ይህን የተዘጋ ምህዳር ማስከፈት መሆኑን አብራርተዋል፡፡

ነገረ ኢትዮጵያ / Negere Ethiopia

የምርጫ ካርድ ያልወሰዱ ዜጎች ስኳር እንዳይወስዱ ተከለከሉ
በምስራቅ ጎጃም ዞን አነደድ ወረዳ የቦቀል ቀበሌ ነዋሪዎች የምርጫ ካርድ ስልልወሰዳችሁ ስኳር አይሰጣችሁም መባላቸውን ለነገረ ኢትዮጵያ ገለጹ፡፡ በአካባቢው ስኳርን ጨምሮ ሌሎች አቅርቦቶች በስፋት እንደሚጠፉ የተናገሩት ነዋሪዎቹ ዛሬ ጠዋት የቀበሌ ካድሬዎች በድምጽ ማጉያ ‹‹ዛሬ ስኳር ስለመጣ ቀበሌ ድረስ መጥታችሁ እንድትወስዱ፡፡ የመጣው ስኳር ውስን በመሆኑ ሊያልቅ ስለሚችል ዛሬውኑ መጥታችሁ እንድትወስዱ እናሳስባለን፡፡ ከዛሬ ውጭ ላታገኙ ትችላላችሁ፡፡›› እያሉ ሲለፉ እንዳረፈዱ ተናግረዋል፡፡

Negere Ethiopia

‹‹ለውጥ ይመጣል፡፡ የመጣው ለውጡ እንደስከዛሬው እንዳይከሽፍ ግን ፖለቲከኞችና የፖለቲካ ቡድኖች በራሳችን ላይ አብዮት ማካሄድ አለብን፡፡ ከእስካሁኑ የተለየ ለውጥ እንዲመጣ የኢትዮጵያን ህዝብ የስልጣን ባለቤት ማድረግ አለብን›› ኢንጅነር ይልቃል ጌትነት

Monday, January 19, 2015

ወዳጃችን ዳዊት ከበደ አቶ ደብረ ጺዮንን በድብቅ ቀዳቸው!

ወዳጃችን ዳዊት ከበደ አቶ ደብረ ጺዮንን በድብቅ ቀዳቸው!
(ንግግሩ ለደደቢት አርቲስቶች (ደደቢት ለተጓዙት ማለት ነው! የተነገረ ነው። ይሄ የአቶ ደብረጺዮን ንግግር በሌላ በየትም ሚዲያ ላይ ያልተሰማ ሲሆን አውራምባ በድብቅ ስለቀዳቸው ድምጹ በቅጡ አይሰማም!) አቶ ደብረ ጺዮን በንግግራቸው አርቲስቶቹን እና ጋዜጠኞቹን ሲያባብሏቸው እና ሲያበረታቷቸው ይሰማል።
ከተናገሩት ውስጥ...
***በፌስ ቡክ የሚነገረንን ነገር እንሰማለን!
***አርቲስቶች ሆዳሞች እንደምትባሉ እናውቃለን!
***መለስን ሳይቀር የሚሳደቡ አሉ! መለስን ብቻ ሳይሆን ሁላችንንም ሲሰድቡን አየተናል!
***እናንተ የፈለጋችሁትን ነገር ንገሩን፤ ስድብም ከፈለጋችሁ ህሊናችሁ ከፈቀደ ስደቡን!
***ዝም ብላችሁ ጥሩ ጥሩ ነገር ብቻ ብትናገሩ አንሰማችሁም አጭበርባሪ ነው የምንላችሁ!
***ዝም ብሎ የሚቆልለንን ፊት ለፊቱ ባንናገረው ዞር ብለን አጭበርባሪ ማለታችን አይቀርም!
***ችግር እንዳለብን እኛም እናውቃለን!
እና የመሳሰሉትን ለደደቢት አርቲስት እና ጋዜጠኞች ሲነግሩ፣ እና ሲመክሩየአውራምባው ወዳጃችን ዳዊት ከበደ በድብቅ ቀድቷቸዋል።
እኛም በርታ ዳዊት ብለን አበረታተነዋል!

ነገረ ኢትዮጵያ / Negere Ethiopia

ሰማያዊ ጸ/ቤት ውስጥ የሚገኘው ታዳሜ ኦባንግ ሜቶን እያዳመጠ ነው፡፡ ‹‹እስክንድር ነጋ፣አንዱ ዓለም አራጌ፣ አብርሃ ደስታ፣ ዞን ዘጠኞች ለኢትዮጵያውያን ሲሉ ታስረዋል፡፡ ኢትዮጵያ ውስጥ እየታገላችሁ ያላችሁ ሁሉ እየታገላችሁ ነው፡፡ እናንተ የኢትዮጵያ ዞን ዘጠኞች ናችሁ፡፡ አብርሃ ደስታዎች ናችሁ፣ እስክንድሮች ናችሁ›› አቶ ኦባንግ

ነገረ ኢትዮጵያ / Negere Ethiopia

‹‹ለህወሓቶች ፖለቲካ ማለት ወዳጅና ጠላት የሚለይበትና ፍልሚያ የሚደረግበት ነው የሚሉት፡፡ አንድ የናዚ ሰውም ፖለቲካ ማለት ወዳጅና ጠላት የሚለይበት ሜዳ ነው የሚለው፡፡ ህዋቶች ያለ ጠላት መንቀሳቀስ አጥችሉም፡፡ ድህነትንም ጠላት ብለውታል፡፡ ሲጀመር እኛ እና እነሱ ይባልና፡፡ ጠላትና ወዳጅ ወደሚለው ያድጋል፡፡›› ዶክተር ዳኛቸው

የኢሕአዴግ የደህንነት መዋቅር መናጋቱን ምንጮች ጠቆሙ።

MLK: “When Will You Be Satisfied?” January 19, 2015

When Dr. Martin Luther King, Jr. [MLK] gave his “I Have a Dream Speech” in August 1963, he asked the “devotees of civil rights” a simple rhetorical question:  “When will you be satisfied?
Professor Alemayehu G. Mariam

In Picture: ESAT Journalists with Freedom Fighters January 19, 2015


The two top notch ESAT (Ethiopian Satellite Television) journalists Mesay Mekonnen and Fasil Yenealem are in Eritrea to gather news and reports about the Ethiopian patriots (freedom fighters), the following pictures are taken from Mesay Mekonnen’s Facebook page.
ESAT Journalists with Freedom Fighters

Should Ethiopians Boycott the Upcoming Fake Election in Ethiopia? January 19, 2015

January 19, 2015
(December 16, 2015. Washington, DC) The Solidarity Movement for a New Ethiopia (SMNE) has no choice but toObang Metho, Executive Director SMNE expose the duplicity and repression of choice in the upcoming Ethiopian National Election due to the dictatorial nature of the ethnic apartheid regime of the TPLF/EPRDF that has been in power for the last 24 years. The SMNE is non-political, non-violent social justice movement that stands up for the freedom, rights, and well being of all Ethiopians, regardless of ethnicity, political view, religion, regional background or other differences. We are very concerned about the future of the country.

More Crackdowns Lock Out Opposition Groups from Political

የ ‪#‎ኢሳት‬ ጋዜጠኛ መሳይ መኮንን ከኢትዮጵያ አርበኞች ግንቦት 7 ጋር በ ኤርትራ ...

***ሴቶች ደፈሩ***

“በማዕከላዊ እስር ቤት ውስጥ ቶርቸር (አካላዊ ስቃይ) የሚፈጸምባቸው ጩኸታቸው ይሰማኛል፡፡ የቃሊቲ ማጎሪያ ውስጥ የታሰሩ ተማሪዎች፣ ጋዜጠኞች፣ ፖለቲከኞች፣ የሃይማኖት መሪዎች፣ ንጹሃን ዜጎች፣ ስቃይ አሁንም ከፊቴ አለ፤ የሚሞቱት ሰዎች ሊረሱኝ አይችሉም፤ የእስር ቤቱ ጠረንና ሽታ ይከተለኛል፤ በአካል ደህና ብመስልም አእምሮዬ ግን አሁን ድረስ ሰላም የለውም” በማለት የስዊድን ጋዜጠኛ ማርቲን ሺብዬ በተለይ ለጎልጉል የድረገጽ ጋዜጣ ተናገረ፡፡
አንድ ዓመት ከሁለት ወር (14 ወራት) ከሥራ ባልደረባው ዮሐን ፔርሶን ጋር ኢህአዴግ አስሮት የነበረው ጋዜጠኛ ሺብዬ ለጎልጉል የአውሮጳ ዘጋቢ ይህንን የተናገረው በዖጋዴን ክልል የተፈጸመውን ጭፍጨፋ የሚያጋልጥ ዘጋቢ ፊልም መሰራጨቱን ተከትሎ ለቀረበለት ጥያቄ መልስ በሰጠበት ወቅት ነው፡፡
“በአካል ሰላም አለኝ፤ አእምሮዬ ግን አልዳነም፤ ሁሌም እረበሻለሁ፤ በዓይኔ ያየኋቸው፣ በጆሮዬ የሰማኋቸውና በበቂ ምስክሮች ያረጋገጥኳቸው ሁኔታዎች ዕረፍት ይነሱኛል” ሲል አስተያየቱን የጀመረው ሺብዬ በኢትዮጵያ እየተፈጸመ ያለው የሰብዓዊ መብት ጥሰትና ግፍ ከሙያው አስገዳጅነት በመነሣት ከተባባሪዎቹ ጋር በመሆን ለዓለም እንደሚያሳውቅ ግልጽ አድርጓል፡፡
ከጥቂት ሳምንታት በፊት “ከፌዴራል ፖሊስ ምርመራ ተገኘ” በሚል ዘወትር እሁድ በሚተላለፈው የፖሊስ ክፍለ ጊዜ የተላለፈውን ዘጋቢ ፊልም (ድርሰት) የኢህአዴግን ዓመታዊ ቋት የምትሞላውን አሜሪካ በእስረኞች አያያዝ የገሃነም ተምሳሌት አድርጎ ያቀረበ ነው፡፡ ኢህአዴግ በልማት ስም የሚያገኘውንና ለባለሥልጣኖቹ የግል ሃብት ማካበቻ እንዲሁም በየጎሬው ለተፈጠሩ እስር ቤቶች ግንባታ የሚደጉሙትን አገራት በሰብዓዊ መብት አያያዝ ከዜሮ በታች አድርጎ ያብጠለጠለ ነበር፡፡ ከተለያዩ ድረገጾችና የዩትዩብ ምስሎች በተለያዩ እስርቤት ያሉትን በማነጋገር ተገጣጥሞ የቀረበው “ድርሰት” (ዘጋቢ ፊልም) ተከትሎ ይሁን አይሁን በግልጽ ባይታወቅም የኢህአዴግ የልብ ወዳጅ ኖርዌይ እነ ሺብዬ ያዘጋጁትን ዘጋቢ ፊልም ይፋ አድርጋለች፡፡
Nrk2 በተሰኘው የኖርዌይ መንግሥታዊ ቴሌቪዥን ማስተባበል በማይቻልበት ደረጃ በዖጋዴን የተፈጸመውን ርኅራኄ የሌለውን ዘግናኝ ሰቆቃ ለመመልከት ተችሏል፡፡ (በተለይ በአውሮጳ የሚኖሩ ቪዲዮውን እዚህ ላይ መመልከት ይችላሉ -http://tv.nrk.no/program/KOID27002013/fanga-i-etiopia)
የቀድሞ የክልሉ ፕሬዚዳንት አማካሪና የሚዲያ ክፍል ኃላፊ የነበረው አቶ አብዱላሂ ሁሴን ከሱማሌ ክልል ይዞት ወደ አውሮጳ ባመጣው በራሱ በኢህአዴግ ባለሙያዎች የተቀዱ ማስረጃዎች፣ ሰለባዎችና የክልሉ (ምክትል) ፕሬዚዳንት በግልጽ ሰቆቃና ግፍን ሲያውጁ በሚሰማበት፤ ወታደሮች ሲገድሉ፤ በቢሮ ግምገማ ላይ ተቀምጠው ስለፈጸሙት የግፍ ጀብዱ ሲተርኩና የፈጸሙት ግፍ አልቃም ተብሎ ሲገመገሙ እንደወረደ በሚያሳየው በዚህ ዘጋቢ ፊልም የእነ ሺብዬ መከራ በውል ቀርቧል፡፡ (ቪዲዮውን እዚህ ላይ መመልከት ይቻላል - http://vimeo.com/73861187) በተለይም ፎቶ አንሺው ዮሐን ፔርሶን የክንዱ አጥንት በጥይት ተሰብሮ፣ ጭንቅላቱን አሸዋ ውስጥ ቀብረው ስቃዩን ሲያዳምጡ የሚያሳየው ምስል እጅግ የሚዘገንን ነው፡፡ ኢህአዴግ በእስረኞች አያያዝ “ጻድቀ ጻድቃን” ነኝ ባለ 24 ሰዓት ባልሞላ ጊዜ ውስጥ የኖርዌይ ቴሌቪዥን ያሰራጨው ዘጋቢ ፊልም የኢህአዴግን አውሬነት ያሳየ ለመሆኑ አብዛኞች አስተያየት እየሰጡ ነው፡፡
የኢህአዴግ የልብ ወዳጅና የልማት አጋር ኖርዌይ እንዲህ ዓይነት ጠንካራ የዲፕሎማሲ ጉዳዮችን ሊነካካ በሚችል ጉዳይ ጣልቃ ስትገባ ይህ በመጀመሪነት የሚጠቀስ ነው፡፡ እንግዲህ ይህንን ተከትሎ ነበር ጋዜጠኛ ሺብዬ አስተያየት የሰጠው፡፡ እርሱ እንደሚለው ሙያዊ ኃላፊነቱ በዚህ በዖጋዴን የሚፈጸመውን ጭፍጨፋ እንዲጋልጥ አነሳስቶታል፡፡ ለወትሮው ወደ ዖጋዴን አንድም ሚዲያ እና የሲቪክ ተቋማት ድርሽ እንዳይሉ በሩን ጠርቅሞ የዘጋው ኢህአዴግ ባላሰበውና ባልጠበቀው መንገድ እነ ጋዜጠኛ ሺብዬ ይህንኑ ለመዘገብ ክልሉን ዘልቀው ሊገቡ ችለው ነበር፡፡
“ያየነውን ለዓለም ማሳየት፣ የኢህአዴግን ፕሮፓጋንዳ ማጋለጥ ዓላማችን ነው” የሚለው ሺብዬ በፖሊስ ፕሮግራም ቀረበ ስለተባለው የኢህአዴግ “ድርሰት” የሰጠው ምላሽ (ኢህአዴግ ይህንን ያህል ከሚለፋ) ማዕከላዊን እና ቃሊቲን ለጋዜጠኞች፣ ለቀይ መስቀልና ለዓለምአቀፍ ተቋማት ክፍት በማድረግ ምስክር ማግኘት ብቻ ይበቃዋል ሲል ፕሮፓጋንዳውን አጣጥሎታል፡፡ በቃሊቲ እስረኞች እንደሚሞቱ፣ በቂ የሚባል መጸዳጃ እንኳን እንደሌለ የተናገረው ሺብዬ አሁን ያለሁበት ቦታ የፈለኩትን ማድረግ የምችልበት ቢሆንም እዚያ ያሉትን ንጹሃን መዘንጋት ግን አይቻለኝም፤ ዘወትር እረበሻለሁ” በማለት ተናግሯል፡፡ በማያያዝም ይህንኑ ኢህአዴግን የሚያጋልጥ በእንግሊዝኛ የተጻፈ መጽሐፍ በሚቀጥለው ወር ለገበያ እንደሚበቃ አስታውቋል፡፡ በመጨረሻም በኢትዮጵያ ውስጥ በእስር ለሚማቅቁ ወገኖች መልካም ቀን እንዲመጣ ምኞቱን ገልጾዋል፡፡
ይህ በእንዲህ እንዳለ ዘጋቢ ፊልሙ ይፋ በሆነ ማግስት ዓለምአቀፉ የጦር ወንጀለኞች መርማሪ ኮሚሽን በክልሉ ምክትል ፕሬዚዳንት አብዱላሂ ወሬራ እና በመመሪያ ሰጪዎቹ የህወሃት/ኢህአዴግ ባለሥልጣናት በጦር ወንጀለኝነት ለመክሰስ ምርመራ ማካሄድ መጀመሩ ታውቋል፡፡
ሁለቱ የስዊድን ጋዜጠኞች በእስር በነበሩበት ወቅት አቶ መለስ “የጥቁርም የነጭም ደም ቀይ ነው” በማለት ለፈጠሩት ፓርላማ ሲፈላሰፉና በህግ የበላይነት እንደሚያምኑ እያስጨበጨቡ ሲናገሩ ቢቆዩም የልመና ኮሮጃቸውን የሚሞሉት የምዕራባውያን ዜጎችን አስረው መቀጠል እንደማይችሉ ሲረዱ “በዕርቅ” መፍታታቸው መዘገቡ አይዘነጋም፡፡
በሌላ በኩል ጎልጉል የድረገጽ ጋዜጣ ዖጋዴን ዙሪያው ገባ ታጥሮ ሰሚና ተመልካች እንዳይኖር ተደርጎ የከፋ ወንጀል ሲካሄድ እንደነበር የስዊድን ጋዜጠኞች ዜና ሳይሰማ ያገባናል ለሚሉ ወገኖች ሁሉ የማሳሰቢያ ዜና መስራቱ ይታወሳል፡፡ በተለይም የአዲሲቷ ኢትዮጵያ የጋራ ንቅናቄ በቀጥታ ድርጊቱን በማውገዝ መግለጫ ማውጣቱ አይዘነጋም፡፡ ከመግለጫው የተወሰደው ቃል እንዲህ ይነበባል፡-
“… ለወራት ያህል በመለስ ታማኞች ትዕዛዝ ሰጪነት የተከበቡት ኦጋዴኖች በረሃብ ተጠበሱ። ችግሩ ሲጠናባቸው ሽማግሌ በመላክ “በረሃብ ማለቃችን ነው። እኛ ንፁሃን ዜጎች ነን። ህፃናት እየተጎዱ፣ ከብቶቻችን እያለቁ ነው’’ በማለት ከከበባው ለመውጣት ጥያቄ ቢያቀርቡም ትእዛዝ ከተላለፈላቸው የጦር አዛዦች ያገኙት መልስ ጥይት ነበር። በተፈጥሯቸው አንድ ቀበሌ መኖር የማይችሉ ዘላኖች (አርብቶ አደሮች) ከቦታ ቦታ መዘዋወር ተከልክለው ለአራትና አምስት ዓመታት እንዴት ኖሩ? ምን ያህልስ ሰብዓዊ ቀውስ ደረሰ? ከአመታት የስቃይ ኑሮ በኋላ የመጨረሻው የፍርድ ቀን ደርሶ በኦጋዴን የጅምላ ጭፍጨፋ ተካሄደ። ንፁሃን ጉድጓድ ተምሶ በጅምላ እንዲቀበሩ ተደረገ። ከዚያን ጊዜ ጀምሮ መለስ ስለ ኦጋዴን ሲነሳ ያማቸው ጀመር። ከዋናው የኦጋዴን ነፃ አውጪ ግንባር ጋር የሰላም ስምምነት አድርጌያለሁ ቢሉም አካባቢውን ገለልተኛ ወገኖች ገብተው እንዲመለከቱት ፈቅደው አያውቁም። ሰሞኑን የስዊድን ጋዜጠኞች ላይ የተወሰደው ርምጃም የዚሁ ‹ምስጢር ይወጣብኛል› ፍርሃቻ አካል ስለመሆኑ ጥርጥር የለንም … ”
“… ኦጋዴን በሚኖሩ ዜጎቻችን ላይ የተፈጸመው ጭፍጨፋ ተድበስብሶ ቢከርምም ዛሬ በሶማሊያ የተከሰተውን አስፈሪ ርሃብ ተከትሎ ይፋ መሆን ጀምሯል። ድርጅታችን በጋምቤላ፣ በደቡብ፣ ክልል፣ በአዲስ አበባና በተለያዩ የአገራችን ክፍሎች የተፈፀሙትን ጭፍጨፋዎች በመቃወም እንዳደረገው ሁሉ በኦጋዴን የተፈፀመው ጭፍጨፋ በገለልተኛ ወገን እንዲጣራ አስፈላጊውን ሁሉ እያደረገ ነው። የኦጋዴን ጉዳይ የሁሉም ኢትዮጵያዊያን ጉዳይ በመሆኑ ይህ መግለጫ የሚደርሳችሁ አካላት በሙሉ ድርጊቱን በመቃወም አግባብ ያለው ተፅዕኖ በማድረግ በአገር ውስጥና በዓለም አቀፍ መድረክ ትግላችሁን እንድትቀጥሉ አጥብቀን እናሳስባለን” ሲል ጥሪውን አስተላልፎ ነበር። (የመግለጫው ሙሉ ቃል እዚህ ላይ ይገኛል)
በዖጋዴን የደረሰውን በተመለከተ እንዲሁም የሁለቱን ጋዜጠኞች በተመለከተ እስካሁን የዘገብናቸውን ከዚህ በታች ተዘርዝረዋል፡፡
ኢትዮጵያ፡ በፖለቲካ እስረኞች ላይ የማሰቃየት ድርጊት ይፈጸማል፤ ፖሊስ በጋዜጠኞች እና በተቃዋሚዎች ላይ በደሎችን ይፈጽማል።
(http://www.goolgule.com/t-h-e-y-w-a-n-t-a-c-o-n-f-e-s-s-i-…/)
በሚዲያ መረሳት ያስፈራል፤ “ነጻ ፕሬስ ከሌለ አገር አደጋ ላይ ነው”
http://www.goolgule.com/when-the-media-forgets/
“የጥቁርም የነጭም ደም ቀይ ነው” የመለስ ድራማ!! ኢህአዴግ ለመክሰስ ሲፈልግ ፊልም እንደሚደርስ ተረጋገጠ
http://www.goolgule.com/the-plight-of-swidish-journalists-…/
*********************************************
ማሳሰቢያ፤ በተለይ በስም ወይም በድርጅት ስም እስካልተጠቀሰ ድረስ በጎልጉል የድረገጽ ጋዜጣ® ላይ የሚወጡት ጽሁፎች በሙሉ የጎልጉል የድረገጽ ጋዜጣ®ንብረት ናቸው፡፡ ይህንን ጽሁፍ ለመጠቀም የሚፈልጉ ሁሉ የዚህን ጽሁፍ አስፈንጣሪ (link) ወይም የድረገጻችንን አድራሻ (http://www.goolgule.com/) አብረው መለጠፍ ከጋዜጠኛነት የሚጠበቅና ህጋዊ አሠራር መሆኑን ልናሳስብ እንወዳለን፡፡