Friday, January 23, 2015

Negere Ethiopia 41 mins ·

የሰማያዊ አባላትና ደጋፊዎች ‹‹ካርድ አልቋል›› እየተባሉ እንደሆነ ገለጹ
በምስራቅ ጎጃም ዞን የተለያዩ የምርጫ ጣቢያዎች ላይ የመራጮች ካርድ እጥረት አልቋል እንደተባሉ የነገረ ኢትዮጵያ ምንጮች አስታወቁ፡፡ ምንጮቹ የመራጭነት ካርድ ለመውሰድ ባመሩባቸው የምርጫ ጣቢያዎች ካርድ እንደሌለ ተገልጾላቸው እንዲመለሱ መደረጋቸውን ገልጸዋል፡፡
ኢህአዴግ በተለያዩ አደረጃጀቱ በመጠቀም ኢህአዴግን ይመርጣሉ ብሎ ያሰባቸውን ዜጎች ቤት ለቤት ሳይቀር እየቀሰቀሰ ምርጫ ካርድ እንዳደላቸው የገለጹት ምንጮች፣ የተቃዋሚ ፓርቲዎችን ይመርጣሉ ተብለው የተገመቱት ዜጎች ግን ከወዲሁ ካርድ አልቋል እየተባሉ ወደ ቤታቸው እየተመለሱ መሆኑን ለማወቅ አስታውቀል፡፡

‹‹የምርጫ ካርድ እጥረቱ መኖሩን የኢህአዴግ የምርጫ ግብረ ኃይል ሳይቀር አረጋግጧል፤ ቢሆንም ግን ካርዱ በዋናነት ለሰማያዊ አባላትና ደጋፊዎች ነው እየተከለከለ ያለው›› ሲል የምስራቅ ጎጃም የሰማያዊ አደረጃጀት ዋና ጸኃፊ አቶ ሳሙኤል አወቀ ለነገረ ኢትዮጵያ ገልጹዋል፡፡ በተለይ በባሶ ሊበን ወረዳ የጁቤ አካባቢዎች የሰማያዊ ፓርቲ አባላትና ደጋፊዎች ‹‹ካርድ አልቋል›› ተብለው መመለሳቸው ታውቋል፡፡
‹‹አንዳንድ ጣቢያዎች ዝግ እየሆኑ ነው፤ በጣም ገጠራማ አካባቢዎች ደግሞ ምርጫ ስለመኖሩ እንኳ የሚያውቁት ነገር የለም፡፡ የብአዴን ሰዎችን ብቻ ምርጫ እንደተካሄደ በማስመሰል ለማሳለፍ የታሰበ ነው የሚመስለው፡፡ ሌላው ነገር ደግሞ በአንዳንድ አካባቢዎች የ2002 ካርድ ተበትኖ አስተውያለሁ፡፡ ይሄም ለውንጀላ እንዲመቻቸው ያደረጉት ሊሆን ይችላል›› ያለው አቶ ሳሙኤል ‹‹በእኛ በኩል መረጃዎችን እየሰበሰብን ነው፤ በፓርቲያችንም እንነጋገርበታለን›› ብሏል፡፡

No comments:

Post a Comment