Tuesday, January 27, 2015

የአንዳርጋቸው ጽጌ ልደት በዋሽንግተን ዲሲ ሊከበር ነው * (አዳዲስ የአንዳርጋቸው ፎቶዎች ይዘናል)

andargachew
mesay 1
andualem 2
በሕወሓት የማሰቃያ እስር ቤት ውስጥ የሚገኙት አቶ አንዳርጋቸው ጽጌ 60ኛ ዓመት የልደት በዓል በዋሽግተን ዲሲ እና በተለያዩ ሃገራት እንደሚከበር ለዘ-ሐበሻ የሚደርሱ የጥሪ ወረቀቶች አመለከቱ::
ከ3 ቀን በፊት ዘ-ሐበሻ በኖርዌይ የአንዳርጋቸው ጽጌ የልደት በዓል እንደሚከበር የዘገበች ሲሆን; ዛሬ ለዘ-ሐበሻ የደረሰው ማስታወቂያ ደግሞ በዋሽንግተን ዲሲም እንደሚከበር ይጠቁማል::
“ለአገራችን ኢትዮጵያ ክቡር ሕይወቱን መስዋእት በማድረግ እየታገለና በአሁኑ ሰዓት በህወሓት/ወያኔ የማሰቃያ እስር ቤት ውስጥ ከፍተኛ ስቃይ እየደረሰበት የሚገእው የነፃነት ተመሳሌት የአርበኛውና ጀግናው አንዳርጋቸው ጽጌ የልደት በዓለ በዓለም አቀፍ ደረጃ በደማቅ ሁኔታ ይከበራል” በሚል የሚጀመረው የዋሽንግተን ዲሲው የጥሪ ወረቀት ቀጥሎም “እኛም በዋሽንግተን ዲሲ አካባቢ የምንገኝ ኢትዮጵያውያን ይሄን የልደት በዓል ተሰባስበን በደማቅ ሁኔታ እንድናከብር የአክብሮት ጥሪያችንን ለሁሉም ሃገር ወዳድ ኢትዮጵያውያን እናቀርባለን” ይላል::
ሰኞ ፌብሩዋሪ 9 ቀን 2015 ዓ.ም ከጠዋቱ 9:00 ሰዓት በብሪታኒያ ኢንባሲ ደጃፍ የአንዳርጋቸው ጽጌ ልደት የሚከበር መሆኑን ያስታወቀው የዋሽንግተን ዲሲ አካባቢ የጋራ ግብረ ኃይል ለበለጠ መረጃም 571-40302474 እንዲደውሉ ጥሪውን አቅርቧል::
የብሪታኒያ ኢምባሲ አድራሻ British Embassy
3100 Massachusetts Avenue NW Washington DC 20008 ነው::
በሌላ በኩል ጋዜጠኛ መሳይ መኮንን የአንዳርጋቸው ጽጌን በረሃ የወረደባቸውን አዳዲስ ፎቶ ግራፎች በፌስቡክ ገጹ ለቋቸዋል:: ጋዜጠኛ መሳይ አስመራ በነበረበት ወቅት 5 አዳዲስ የአንዳርጋቸው ፎቶ ግራፎችን የለቀቀ ሲሆን ዛሬም 3 አዳዲስ ፎቶዎች አሳይቶናል – ለዘ-ሐበሻ አንባቢዎችም እነዚህን አዳዲስ ፎቶዎች ቅክቅፍለናል::

No comments:

Post a Comment