Thursday, January 29, 2015

Negere Ethiopia

የሰማያዊ አመራሮችና አባላት ቅጣት ተላለፈባቸው
ሰማያዊ ፓርቲ ሚያዚያ 19 ቀን 2006 ዓ.ም በአዲስ አበባ ሰላማዊ ሰልፍ ባደረገበት ወቅት ሰላማዊ ሰልፉን በተመለከተ በራሪ ወረቀት ሲበትኑ በቁጥጥር ስር ውለው በየካ ፖሊስ ጣቢያ በነበሩበት ወቅት ‹‹ጣቢያ ውስጥ ደንብ ተላልፋችኋል›› በሚል ክስ የተመሰረተባቸው 14 የፓርቲው አመራሮችና አባላት ዛሬ ጥር 21 ቀን 2007 ዓ.ም በቀበና ፍርድ ቤት በዋለው ችሎት በቀረበባቸው ክስ ጥፋተኛ በመሆናቸው 13ቱ እያንዳንዳቸው 200 ብር እንዲቀጡ ተወስኗል፡፡
ተስፋዬ መርኔ የተባለው ተከሳሽ ግን ‹‹ከዚህ በፊት ተመሳሳይ ሪኮርድ ያለበት በመሆኑ›› በሚል የ600 ብር ቅጣት ተጥሎበታል፡፡
14ቱ የፓርቲው አባላት በፖሊስ ጣቢያ እያሉ ‹ፍትህ የለም›፣ ‹ዴሞክራሲ የለም›፣…በማለት ጮክ ብለው ድምጻቸውን በማሰማት የጣቢያውን ደንብ እንደተላለፉ አቃቤ ህግ ያቀረበውን ክስ ማስረዳት ችሏል በሚል ፍርድ ቤቱ የጥፋተኝነት ውሳኔ ለማስተላለፍና ቅጣቱን ለመጣል ተጠቅሞበታል፡፡
በመሆኑም 14ቱም የፓርቲው አመራሮችና አባላት የተጣለባቸውን የገንዘብ ቅጣት ከፍለዋል፡፡ ሆኖም ግን የፓርቲው አመራሮችና አባላት በውሳኔው ላይ ይግባኝ እንደሚጠይቁ ገልጸዋል፡፡

No comments:

Post a Comment