ሸዋ ሮቢት
በሸዋ ሮቢት ሰልፉ በጣም ደምቋል። የስርዓቱ ደህንነቶች ህዝቡ እንዳይወጣ ቢያከላክሉም ህዝቡ ግን ጥሶ ወደ ሰልፉ እየመጣ ነው። ህዝቡ በከፍተኛ መነቃቃት ድምጹ እያሰማ ነው። በደብረ ማርቆስም ብዙ ህዝብ በተገኘበት ሰልፉ እየተካሄደ ነው። በሸዋ ሮቢት በሺሆች የሚቆጠሩ ሰልፉን ተቀላቅለዋል። ሰልፉ በጣም ደምቋል። የስርዓቱ ደህንነቶች ህዝቡ እንዳይወጣ ቢያከላክሉም ህዝቡ ግን ጥሶ ወደ ሰልፉ እየመጣ ነው። ህዝቡ በከፍተኛ መነቃቃት ድምጹ እያሰማ ነው። በደብረ ማርቆስም ብዙ ህዝብ በተገኘበት ሰልፉ እየተካሄደ ነው።
ደብረ ማርቆስ
ደብረ ማርቆስ ሰልፉ በአራት ሰዓት ( 10 ኤም) ተጀምሯል። ብዙ ህዝቡ በሰልፉ ተገኝቷል። የተለያዩ መፈክሮች እየተሰሙ ነው። ድል የሕዝብ ነው ! አንድነት አንድ ነው ! ዉሸት ሰለቸን ፣ ኢሕአዴግ በቃህ፣ ጭኮኖ በቃን፣ ግፍ በጋን፣ ኢሕአዴግ ይወድቃል ! ኢትዮጵያ ነጻነቷን ትሻለች ! ኢቲቪ፣ ኢቢሲ ዉሸት ነህ ! ….የሚሉ መፈክሮች ሰልፈኞቹ እያሰሙ ነው። በአዲስ አበባ እየደረሰ ያለውን ግፍ እናወግዛለን ሲሉም በአዲስ አበባ የአንድነት አባላትን ደጋፊዎች ላይ እየደረሰ ያለውን ኢሰብዓዊ ግፍ አዉግዘዋል !!!
ኮንባ – ገሞጎፋ
በገሞጎፋ ዞን ከንባ ወረዳ ሰልፍ ሊጀመር ነው። የወረዳው ከሰማኒያ በላይ የሚሆኑ አደራጆች በፓርቲው ጽ/ቤት ተሰባስበዋል። በወረዳው 30 ቀበሌዎች አሉ። በዚያ የሚኖሩ በእርሻ ሥራ የሚተዳደር ገበሬዎች ወደ አንድነት ጽ/ቤት እየመጡ ነው።
በኮንባ ፣ አርባ ምንጭ ዞን ሰልፉ ገና አልተጀመረም። ገበሬዎች ወደ ሰልፉ ሲመጡ የከንባ ፖሊስ ታጣቂዎች “ከኢሕአዴግ ጋር መጣላት ምን ያደርግላቹሃል ? የሚያሸንፈው ኢሕአዴግ ነው” እያሉ ብዙዎች ለማከላከል ቢሞክሩም ሰው ወደ ሰልፉ እየመጣ ነው። ከኮንባ ሥት ሰዓት መንገድ ረቆ ፣ ከበርታ ገበሬዎች ወደ ሰልፉ እየመጡ ነው። ሶስት ሰዓት ተጎዞ መምጣት ለመብትና ለነጻነት !!!!!
አዲስ አበባ
11፡ 30 AM አዲስ አበባ ሰዓት
በአዲስ አበባ ፣ በዛሬው ዕለት በህወሃት/ኢህአዴግ ፖሊሶች አንድነት ፓርቲ የጠራውን ሰልፍ ለመበተን ከፍተኛ ድብደባ ተፈፀመ፡፡ ድብደባው የአካል ማጉደልንም ያካተተ ነው፡፡ ጋዜጠኛ ስለሺ ሐጎስና አቶ ዳግማዊ ተሰማ ራሳቸውን ስተዋል፡፡ ዳግማዊ አይኑ ማየት አልቻለም፡፡ በአንባገነኑ ስርዓት ከፍተኛ ድብደባ ከተፈፀመባቸው አመራር አባላትና አባላት መካከል፡-
1. አቶ አስራት አብርሃም (የህዝብ ግንኙነት ተጠባባቂ ሃላፊ)
2. አቶ ዳንኤል ተፈራ (የውጭ ጉዳይ ሃላፊ)
3. አቶ ብሩ ብርመጅ (የፖለቲካ ጉዳይ ሃላፊ)
4. አቶ ፀጋየ አላምረው (ምክትል አፈ-ጉባኤ)
5. አቶ አሻግሬ መሸሻ (የሰሜን ቀጠና ሃላፊ)
6. አቶ ሰለሞን ስዩም (የኤዲቶሪያል ቦርድ ሰብሳቢ)
7. ወ/ት ልዕልና ጉግሳ (የም/ቤት አባል)
8. አቶ ዳግማዊ ተሰማ (የም/ቤት አባል)
9. ጋዜጠኛ ስለሺ ሀጎስ
10. አቶ ስንታየሁ ቸኮል (የአዲስ አበባ የወጣቶች ጉዳይ ሃላፊ)
11. አቶ አሸናፊ አሳምረው (የወረዳ አመራር)
12. አቶ ኢሳያስ ቱሉ (አባል)
13. ወ/ት መስከረም ያረጋል (አባል)
14. አቶ ሃይሉ ግዛው (የወረዳ ሰብሳቢ)
15. አቶ አዲሱ መኮንን (የወረዳ ሰብሳቢ)
16. አቶ ሲሳይ ካሴ (አባል)
17. አቶ ወጋየሁ አድማሴ (አባል)
18. አቶ ክብረት ሃይሉ (የም/ቤት አባል)
19. አቶ ስለሺ ደቻሳ (አባል)
20. አቶ ማሩ አካሉ (አባል)
21. አቶ ክፍሉ በዳኔ (አባል)
22. አቶ ፋሲካ አዱኛ (የወረዳ አመራር)
23. ወ/ሮ ገነት ግርማ (የወረዳ አመራር)
24. ተስፋየ ብዙነህ (አባል) ሲሆኑ በርካቶች የደረሱበት አልታወቀም፡፡ ከፍተኛ ጉዳት የደረሰባቸው ህክምና እየተከታተሉ ሲሆን ተጨማሪ መረጃዎችን ሪፖርት እየተከታተልን እናቀርባለን፡፡
የነፃነት ጥያቄው በድብደባ አይቀለበስም!!!
1. አቶ አስራት አብርሃም (የህዝብ ግንኙነት ተጠባባቂ ሃላፊ)
2. አቶ ዳንኤል ተፈራ (የውጭ ጉዳይ ሃላፊ)
3. አቶ ብሩ ብርመጅ (የፖለቲካ ጉዳይ ሃላፊ)
4. አቶ ፀጋየ አላምረው (ምክትል አፈ-ጉባኤ)
5. አቶ አሻግሬ መሸሻ (የሰሜን ቀጠና ሃላፊ)
6. አቶ ሰለሞን ስዩም (የኤዲቶሪያል ቦርድ ሰብሳቢ)
7. ወ/ት ልዕልና ጉግሳ (የም/ቤት አባል)
8. አቶ ዳግማዊ ተሰማ (የም/ቤት አባል)
9. ጋዜጠኛ ስለሺ ሀጎስ
10. አቶ ስንታየሁ ቸኮል (የአዲስ አበባ የወጣቶች ጉዳይ ሃላፊ)
11. አቶ አሸናፊ አሳምረው (የወረዳ አመራር)
12. አቶ ኢሳያስ ቱሉ (አባል)
13. ወ/ት መስከረም ያረጋል (አባል)
14. አቶ ሃይሉ ግዛው (የወረዳ ሰብሳቢ)
15. አቶ አዲሱ መኮንን (የወረዳ ሰብሳቢ)
16. አቶ ሲሳይ ካሴ (አባል)
17. አቶ ወጋየሁ አድማሴ (አባል)
18. አቶ ክብረት ሃይሉ (የም/ቤት አባል)
19. አቶ ስለሺ ደቻሳ (አባል)
20. አቶ ማሩ አካሉ (አባል)
21. አቶ ክፍሉ በዳኔ (አባል)
22. አቶ ፋሲካ አዱኛ (የወረዳ አመራር)
23. ወ/ሮ ገነት ግርማ (የወረዳ አመራር)
24. ተስፋየ ብዙነህ (አባል) ሲሆኑ በርካቶች የደረሱበት አልታወቀም፡፡ ከፍተኛ ጉዳት የደረሰባቸው ህክምና እየተከታተሉ ሲሆን ተጨማሪ መረጃዎችን ሪፖርት እየተከታተልን እናቀርባለን፡፡
የነፃነት ጥያቄው በድብደባ አይቀለበስም!!!
በአሁኑ ሰዓት -10፡00 AM አዲስ አበባ ሰዓት
ሰላማዊ ዜጎች በአገራቸውና በምድራቸው እንደ ከብት እየተደበደቡ ነው። እጅግ በጣም ከፍተኛ ጉዳይ ደርሷል።በአመራር አባላቱም ላይ ጉዳት ደርሷል።የአንድነት ጽ/ቤት ወደ ዉስጥ ገባ በማለቱ ህዝቡ አስፋልት ላይ እየጠበቀ ቢሆን፣ ሰልፈኞቹ ሰልፉን እንዳይመሩ ከጅምሩ በፌዴራል እየተደበደቡ ነው። በሚሊዮኖ ድምጽ ላይ አምደኛ የሆነችው መስከረም ያረጋል ፣ የሚሊዮኖች ድምጽ ዋና አዘጋጅ ስለዚ ሐጎስ፣ በጣም በጭካኔ ከፍተኛ ድብደባ ደርሶባቸዋል።
እጅግ በጣም በርካታ ፌዴራል ፖሊሶች በአንድነት ጽ/ቤት አካባቢ ሰፍረዋል። እጅግ በጣም ከባድ ጉዳት በሰልፈኞች ላይ እየደረሰ ነው። በሰደፍ አንድነቶች እየተደበደቡ ነው። የሚሊዮኖች ድምጽ ዋና አዘጋጅ አቶ ስለሺ ሃጎስ እጅግ በጣም ተጎዷቷል። ሴቶች እህቶቻችን እይተደበደቡም ብትፈልጉም ግደሉን እያሉ ወደ ፊት ለመሄድ እየተሞከረ ነው። እጅግ በጣም ጭካኔ የተሞላበት ፣ አረመኔያዊ ተግባር በሰላማዊ ዜጎች ላይ እየተፈጸመ ነው።
የአንድነት ፓርቲ ከፍተኛ አመራሮችን ከበር ለማገት የተደረገ ሙከራ ከሸፈ
የአዲስ አበባ መዋቅሮቻችን መላው የብሄራዊ ምክር ቤት መዋቅሮቻችንን ቢሮ እየደረሱ ነው መፈክሮች ተዘጋጅተው አልቀዋል በአካባቢው ከፍተኛ የደህንንነት ቁጥጥር አለ ፡፡ ከፍተኛ አመራሮችን ከበር ለማገት የተደረገ ሙከራ ነበር ግን በአካባቢው ማህበረሰብ እርዳታ አምልጠው የመጡ አመራሮቸረ አሉ፡፡
No comments:
Post a Comment