Monday, January 19, 2015

ወዳጃችን ዳዊት ከበደ አቶ ደብረ ጺዮንን በድብቅ ቀዳቸው!

ወዳጃችን ዳዊት ከበደ አቶ ደብረ ጺዮንን በድብቅ ቀዳቸው!
(ንግግሩ ለደደቢት አርቲስቶች (ደደቢት ለተጓዙት ማለት ነው! የተነገረ ነው። ይሄ የአቶ ደብረጺዮን ንግግር በሌላ በየትም ሚዲያ ላይ ያልተሰማ ሲሆን አውራምባ በድብቅ ስለቀዳቸው ድምጹ በቅጡ አይሰማም!) አቶ ደብረ ጺዮን በንግግራቸው አርቲስቶቹን እና ጋዜጠኞቹን ሲያባብሏቸው እና ሲያበረታቷቸው ይሰማል።
ከተናገሩት ውስጥ...
***በፌስ ቡክ የሚነገረንን ነገር እንሰማለን!
***አርቲስቶች ሆዳሞች እንደምትባሉ እናውቃለን!
***መለስን ሳይቀር የሚሳደቡ አሉ! መለስን ብቻ ሳይሆን ሁላችንንም ሲሰድቡን አየተናል!
***እናንተ የፈለጋችሁትን ነገር ንገሩን፤ ስድብም ከፈለጋችሁ ህሊናችሁ ከፈቀደ ስደቡን!
***ዝም ብላችሁ ጥሩ ጥሩ ነገር ብቻ ብትናገሩ አንሰማችሁም አጭበርባሪ ነው የምንላችሁ!
***ዝም ብሎ የሚቆልለንን ፊት ለፊቱ ባንናገረው ዞር ብለን አጭበርባሪ ማለታችን አይቀርም!
***ችግር እንዳለብን እኛም እናውቃለን!
እና የመሳሰሉትን ለደደቢት አርቲስት እና ጋዜጠኞች ሲነግሩ፣ እና ሲመክሩየአውራምባው ወዳጃችን ዳዊት ከበደ በድብቅ ቀድቷቸዋል።
እኛም በርታ ዳዊት ብለን አበረታተነዋል!

No comments:

Post a Comment