ተቃዋሚ ሃይሎች ከበፊቱ በተሻለ ሁኔታ ሰብረው በመግባት ስርአቱን ማፍረስ ያለባቸው ወቅት ነው::
ኢትዮጵያ ውስጥ የተከሰተውን የፖለቲካ የምጣኔ ሃብት እና የማሕበራዊ ቀውስ እና ውጥረት ተከትሎ የባለስልጣናት አረመረጋጋት ታክሎበት በገዢው መደብ የተዋቀረው የደሕንነት ተቋም መናጋቱን ውስጥ አዋቂ ምንጮች ለምንሊክ ሳልሳዊ የላኩት መረጃ ጠቁሟል::እንደውስጥ አዋቂ ምንጮች ዘገባ ከሆነ የደህንነት አባላቱ ቡድን እና ብሄር በመለየት በሃላፊዎቻቸው ላይ ያላቸውን ጥላቻ እና ተቃውሞ እያሰሙ ሲሆን ለአንድ ብሄር ብቻ ተለይቶ የሚደረገው የበላይነት አድሎአዊ አሰራር ፍትሃዊነትን ሳይሆን የበታችነታችሁን ያሳብቅባቹሃል የሚሉ ጠንካራ ቡድኖች ከኢሚግሬሽን እና ደህንነት መምሪያ አከባቢ መከሰታቸውን ምንጮቹ ገልጸዋል::
የደህንነት አባላቱ በዜጎች መካከል በሚደረግ አድሏዊ አሰራር ለሃገር ይጠቅማሉ የተባሉ አባላትን በየክፍለ ሃገሩ በማዘዋወር ከችሎታቸው እና ከሰለጠኑት የደህንነት ሙያ ጋር የማይገናኝ ስራ ላይ በመመደብ መረጃ አምጡ ማለት የስርአቱን ዝቅጠት ከማሳየቱም በላይ በቀበሌ ካድሬዎች እና በመንደር ጆሮ ጤቢዎች የሚሰበሰቡ መረጃዎችን አሜሪካ እና እስራኤል ሰልጥነው በመጡ የአማራ እኦሮሚያ እና የደቡብ ክልል የደህንነት አባላት ማሰለል ስር አቱ ምን ያህል መዋቅሩን እንደሳተ እና በሰለጠኑ ዜጎች ላይ ሃገራዊ እምነት እንዳሌለው ያሳያል ሲሉ ምንጮቹ ተናግረዋል::
በውጭ አገር ሰልጥነው የመጡ የደህንነት አባላት ወደ ሃገራዊ የደህንነት መረጃ ሃይሎች እና ጉዳዮች እንዳይጠጉ የሚደረግ ሲሆን በቦታው ከዚህ ቀደም የተመደቡም ቢሆኑ በመረጃ መውር ውስጥ እንዳይሳተፉ ሲደረግ የአንድ ብሄር ተወላጆች በዚህ ላይ እንዲቀሳቀሱ መደረጉ ለስር አቱ ሰዎች አደጋ እና የመዋቅር መናጋት የፈጠረ ሲሆን አንዳንድ የሕወሓት አባላት አብረውን ውጪ አግር ሰልጥነው የመጡ አባሎቻችን የት ሄዱ ለምን አብረውን አይሰሩም በማለት በመዋቅሩ ውስጥ አደጋ ሆነው በመገኘት መናጋቱን እንዳጦዙት ታውቋል::
እንደ ምንጮቹ ከሆነ በአሁኑ ውቅት በሰራዊት ውስጥ እና በደህንነቱ ውስጥ የመዋቅር መናጋት አለመተማመን እና የእርስ በርስ ፍትጊያዎች በስፋት እየታዩ በመሆኑ በሃገር ውስጥ እና በውጭ አገር ያሉ ተቃዋሚዎች ይህንን ክፍተት እና የመዋቅር መናጋት እንዲሁም የውስጥ ሽኩቻን ተገን በማድረግ ሰርገው በመግባት ለስርአቱ መውደቅ ተጨማሪ ሃይል ሊሆኑ ይገባል ሲሉ ምክራቸውን ለግሰዋል::
በምኒልክ ሳልሳዊ
በምኒልክ ሳልሳዊ
No comments:
Post a Comment