Wednesday, January 28, 2015

እንካን ለ94 ኛው አመትህ ጥር /20 2007 በሰላም.አደረሰህ ውድ እና ብርቅ በኢትዪጵያውያን ልብ ውሰጥ በክብር ላለህው ተወዳጁ አባቴ እግዚሐብሄር ረጅም እድሜና ጤና እንዲሰጥህ የዘወትር ምኞቴ.ነው ። ልጅህ የትምወርቅ ጃጋማ

##### ታሪክን የኋሊት #####
(ጥር 20 ቀን 1913 ዓ.ም)
/ ሌ/ኮ/ጃገማ ኬሎ/
"…አዋሽ ከወንዞች ሁሉ የተለየና የተመረጠ ባህሪ አለው። ይህ ወንዝ ከጀግናው ጃገማ ህይወት ጋር ቀጥተኛ የሆነ የህይወት እንቅስቃሴና ቁርኝት ያለው ይመስላል።
ጃገማ አዋሽ ወንዝ ከአንድ አካባቢ የመነጩ ናቸው። ጃገማ ገና በህፃንነቱ የታላቅ ወንድሞቹ አለቃ የሆነ፣በአፍላ ወጣትነቱ የሶስት ሺህ አምስት መቶ አርበኞች አለቃ የሆነ፣ የራሱን ፅኑ እምነት የሚከተል፣ ዘመናዊ ትምህርት ያላቸው፣ ውቂያኖስ አቋርጠው ሄደው ዘመናዊ የውትድርና እውቀት የቀሰሙና ዘመናዊ ኑሮ የነበራቸው ሰዎች ገባሩ የሆኑለት ጀግና ነው።"…
* ጃገማ ኬሎ የበጋው መብረቅ (የህይወት ታሪክ) _ ፍቅረ ማርቆስ ደስታ
የኢጣሊያ ጦር የአድዋ ላይ ሽንፈቱን ሊወጣ ጦሩን እጅግ አግዝፎ ከ40 ዓመት ዝግጅት በኋላ በድጋሚ ሀገራችንን ወሮ ህዝብ ሲፈጅ ሀገሩን ሊታደግ ሁሉም በየፊናው ሲራወጥ በ15 ዓመት ዕድሜ የአባታቸውን ጀብድ ሊደግሙ በዱር ዘምተው ጠላትን አርበድብደዋል። በዚህም "የበጋ መብረቅ" ተብለው ተሰይመዋል።
ጠላት ከሀገር ከተባረረም ኋላ ዘመናቸው ኢትዮጲያን ሲያገለግሉ ኖረዋል።
የዛሬው ቀን እኚህ ጀግና አርበኛ ሌተናል ኮሎኔል ጃገማ የተወለዱበት ቀን ነው! ከተወለዱም 94 ዓመታቸው።
መልካም ልደት እንዲሁም ዘላለማዉ ክብር ለብርቅዬው አርበኛ ጃገማ ኬሎ! ረዥም ዕድሜ ከጤና ጋር ያድልልን!
ኢትዮጲያ ለዘላለም ትኑር!!!
* ለመረጃ… ልደታቸው ላይ መገኘት የሚችል Yetmwrok Jagema Kello ን አናግሯት።

No comments:

Post a Comment